በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሀዱ አምላክ አሜን👏እንኳን ለአባታችን ለሊቀ መላእክት ቅዱስ ገብረኤል ወርሀዊ ክብር በአል በሰላም አደረሳችሁ
ዘመነ ሰማእታት አምልኮት ፃኦት በተስፋፋበት አምልኮተ እግዚአብሔር በጠፋበት ዘመን መምለኬ ፃኦት የነበር ገዥ አለ ፣እስክንድሮስ፣በክርስቲያኖች ላይ ስደትን ስላወጀ ቅድስት እየሉጣን
የሶስት አመት ህፃን ቅዱስ ቂርቆስን ይዛ ወደ ሌላ ሀገር ተሰደደች👈
ጌታ በወንጌል በአንዲቱ ከተማ መከራ ሲያአሳያአችሁ ወደ ሌላይቱ ሽሹ(ማቴ፣ 0፪3) ያለውን በማሰብ ተሰዳ ሳለች የአላዊዉ መኰንን ወታደሮች ተከታትለው ደርሰው ለፃኦት ስገጂ ፈጣሪሽን ካጂ ቢሏት የዚህን ሚስጥር የሚያየው የሦሥት አመት ህፃን አለ እርሱን ጠይቁት አለቻቸው✍
ከዚህ በሗላ ህፃኑን አስፈልገው ቢጠይቁት፣ ነብዩ ዳዊት የተናገረውን ሀይለ ቃል፣መንፈስ ቅዱስ ተገለፀለት የአሕዛብ ጣኦታት የወርቅ እና የብር የሰው እጅ ስራዎች ናቸው✍
የሚታመኑባቸውም ሁሉ እንደ እርሱ ይሁኑ መዝ ፣(3'፯;፩3፣05)በማለት ሲዘልፏቸው አገር ገዥው ሰምቶ ተቆጣና የብረት ጋን ፣አስመጥቶ፣ ውሃ ሞልቶ፣ከአቶን እሳት፣ላይ ጥዶ፣ ልዩ ልዩ ማገዶዎች በመጨመር ነበልባሉ ከመጠን በላይ ሆነ፣የብረት ጋኑ ድምፅ ክረምት መብረቅና ነጕድጓድ እስኪያስፈራራ ድረስ አስነድዶ ሕፃኑ ከእናቱ ወስዳችሁ ጨምሩአቸው ብሎ አዘዘ👈
በዚህ ጊዜ ቅድስት እየሉጣን በጣም ፈራች የእግዚአብሔር ስራ እፁብ ድንቅ ግሩም ረቂቅ ነው አፉን ያልፈታ የሶስት አመት ሕፃን እናቴ ሆይ ገድላችን እንፈፅም ዘንድ ጨክኝ በርቺ አላት ቅድስት እየሉጣንም ፣ልጄ የነፍስ አባት ሁነኝ አለችው ፣ሕፃኑ ቅዱስ ቂርቆስም፣ከዘመናቸው ሳይደርስ ታሪካቸውን ሳይማር፣የስለስቱን ደቂቅን ታሪክ መንፈስ፣ተገልፆለት፣አናኒያን አዛሪያን፣ ሚሳኤልን ያዳነ አምላክ፣ያድነናል ቢላት ፍርሃቱ ሊለቃት ባለመቻሉ ወደ እግዚአብሔር፣ እንዲህ ሲል ፀለየ፣ ጌታ ሆይ የወይ ፍሬ ስትሻ ግንዱን ታጠፋለህን?
እንደዚህስ ሁሉ እኔን አድነህ እናቴን፣ታጠፋለህን? ብሎ በፀለየ ግዜ መንፈስ ቅዱስ አደረባትና፣መንግስተ ሰማያት፣በአይነ ስጋ እንድታይ አደረጋት
ከዚህ በሗላ ፍርሃቱ ለቀቃት፣ ልጄ ሆይ ከዛሬ ጀምሮ መምህሬ አባቴ መካሪዬ እልሃለሁ እንጂ ልጄ አልልህም ብላ በጭካኔ ከልጅዋ ጋር ወደ ፈላው፣የብረት ጋን፣ገባችበት፣በዚህን ግዜ ህፃኑ ቂርቆስ፣አናኒያን አዛሪያን ሚሳኤልን ያዳነ አምላክ፣ ያድነናል ያለው ቃል፣ለመፈፀም እግዚአብሔር አምላክ፣ መልአኩ ቅዱስ ገብረኤልን ላከላቸው፣መልአኩም በትእምርተ መስቀል እሳቱን ቢባርከው እንደ በረዶ ቀዝቅዞላቸዋል፣
በመልካቸውም እንደ ፅሀይ አበራ ከእግር ጥፍራቸው እስከ እራስ ፅጉራቸው አንድም ሳይጎዳቸው፣በደሕና ወጡ👈
በመጨርሻም ህፃኑ ሰማእተ ቅዱስ ቂርቆስ እንዲህ አለ ይህን ያህል ገደል ተጋድዬ ምን ያክል ዋጋ ትሰጠኛለህ ቢለው ጌታ ያለውን ሁሉ እሰጥሃለሁ፣አለው✝
ዳግመኛም ስጋህ በምድር ላይ እንዳይፈርስ እንዳይበሰብስ በኤሊያስ ስረገላ ላይ አኖርሃለሁ አለው✝
ስለሆነም በዚህ እለት ቤተክርስቲያናችን መልአኩ ቅዱስ ገብረኤል ለእናታችን ለቅድቅት እየሉጣን እና ለህፃኑ ለቅዱስ ቂርቆስ፣ያደረገውን ይህንን ታላቅ ተአምር፣ፅድቅ ስራ በማሰብ ከዋዜማው፣ ጀምራ እግዚአብሔርን ስታመሰግን ትውላለች ታድራለች✍
የመለአኩ የቅዱስ ገብረኤል በረከት✝ ተራዳይነቱ ከሁላችንም ጋር ይሁን አሜን፣
ወስበሀት ለእግዚአብሔር✝
ወለወላዲቱ ድንግል✝
ወለመስቀሉ ክቡር አሜን
@fkl26. @fkl00.