ካሸካከምህ
✍🏿 ✍🏿 ✍🏿 ✍🏿 ✍🏿 ✍🏿 ✍🏿 ✍🏿
ስማኝማ ወንድም ፤ ስማኝ ልምከርህ
ኑሮን አታማረዉ ፤ ምንም ቢከብድህ
ችግሩ ይሆናል ካሸካከምህ፡፡
ሁሉም ጫና አለበት ፤ የኑሮ ፈተና
ይዞት የሚዞረዉ ፤ ብሎ ደፋ ቀና፡፡
በእርግጥ ይለያያል ፤ የኑሮ ክብደቱ
እንደ ፍላጎቱ ፤ እንደ እየ ትልምቱ፡፡
ያተ ግን ከታየህ ፤ እጅጉኑ ገዝፎ
የሚጥልህ ከሆነ ፤ ጉልበት አዝለፍልፎ
ለይተህ እወቀዉ ፤ መጀመሪያ አቅምህን
ከዚያም አስተካክለዉ ፤ አሸካከምህን፡፡
ብለኸዉ ብለኸዉ ፤ ካልሆነ ነገሩ
ሳይሻል አይቀርም ፤ ፈትቶ መቋጠሩ፡፡
“ አንተም ከከበደህ ፤ አዉርደህ ተሸከም ወንድሜ ! ”
Via website - https://uutaye.com/post/takeiteasy
https://www.youtube.com/watch?v=tXXQjx1wZR0
@uutaye
@uutaye
✍🏿 ✍🏿 ✍🏿 ✍🏿 ✍🏿 ✍🏿 ✍🏿 ✍🏿
ስማኝማ ወንድም ፤ ስማኝ ልምከርህ
ኑሮን አታማረዉ ፤ ምንም ቢከብድህ
ችግሩ ይሆናል ካሸካከምህ፡፡
ሁሉም ጫና አለበት ፤ የኑሮ ፈተና
ይዞት የሚዞረዉ ፤ ብሎ ደፋ ቀና፡፡
በእርግጥ ይለያያል ፤ የኑሮ ክብደቱ
እንደ ፍላጎቱ ፤ እንደ እየ ትልምቱ፡፡
ያተ ግን ከታየህ ፤ እጅጉኑ ገዝፎ
የሚጥልህ ከሆነ ፤ ጉልበት አዝለፍልፎ
ለይተህ እወቀዉ ፤ መጀመሪያ አቅምህን
ከዚያም አስተካክለዉ ፤ አሸካከምህን፡፡
ብለኸዉ ብለኸዉ ፤ ካልሆነ ነገሩ
ሳይሻል አይቀርም ፤ ፈትቶ መቋጠሩ፡፡
“ አንተም ከከበደህ ፤ አዉርደህ ተሸከም ወንድሜ ! ”
Via website - https://uutaye.com/post/takeiteasy
https://www.youtube.com/watch?v=tXXQjx1wZR0
@uutaye
@uutaye