የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ፕሬስ አውደርዕይ!
አስራ ስድስተኛው የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ፕሬስ የመፅሐፍ አውደርዕይ እና ሽያጭ ከነገ ሰኞ ሚያዝያ 7 እስከ ፊታችን እሁድ ሚያዝያ 13 2016 ዓ.ም ለተከታታይ ሰባት ቀናት ስድስት ኪሎ በሚገኘው የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ዋናው ግቢ ውስጥ ይካሄዳል።
በዚህ የመፅሐፍ አውደርዕይ እና ሽያጭ ላይ የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ፕሬስ ሰባት አዳዲስ መጻሕፍት ይዞ አውደርዕዩ ላይ ይገኛል።
የእነዚህ ሰባት አዳዲስ መጻሕፍት አዘጋጆችም ማክሰኞ ፣ ረቡዕና ሐሙስ ስለ መጻሕፍቶቻቸው ማብራሪያ የሚሰጡበት መርሐግብርም እንደተዘጋጀ ኤቨንት አዲስ ድረገጽ ያገኘው መረጃ ያመለክታል።
በአውደርዕዩም በርካታ ከ30 በላይ አሳታሚዎችና አከፋፋዮች በቅርቡ የታተሙ፣ ከገበያ የጠፉ ፣ የህፃናት መጻሕፍት፣ የሐይማኖት መጻሕፍትን ይዘው ይገኛሉ ተብሏል።
ለተጨማሪው:
https://t.me/EventAddis1ማስታወሻ: ላይብረሪውን በተለያዩ መጽሐፍቶች ማገዝ ለምትፈልጉ አባላትና ምእመናን ይሄንን የመጽሐፍት አውደርዕይ ማየት ትችላላችሁ።