"ቢያንስ 7 ጋዜጠኞች በሽብር ወንጀል ተጠርጥረው ተይዘዋል" CPJ
በግል በሚተዳደረው የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ሳተላይት (EBS) መንግስት ሀሰተኛ ዶክመንተሪ ተሰርቷል በሚል ወንጀል መያዛቸውን አለማቀፉ የጋዜጠኖች ጥበቃ ኮሚቴ (CPJ) አስታውቋል፡፡
ጋዜጠኞቹ የታሰሩት ብርቱን ተመስገን የተባለች ግለሰብ በአዲስ ምዕራፍ ፕሮግራም ቀርባ ተማሪ በነበረችበት ወቅት የደረሰባትን የመደፈር ወንጀል በመናገሯ ነው ብሏል፡፡
ሲ ፒ ጄ የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ሳተላይት (EBS) ከኢትዮጵያ ሚዲያ ባለስልጣን "አስተዳደራዊ ማዕቀብ ፈተና ተጋርጦበታል" ሲል ገልጿል፡፡
የፍርድ ቤት የክስ ዶክመንት እንደደረሰው የገለጸው ተቋሙ ጋዜጠኞቹ በአማራ ክልል ከሚገኙ ጽንፈኛ ቡድኖች ጋር ተባብራችኋል የሚል ክስ እንደቀረበባቸውም አስታውቋል፡፡
ከዚህ በተጨማሪም ህገመንግስቱን ለመናድ እና መንግስትን ለመጣል አሲራችኋል በሚል ክስ ቀርቦባቸዋል ብሏል፡፡
በፍርድ ቤት ከሚገኙት መካከል ነብዩ ጥኡመልሳን፣ ታሪኩ ሀይሌ፣ ህሊና ታረቀኝ፣ ንጥር ደረጀ፣ ግርማ ተፈራ፣ ሄኖክ አባተ እና ሀብታሙ አለማየሁ መሆናቸውን አስታውቋል፡፡
@ThiahEth