ትዝታዊ🐣


Гео и язык канала: Эфиопия, Амхарский
Категория: Книги


ስላላቹ አመሰግናለው !!
ለሃሳብና አስተያየታቹ . . . . @tiztawe1_bot ይጠቀሙ

Связанные каналы

Гео и язык канала
Эфиопия, Амхарский
Категория
Книги
Статистика
Фильтр публикаций


🦋🦋

. . . ባንድ ወቅት በፍቅር እልም ያልኩበትን ወቅት አስታውሳለው . .

ስለለበሰው ልብስ ሳይሆን ተጨንቄ ስለለበስኩት ልብስ አስባለው ፣ ልሰጠው ብዬ ስለተሸከምኳቸው  መፅሃፍቶች . .  በዝናብ ስለተጠለልኩት ዣንጥላ . . . ፣ በመተዋወቅና በመተፋፈር ስለበላነው አስቂኝ ምሳ . . . ገብተን ሳናይ የወጣንበትን ቲያትር ቤት . . እሩቅ እንደሆነ ሁላ ወደዋላ ገስግሼ የትዝታ ሳቅ ስቃለው. . .

አንዳንድ ጥንድ የፍቅር እርግቦች ህይወት ኖር ብላ ልትቀበላቸው ከቦታዋ ከመነሳቷ እንደ ጤዛ  ይተናሉ. . . የኛም አጭር ታሪካችን ሳንቀመጥ ነው ያበቃው . . . ሳንኖር ነው የተነፈሰው. . .  ቢሆንም እብድ ፍቅር ነበር . . .

     /ትዝታ /


| ❀:✧๑♡๑✧❀|
         @tiztawe
         @tiztawe
ೋ•✧๑♡๑✧•ೋ


ሰላም ሰላም 🙏

እጃችን ላይ የቀረ የባለቅኔዋ ሶሪት መጽሐፍ 7 Copy አለ። የአምስቱን Copy ገቢ በማድረግ በ12/2/2016 በተስፋ አዲስ የሕጻናት የካንሰር ሕሙማንን ለመጠየቅ ለሚካሄደው program ልናውለው አቅደናል።

ምንም እንኳ የአንዱ መጽሐፍ ዋጋ 150 ብር ቢሆንም ለተስፋ አዲስ ገቢ ማሰባሰቢያ እንዲሆን አንዱን copy በ 500 ብር እንዲገዙ አምስት ሰው እንፈልጋለን። 

ስለዚህ ከታች ባለው አካውንት ቁጥር 500 ብር በማስገባት የዚህ የተቀደሰ መርሐግብር እንዲሆኑ በአክብሮት እንጋብዛለን!

1000515382643
ዘነበወርቅ ስዒድ፣ ኤልሳ ዳግማዊ


እናመሰግናለን


የኔ መንገድ ---=፩=-----🪔

. . . "ከአይን ያውጣት "ተብዬ እድሜዬ ከሚያስገድደኝ በላይ ከፈጠንኩባቸው ጊዚያቶች በላይ ፣ በራሴ ዛጎል ተወሽቄ ለሰው እየታ የደበዘዝኩበትን አሁን የበለጠ ወደዋለው. . . ሰው ደስታው ባድናቂው ሲከበብ ሳይሆን በራሱ ነፍስ የእርካታ ሙገሳ ሲያገኝ እደሆነ በፀጥታ አለሜ ውስጥ የተረዳሁት እውነት ሆኖልኛል. . .

. . . የሆነ ወቅት ላይ ለዓለም "ማጠልቀዋን ፀሃይ፣ ማታቃጥለውን ጨረቃ " የመሆን ከፍተኛ ትግልና ምኞት ላይ እደነበርኩ ዛሬ ላይ ቆሜ ሳስብ ያስቀኛል. . .

አንድ ሰው የሌላውን ድንበር ሳያልፍ ተሰብስቦ በራሱ ዓለም እርጋታን ከሰጠ ለዓለም ትልቅ ውለታ እንደዋለላት ምን አልባት ሂደት ያስተማረኝ ነገር ይሆናል . . .

ይቺን የአሁኗን እኔን ወዳታለው . .ሌላዋን ምወዳት እኔን እስክትዋወቃት . . ምን አልባት . . . . .

/ትዝታ /


| ❀:✧๑♡๑✧❀|
         @tiztawe
         @tiztawe
ೋ•✧๑♡๑✧•ೋ




🌼🌼
.
.
.

ስለቅዝቃዜው ማብቃት ፣  ስለፀሐይ መታየት . . ከጭቃ ወደ አፈር መሻገር .፣ .  ስለዶሮው ጠዐም ፣ ስለጠጁ ሽታ . .  ፣ የህፃናት ዜማ ፣ ስለእጅ ጥበባቸው . . . ስለየትኛው ግድ ይለኝም . .

መስከረም ለኔ ልክ እንደ ወዳጆቿ ወራት ሆና ትቀር ነበር አደይ ባታብባት . .  አደይ ባትፈካባት. .

ለአበባዋ ነው ፍቅሬ. . . የታቀፈች  ህፃን ትመስለኛለች .መዓዛዋ አጭር ነው. ... የዓለምን ክፋት ማፈስ ስንጀም የልጅነት የአንገት ጠረናችን በሚከረፋ ሃጥያት ይነከራል . .  የእሷ እድሜ ግን አጭር ነው . .  ጠራኗ እንዳማረ መቶ ይሄዳል. . . .

የተደበቀች ነፍስ ትመስለኛለች. .ለሊት ድንገት ከቅዠታችን ምትቀሰቅስ ፣ በሃሩር በርሃ ውስጥ ብርድ ብርድ ምትለን . . .

ተስፈኛ ሃገርም ትመስለኛለች . . . ፤

ልጆቿን ብቻዋን ምታሳድግ ከዓለም የተደበቀች ውብ እናትም ትመስለኛለች . . . .፤

የምትናፈቅ ፣ የማትጠገብ ወዳጅ . .   . .
የመስቀል ወፍ ተጣሪ . . . የጫወታ መሃል እውነት .  . .  አደይ🌼🌼

እንኳን ደህና መጣሽ እላለው ከበቀልሽበት መስከረም በላይ በአንቺ ፍቅር እየናኘው  . .   🌼

🌼🌼🌼🌼

                  /ትዝታ/


| ❀:✧๑♡๑✧❀|
         @tiztawe
         @tiztawe
ೋ•✧๑♡๑✧•ೋ


እነዚህ ምስኪን ወላጆች  አካል ጉዳተኛ አባት እናት በልመና የሚተዳደሩ ደርሳ ትረዳናለች ታግዘናለች ያሏት 13አመት እድሜ ያላት አንድ ልጃቸው  ጳዉሎስ የ ህፅናት ፅኑ ሕክምና ክፍል ተኝታባቸው እየተሰቃዮ ነው ልለምናችሁ ያላችሁን 50 ብር መቶ ብር ሳትሉ  በዚህ በአባትየው አካውንት ገቢ አድርጉ🥺 1000366869887Almar awol  ትንሽ እናግዛቸው🤲




ይችን ጥያቄ /አዳምዬ❤️./ ተጠየቀ👇

"ድርሰት የምትፅፍበት የተለየ ጊዜና ሁኔታ አለ? የአፃፃፍ ልምድህስ ምን ይመስላል?"

አዳምዬ❤️ ሲመልስ

አ.ረ - "እኔ በማንኛውም ጊዜ ነው የምፅፈው። አሁን ልፅፍ እችላለሁ። ለምሳሌ ከኋላህ መደርደርያ አለ። ከላይ አሻንጉሊት አለች። ይሄ material አለ።

ይሄን እንዳየሁ አንተ አታውቅም።

ይሄን material ስፍራውን ቀይሬ ሌላ ቦታ አንድ ገፅ ልፅፍበት እችላለሁ።

ብታነበው እንኳን ያንተ ክፍል መሆኑን አታውቅም።

አሻንጉሊቷ ውሻ ነች - ድመት አደርጋታለሁ፣
ቢጫ መፅሀፍ አለ - ቀይ አደርገዋለሁ፣
ነጭ መደርደሪያውን ሰማያዊ አደርገዋለሁ፣ ሰፋ አደርገዋለሁ።

ይሄ መነሻ ሰጥቶኝ ድርሰት አደርገዋለሁ . . . .

እያንዳንዱ ቅፅበት ለድርሰትህ አስተዋፅኦ የማድረግ አቅም አለው።

ልጅህን እንኳን እያጠብከው፣ በሚሰደደው ሃሳብህ ሁልጊዜም material አለህ። ልጁን ስታጥብ አሳሳቁ material ይሰጥሃል። "እሱን ሳክል እኔ እንደዚህ እስቅ ነበር?" ልትል ትችላለህ። ወይም የሱ ሳቅ፤ ስትሰማው የነበረውን ዜና ያጠፋዋል። ያ ቅፅበት ራሱ material ነው። "

. . .

You’re not over the hill, you’re just on your final chapter! Happy birthday!❤️



| ❀:✧๑♡๑✧❀|
         @tiztawe
         @tiztawe
ೋ•✧๑♡๑✧•ೋ


ለምን "እግዚሀር" ብለው አይጠሩኝም ነበር? እሱ እንደኔ ተቀምጦ ከማየት ሌላ ምን ሰራ?»
================================
አዳም ረታ የምናብ ፈጣሪያቸው ከሆኑት እልፍ ነፍሳት (የዝንብና የቁራውን ጨምሮ) መካከል መዝገቡ ዱባለ ይለያል። መዝገቡ ከልጅነት እስከ እውቀት የገሃዱ አለም ሰዎችን የህይወት ገፅ ይዳስሳል። በሚፈቅድለት የማሰብ ልክ አይነኬዎችን ይጠይቃል፣ ይከስሳል።

ከተከሳሾቹ መካከል አንዱ ደግሞ ፈጣሪ ነው። ክፉ የእንጀራ እናት ስለሰጠው ይጠይቀዋል። የሰፈራቸው አሮጊት ሴትዮ በእሱ እናት ፈንታ ባለመሞታቸው ይሞግተዋል። ስሙ ዱባለ የሆነ ፀጉር ቆራጭ አባት ስለተሰጠው 'ለምን' ይላል። ባዘቦቱ ቀን የባቄላና የሽንብራ አሹቅ፣ በበዓል ቀን ደግሞ ፈርሱ ያልተራገፈ ጨጓራ በሚበላበት ጣሪያ ውስጥ ምን እያበሏት እንደሆነ ሳያውቀው ወፍራም ስለሆነች እህቱ ያማርራል። ወፍራም እህት ስለሰጠው ፈጣሪውን ይከሰዋል።

ከመዝገቡ ክሶች መካከል ከስሙ ጋር አያይዞ የሚጠይቃት ይቺ ጥያቄ ፈገግ አድርጋ መልሳ ታስደነግጠኛለች።

«'መ! ዝ! ገ! ቡ!' የሚገርም ስም ነው። መዝ...መዘዝ ሊሆን ይችላል። መዘዘኛ ለማለት። ገ...ገጣባ። ቡ...ቡቃያ። ሲጠቃለል፣ መዘዘኛ የሆነ ገና ካሁኑ የተገጠበ ቡቃያ። ካልጠፋ ስም ይሔን ይሰጡኛል? ሌላ ሌላ ጠፋ እንዴ!? ለምን "እግዚሀር" ብለው አይጠሩኝም ነበር? እሱ እንደኔ ተቀምጦ ከማየት ሌላ ምን ሰራ?»

መዝገቡ ይሔን ያለበት ምክንያት ፀጉር ቆራጭ አባቱ ዱባለ እና ቤተሰቡ የሚያደርሱበትን በደል እግዜር ብቻ እንደሆነ የሚያውቀው ያምናል። እናም ዝምታን መምረጡን አልወደደለትም። ለዚያም ነው በሾርኔ ሊነግረው የፈለገው።

በርግጥ ሀበሻ በገሃዱ አለምም ለዚህ መሰል ደፋር ጥያቄዎች ባዕድ አይደለም። አንዳንዴ በሰውኛ መነፅር ሲታዩ ፈፅሞ መሆን የሌለባቸው ነገሮች ሲደረጉ የፈጣሪን ኑባሬ አምነው፣ ግን ደግሞ ስለልክነቱ (Fairness) የሚጠይቁ ሰዎች በየዘመኑ ነበሩ። ከዚህ ጋር በተያያዘ በሙሾ ወቅት የተለመደች አንዲት ስንኝን መጥቀስ እንችላለን።

"አለህም እንዳንል እንዲህ ይደረጋል
የለህም እንዳንል ቀን መሽቶ ይነጋል።"

እኛም በጨነቃችሁ ጊዜ እጆቻችሁን ወደፈጣሪ ዘርጉ የተባለልን ህዝቦች ነንና፣ ሃገራችን ላይ እየሆነ ያለው ሁሉ የሚገባት አልመስል ሲለን የመዝገቡ ዱባለን ጥያቄ እንዋሳለን። ዝም (ቁጭ) ብሎ የሚያያት ምን እስክትሆን ይሆን?

መልስ እንዳለው እናምናለን፣ መጠበቅ ግን ቢደክመን በማን ይፈረዳል?!

/ገረመው ፀጋው/


| ❀:✧๑♡๑✧❀|
         @tiztawe
         @tiztawe
ೋ•✧๑♡๑✧•ೋ




ሮማን ተወልደ በፌስቡክ ገጿ ላይ ያጋራችውን ፅሁፍ ሳነብ እኔ ልለው ምፈልገውን ሁሉ አስጠፋችኝ ፣ በርግጥ ከዚህ በላይ ልለው ብችል ብሻም ግን የነፍሴን ገልፃልኛለችና እስካጋራችው ፎቶ ጭምር ልለቅላቹ ፈለኩኝ !

👇👇👇👇

ያያ ምናምን የሚባለው ልጅ ለቴዲ ልደት የጻፈው መልእክት አለ አይደል -- የትላንቱ
“ ... እኔ ላንተ ያለኝ ፍቅርና አክብሮት ... በአካል ባገኘሁህ ቁጥር በደወልኩ ቁጥር የልቤ ምት የሰውነቴ መንቀጥቀጥ ያሳብቅብኛል ...”
የዚህ ጽሑፍ ቢጤ መነሻዬ ነው

እና

* አዳምን ያገኘሁት ዕለት *

-- ያኔ እኮ አዲስአበባ መምጣቱን አውቄ እያለሁም
ሚሊዮን ጊዜ መልእክት ልጻፍለት --
ሺህ ምንተ ሺህ ጊዜ እገሊትን አገናኝኝ ልበላት -- ወይስ እገሌ ይሻለኛል እያልኩ ሳውጠነጥን ሰንብቼ
.
ከዛ ደግሞ ሳገኘው ምንድነው የምለው?! _ ፍርሃት ቢጤ
መቼም “ማሕሌትን እንዴት ሳልካት?” ብዬ የጋዜጠኛ መሰል ጥያቄ ነው የምጠይቀው ወይስ እንደ ሰማያዊው ፈረስ አክተር “መቼ መቼ ነው የምትጽፈው?” ብዬ ነው የምጠይቀው

“እኔም ገና ለገና ለመጻፍ ገና ያሰብኩት ነገር አለ፤ ግን አልጻፍኩትም ገና ገና ነው እና ታይልኛለህ ወይ?” ብዬ አጓጉል ነገር ነው ወይ የምለው
.

ማለቴ --
📖 ከአስራ በላይ መጻሕፍት የጻፈልን ደራሲያችን ነው እኮ
እ የአማርኛ ጣዕሜ ነው
ኦ አዳም የሁላችንም የኢትዮጵያዊያን ብቻ ሳይሆን -- ብቻ

የሚወዱት ደግሞ እጅግግ ሲበዛ ልክ እንደ ግል ሀብታቸው አድርገው የሚያዩት እና በጣም አጥብቀው የሚወዱት እና
“አዳምን አትንኩብን” ብለው የሚከልሉት እና የሚጠብቁት (ጥብቅና ሳያስፈልገው ጥብቅ ጥብቅና የሚቆሙለትም) ናቸው እና
ይኼንን ደራሲ ማግኘት ለኔ መቼም የነበረውን ስሜት መግለጽ ያዳግተኛል ከምር (የልቤ ምት ነው ያለው ያ ልጅ - እንደዛ ነገር ነው)

__ ብቻ ምኞቴን እውን ያደረገችልኝ የልቤ ወዳጄ ናት (እጅግ ከባድ ውለታዋ ሁሌም በልቤ ውስጥ ታትሞ የሚቀር ነው - እሷን ማመስገን ብቻ በቂዬ አልሆነልኝም ---)

እሷን ብቻዋን የማገኛት መስሎኝ እየተንጦለጦልኩ ቀጠሮ ቦታችን ስደርስ

There he was – the one and only Adam …

ዘ ይ ገ ር ም

-- ቅልል ያለ - ማለቴ እጅግ ግርማ ሞገሳም ሆኖ ምንም የማይከብድ
-- ሲበዛ ተጫዋች - ፌዘኛ ነገር ነው ኧረ -- ኮሚክ ቢጤም
-- አራዳ የመጬ አራዳ (የአራዳ ጨዋታ ብላልኛለች ደግሞ መዲሂኔ)
-- ደራሲ ነኝ ብሎ ቅንጣት የማይኮፈስ
-- ዝቅ ብሎ ጭራሽ እሱ እኔን ጠያቂ የሆነ “ሥራ እንዴት ነው?” “የመጻሕፍት ጉዳይ ምን ይመስላል?” “ምን አዲስ ነገር አለ?” ብሎ የጠየቀኝ የመጨረሻ ትሁት -- ያ so humble and gentle
A true gentleman

መልካም ልደት በድጋሚ የሁላችንም አዳምዬ 🙏❤🙏❤🙏❤

Today is history and will remain so for always and ever in our literature history of Ethiopia.

_ _ _


| ❀:✧๑♡๑✧❀|
         @tiztawe
         @tiztawe
ೋ•✧๑♡๑✧•ೋ




. . . . 🐝🦋. .
.
.
ቢራቢሮ🦋
.
.

ሳፈቅረው ነው የጠላሁት ፣ መናፈቅ ከመጀመሬ ነው የረሳሁት ፣. . .አለ ከማሌቴ ነው አለመኖሩን ያመንኩት. . .

አዎ . . .አይን ጨፍኖ እንደመግለጥ ያለ መብነን እንደሱ ነው ለእሱ ያለኝ ስሜት የሆነው. . /ደግሞ ሳይናፍቀኝ በፊት /

እሱ ንብ ነው ፣ እኔ ቢራቢሮ ውብ ቀለማት ካላቸው አበባ ጣፋጭን መቅሰም እንጂ ማር መስራት አላውቅበትም . . . ጓጆዬ ከተመቸኝ ነው ፣ ጓጆው ከቀፎው ነው . . . ለማጣፈጥ ሲከንፍ ፣ ለነፃነቴ በራለው . . . ሚይዘኝ ህግ የለም ህጌ ለራስሽ ጥረሽ ግረሽ ብይ ነው ፣ የሱ ህግ ለሌላው ጥረህ ግረህ አብላ ነው. .

የሁለት ፅንፍ ክንፎችን ያገናኘን ፍቅር ነው. . . አልነደፈኝም . . . ከአበባቤዬ አልተቀናቀነም. .
አዲስ ምዕራፍ ከፈተለኝ. . . በፍቅር ደሴት ላይ ጠፋን . .  ቀዘፍን . .  በጨረቃማ ምሽት ቀስ እያልን  ለስላሳ  ዳንስ ደነስን ፣ ከዋክብትን ተደብቀን አንዳችን በአንዳችን ተከናነብን - ከማሩ ቀመስኩ . .  ከውበቴ ረካ . . .. .  ወቅት ስለመቀዝቀዙ አልተሰማንም በመኖር እየሞቅን ነበር. . .

. . .

በአንዲት ፍልቅልፍ ፀሃያማ ጠዋት ውብ የአበባ ጣፋጭ መዓዛ ለአፍንጫዬ መልዕክት ላከ. .  ትላንቴ ናፈቀኝ . .  ለብቻዬ የቦረኩትን ለምለም ዓለም ድጋሚ ተመኘው . . ለራስ መኖር ፣ ለራስ መጣፈጥ . . . 

ቀፎው ወበቀኝ የማሩ ጣም እጅግ ወደሚመር ግዑዝነት ተለወጠብኝ አሁኔን ጠላሁት. . .

"ልበር ነው. .  'ብቻዬን'  " አልኩት

"የመጨረሻ ቁርስ እንብላ . .  'ነገ ' ?" ጠየቀኝ
. .  ግራ ሚያጋባ ክፉ  ጥያቄ . .

"ለሊቱን የመታገስ አቅሙ የለኝም ፣ ክንፎቼ ስለዋል . . . አሁን እንዲያልፈኝ አልፈልግም "

"ከመጣሽ አለው . . . "

"ቦታውን ማስታውሰው አይመስለኝም"

"ደህና ሁኚ "

"አንተም ሁን . . "

. .   . .

ጠዓሙንም ፍቅሩንም ለመርሳት የአነሳሴን ደቂቃዎች አልፈጁብኝም . . . . ከፍ ብዬ በረርኩ . .  ፍቅር ለቢራቢሮ እስር ቤት ነው ፣ አቀማጣይ አባባይ ' እስር ቤት' . . ከናፈኩት መስክ ፣ ካማሩኝ አበባዎች ተንሸራሸርኩ . .

. .

በኃላ አለፍ አለፍ ያሉ ጠዋቶች ላይ. . ጎህ ሳይቀድ ከአልጋዬ ተነስቼ በልቤ ውስጥ እንዳለ ስዳብሰው ነፍሴ ሲለሰልሳት ምን ያህል ደስታ ይሰማኝ እንደነበረው አይነት ደስታ ናፈቀኝ

ያለመኖሩ ጅማሬ ቀላልና ልክ እንደሌሎቹ ትናንሽ ህይወት ሁሉ ተራ ሆኖ እደታየኝ አሁን አልታይ አለኝ ፣  . . .  ወደሱ ከነፍኩ . . .

. . .  በናፋሻማ ሜዳ ላይ የምንወደውን ቁርስ አቅርቦ ነበር . . .  አየኝ አየሁት ፣ ያን ቁርስ ልትበላ ምትመጣ ንብ ካለች ብዬ ጠበኩ ወደቦታው የመጣ ነፍስ አልነበረም . . . .
.
.
.

ንብ🐝
.
.
. በአንዱ ጠዋት እንደምትመጣ አውቃለው ፣ ስለምወዳት ነው የለቀኳት ፣ እንደምትወደኝ ስለማውቅ ነው የጠበኳት . .  ተፈጥሮዋ ነው ያበረራት ያን ያሸነፈ ፍቅር ነው ያመጣት . . .
. . . አንድ አይነት አደለንም . .  አንድ አይነት ፍላጎት አልጠብቅም. . . 

. .  አሁንም ትሄዳለች  . .  እኔንም ፍቅሬንም ትረሳለች. . .   .

ተፈጥሮዋ ነው መብረር . .  ትጠፋለች . .  ፍቅር ነው እውነቷ ተመልሳ ትመጣለች . . 

           /ትዝታ /

| ❀:✧๑♡๑✧❀|
         @tiztawe
         @tiztawe
ೋ•✧๑♡๑✧•ೋ


እንዴት አለፈዳቹ 💚. . .

ከ - ህሌኒ ፣ zowi ፣ wijdan ፣ Nar di . . . ተጨማሪ ቤተሰቦችን ብጠብቅ ብጠብቅ ሚልክልኝ ጠፋ 😢. . .

እናላቹ ውድድሩን ለመጨረስና አሸናፊውን ለመሸለም ወሰንኩ . .

እናላቹ የላካቹልኝን ሁላቹንም በሃይል አመሰግናለው ፣ ፅሁፍን በማንበብና በማበረታታት አብራቹ የነበራቹ ቤተሰቦችንም
በሃይለኛው አመሰግናለው . . !!

እና ከአሁን በኃላ የሚጨመሩ (❤️😍👍🙏👎. . . ወዘተዎች) ለውድድሩ ቆጠራ ውስጥ አይገቡም . .

አሁን በመጨረሻ በቆጠርኩት መሰረት. .

ህሌኒ . . . አንድ ቤተሰብ እንደላይክ ይቆጠርልኝ ያለውን ድምፅ ጨምሮ 27 ድምፅ ሽልማቱን ምትወስድ ይሆናል. . .

ሁላቹንም ግን ላያቹበት እይታ ፣ ስለ ቆንጆ ፅሁፋቹ እጃቹም አምሯቹም ይባረክ😊

❤️


🪔. . . . . . .


ምን እንደሆንኩ እንጃ አስታውሻት የማላውቀው ትርሲቴ ትዝ አለችኝ።እየትኮላተፈች  "ሊወድቅብህ ነው ጋሼ" ብላ ወደ ኪሴ ጠቆመችኝ ።በመውደቅ እና በመኖር መሀል ያለችውን ያየቻትን አስር ብር ሰጠዋት።
ትርሲት የት ትሆን ?ይሄኔ አግብታለች ተመርቃለች ...አይ ትርሲት ደስ እምትል ሰው ነበረች።" አልሁት ለራሴ።

....ከአመት  በዋላ ግን አለም ምን ያህል ጠባብ እንደሆነች አየሁ...እራሴን ፈራሁት እራስ ወዳድነቴ አስደነገጠኝ። "አይንዋ! እራስዋ ናት"።
እዪኝ
በቬሎ ሞሽርያት እድሜ ልኬን የስዋ ለመሆን በእግዜሩም በስዉም ፊት ቃሌን የስጠዋት ሴት በደስታ የምሆነው አታ ትፍነከነካለች በሚዜዎችዋ ታጅባ ትዘፍናለች
""ለለኔ ደስታ በማሰብ አንተ ደስታህን አተህ እንደኖርክ እኖራለሁ ደስ ብሎኝ ደስ ሲልህ
የማልቀይረው የማለውጠው ላንተ ያለኝ ፍቅር እኔ
ቃላት የለኝም አብሮኝ ይኖራል ለዘለአለም....""
....እየሰማዋት አልነበረም።
እይዋት
በቃሌ የስበርኩዋት ፤በቀቢፀ ተስፍ የሞሸርኩዋታ፤ እነዝያን ተስፈኛ ቀኖችዋን አንድ በአንድ ጨፈላልቄ የገደልኩባት ድሪቶ አልብሼ የነፍሴን ክፍይ አስታቅፊያት ከሩቅ የድንኳን በር ተለጥፍ ታየኛለች ....እንደ ደቀልድ ብለን ያለፍናቸው ልጅነት ነው ያልንላቸው እኛ ባስቀመጥናቸው ልክ የተቀመጡ የመሰለን  ብዙ ትላንቶቻችን ውስጥ ከቁም ነገር ቆጥረውን ዛሬያቸውን እኛ ውስጥ ለመስራት  ሲዳክሩ ስንት ጉድ የሰራናቸው ይኖሩ ይሆን...

.............
አላለቀስኩም ፤አላማረርኩም ፤ከርቀት ደንዝዤ ነበር  ያየሁት  ።አልገረመኝም ምክንያቱም እያየሁ ያደኩትን ነገር ነው ያደረገው ከአባቴ የሚለየ ባደባባይ አስጨብጭቦ ና በእልልታ ትጅቦ  መካዱ ነው ምፅ ለኔና ለእናቴ ! ።ጥልቅ ሀዘን እብደትን ይወልድ ይሆን እንጃ። በሌባ ጣቴ እየጠቆምኩዋት  "አየሽው ነጭ ሱፍ ለብሶ ቁጭ ያለው አባትሽ ነው አልኩዋ  እናቴ ያወረሰችኝን እጣፈንታ እንዳላወርሳት ልሸሻት ስለፈለኩ።

/Nar di/


| ❀:✧๑♡๑✧❀|
         @tiztawe
         @tiztawe
ೋ•✧๑♡๑✧•ೋ

#4


🪔. . . .

ያልዋኘሁት ውቅያኖስ
ያልደረስኩበት ሰማይ
ያላየሁት ተፈጥሮ ያልቀመስኩት ጣዕም ያልኖርኩትንንን ሁሉ አስታወሰኝ.....

እግሬን ካነሳሁበት ከተወቺኝ ከራኩዎት ከመሰለኝ ሀገሬ ከወጣሁ የእድሜ ፍርድ ሚዛኑ ይሁን ?? ወይ ከሀሳቤአልተማዘኑም እንጃ ግን አልተወሳሰቡም....
ሙቅ ፍቅሬን በአንዳች ሀይል አምቄ ሙቅ ፍቅሬን ከደረቴ እንዳተምኩ በድኑ እኔን ተሸክሜ ነበር የምተራመሰው.....
"በውስጡ የሚያረግፋቸውና ቀጥሎም የሚያበሰብሳቸው እነሱንም ሌላ ለሚያድጉ ተፈጥሮዋች ማዳበርያ ማድረጉ ነው"
አይኖቾ ውስጥ ፀዳል አይቻለሁ አልተማፀነችም ስለመቅረት ስለ ሰጋቶም አልነገረችኝም ፍቅሯ ልጅነቷ ውብ ናቸው..
ትርሲቴ ሰዋዊነቷ ስብዕናዋ ሁሉ ገዝቶኛል ወደ ሇላ ጥሎት የመጣው የኔ ገላ አልመስል አለኝ...
'ሄኖኬ'
'አቤት'
'ትወደኛለህ?' 'አዎና '
'ምን ያህል?' 'ከእቅፌ መውጣት ባሰብሽ ቅፅበት ልቤ ምትደነግጠውን ያህል'
አልኳት በዛ በሙቅ አልጋ በእቅፌ እንደደበኳት
አይን አይኔን እያየች ከውስጤ ምትመረምረው እውነት ያላት እየመሰለኝ በልስላሴቸው ግራ ሚያጋቡ ጣቷቾን ፊቴ ላይ እያተራመሰች....
'አፈቅርሀለሁ የልጅነቴ ውብ ክፍል አንተ እቅፍ ውስጥ ባለሁባቸው ቀናቶች ውስጥ የተፃፉ ናቸው' ያለቺኝ...
እውነት ውብ ልጅነቷ ያኔ ነበር ወይስ የኔ የጨለመ ልጅነት ጥላ ያረፈበት ያ ወቅት ነበር ??..ልቤ ራስ ወዳድነት ፍቅር ስላይደለ ለኔ ያዘነበለ መሰለኝ የለመለመ ጨፌ ቀስ በቀስ እያንኮታኮትኩ ፀጥ ያለው ውቅያኖስ በዝግታ ያደፈረስኩ ያህል..



ብስራት የያዘ መሳይ መርዶ ነጋሪ የልጅነት ውበት
የቱን ይሆን የሰጠችኝ??
የቱንስ ይሆን የቀማሁዋት??
ምን አገኘሁ ብዬ ምኖንስ ነስቻት ይሆን??
አሁን ማዘን አልቻልኩም ማለፍም መመለስም አልፈቀድኩም ያኔ አለማፍቀር እንዳልቻልኩት..

'ልጅነት ሲያብብ ውበቱ ይጨምራል ዋጋው በጥንካሬ ይከበባል '
'ሰውነት ፍቅር ነው ሰው መሆን ማለት ያለ ስስት ማፍቀር ነው'  ትረሲቴ ሰው ነበረች ..

ትልቅ ጩሀት ነበር ከሀሳቤ ያነቃኝ ኑኑ እሶን ወደሇላ ትቶ ወደፊት የለም ብዬ ነበር ባገኘሇት መስመር እየተመለስኩ የነበረው መድረሴንም አላስተዋልኩም ነበር ..መኪናዬን ያቆምኩበትና የወረድኩበት ቅፅበታዊ ነው
በፈጣሪ ስም ራሴን ማመን አልቻልኩም ጉልበቴ ሲታጠፍ መሬቱ እንጂ እኔ አልተሰምኝም.....

ሀኪም ቤት ለመድረስ አልዘገየሁም እነዛ እምቡጥ የወይን ፍሬ የመሰሉ እግሮቾ ከነካኩት ጨሸቃማ ጨርቆች ላይ ቀይ ደም ማድመቂያ መስለው ተቀብተዋል እነዛ ስስ የደረቁ ከንፈሮች መንቀሳቀስ አቅቶቸዋል እነዛ በተማፅኖ ተመልክተውኝ የነበሩ አይኖች አሁን ተከድነዋል..

ሰውነቴ እስከዛሬ የኔ እንዳልሆነ ከብዶኛል እንዴት አዝዤው እንደሆነ እንጃ አልጋውን እየገፋሁ ሶምሶማ ላይ ያለሁት ..
'ከዚ ማለፍ የተከለከለ ነው'

የማሽቀንጠር ያህል የወረወረኝ መሰለኝ በሩ እላዬ ላይ ሲዘጋ ባለሁበት ተዘረርኩ
'ባቦቦቦ'
ልቤን የወጋኝ ቃል
መራቅ ያልቻልኩት ያስደነገጠኝ የኑኑ እናት ድምፅ የሆነው ሁሉ ህልም ነው አልያስ ሆኖል አይኔ እምባ አምቆል..



'ልጅነቴን'
'ህይወት አለሜን'
በሁለት ሰዎች ተይዛ ጩሀቶ ክሊኒኩን እያናወጠው ... ተበጥሮ ውሀ  ነክቶት ማያውቀው ሚመስለው ፀጉሯ ላይ ሻሽ አስረለች በፀሀይ ከበለዘው ፊቶ ውስጥ ድብቅ  ውበቶ ያሳብቃል ወፈር ያለ አንድ እጁ ጉርድ ሹራብ አርጋለች  ረዘም ያለ መሀል መሀሉ ቅድ ያለበት ጉርድ ለብሳለች በወገቦ የታሰረውን ረጅም ሻሽ ጫፍና ጫፉን ይዛ ጉልበቶ እየተንቀጠቀጠ እጇን እያወናጨፈች ታለቅሳለች....
ቀና ማለት ፈራሁ ሰውነቴ ግራ አጋባኝ አይቼ ለማዘን ወይ ችላ ለማለት መኖሬ ልጀነቴ ዳርቻውም ጨለማ የሆነ ያህል ,,,
ኑኑ- የናቷ የተስፋ ጭላንጭል -የመኖር ብርሀን
-ነፃ አውጪ መሆንዋን አዋጅ ትላለች ,,,
ያቀረቀርኩት አንገቴን አቀናሁ  አይኖቼን ከፈትኩ...

'ትርሱ'


/✍wijdan/


| ❀:✧๑♡๑✧❀|
         @tiztawe
         @tiztawe
ೋ•✧๑♡๑✧•ೋ

#3


🪔. . . . . . .

ወደኋላ የቀረውን እኔን ለመመለስ ለምን ይሆን የከበደኝ?ያን "ኑኑ" የሚል ሙቅ ድምጽ የት ነበር የማውቀው?ከዚህ ሀሳብ ለመላቀቅ ለምን ይሆን የከበደኝ?.....ሌሊት ላይ አንድ የዘነጋሁት የረሳሁት ነገር ከእንቅልፌ አነቃኝ....ወደ አውስትራሊያ ከመሄዴ በፊት የነበረኝ የፍቅር ግንኙነት....ትርሱ...አዎ የእሷ ድምጽ ነው....እንዴት ሊሆን ይችላል?እንዴት እንደዚ ዓይነት ህይወት...ከመለያየታችን በፊት ያሳለፍነው ሁሉ በአይኔ ውልብ አለ።ሌሊቱን ይህን ሳብሰለስል አድሬ ሲነጋልኝ ወደ ትላንቱ ቦታ አመራሁ....ትርሱን እና ኑኑን ማየት ናፈቀኝ።ምክንያቶችን ማወቅ ፈለግኩኝ።....ከአውስትራሊያ ከመጣሁ በኋላ ትርሱን ፍለጋ ወደ ህፃናት ማሳደጊያው ሄጄ ነበር።ግን ምንም መረጃ ማግኘት አልቻልኩም ነበር....ያጋጣሚ ነገር እንዲ ሊያገናኘን ወደደ መሰለኝ በዚህ መልኩ ልንገናኝ ነው...ከቀናኝ....
.
.
.
ሌሊቱን ሙሉ ስለ እሱ ሳስብ አደርኩ።ለምን ተደበቅኩ ግን?...እንዳይጠላኝ ይሆን?ወይስ እንዳይሳለቅብኝ?ወይስ ተስፋ አድርጌ ስጠብቀው የኖርኩት እሱ ለእኔ ግድ እንደሌለው እንዳይነግረኝ ፍራቻ?ወይስ ኑኑዬን እንዳይወስድብኝ?...መልስ ያላገኘሁለትን ጥያቄ ሳሰላስል አደርኩ...ጠዋት ፀሀይ ሙቀቷን ለፍጥረት ያለማድላት በምትሰጥበት ሰዓት እኔና ኑኑዬም ይቺኑ ፀሀይ እየሞቅን ሳለ ሄኖኬን ከርቀት አየሁት(እኛን እየፈለገ ይሆን ወይስ እዚህ አካባቢ የሚያስመጣ ነገር ኖሮት?)...ምንም ያክል ምክንያቱን ለማወቅ ብጓጓም እንኳን ከእሱ ጋር የመተያየት ድፍረትን ስላጣሁ ኑኑዬን ይዤ ከአካባቢው ተሰወርኩ።
.
.
.
በጠዋት ኑኑዬን ወደ አገኘሁበት አካባቢ ሄድኩ።አይኖቼ እሱዋኑ ፍለጋ እዚም እዛም ተቅበዘበዙ።ግን አይኔ ውስጥ አልገባ አለች።የት ይሆን ከዚህ ስፍራ ውጭ ላገኛቸው የምችለው?...ትናንት ወድያው የትርሱን ድምጽ ስሰማ ባለማስታወሴ እራሴን እየወቀስኩ ተመለስኩ።ግን ከአይምሮዬ ውስጥ ሊወጡልኝ አልቻሉም።...ትርሱ ምን አይነት ሁኔታ ላይ እንዳለች ለማወቅ ልቤ አብዝቶ ጓጓ።እናም ተስፋ ሳልቆርጥ ላፈላልጋቸው ለራሴ ቃል ገባሁ።
.
.
.
እኛ ምንኖርበት አካባቢ በተደጋጋሚ እየመጣ አይኖቹ ሲቅበዘበዙ አየው ነበር።እኛን እየፈለገ እንደሆነ ግልጽ እየሆነልኝ መጣ።ግን እኔ ፊት ለፊት እሱን ለመገናኘት ድፍረትን ለምን አጣሁ?ይሄን ያህል ምን አስፈራኝ?የማውቀው፣የምናፍቀው፣የምወደው ሄኒ አደል እንዴ?....ግን አገኛታለሁ ብሎ ባላሰበበት ሁኔታ እሱን ማግኘት ከብዶኛል።ግን ቢሆንም ለመጋፈጥ ወሰንኩ።
.
.
.
በቀጣይ ቀን
.
.
.
እንደለመደው ወደ ሰፈራችን በጠዋት መጣ።እኔና ኑኑዬ ፀሀይ እየሞቅን ነበር።ልክ እንደሌላው ጊዜ አልተደበቅኩም።ባለሁበት ሆኜ እየተከታተልኩት ነበር።ኑኑዬ እንደለመደችው(ሁሌ ሰው ስታይ እንደምታደርገው)ሮጣ ሄዳ እግሩ ስር ቆመች።በጣም በመደሰትና በርህራሄ አቅፎ አገላብጦ ሳማት።አይኖቼ እንባ እንዳረገዙ በዝምታ አያቸዋለሁ።ከዛም ዞር ዞር ብሎ ሲያይ አይን ላይን ተጋጨን።ኑኑዬን እንዳቀፋት ወደ እኔ መጣ።ምን እንደያዘኝ አላውቅም ግን ከተቀመጥኩበት ቦታ መነሳት እንኳን አልቻልኩም ነበር...በዝግታ ከጎኔ ተቀመጠ።በመገረምና በስስት አይኖቼን ያያል።እጆቹ እየተንቀጠቀጡ ወደ እኔ ዘረጋቸው...አቀፈኝ...ታቀፍኩለት።ከአይኖቼ የሚወርደውን እንባ በሚንቀጠቀጡ ጣቶቹ አበሰልኝ...አልከለከልኩትም።ድሮ የማውቀውን ጠረኑን አሸተትኩ...አልተለወጠም።
.
.
.
ትርሱን ሳያት ድብልቅልቅ ያለ ስሜት ተሰማኝ።ደስታ...ሀዘን...ራስ ወዳድነቴ ያመጣው ጣጣ...ትርሱ ተጎሳቁላለች...ያኔ በህፃናት ማሳደጊያ ውስጥ ያየኋት ቆንጅዬዋ፣እንቡጧ ትርሱ የለችም...ተለውጣለች።ስንለያይ የገባሁትን ቃል አስታወስኩ...ቃሌን ባለመጠበቄ በራሴ  አፈርኩ...ተሸማቀቅኩ።ለመጨረሻ ጊዜም የተናገረችውን ነገርም አስታወስኩ...ልትነግረኝ የፈለገችው ነገር ነበር ግን እኔ ራስ ወዳጅነቴ አሸንፎኝ ልሰማት አልደፈርኩም ነበር...አሁን ምን ልትለኝ እንደነበር ገባኝ...የትርሱን ህይወት አመሰቃቅዬውም እንደ ኮበለልኩ ገባኝ...ብቻዋን በዚህ ሁሉ መከራ እንድታልፍ እንደፈረድኩባት ገባኝ...ፀፀት አንገበገበኝ...እንባ ከአይኖቼ ሲወርድ ልብ አላልኩም ነበር።ትርሱ በጣቶቿ ስታብስልኝ ከሰመጥኩበት የሃሳብ ባህር ነቃሁ....እሷ ይቅር ባይ ናት...በዚህ ሁሉ እንድታልፍ ምክንያቱ እኔ ብሆንም አልገፋችኝም አልተቀየመችኝም...የኔ የዋህ...የኔ እርግብ...ከዚህ በኋላ ኑኑዬን እና ትርሱን መልቀቅ አልችልም...
.
.
.
ምን እያሰበ ይሆን?አይን አይኔን እያየ በሃሳብ ጭልጥ ብሏል።ከአይኖቹ እንባው ይፈሳል....ቃል ሳንለዋወጥእየተነጋገርን እየተግባባን ነበር።ኑኑዬ ግራ በመጋባት ሁለታችንንም ታየናለች።ሄኒ ከእጁ የምታመልጠው ይመስል ጥብቅ አድርጎ ይዟታል....ኑኑዬ በመጨረሻ አባቷን አገኘች....እሷ እንዳረፈደባት በማየቴ እረፍት ተሰማኝ....ተመስገን!!!

                /Zowi /


| ❀:✧๑♡๑✧❀|
         @tiztawe
         @tiztawe
ೋ•✧๑♡๑✧•ೋ


#2


@tiztawe1_bot ላይ እምቢ ካላቹ . . @Afho19 ላኩልኝ🙏


እረ ተዉ ግን ላኩልኝ😢. . .

. . .. እንደ ፀሃይ መንግስታቹ ሽልማቷ ከወሬ አያልፍም ብላቹ ነው ኣ😔


🪔. . . . . .


አልፎ አልፎ ፀጉሩን አንጨባሮ በመጠጥና ሲጋራ ተነክሮ እጁ ላይ የሚበሉ ነገሮችን አንጠልጥሎልን  ይመጣል ከኑኑ ጋር የናፍቆቱን ይወጣና እንደ አባት አቅፎ ካሰተኛ በኋላ....

"ትርሱ"
"አትበለኝ"
"ለምን?"
"የተፈቀደው ለሄኒ በቻ ስለሆነ"
"ብሸቅ ሄኖክ"
"ትርሲትዬ"
"ወዬ"
"እናቴ ትሙት ቆንጆ ነሸ"
"እሺ"
"ላግባሸ ለኑኑም ጥሩ አባት ልሁናት ጥሩ ቤት ትኖራላችሁ ይሄ ለእናንተ አይመጥንመ"
"ሰካራም  ጥሩ አባት አይሆንም"
"እናቴ ትሙት እናተ ከመጣችሁ እኔ ተዋለው"
"እኛ ሄኖክን እንጠብቀዋለን"
"ብሸቅ ሄኖክ ከንቱ ነው"
   
 "ግን ጥበቃው ሲሰለችሽ ነይ ጠብቅሻለው"

"አይሰለቸኝም ሁሌም ጠብቀዋለው ምኖረው እሱን በመጠበቅ ውስጥ ነው"
      
"ብሸቅ ሄኖክ ከንቱ ዓለም"

**

I met you
in the dark, you lit me up
You made me feel as though I was enough
We danced the night away, we drank too much
I held your hair back when
You were throwing up.....

ለሰርጋችን የምዘፍንላትን ሙዚቃ መርጠናል ሙዚቃ ነፍሷ ነበር! ትርሱ የሁልግዜም ፀፀቴ  ልጅነቷ አጓግቶኝ እንጂ ፈቅር ይዞኝ እንዳልነበር አሁን ያፈቀርኳትን መቲን ሳገኝ የተሰማኝ ስሜት ነበር ያሳወቀኝ!

"እንዴት ሆና ይሆን?"

"ዩንቨርስቲ ገብታ እየተማረች ይሆን?"

"እንደኔ የልጅነት ሰሜት መሆኑ ገበቷት እውነተኛ ፍቅር አግኝታ ወልዳ ከብዳ እየኖረች ይሆን?"

ትርሱ የልጅነት ፀፀቴ መልካሙን ይግጠማት።

**

I'll wake you up with some breakfast in bed
I'll bring you coffee with a kiss on your head
And I'll take the kids to school
Wave them goodbye
And I'll thank my lucky stars for that night . . .

ሃሃሃ እየተረጎመልኝ የሰማሁት ሙዚቃ  ነበር ስንት አልሜበታለው  ለሰርጋችን ሚጋበዘኝ ዘፈን ሃሃሃ ሄኒ የኔ ፍቅር አሁን ግዜው ደርሷል
በየቀኑ 11:00 ሰአት ላይ በኮሰሰችው የላስቲክ ቤታችን በኩል ነፋሰ ይቀበላል ሁሌም ኑኑ ሮጣ ትሄድና ገንዘብ ትጠይቀዋለች እሱም አይከለክላትም ምን አልባት በውስጣቸው ታወቋቸው ይሆን? ወይ ኑኑ እኔን ስለምትመሰል እኔን እያሰታወሰባት ይሆን?
ልነግረው ልታየው ወስንኩኝ ኑኑ የፍቅራችን ፍሬ ናት፣ካንተ ያገኘኋት ስጦታ ናት እሰካሁን በታማኝነት ያለመሰልቸት ጠብቀህናል ልለው ወሰንኩ!

ሲስመኝ የሚሰማኝ ሙቀት ናፍቆኛል...ከሱ ጋር የምሰማው ሙዚቃ ናፈቆኛል....ጠረኑ ናፈቆኛል....ኦው ሄኒ.....

**

ኑኑዬን ለብቻዬ ስወልዳት እንደዚህ ባዶነት አልተሰማኝም!

የጎዳናው ብርድ ከዛሬው ብርድ አልበረደኝም!

ምግብ ፈለጋ ስዞር የሰው ፊት እንደዛሬ አላቃጠለኘም!

ጎዳና ላይ እኔንም ልጄንም ከሰው ከብቶች ሰጠብቅ እንደዛሬ ጉልበት አላነሰኝም!

የፖሊሶች ድብደባ እንደዛሬ አላመመኝም!

ልክ አባቴ እናቴን ሲገላት የነበረውን ህመም አመመኝ!

ሄኒ የሌላ ሴት እጅ ይዟል በኑኑ ፋንታ ሌላ ልጅ አቀፏል!

ጠረኔን ረሰቷል ሌላ ለምዷል!

የኔ ብቻ ሚመስለኝን ሙቀቱን ለሌላ አጋርቶታል!

የገባልኝ ቃልኪዳን የት ሄደ?

ሰው በሕይወቱ ሰንቴ ይከዳል መገፋት እጣ ፋንታ የሆናል?

ብሽቅ ትርሲት ከንቱ ዓለም!!

       
             / . . .ህሌኒ . . /



| ❀:✧๑♡๑✧❀|
         @tiztawe
         @tiztawe
ೋ•✧๑♡๑✧•ೋ


#1

Показано 20 последних публикаций.