“ራሱን ነጥሎ የወጣው የህወሓት አንጃ የፕሪቶሪያው ስምምነት ሙሉ ለሙሉ እንዳይተገበር እንቅፋት ሆኗል" ዶ/ር ጌዲዮን ጢሞቲዎስ የዉጪ ጉዳይ ሚኒስትሩ
📌አቶ ጌታቸዉ ረዳ ከዉጪ ጉዳይ ሚኒስትሩ ጋር በመሆን ስለ ትግራይ ክልል ወቅታዊ ሁኔታ ከዲፕሎማቶች ጋር ውይይት አካሂደዋል
📌የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶ/ር ጌዲዮን ጢሞቲዎስ እና የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ርዕሰ መስተዳድር ጌታቸው ረዳ የተመራ ውይይት በትግራይ ክልል ወቅታዊ ሁኔታ ዙሪያ በኢትዮጵያ ከሚገኙ የዲፕሎማቲክ ማህበረሰብ አባላት ጋር አካሂደዋል።
📌በመድረኩ ዶ/ር ጌዲዮን ጢሞቲዎስ፤ “ራሱን ነጥሎ የወጣው የህወሓት አንጃ የፕሪቶሪያው ስምምነት ሙሉ ለሙሉ እንዳይተገበር እንቅፋት” መሆኑን ገልጸዋል።
📌በተጨማሪም ምርጫ ቦርድ ጠቅላላ ጉባኤ እንዲያካሄድ የሰጠውን መመሪያ አለመቀበሉን አስረድተዋል።
📌“የፌደራል መንግስት የፕሪቶሪያው ስምምነት ሙሉ ለሙሉ እንዲተገበር እየሰራ መሆኑን” የገለጹት ሚኒስትሩ፤ መንግስት የክልሉን ወቅታዊ ሁኔታ በጥሞና እየተከታተለ ነው ብለዋል፡፡
📌ዓለም አቀፉ ማህበረሰብም በክልሉ የተፈጠረውን ችግር ለመፍታት አስፈላጊውን እገዛ እንዲያደርግ ጥሪ አድርገዋል፡፡
📌በክልሉ ወቅታዊ የሰላም እና ፀጥታ ዙሪያ ማብራሪያ የሰጡት አቶ ጌታቸው ረዳ በበኩላቸው፤ “ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ራሱን ነጥሎ የወጣው የህወሓት አንጃ የጊዜያዊ አስተዳደሩ የዕለት ተለት ተግባራት ላይ እክል እየፈጠረ መምጣቱን” አስረድተዋል።
📌ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ እና የፌደራል መንግሥት በክልሉ ዘላቂ ሰላም ግንባታ ያላቸውን ሚና አጠናክረው እንዲቀጥሉም ጥሪ አቅርበዋል።
የቴሌግራም ቻናሉን Join በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ📥
https://t.me/+WNLm9dbzuIlp9DF4https://t.me/+WNLm9dbzuIlp9DF4ይህንን በቅንነት ሰብስክራይብ በማድረግ ተባበሩ 🔽
https://www.youtube.com/channel/UCrdWHrcXNEhMfbp1ucgxd1g