🫴"ዋስትና መስጠት እችላለሁ" ፋብሪዚዮ ሮማኖ የማንችስተር ዩናይትድ የዝውውር መረጃ ደጋፊዎችን ያስደስታቸዋል
ማን ዩናይትዶች በክረምቱ የዝውውር መስኮት ሰፊ የቡድኑን ማሻሻያ ለማድረግ በዝግጅት ላይ ናቸው ሲል የዝውውር ኤክስፐርት ፋብሪዚዮ ሮማኖ ተናግሯል ክለቡ አስከፊ የውድድር ዘመን እያሳለፉ ቢሆንም ፋብሪዚዮ ሮማኖ ማንችስተር ዩናይትድ ስራ የበዛበት ክረምት እንደሚኖረው ተናግሯል
የፋይናንሺያል ፌር ፕሌይ FFP እገዳዎች የዩናይትድን ወጪ በጥር ወር ሲገድብ ነበር ለዛም ነው አንድ ተጨዋች ብቻ አስፈርመው ወሩ የተጠናቀቀው ይሁን እንጂ ሮማኖ በክረምቱ የዝውውር መስኮት ላይ ቡድኑን እንደገና ለመገንባት እንደተዘጋጁ አረጋግጧል
በዩቲዩብ ቻናሉ ላይ ሲናገር ሮማኖ እንዲህ ብሏል
"በFFP ምክንያት በጥር ወር ገንዘብ አላወጡም ስለሆነም በክረምቱ ብዙ ነገሮችን ለማድረግ ዝግጁ ናቸው በርካታ ቦታዎችን በክረምቱ ያጠናክራሉ በተጨማሪም ብዙ ተጫዋቾችን እንደሚለቁ ይጠበቃል በአጠቃላይ ማንችስተር ዩናይትዶች በተጫዋቾች ረገድ ብዙ ይሰራሉ ሥራ የሚበዛበት ክረምት ያሳልፉ ይሆናል
ማንቸስተር ዩናይትዶች በጥር ወር አንቶኒን ጨምሮ በርካታ ተጨዋቾችን አሰናብተው ነበር ብራዚላዊው በቋሚ ኮንትራት ይለቃሉ ተብሎ ከሚጠበቁ ተጫዋቾች መካከል አንዱ ሲሆን እሱን ለማስፈረም ፍላጎት ካላቸው ክለቦች መካከል ባየር ሙኒክ ይገኝበታል ከሩበን አሞሪም ጋር አለመግባባት የፈጠረው ማርከስ ራሽፎርድ ለአስቶን ቪላ በውሰት ሲሰጥ በክለቡ የረጅም ጊዜ ቆይታውም እርግጠኛ ስላልሆነ በክረምት የመልቀቅ እድል አለው
ጃዶን ሳንቾ፣ ክርስቲያን ኤሪክሰን፣ ካሴሚሮ ፣ ቪክቶር ሊንደሎፍ እና ጆኒ ኢቫንስ እንዲሁ በክረምቱ ክለቡን በቋሚነት እንደሚለቁ የሚጠበቅ ሲሆን ይህም የክለቡን የደሞዝ ክፍያ በከፍተኛ ሁኔታ በመቀነስ በዝውውር ገበያው ላይ የበለጠ ተለዋዋጭነት እንዲኖራቸው ያደርጋል
https://t.me/Capybara_Store_VPN_bot?start=_tgr_bc1e8xQ5NDVk