Фильтр публикаций


አሜሪካ 1600 ከባድ ቦምቦችን ለእስራኤል ላከች።

MK-84 የተሰኙ ከባድ ቦምቦችን የጫኑ መርከቦች በዛሬው እለት በእስራኤል የአየር ሀይል ዋና ቢሮ ተራግፈዋል።

በተያያዘ መረጃ የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማርክ ሩቢዮ እስራኤል ይገኛሉ።

ሩቢዮ ከጠቅላይ ሚኒስትር ኒታንያሁ ጋር ባደረጉት ውይይት በጋዛ የተኩስ አቁም ዙሪያ መምከራቸው ተገልጿል።

በአዲሱ ኃላፊነት ለመጀመሪያ ጊዜ ወደ መካከለኛው ምሥራቅ የመጡት ማርክ ሩቢዮ በቀጣይ ወደ ሳዑዲ በማቅናት ከከፍተኛ የሀገሪቱ ባለሥልጣናት ጋር ይወያያሉ ተብሎ ይጠበቃል።
#ynetnews #ashiraqalawusat

@ThiqahEth


የጅቡቲ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የነበሩት መሐመድ ዓሊ ዩሱፍ የአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ሆነው ተመረጡ።

ከአውሮፓውያን 2005 ጀምሮ ጅቡቲን በውጭ ጉዳይ ሚኒስትርነት ያገለገሉት ዩሱፍ፣ በአፍሪካ ኅብረት አዳራሽ በተካሔደውና ብርቱ ፉክክር በታየበት፣ እስከ ሰባተኛ ዙር ድረስ በዘለቀ ምርጫ ሁለት ሦስተኛ ድምጽ በማግኘት ማሸነፍ ችለዋል።

የ60 አመቱ ዩሱፍ፣ የኬንያውን የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር ራይላ ኦዲንጋ እና የማዳጋስካር የቀድሞ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሪቻርድ ራንድሪያማንድራቶን በማሸነፍ ኮሚሽኑን ለአራት ዓመታት እንዲመሩ ተመርጠዋል።

መሐመድ ዓሊ ዩሱፍ በአፍሪካ አህጉር ለረጅም ዓመታት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሆነው ያገለገሉ ብቸኛ ሰው ናቸው።
#au #radiotamazuj

@ThiqahEth


''በየአመቱ ወደ 400,000 የሚጠጉ ህጻናት በካንሰር በሽታ ይያዛሉ''  - ዶክተር ቴዎድሮስ አድሃኖም

በመላው ዓለም በካንሰር በሽታ የሚጠቁት ህጻናት ቁጥር ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መምጣቱን የዓለም ጤና ድርጅት አስታውቋል፡፡

የድርጅቱ ዳይሬክተር ቴዎድሮስ አድሃኖም  (ዶ/ር)፣ ዓለም ዓቀፍ የጤና ጉዳዮችን አስመልክቶ በበይነመረብ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡

ቴዎድሮስ በመግለጫቸው፣ ''ከፍተኛ ገቢ ባላቸው ሀገራት 90 % የሚሆኑ ህጻናት የመዳን እድል ሲኖራቸው በታዳጊ ሀገራት ግን የመዳን እድል ያላቸው ህጻናት 30 % ብቻ ናቸው'' ሲሉ አብራርተዋል፡፡

የመካከለኛ ገቢ እና አነስተኛ ገቢ ባላቸው ሀገራት የህይወት አድን ህክምና እየተሰጠ እንደሚገኝ ገልጸዋል፡፡

"በየዓመቱ ወደ 400,000 የሚጠጉ ሆጻናት በካንስር በሽታ ይይዛሉ" ሲሉም ተናግረዋል።
#peoplesgazette

@ThiqahEth


ኮንጎ ለሩዋንዳ አየር መንገድ የአየር ክልሏን ዘጋች፡፡

ድሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ለኤም 23 "አማጺ ቡድን ትደግፋለች" በማለት የምትከሳት ሩዋንዳን በስሟ የተመዘገቡ አውሮፕላኖች የአየር ክልሏን መጠቀም እንዳይችሉ ሙሉ በሙሉ ዘግታለች፡፡

የሩዋንዳ አየር መንገድ በበኩሉ ደህንነታቸው የተጠበቁ አማራጮችን እያማተረ እንደሆነ አስታውቋል፡፡

ሩዋንዳ፣ "የኮንጎ መንግስት ለገጠመው ውድቀት በሩዋንዳ ላይ እያሳበበ ነው" ስትል የሚቀርብባትን ውንጀላ አጣጥላለች፡፡

ሩዋንዳ በ2022 ወደ ኮንጎ የምታደርገውን በረራ በራሷ ውሳኔ አቁማ ነበር፡፡
#allafrica

@ThiqahEth


''ሀማስ ታጋቾችን እስከ ቅዳሜ ድረስ ካልለቀቀ ስምምነቱ ይፈርሳል''  - እስራዔል

''እስራዔል ስምምነቱን ቀድማ ስለጣሰች ታጋቾችን የመልቀቅ እቅዴን አዘግይቸዋለሁ''  - ሀማስ

ጠቅላይ ሚኒስትር ቢኒያም ኒታንያሁ እስራዔላዊ ታጋቾች እስከ ቅዳሜ እኩለቀን ድረስ ካልተለቀቁ እስራዔል እርምጃ እንደምትወስድ አስጠንቅቀዋል፡፡

ኒታንያሁ ከብሄራዊ የጸጥታ ኮሜቴው ጋር ባደረጉት ስብሰባ በአሁኑ ወቅት 76 ዜጎች በሀማስ እገታ ስር መሆናቸውን አብራርተዋል፡፡ 

ሀማስ በበኩሉ፣ እስራኤል ስምምነቱን ቀድማ ስለጣሰች ታጋቾችን የመልቀቅ እቅዴን አዘግየቸዋለሁ" ብሏል።

ወደ ፊትም ዝርዝር መረጃዎች እንደሚያሳውቅ ገልጾ፣ ለስምምነቱ መጣስ እስራዔልን ተጠያቂ አድርጓል፡፡
#scroll

@ThiqahEth

4k 0 1 16 33

"ዩክሬን በድርድሩ ሂደት ግዛቶችን ለመቀያየር ተዘጋጅታለች''  - ፕሬዜዳንት ዘለንስኪ

''ሩሲያ የግዛት መቀያየር ሃሰብን ፈጽሞ አትቀበለውም''  - ድሜትሪ ሜድቬዴቭ

የዩክሬኑ ፕሬዝዳንት ቮለድሚር ዘለንስኪ ከሩሲያ ጋር በሚያደርጉት የሰላም ድርድር ከስድስት ወራት በፊት የተቆጣጠረችውን የኩርስክ ክልል ይዞታዎች ለመመለስ መዘጋጀቷን ተናግረዋል፡፡

''በምላሹም ሩሲያ ኬርሶን፣ ሉሃንስክ እና ዛፓሮዥያን ለቃ እንደምትወጣ እንጠብቃለን'' ብለዋል ዘለንስኪ፡፡

የክሬሚሊን ቃል አቀባይ ድሜትሪ ፔስኮቭ ደግሞ፣ ''ሩሲያ ግዛቶቿን የመለዋወጥ ሀሳብ ኑሯት አያውቅም፤ ወደ ፊትም አይኖራትም'' ብለዋል፡፡

በሩሲያን ግዛት የሚገኙ የዩክሬን ወታደሮች ''ወይ ይወጣሉ ወይ ይደመሰሳሉ'' ሲሉ ተናግረዋል፡፡
#kyivpost   #thenewarab

@ThiqahEth


ፈረንሳይ በአይቮሪ ኮስት ያለውን ብቸኛውን የጦር ሰፈር "ለቃ ልትወጣ ነው" ተባለ፡፡

ፈረንሳይ በምዕራብ አፍሪካ የሚገኘውን ብቸኛውን የፖርት ቦውት የጦር ሰፈር በቅርቡ አሳልፋ እንደምትሰጥ ተዘግቧል፡፡

ፈረንሳይ ጦሯ እንደምታስወጣ ያስታወቁት አይቮሪኮስት ፕሬዝዳንት አላሳን ኦታሬ ናቸው፡፡

ውሳኔው የምዕራብ አፍሪካ ሀገራት ከቀድሞ ቅኝ ገዥ ፈረንሳይ ጋር ያላቸውን ወታደራዊ ግንኙነት የማቋረጥ ሂደት አካል ነው ብለዋል፡፡
#rtl

@ThiqahEth


ኒውዝላንድ፣ ''ኢንቨስተርስ ፕላስ ቪዛ (IPV)'' የተሰኘ አዲስ የቪዛ አገልግሎት አስተዋወቀች፡፡

አዲሱ የቪዛ ሲስተም ለኢንቨስተሮች ብቻ የሚያገለግል ሲሆን፣ የውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንትን (FDI) ለመሳብ  ያለመ መሆኑ ተገልጿል፡፡

''ኒውዝላንድ የኢንቨስትመንት መዳረሻ መሆኗን ለማሳየት ይጠቅማል'' ያሉት የሀገሪቱ የኢኮኖሚ እና እድገት ሚኒስትር ኒኮላ ዊሊስ፣ አዲሱ ኢንቨስተርስ ፕላስ ቪዛ (IPV) ከመጪው ሚያዚያ ወር ጀምሮ ተግባራዊ እንደሚደረግ አረጋግጠዋል፡፡

የኢሚግሬሽን ሚኒስትር ኢሪካ ስታንፎርድ፣ ''አዲሱ የቪዛ ፕሮግራም በዚህ በሰለጠነ ዓለም ኢኮኖሚ ካፒታልን ለመሳብ ይጠቅማል'' ብለዋል።
#nairametrics

@ThiqahEth


"ለገጠመን የኑሮ ውድነት ችግር ጥብቅ የሞነታሪ ፖሊሲ መከተል ግድ ይለናል'' - የህንድ ባንክ

ህንድ ሁሉም ባንኮች ወለድ እንዲያቆሙ አዘዘች፡፡

የህንድ ማዕከላዊ ባንክ የኢኮኖሚ ቀውስን ለመግታት በሚል ለመጀመሪያ ጊዜ የባንክ ወለድ እንዲቀር ትዕዛዝ አስተላልፏል፡፡ 

የባንኩ ገዥ ሳንጃይ ማልሆትራ፣ ''ለገጠመን የኑሮ ውድነት ችግር ጥብቅ የሞነታሪ ፖሊሲ መከተል ግድ ይለናል'' ሲሉ ተናግረዋል፡፡ 

ማልሆትራ፣ ''የዋጋ መረጋጋትን፣ ዘላቂ የኢኮኖሚ እድገት እና የፋይናንስ መረጋጋትን ለመፍጠር የማክሮ ኢኮኖሚክ መሻሻያ ማድረግ አስፈላጊ ሆኖ አግኝተነዋል'' ብለዋል፡፡

በህዝብ ቁጥር ከዓለም አንደኛ ደረጃ ላይ የምትገኘው እስያዊቷ ሀገረ ህንድ የምጣኔ ሃብት እድገቷ ላለፉት አምስት ተከታታይ አመታት እየቀነሰ መምጣቱን ሪፖርቶች አመላክተዋል፡፡
#aljazeera

@ThiqahEth


''የሆነ ቀን ዩክሬን የሩሲያ ሆና ልናያት እንችላለን'' - ትራምፕ

የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከፎክስ ኒውስ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ የዩክሬንን ባለስልጣናት፣ ''ስምምነት ሊያደርጉ ይችላሉ ላያደርጉም ይችላሉ፤ አንድ ቀን የሩሲያ ሊሆኑ ይችላሉ ላይሆኑም ይችላሉ'' ሲሉ ተናግረዋል፡፡

ትራምፕ ዩክሬን በጦርነቱ ከአሜሪካ የተደረገላትን ወደ 500 ቢሊዮን ዶላር የሚገመት ድጋፍ፤ ያሏትን ማዕድናት በካሳ መልክ እንድታቀርብ አዘዋል፡፡

የዩክሬን ፕሬዝዳንት ጽህፈት ቤት ኃላፊ አንድሪ የርማክ በበኩላቸው፣ ከሩሲያ ጋር ለሚደረገው ስምምነት ዝግጁ መሆናቸውን ገልጸው፤ የደህንነት ዋስትና እንዲሰጣቸው ጠይቀዋል፡፡
#aljazeera    #associatedpress

@ThiqahEth


ግሪክ ባጋጠማት ተደጋጋሚ የመሬት መንቀጠወቀጥ በሀገሪቱ ቱሪዝም እንቅስቃሴዋ ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ አሳድሮባታል ተባለ፡፡

ከቀናት በፊት በውጭ ቱሪስቶች በስፋት የሚጎበኘው የሳንቶሪኒ ደሴት ለተከታታይ ሰባት ጊዜ  በሬክተር ስኬል ከ4 እስከ 5.2 የተመዘገበ የመሬት መንቀጥቀጥ ተከስቷል፡፡

ይህን ተከትሎ ባለስልጣናት የአስቸኳ ጊዜ አዋጅ አውጀዋል፡፡

የመሬት መንቀጥቀጥ አደጋውን ተከትሎ ከ11,000 የሚበልጡ ነዋሪዎች ከሳንቶሪኒ ደሴት መውጣታቸው ተሰምቷል፡፡  
#france24

@ThiqahEth


''ፑቲን የሰዎች ሞት ሲያበቃ ማየት ይፈልጋል'' - ትራምፕ

ትራምፕ ወደ ነጩ ቤተመንግስት ከተመለሱ በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ከቭላድሚር ፑቲን ጋር የስልክ ውይይት አደውርገዋል፡፡

ሁለቱ መሪዎች የዩክሬንን ጦርነት ለማቆም በሚያስችሉ ጉዳዮች ዙሪያ መክረዋል ተብሏል፡፡

ፑቲን፣ "የሰዎች ሞት ሲያበቃ ማየት ይፈለጋል" ብለዋል።

ትራምፕ በምርጫ ቅስቀሳ ወቅት የሁለቱን ሀገራት ጦርነት ስልጣን በያዝኩ ማግስት አስቆመዋለሁ ቢሉም ጦርነቱ እስካሁን ድረስ እንደቀጠለ ነው፡፡ #thekoreatimes   #thenewyorkpost

@thiqahEth


''ቲክቶክን የመግዛት እቅድ የለኝም'' -ኤለን መስክ

የቴስላ እና ስፔስ ኤክስ ባለቤት መስክ በቻይናው የባይት ዳንስ ኩባንያ የሚተዳደረውን የቪዲዮ ማጋሪያ ቲክቶክ ለመግዛት እንደማያስብ አስታውቋል፡፡

መስክ፣ ''ቲክቶክ ቢኖረኝ ምን እንደምሰራበት እቅድ ስሌለለኝ ለጨረታ አልተዘጋጀሁም'' ብለዋል።

አሜሪካ የብሔራዊ ደህንነት ስጋት አለው ባለችው የቻይና ኩባንያ ላይ በመላ ሀገሪቱ እንዲዘጋ አልያ ከፊል ድርሻው ለአሜሪካውያን ባለሃብቶች እንዲሸጥ ጠይቃለች፡፡

ከሚሸጥ መዘጋቱን የሚመርጠው የባይትዳንስ ኩባንያ በባይደን ዘመን ተዘግቶ የነበረ ቢምንም፤ ትራምፕ እገዳው ለ75 ቀናት እንዲቆይ ወስነዋል፡፡ #cnn

@thiqahEth


የባንግላዴሽ ተቃዋሚዎች የቀድሞዋን ጠቅላይ ሚኒስትር ቤተሰብ መኖሪያ ቤት  "ማቃጠላቸው" ተሰምቷል።

በሺዎች የሚቆጠሩ ተቃዋሚዎች በአንድ ሌሊት በፈጸሙት ጥቃት የሼክ ሀሲና ደጋፊዎች ቤት እና ንብረት ላይ ያነጣጠረ ጥቃት ፈጽመዋል፡፡

የጥቃቱ መንስዔ የሼክ ሀሲና ደጋፊዎች የሽግግር መንግስቱን ለመቃወም አደባባይ ለመውጣት በማህበራዊ ሚዲያ ዘመቻ ማድረጋቸው ነው፡፡

የቀድሞዋ ጠቅላይ ሚኒስትር ሼክ ሀሲና በስደት ከሚገኙባት ህንድ ሆነው ስለተቃውሞው ንግግር ያደርፋሉ ተብሎ ተጠብቆ ነበር፡፡ 

ተቃዋሚዎቹ ቤቱን ለማፍረስ ዶማና ሌሎች ቁሳቁሶችን ይዘው የገቡ ሲሆን፤ ኤክስከቫተር መኪና ይዘው የገቡ መኖራቸውም ተዘግቧል፡፡
#Algezira

@ThiqahEth


ትራምፕ "አናሳ ነጮችን ጨቁናለች" ባሏት ደቡብ አፍሪካ ላይ ማዕቀብ ጣሉ።

የደቡብ አፍሪካ መንግስት በነጮች የሚተዳደር መሬት ያለ ካሳ እንዲወረስ የሚፈቅድ ህግ አፅድቋል። 

ደቡብ አፍሪካ እስራኤልን በጋዛው ጦርነት በዘር ጭፍጨፋ ወንጀል በዓለም አቀፍ ፍርድ ቤት መክሰሷ የፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ አስተዳደርን ማስቀየሙ ተገልጿል።

ከዚህ ባለፈም ኢራን ጋር በንግድ፣ ፀጥታ እና የኑክሌር ማበልጸግ ፕሮግራም የጋራ መግባቢያ ስምምነት መፈጸሟ በአሜሪካ ዘንድ አልተወደደም። #thenationalpulse

@ThiqahEth


ከራዳር ተሰውሮ የነበረው አውሮፕላን ተከስክሶ ተገኘ።

የአሜሪካ ባህር ጠባቂ ኃይል የተሰባበረውን የአውሮፕላን ቅሪት ማግኘታቸውን አረጋግጠዋል።

አውሮፕላኗ በአላስካ ግዛት 10 ሰዎችን ጭና የነበረ ሲሆን፣ ወንዝ ዳር ተከስክሳ ተገኝታለች።

አውሮፕላኗ ከአናክላት ወደ አላስካ እየበረረች በነበረበት ወቅት ነበር ከራዳር የተሰወረችው። #bernama

@ThiqahEth



Показано 17 последних публикаций.