አንድ ትምህርት ቤት የሚማር ተማሪ ቲቸሩ ጋር ሄዶ “ቲቸር የሂሳብ ቀመሮችን መስራት እንደምችል ታዉቂያለሽ? ሰዎች 'ከባባድ' ናቸዉ የሚሏቸዉን መፃህፍትን ሳይቀር እንዳነበብኩ አልሰማሽም??” እያለ ያደረገዉንና ጥግ የደረሰ እዉቀት ባለቤት መሆኑን ሊገልፅላት መሞከሩ አስገርሟታል፡፡
አስተማሪዋም ያወራዉን ሁሉ አዳምጣ ከጨረሰች በኋላ እንዲህ አለችዉ “ሂድና ግማሽ ዉሃ በዚህ ኮዳ ይዘህ ና!”ሔዶ ግማሽ ዉሃ አመጣ...ኮዳዉን አንስታ ስታወዛዉዘዉ አያት፡፡ “ምን ትሰማለህ?” አለችዉ
“የዉሀዉ ድምፅ ይሰማኛል” አላት “ጥሩ! አሁን ደግሞ ይህንን ኮዳ እስከአፉ ድረስ ሞልተኸዉ ና” አለችዉ፡፡ ሄዶ ሞልቶ ሲመጣ ኮዳዉን ተቀብላ ስታወዛዉዘዉ አየና “አሁን ምንም ድምፅ የለዉም” አላት፡፡
እንዲህ መለሰችለት..
.“እዉቀትም እንደዚሁ ነዉ፡፡ በትንሹ ወይም በግማሹ የሚያዉቁ ሰዎች ብዙ ያወራሉ...'ካልተደመጥኩ!፣ጆሮ ካልተሰጠኝ' ብለዉ ችግር ይፈጥራሉ...ነገር ግን ምርጥ ጭንቅላትና የበሰለ እዉቀት ያላቸዉ ባገኙት ነገር ላይ በሙሉ 'እኔ እኔ እኔ!' እያሉ እጃቸዉን አያወጡም፡፡
ማዉራት ሲኖርባቸዉ ብቻ ጥቂት ያወራሉ፡፡በእዉቀት እስከ ገደፉ የተሞሉ ሰዎች ጩኸት አያበዙም፡፡
ረጋ ያሉ ናቸዉ!
"ብልህ ሰዎች ማዉራት ያለባቸዉ ሃሳብ ስላለ ብቻ ያወራሉ ሞኞቹ ግን ማዉራት ስላለባቸዉ ያወራሉ"
http://t.me/worldfunfacts