Yalelet Wondye Gebeyehu


Гео и язык канала: Эфиопия, Амхарский
Категория: Политика



Гео и язык канала
Эфиопия, Амхарский
Категория
Политика
Статистика
Фильтр публикаций


EBC የሚባል የተረኞች ሁሉ ልሳን የሚያስተጋባውን አደገኛ ትርክት ተመልከቱት!!!!!!
ከ12ሺ ዓመታት በፊት ከኦሮሞ ውጭ ያለው የኩሽ ነገድ ሁሉ የኢሬቻን በአል ያከብረው ነበር ብሏል። ለዚህ ታሪካዊ ዘገባ ያስቀመጠው አስረጂ ማጣቀሻና ሎጂክ ግን ማቅረብ አልቻለም።

የገማ ተቋም‼️


የአገዛዙ ፓርቲ ደጋፊም ሁን ችግር የለብኝም። የግለሰብም አምላኪ ሁን ይሄም ግድ አይሰጥኝምም። በአማራ ኮዝ ላይም ወጥ የሆነ መረዳትና የጋራ መግባባትም አይኑረን። ምን አይነት ስብዕናና ሞራል ቢኖራቸው ነው አማራ ሆነው በንፁሃን አማራዎች የዘር ጭፍጨፋና ሞት ላይ የሚሳለቁት?

3.4k 0 2 20 101

አዝኛለሁ የሚለው ቃል የልብ ሀዘንን ይገልፅ ይሆን?
ነፍስሄር


እንኳን ለመስቀል በዓል አደረሳችሁ!
ፈጣሪ ታርቆን አገራችንን ሰላም እንዲያደርግልን እመኛለሁ!


የጋዜጠኞቹ የችሎት ውሎ
*******************
ፍ/ቤቱ በጋዜጠኛ መዓዛ መሃመድና ጎበዜ ሲሳይ እና አሳዬ ደርቤ ላይ ተጨማሪ ቀጠሮ ሰጠ።

ዛሬ መስከረም 16/2015 ዓ.ም የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ የጊዜ ቀጠሮ ችሎት የቀረቡት ጋዜጠኛ መዓዛ መሃመድና ጎበዜ ሲሳይ ለቀጣዩ አርብ መስከረም 20/2015 ዓ.ም ተቀጥረዋል፡፡
ጋዜጠኞቹ ለአርብ የተቀጠሩት ዓቃቤ ህግ በባለፈው ችሎት በተሰጠው የአምስት ቀን የጊዜ ቀጠሮ ውስጥ“ መረጃ ሰብስቤ ስላልጨረስኩ ክስ መመስረት አልቻልኩም ፣ ስለዚህ ተጨማሪ ቀን ይሰጠኝ” ማለቱን ተከትሎ ነው፡፡

አቃቤ ህግ ይህንን ያለው” በመሃል ቅዳሜና እሁድ ስለነበር ግዜ አጥሮኛል፣ በዚህም ያልተመለከትኳቸው የቪዲዮ ማስረጃዎች አሉ” በማለት እንደሆነ የጋዜጠኞቹ ጠበቃ ሄኖክ አክሊሉ ለሮሃ ቲቪ ተናግረዋል፡፡

የጋዜጠኞቹ ጠበቆች ይህንን የአቃቤ ህግ ጥያቄ በመቃውም መከራከራቸውን የገለጹት አቶ ሄኖክ ፍርድ ቤቱም የግራ ቀኙን ክርክር ካደመጠ በኋላ ለመስከረም 20/2015 ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡

በተያያዘ አሳዬ ደርቤ ዛሬ ፍርድ ቤት የቀረበ ሲሆን መርማሪ ፓሊስ የምርመራ ጊዜዬን ጨርሻለው ክስ ለመመስረት ጊዜ ይሰጠኝ ባለው መሰረት ለዓርብ 20/1/2015 ተቀጥሯል!!


ትህነግ/ህወሓትን ከ4 ኪሎ ቤተመንግስት ያስባረረው የአማራ ህዝብ ቁልፍ ጥያቄዎች ምን ምን ነበሩ?

ዋና ዋናዎቹን ለማስታወስ ያህል፤

~ የህገ-መንግስት ማሻሻያ ፣
~ የተዛባ የታሪክ ትርክት፣
~ የወሰንና የማንነት ጉዳይ፣
~ የህዝብ ቁጥር (የተዛባ የህዝብ አቆጣጠር)፣
~ የሰላምና ደህንነት (በህዝብ ላይ የሚፈጸም ማንነት ተኮር ጥቃትን ማስቆም)፣
~ የአዲስ አበባ ጉዳይ፣
~ ፍትሀዊ የፓለቲካ ውክልና ፣
~ ፍትሃዊ የሃብት ክፍፍል (የኑሮ ውድነት ማቃለል) ወዘተ ናቸው::

ትህነግ/ህወሓት ከ4 ኪሎ ቤተመንግስት ከተባረረ 4 ዓመት ሆነው:: ከላይ የተዘረዘሩት ውስጥ አንዱም እስከአሁን አልተፈታም!! እንደውም ተባብሰው የቀጠሉ ችግሮች ውስጥ እንገኛለን::

ችግሮቹም ተባብሰው የቀጠሉበት ሁኔታም እንደሚከተለው ነው!!

~ ሱዳን በአልፋሽጋ በኩል የጎንደርን መሬት ከ60 ኪሎሜትር በላይ ወረራ ፈጽማለች።

~ ትህነግ/ህውሓት በህዝብ ትግል ከህዝብ ጫንቃ ላይ ወርዶ ከ4 ኪሎ ከተባረረ በኋላ ነፍጥ አንስቶ ጦርነት ከፍቶብናል፣ በዚህም የተነሳ አማራ ክልል 288 ቢሊዮን ብር የሚገመት ውድመት አስተናግዷል፣ በሺዎች የሚቆጠሩ አማራዎች ውድ ህይወታቸው አጥተው ከ13ሺህ በላይ ህጻናት ወላጅ አልባ ሲሆኑ በርካታ አዛውንቶችም ያለጧሪ ቀርተዋል፣ በጦርነቱ የተፈናቀሉ አማራዎች በየመጠለያው የስቃይ ኑሮ እየገፉ ነው።

~ ኦነግን የአማራ ህዝብን ከመጨፍጨፍና ከማፈናቀል የሚያስቆመው አልተገኝም፣ ከኦሮሚያ እና ከቤኒሻንጉል ከሞት የተረፉ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ አማራዎች በየመጠለያው የስቃይ ኑሮ እየገፉ ነው።

~ የጉሙዝ እና የቅማንት ታጣቂ ጊዜ የሚጠብቁ ናቸው።

~ የኑሮ ውድነት፣ ድህነት እና ዝርፊያ (የሙስና ወንጀል ) ከምንግዜውም በከፋ ሁኔታ ተባብሶ ቀጥሏል።

ታዲያ ብልጽግና ወይም ለውጡ ለአማራ ህዝብ ምን ለውጥ ፈጠረለት? ምንም!!

ይህ ሁሉ ችግር ያለበት ህዝብ አካል የሆኑት የአማራ ሊሂቃን እስካሁን በጥልቅ እንቅልፍ ውስጥ ናቸው::

ሲሳይ አውግቸው ወንድምተገኝ እንዳስታወሰን!


Видео недоступно для предпросмотра
Смотреть в Telegram
የወሎ ሽለላ እና ፉከራ !

ጎጃም ሀሳብ ገባው ከሳ መነመ፤
በፊት በእነ በላይ አሁን በዘመነ።
    
ያ ዘመነ ካሴ አንድ ሰው ሁኖብኝ፤
እሱን የማይበት አይኔ ደከመብኝ።

እናቱ መነኩሴ ዘወትር አስቀዳሽ፤
ልጅየው አርበኛ የተማረ ተኳሽ።


"ውሻህ አንተ ላይ መጮህ ሲጀምር ሌላ ሰው እየመገበው እንደሆነ ተረዳ"


ጎጃም ጎንደር ወሎ ሽዋ ጉልላቱ
በጥቅሻ ሚግባባ አንድ ነዉ አንገቱ
አንድ ኢትዮጵያ ማለት ነዉር ከሆነማ
ነዉር ይሁንብኝ ማነንም አልሰማ
ነፃነት ነዉ እንጅ ልብ አይታሰርም
ለጊዜዉ ቢያናቅፍ ገል ብረት አይሰበርም
የድሮ ናፋቂዉ ቀድሞ የዘመነዉ
ጥንትም ፋኖ ነበር ዛሬም ያሳምነዉ
ጥቁሬ ነኝ የዘሜ ወንድም

@ ዳኘ ዋለ (የጨነቀለት)


የውሻ ቀዳዳ እየከፈቱ የቀን ጅብን ከሚያስገቡ አደረጃጀቶች እራሳችሁን ጠብቁ። የአዛኝ ቅቤ አንጓቾች መቀለጃ ሆነን እስከመቼ ነው የምንቀጥለው?


አፄ ቴዎድሮስን ያስበላ የባንዳ ቅሪት በዚህ ዘመን መኖሩን ሳይ ማመን አቃተኝ‼️
እግዚኦ


Видео недоступно для предпросмотра
Смотреть в Telegram
በአንድ ዘመነ ካሴ እረፍት ያጣችው ሀገር ይሄን ሁሉ ጉድ ተሸክማ እንደምትኖር እናውቃለን!


በዘመነ ካሴ መታሰር ብዙም አትናደዱ! የታቀደለት ሞት ነበረና።
ዘመነ ካሴ ታሰረም አልታሰረም ለውጥ የለውም። ይልቁንም ዘመነ ካሴን የ "ይገደል" ዘመቻ የጀመሩ ሰዎችን/ቡድን ያሳፈረ ነው። ትላንት ጀግናው አሳምነው ፅጌን አስገድለን በብዙ ተጎድተናል።
ዛሬም ዘመነ ካሴ ባለመገደሉ ደስ ሊለን ይገባል። በመታሰሩ የምናጣው ጥቂት የምናተርፈው ብዙ ነውና።

ችግሩ ግን በዘመነ መታሰር አማራን ከፋፍሎ መጠቀም የሚፈልግ 3ኛ ወገን መኖሩ ነው፤ (ለዚህ ተግባርም ብዙ አማራዎች ተሳታፊ እንደሆኑ እናውቃለን)።
ስለዚህ እንረጋጋ!
አማራ ክልል በተለይም ባህር ዳር ከተማ ውስጥ በፍፁም ሰላም አናደፈርስም። ዘመነ በታሰረበት ፖሊስ ጣቢየም መረበሽ የለብንም። ብልጽግና በባህር ዳር ብዙ ቀይ ለባሾችን ማሰማራቱም የታሰበልልን የሚያሳይ ነው።
ትግላችን ስልታዊ እና የተገመገመ ይሁን። ትላንት ሰሜን ላይ በጦርነት ማግደው መሃል አገር ምን እየሰሩ እንደነበር እናውቃለን። የቅርብ ግዜው እንኳን እነሱ በ 10 ሺዎች ጄኔሌተር ለአርሶ አደራቸው ሲያከፈፍሉ ለእኛ የእህል ጣሳ አሰራጩልን፣ የግዕዝን ፊደል ለ Greece በመስጠት፣ በላይ ዘለቀን ማወረም፣ ወዘተ።
..
ሌላው ባህር ዳር ላይ ዘመነን ለማስለቀቅ የምናደርጋቸው ሙከራዎች ሁሉ እንደ ምክንያት ተቆጥረው ዘመነ ካሴን ወደ አዲስ አበባ ለመውሰድ እንደሚያስቡ መገንዘብ አለብን።

በአጭሩ ዋናው ነገር የዘመነ ካሴ በህይወት መኖር ነው።

#ነገር_ግን አርበኛ ዘመነ ካሴን ወደ አዲስ አበባ ለመላክ መሞከር ትልቅ ዋጋ እንደሚያስከፍል መገንዘብ ተገቢ ነው። የአማራ ክልል ፖሊስ ዛሬ ካወጣው መግለጫ አፈንግጦ ወደ አዲስ አበባ አሳልፎ እንደማይሰጠው ተስፋ አደርጋለሁ።

የእንዳላማው ክንዴ ሃሳብና አቋም የኔም ሃሳብና አቋም ነው።


አዊማ
ኑሀሱ‼️

5k 0 0 11 22



ከትህነግ የከፋ ልክስክስ ስረዓት‼️
****
አንድ የመንግስት ተቋም በዚህ ደረጃ ውሸትና ማጭበርበር ውስጥ ተዘፍቆ ማየት እጅግ ያስገርማል። መጀመሪያ መጽሐፉን ግዕዝን በተመለከተ እራሳቸው አዘጋጅተው ከበተኑት በኋላ እንደገና ሲተቹ ሀሰተኛ መረጃ ነው ብለው ህዝብን ዋሹ።

አዝናለሁ !

#ከዚህ በፊት አዲስ አበባ ግራጫ ትቀባለች ብለው ወስነው ዜና አሰርተው ህዝቡ ሲቃወም ሀሰተኛ መረጃ ነው አሉ። መልሰው ከሰዓት ከግራጫ አይነቶች ምረጡ ብለው በፌስቡክ ለህዝብ ምርጫ አቀረቡ።

እንዲህ አይነት ከወያኔ የከፋ ልክስክስ ዲቃላ ስረአት ነው የገጠመን‼️


አሳዬ ደርቤ የተከሰሰው ከወያኔ ተልእኮ ተቀብሎ በመስራት፣በመተባበር ነው ።
ጆሮ አይሰማው የለ መቼም !!!!!
ወያኔን በሚያስንቅ ስረአት ውስጥ የሚጠበቅ ክስ ነው!


ጋዜጠኝነት ወንጀል አይደለም!
እውነትን በማፈን የሚፀና ስረአት የለም!!
ፍትህ እውነትን ይዘው ለሚታገሉት‼️


♦ በአዲሱ የትምህርት ዘመን በተማሪዎች መማሪያ መጽሐፍ ላይ የተገኘ "መርዝ ቁጥር -፩
መምህራን ይሄንን ለልጆች ቢያስተምሩ ወላጆች ትክክለኛውን እውቀት በማስረጃ ያስረዷቸው ዘንድ ሀላፊነት አለባቸው።

ወላጆች ልጆቻቸው የሚማሩባቸውን መጽሐፍት ማየትና መገምገም ያስፈልጋል።

መምህራንም በሚያስተምሯቸው ተማሪዎች ላይ ሀላፊነት አለባቸውና እውነቱን በመናገር ፣ሀሰቱን በማጋለጥ ተማሪዎቻቸውን እንዲያስተምሩ ይገባል።

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክሳዊት ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ላይ የተጻፈ ስህተት፣ጥላቻ እና በመጽሐፍቶቹ እንክርዳድ ተዘርቶባቸው ከሆነም መምህሩ እውነታውን በማጋለጥ የትውልድ ሀላፊነቱን ይወጣ።

የታሪክ ቅሚያና ጥላቻ ካለበት ያስተውል፣ እውነትን ይናገር።

የኢትዮጵያ ፊደላት(የግዕዝ ቁጥሮች) በኢትዮጵያውያን አባቶቻችን የተፈጠሩ ናቸው።


የትዊተር አካውንቴ ነው። እየተወዳጀን መረጃ እንለዋወጥ!

https://twitter.com/yaleletwondye1?t=S8y3VkEjnKNDFJCJXqazaQ&s=09

Показано 20 последних публикаций.

8 979

подписчиков
Статистика канала