የ666(ኢሊሚናቲ) እና ሌሎች ያልተነገሩ ምሥጢራት


Гео и язык канала: Эфиопия, Амхарский
Категория: Эзотерика


በዚህ ቻናል በዓለማችን ውስጥ ስላሉ ድብቅ ምሥጢር ስለሆኑ
ቦታዎች
ፍጥረቶች 🐾
ሀሳቦች
እና አካላት
የሚያትት ሲሆን ኢትዮጵያም በነዚህ ትላልቅ ምሥጢራት ውስጥ ያላትን ትልቅ ቦታ እንመለከታለን።

Связанные каналы

Гео и язык канала
Эфиопия, Амхарский
Категория
Эзотерика
Статистика
Фильтр публикаций




Репост из: 乙ε ო£Łムk
Gaaffilee Ortodoksootaa hatattamaan deebii Mootummaa barbaadan!
1. Ergaalee fi qabiyyeen Heera mootummaa, ejjennoo siyaasa partilee, Barumsa idilee fi qabiyee midiyaalee keessaatti kalaqamuun Ortodoksootaa fi Barumsa Ortodoksii jibbaa fi balaa adda addaaf saaxilan hatattamaan seeraan akka dhorkaman.
2. Ortodoksoota adda baasee Carraa hojii kan dhorku, angoo itti gafatamummaa mootummaa keessatti akka gahee hin arganne, carraa qabeenya horachuutti akka hin fayyadamne kan taasisu, Caasaan mootummaa Amantaa sadarkaa federaalaa hanga gandaatti diriire hatattamaan dhaabbatee, Amantaa kan bu’uureffate osoo hin taane Ummata giddu gala kan godhate ta’uun isaa hojiin akka mul’atu.
3. Mana Kiristaana Ortodoksii Tawaahido Itophiyaa shira siyaasaatiin qooqaaniifi Sabaan diiguuf yaaliin taasifamu, akkasumas maqaa qorannoo sayinsiitiin shirriiwwan tokkummaa Mana Kiristaanaa diiguuf taasifaman akka dhorkaman.
4. Gochaaleen Ortodoksoota dimshaashaan ajjeesuu, qe’ee isaaniirraa buqqisuu, miiraan daraaruu, Mirgoota isaanii sarbuu, hirmaannaa Siyaasaa fi waltajiilee biyyoolessaa keessaa fo’u hatattamaan akka dhabbatan.
5. Yaakkawwan hanga Ammaatti Mana Kiristaanaa fi Ortodoksoota irratti rawwatamaniif yakkamtoonni seeratti akkaa dhiyaatan. Akkasumas midhamtoonni hundii fi kanneen qe’ee isaaniirraa buqa’an Beenyaa fi gumaa akka argatan.
6. Guutuu biyyatitti Ortodoksoonni qe’ee isaaniirraa buqa’an hatattamaan gara qe’ee isaanitti akka deebi’anii fi mirigi isaanii akka kabajamu.
7. Moqsa Itoophiyaa ishee haraa ijaarra jedhuun Ashaaraa fi Mallatoolee seenaa Ortodoksii balleesuuf adeemsi taasifamu hatattamaan akka dhaabbatuu fi shira ummatarratti jalqabame kanaaf ifaan dhiifamni akka gaafatamu. Gochaaleen badii rawwatamanis akka sirreeffaman.
https://chng.it/2zsqkZ9QLN


Репост из: 乙ε ო£Łムk
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን
ሞዐ ተዋሕዶ
የሞዐ ተዋሕዶ ጥሪ ለኦርቶዶክሳዊያንና በማንኛውም የእምነት መሥመር  ውስጥ ለሚገኙ እና ለሰው ልጅ እኩልነት፣ በነፍስ የመኖር መብት፣ የዜግነት ክብር
የማግኘት እና አምልኮተ እግዚአብሔርን በነፃነት የመፈጸም መብት ለምታምኑ ሁሉ፡- 
ጉዳዩ፡- የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ክርስትናን  ማንነት (Cultural and religious identity) እና የኦርቶዶክስ ክርስቲያንን ዘር ማጥፋትን (Orthodox Christian Genocide ) ስለ መከላከል ፡-
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያንን እንደ አንድ የሃይማኖት ሥርዓታዊ ተቋም ለማዳከምና ተከታዮቿ ክርስቲያኖችን ለማጥፋት ግልጽ ርእዮተ ዓለማዊ፣ ሥርዓታዊና መዋቅራዊ ጥቃት ከተጀመረበት ከ1966 ዓ.ም. እስከ ዛሬ ድረስ ጥቃቱ ቀጥሏል።  በአብዮት፣ በብሔር እኩልነት፣ በመንግሥት ለውጥ እና በጎሣ ግጭት ስም ተሸፍኖ  ሲካሄድ ቆይቶ በአሁኑ ጊዜ ወደ ግልጽ ጥቃት ተሸጋግሯል።  
በተለም ባለፉት 4 ዓመታት በቤኒሻንጉል ጉምዝ፣ በደቡብ ክልል፣ በኦሮሚያ ክልል፣ በአዲስ አባባ ከተማ፣ በአማራ ክልል ልዩ ዞኖች፣ በሶማሌ ክልል፣ በትግራይ ክልል አክሱም  ዳንግላት ማርያም ወዘተ ኦርቶዶክሳዊያን በሃይማኖታቸው ምክንያት ከፍተኛ ፍጅትና ጥቃት ተፈጽሞባቸዋል፣ አቢያተ ክርስቲያናት ተቃጥለዋል፣ ክርስቲያኖች ተፈናቅለው ተሰዳዋል። ኦርቶዶክሳዊንን ማግለል፣ መግደልና ሁለገብ ጥቃት ሥር ማዋል በግልጽ ቢካሄድም አጥፊዎች ሲቀጡ፣ የዜጎችን ደኅንነት መጠበቅ የሚገባው የመንግሥት መዋቅር ግዴታውን ከመወጣት ይልቅ ሲሸፋፍን ማየት የተለመደ  ሆኗል።  
ኦርቶዶክሳዊያንን በገዛ አገራቸው በዘር በቋንቋ እየከፋፈሉ፣ ድብቅ የዘር ፖለቲካ አጀንዳን ወደ ፖለቲካዊ ርእዮት በማሳደግ፣ በመደራጀት፣ በመዋቀርና አመራር በመሥጠት ኦርቶዶክሳውያንን የማጥፋት ሂደቱን ዝም ሊባል ከማይገባው ደረጃ ላይ ደርሷል።  
በመሆኑም የፌዴራል መንግሥት እና የክልል መንግሥታት እና መዋቅሮቻቸው  የዜጎችን ሰላምና ደኅንነት የኃላፊነታቸውን እንዲወጡ ግፊት ለማደርግ የተባበረ ድምጽ ማሰማት ጊዜ የሚሰጠው አይደለም። 
 እናም “እዚህ ላይ ይበቃል” ማለት ይገባል የምትሉ ሁላችሁ ኦርቶዶክስ ክርስቲያኖች እና በሰው ልጅ እኩልነትና ክብር የምታምኑ የሌላ እምነት ተከታዮች ሁሉ ይህን ፔትሽን በመፈረም ለእውነት፣ ለፍትሕ፣ ለሰብአዊነት እንድትቆሙ ጥሪያችንን እናቀርባለን። እውነትና ፍትሕ ለዘላለም ያሸንፋሉ!!!
አስቸኳይ የመንግሥት ምላሽ የሚፈልጉ የኦርቶዶክሳዊያን ጥያቄዎች
1.      በሕገመንግሥት፣ በፖለቲካ ማኒፌስቶ፣ በመደበኛ ትምህርት፣ በሚዲያና መሰል መንገዶች ኦርቶዶክሳዊ አስተምህሮንና ኦርቶዶክሳዊያንን ለጥቃት የሚያጋልጡ መልዕክቶች በአስቸኳይ በሕግ እንዲታገዱ::
2.     ኦርቶዶክሳዊያንን ለይቶ ከሥራ፣ ከመንግሥት ኃላፊነት፣ ከሀብት ማፍራት እድሎች የሚያገል ከቀበሌ እስከ ፌደራል የተዘረጋው ሃይማኖታዊ መንግሥትና መዋቅር በአስቸኳይ እንዲቆምና ሃይማኖታዊ ሳይሆን ሕዝባዊ መሆኑን በተግባር እንዲያረጋግጥ::
3.     ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያንን በቋንቋና በተለያዩ ዘውጎች ለመከፋፈል የሚደረገው ፖለቲካዊ ጥረት በጥናትና በምርምር ስም የሚደረጉ የመከፋፈል ዘመቻዎች እና ተግባራት እንዲታደጉ::
4.     በኦርቶዶክሳዊያን ላይ ያነጣጠሩ የአካል፣ የሥነልቦና፣ የኢኮኖሚ፣ የማኀበራዊ፣ የፖለቲካ፣ የማፈናቀል፣ ከአገራዊ ተሳትፎ የመገለልና የፍጅት ጥቃቶች በአስቸኳይ እንዲቆሙ::
5.     እስከ አሁን የተፈጸሙ ጥቃቶች በዝርዝር ተገልጾ አጥፊዎች ለሕግ እንዲቀርቡ እና የተጎዱት እንዲካሱ::
6.     በመላው አገሪቱ የተፈናቀሉ ኦርቶዶክሳዊያን ወደ ቀደመ ቦታቸው እንዲመለሱ::
7.     “አዲሲቷ ኢትዮጵያ” በሚል ሽፋን ኦርቶዶክሳዊ አሻራዎችን የማጥፋት ፖለቲካዊ ሂደት በአስቸኳይ እንዲገታ እና በግልጽ ይቅርታ ተጠይቆ እርምት እንዲወሰድ


https://chng.it/2zsqkZ9QLN


Репост из: የማንቂያ ደወል / Yemankiya Dewel
ሰበር ዜና - አስቸኳይ የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ተጠራ !!!

ጥር 2 ቀን 2014 ዓ.ም (ተሚማ/አዲስ አበባ)

***

የቅዱስ ሲኖዶስ ጽ/ቤት በመስቀል አደባባይ ጉዳይ ለመነጋገር አስቸኳይ የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ጠርቷል።

በሀገር ውስጥ የሚገኙ ብፁዓን አባቶች በምልዓተ ጉባኤው እንዲገኙ የቅዱስ ሲኖዶስ ጽ/ቤት ለብፁዓን አባቶች የስልክ ጥሪ እያደረገ እንደሚገኝ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

የቅዱስ ሲኖዶሱ ምልዓተ ጉባኤ ነገ ከቀትር በኋላከ 9:00 ሰዓት ጀምሮ እንደሚከናወን ይጠበቃል

#Ethiopia
ተዋሕዶ ሚዲያ ማዕከል
አባቶች አለን ካሉን እኛም አለን ብለን ልንከተላቸውና ረቡዕ ቦሌ መድኃኔዓለም 10 ሰዓት ላይ እንገናኛለን።


Репост из: የማንቂያ ደወል / Yemankiya Dewel
Видео недоступно для предпросмотра
Смотреть в Telegram


Видео недоступно для предпросмотра
Смотреть в Telegram


​​#ጾመ_ነቢያት (የገና ጾም)
ኅዳር 15 ቀን 2014 ዓ.ም

ጾመ ነቢያት በየዓመቱ ከኅዳር ፲፭ ቀን ጀምሮ እስከ በዓለ ልደት ዋዜማ ድረስ የሚጾም፤ #ከሰባቱ አጽዋማት መካከል አንደኛው ጾም ነው፡፡ እግዚአብሔር አምላክ ዓለምን ለማዳን ሲል የሰውን ሥጋ ስለ መልበሱ፤ ወደ ግብጽ ስለ መሰደዱ፤ በባሕረ ዮርዳኖስ ስለ መጠመቁ፤ በትምህርቱ ብርሃንነት ጨለማውን ዓለም ስለ ማብራቱ፤ ለሰው ልጆች ድኅነት ልዩ ልዩ መከራን ስለ መቀበሉ፤ ስለ መሰቀሉ፣ ስለ ሞቱ፣ ትንሣኤው፣ ዕርገቱና ዳግም ምጽአቱ በየዘመናቱ የተነሡ ቅዱሳን ነቢያት በመንፈስ ቅዱስ ተቃኝተው ትንቢት ተናግረዋል፤ ትንቢቱ ደርሶ፣ ተፈጽሞ ለመመልከትም ‹‹አንሥእ ኃይለከ ፈኑ እዴከ፤ ኃይልህን አንሣ፤ እጅህን ላክ›› እያሉ በጾም በጸሎት ተወስነው አምላክ ሰው የሚኾንበትን ጊዜ በቀናት፣ በሳምንታት፣ በወራትና በዓመታት እያሰሉ ሲጠባበቁ ቆይተዋል፡፡

ይህ ጾም የእግዚአብሔርን ሰው መኾን ሲጠባበቁ የኖሩት የነቢያት ትንቢትና ጸሎት በጌታችን መወለድ ፍጻሜ ያገኘበት ወቅት በመኾኑ ‹‹ጾመ ነቢያት (የነቢያት ጾም)›› እየተባለ ይጠራል፡፡ ለአዳም የተነገረው የድኅት ተስፋ ስለ ተፈጸመበትም ‹‹ጾመ አዳም (የአዳም ጾም)›› ይባላል፡፡ ስለ እግዚአብሔር ሰው መኾን በስፋት ትምህርተ ወንጌል የሚሰጥበት ወቅት በመኾኑም ‹‹ጾመ ስብከት (የስብከት ጾም)››፤ የጾሙ መጨረሻ (መፍቻ) በዓለ ልደት በመኾኑ ደግሞ ‹‹ጾመ ልደት (የልደት ጾም)›› በመባል ይታወቃል፡፡

እንደዚሁም ‹‹ጾመ ሐዋርያት›› ይባላል፡፡ ቅዱሳን ሐዋርያት ‹‹በዓለ ትንሣኤን ዐቢይ ጾምን ጾመን እናከብረዋለን፤ በዓለ ልደትንስ ምን አድርገን እናከብረዋለን?›› በማለት ነቢያት የጾሙትን ከልደተ ክርሰቶስ በፊት ያለውን ጾም ጾመዋልና፡፡

በተመሳሳይ መልኩ ይህ ጾም ‹‹ጾመ ፊልጶስ (የፊልጶስ ጾም)›› ተብሎ ይጠራል፡፡ ሐዋርያው ቅዱስ ፊልጶስ በአፍራቅያና አውራጃዋ ዅሉ እየተዘዋወረ በጌታችን አምላካችንና መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስም ወንጌልን በማስተማር፣ ድንቅ ድንቅ ተአምራትን በማድረግ ብዙዎችን ወደ አሚነ እግዚአብሔር ሲመልስ ቆይቶ ትምህርቱን በማይቀበሉ የአፍራቅያ ሰዎች አማካይነት በሰማዕትነት ዐርፏል፡፡

ደቀ መዛሙርቱ ሥጋውን ሊቀብሩ ሲሉም ስለ ተሰወረባቸው የሐዋርያውን ሥጋ ይመልስላቸው ዘንድ ሱባዔ ይዘው፣ በጾም በጸሎት ተወስነው በለመኑት ጊዜ እግዚአብሔር ልመናቸውን ተቀብሎ በ፫ኛው ቀን መልሶላቸው ሥጋውን (አስከሬኑን) በክብር አሳርፈውታል፡፡ ደቀ መዛሙርቱ የሐዋርያውን ሥጋ ካገኙ በኋላ እስከ ጌታችን ልደት ድረስ ጾመዋል፡፡ ስለዚህም ጾመ ነቢያት ‹‹ጾመ ፊልጶስ›› እየተባለ ይጠራል፡፡

ከዚሁ ዅሉ ጋርም ወልደ አምላክ ክርስቶስን በግብረ መንፈስ ቅዱስ እንደምትፀንሰው እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምን መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል ካበሠራት በኋላ እመቤታችን ‹‹ሰማይና ምድር የማይወስኑትን አምላክ ፀንሼ ምን ሠርቼ እወልደዋለሁ?›› በማለት ጌታችንን ከመውለዷ አስቀድማ ጾማዋለችና ይህ ጾም ‹‹ጾመ ማርያም›› በመባልም: ይታወቃል፡፡

በአጠቃላይ በዚህ በገና ጾም ነቢያትም ሐዋርያትም ጾመው በረከት አግኝተውበታል፡፡ እኛ ምእመናንም እንደ እነርሱ በረከትን እናገኝ ዘንድ ይህንን ጾም መጾም እንደሚገባን የቤተ ክርስቲያን አባቶች ሥርዐት ሠርተውልናል፡፡

በዚህም መሠረት የነቢያት፣ የሐዋርያት፣ የጻድቃንና የሰማዕታት አምላክ ከእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም፣ ከቅዱሳን ነቢያትና ሐዋርያት በረከት እንዲያሳትፈን፤ መንግሥቱንም እንዲያወርሰን ዅላችንም በዚህ በጾመ ነቢያት ወቅት በጾም በጸሎት ተወስነን እግዚአብሔርን ልንማጸነው ይገባል፡፡

ምንጭ፡- ፍትሐ ነገሥት ንባቡና ትርጓሜው፣ አንቀጽ ፲፭፡፡
ጾምና ምጽዋት፣ ዲያቆን ቃኘው ወልዴ፤ ገጽ ፵፯ -፶፡፡

ወስብሐት ለእግዚአብሔር፡፡


ይቀጥላል ብለን እስካሁን ዝም ያልንው በደረሰብን ችግር ነዉ አሁን ከዛው እቀጥላለን ሼር ማድረጉን አይርሱ።
ሀብ ሲቲ ላይቭ ማነው?
ሀብ ሲቲ ላይቭ ይህ ፕሮጀክት ሲነሳ ተደጋግሞ የሚነሳ ስም
ነው፤ በአሜሪካ አገር የሚገኝ ድርጅትና የፕሮጀክቱ ሃሳብ
አፍላቂም ተደርጎ ይነገራል። ሀብ ሲቲ ላይቭ ማነው?
በእኛ በኩል ስለ ድርጅቱ ለማወቅ ጥረት ብናደርግም ጥቂት
ሰዎች ከወደዱት የፌስቡክ ገፅና በቅርቡ አገልግሎት
እንደሚሰጥ ከሚገልፅ ድረ -ገፅ
(www.hubcitylive.com) በስተቀር በቂና የተደራጀ
መረጃ ማግኘት አልቻልንም።
ይህንኑ አስመልክተን የጠየቅናቸው ሚኒስትር ዲዔታው
የቴክኖሎጂ ከተማ የመገንባቱን ሃሳብ በምክክር መድረኩ
ወቅት ያቀረበው ሚካኤል ካሚል የተባለ ጥቁር አሜሪካዊ
እንደሆነና በመስሪያ ቤቱም በተደጋጋሚ ሲመላለስ ያዩት
እርሱን እንደሆነ ገልጸውልናል።
ድርጅቱ ከኢትዮጵያ አሊያም ከመስሪያ ቤቱ ጋር የቀደመ የስራ
ግንኙነት ስለመኖር አለመኖሩም ዕውቅናው እንደሌላቸው
ተናግረዋል።
"ያገኙትን አፍሰው ቢበሉት፣
ያስቸግር የለም ወይ ሲውጡት" እንዳለችው ድምጻዊቷ
ይህ ባልሆነበት ሁኔታ እንዴት ስምምነት ላይ መድረስ ተቻለ
ያልናቸው ሚንስትር ዲዔታው፤
የአንድን ፕሮጀክት ተግባራዊነት ደረጃ የማወቂያ ጥናት
(Feasibility study) ሃሳባዊ፣ ቅድመ ትግበራና ትግበራ
በሚባሉ ሶስት ደረጃዎች ማለፍ እንደሚገባው ያብራራሉ።
በመሆኑም "ፕሮጀክቱ በሃሳባዊ ደረጃ ያለ በመሆኑ፤ ግንዛቤ
የመፍጠርና ፕሮጀክቱን የማስተዋወቅ ስራ ነው የሚሰራው፤
እኛም እሱ ላይ ነን" ሲሉ ይናገራሉ።
በዚህም መሰረት ጥቅምና ጉዳቱን፣ ማህበራዊ፣
ኢኮኖሚያዊ፣ አካባቢያዊ ተግዳሮቶችና ሌሎች ጥናቶች
ይደረጋል፤ የጥናቱ ውጤት ታይቶ ፕሮጀክቱ ሊቀር ይችላል፤
በከፊል ሊስተካከል ይችላል፤ አሊያም እንዳለ ሊቀጥል
ይችላል።
ይህ ፕሮጀክትም ከሶስቱ የአንዱ እጣፈንታ ሊገጥመው
ይችላል ይላሉ።
ቴክኖ ቱሪዝምን፣ ፈጠራንና ኢንዱስትሪን ያስፋፋል ብለው
በማመናቸው ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ፕሮጀክቱን በሃሳብ
ደረጃ እንደተቀበለው ደጋግመው ያስረዳሉ።
የገንዘብ ምንጩ
20 ቢሊየን የአሜሪካ ዶላር እንደሚፈጅ የተገመተለት ይህ
ፕሮጀክት ምንጩ ምንድን ነው?
አቅም ያላቸውና በዓለም ላይ የሚኖሩ ጥቁር ህዝቦች
ተባብረው ይገነቡታል፤ ዋናኛው የገንዘብ ምንጭም በተለያየ
ሙያ ዘርፍ የተሰማሩ ጥቁር አሜሪካውያን ባለሃብቶች
እንደሚሆኑም ይታመናል።
ሃሳቡን የሚደግፉ ሁሉ ከተማዋን እንዲገነቡ ይደረጋል፤
በተለይ በአገር ውስጥ ያሉ ባለሃብቶች ድርሻ ከፍ እንዲል
ጥረት እንደሚደረግ ኮሚሽነር አቶ ጌታሁን መኮንን ይገልፃሉ።
"ድርጅቱ ሃሳቡን ይዞ የመጣው፤ ገንዘብ ማሰባሰብ
እንደሚቻል አምኖ ነው" የሚሉት ደግሞ ዶ/ር ሹመቴ ናቸው።
ከዚህ ቀደም ከድርጅቱ ጋር በነበራቸው ውይይትም
እውነተኛውን የቴክኖሎጂ ከተማ ለማየት ፍላጎት ያላቸው
በርካታ ግለሰቦች እንዳሉ ተገልጾላቸዋል።
በመሆኑም የሚጠቅም ሆኖ እስከተገኘ ድረስ እጃቸውን
አጣጥፈው የሚቀመጡበት ምክንያት እንደሌለና እንደ
መስሪያ ቤት የበኩላቸውን አስተዋጽኦ እንደሚያደርጉ
ያረጋግጣሉ።
"ይህ የሚሆነው ግን ጥናቱ ተጠናቆ መተማመኛ ሲገኝ ነው"
ይላሉ።
ይቀጥላል
@yaltenegeru_mistroch
@yaltenegeru_mistroch
@yaltenegeru_mistroch


የፕሮጀክቱ ጥናት
በአማራ ክልል የኢንቨስትመንት ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ
ጌታሁን ሁብ ሲቲ ላይቭ ይዞ የመጣው ሃሳብ ዱብ እዳ
ሳይሆን ላለፉት 7 ዓመታት ጥናት እንደተደረገበት ያስረዳሉ።
"የጥናቱ ውጤትም በተለያየ ጊዜ ይገለጽልን ነበር" ብለዋል።
ብላክ ፓንተር ፊልም ለዕይታ የበቃው በአውሮፓውያኑ ጥር
2018 ነው፡፡ በእርሳቸው ንግግር ፊልሙ የጥናቱ የልጅ ልጅ
ቢሆን ነው።
ሁለቱን የሚቃረኑ ሃሳቦች አድምጠን በጥናቱ ላይ የተሳተፉት
እነማን ናቸው ስንል የጠየቅናቸው ኮሚሽነሩ፤
"በጥናቱ ባለቤትነት ደረጃ ተሳትፈናል ማለት የሚቻል
አይመስለኝም" ሲሉ መልሰዋል፤ ይሁን እንጂ ለከተማው
ግንባታ ወደተመረጠው ቦታ በመሄድ የተመለከቱ
ባለሙያዎች እንዳሉ ተናግረዋል።
ይህንኑ ጥያቄ የሰነዘርንላቸው በሳይንስና ቴክኖሎጂ
ሚኒስቴር ሚንስትር ዲዔታ ዶክተር ሹመቴ ግዛው
"ባለኝ መረጃ መሰረት ፊልሙን ለመስራት የተሰራ ጥናት
ካልሆነ በስተቀር፤ ከተማውን ኢትዮጵያ ውስጥ ለመገንባት
የታሰበው ፊልሙ ከወጣ በኋላ ነው" ይላሉ።
የፕሮጀክቱ ሃሳብ ወደ መስሪያ ቤታቸው ከመጣ በጣም
አጭር ጊዜ እንደሆነ ባይክዱም፤ "ፊልሙን ለመስራት
ሲታሰብ ብዙ የተሰራ ጥናት ሳይኖር አይቀርም" ሲሉም
የምናልባት ምላሻቸውን ሰጥተውናል።
በ20 ቢሊየን ዶላር የሚገነባን ትልቅ የፕሮጀክት ሃሳብ ጋር
በዚህ አጭር ጊዜ መዋሃድ ያስችላል ወይ ስንል
የጠየቅናቸው ዶ/ር ሹመቴ፤
"አንድን ነገር ለመረዳት አንድ ቀን፣ አንድ ወር አሊያም አስር
ዓመት ሊወስድ ይችላል፤ነገር ግን አስር ዓመት የሚፈጀውን
በአንድ ቀን ተገንዝቦ መጨረስ ከተቻለ በቂ ነው" ሲሉ
ይሞግታሉ።
ሊያሳስበን የሚገባው ከጊዜው ይልቅ ጠቀሜታው ነው
ይላሉ።
ሀብ ሲቲ ላይቭ ማነው?
ይቀጥላል
share ማድረግ አይርሱ
@yaltenegeru_mistroch
@yaltenegeru_mistroch
@yaltenegeru_mistroch


እስቲ ትንሽ ወደኋላ መለስ እን በልና ስለ ዋካንዳ እና ስለ ጣና እናውራ ።
በብላክ ፓንተር ፊልም ላይ በምናብ የተሳለው ዋካንዳ
ከተማ በኢትዮጵያ በዕውን ሊሰራ መሆኑ ከተገለፀ አንስቶ
የበርካቶች መነጋጋሪያ ሆኗል።
ከተማው በአንድ በኩል የአፍሪካውያን የባህልና የታሪክ
ማንነት መገለጫዎች የሚሰባበሰቡበት ፣ በሌላ በኩል
በሳይንስና ቴክኖሎጂ ዘርፍ ምርምር የሚካሔድበት፣ ሮቦቶች
የሚርመሰመሱበት፣ ሮኬት የሚመጥቅበት ፣ በሌላኛው ገፅ
የንግድ ልውውጥ የሚካሄድበት እና የሚከናወንበት
የኢንዱስትሪ ክፍለ ከተማ፤ የሚገማሸረውን የአባይ ፏፏቴንና
ሸንተረሮቹን ጠዋት ማታ አሻግሮ ለማየት በሚያመች መልኩ
ይገነባል ተብሏል።
ይሁን እንጂ ዕቅዱን ቅዠት ነው፤የአገሪቱን ነባራዊ ሁኔታ
ያላጋናዘበ ነው ሲሉ ያጣጣሉትም አልታጡም።
ፕሮጀክቱ ሀብ ሲቲ ላይቭ በሚባል ፕሮጀክት ስም በፊልሙ
ላይ የሚታየውን የምናብ ከተማ በእውነት ለመገንባት
ታቅዷል።
"ኢትዮጵያ የጥቁር ህዝቦች መኖሪያ፣ የቀደመ ስልጣኔ
ምንጭና መገኛ ቦታ ነች፤ ስለዚህ ምንጩ ላይ በአጠቃላይ
በዓለም ላይ የሚኖሩ ጥቁር ህዝቦች የሚጋሩትንና
በቴክኖሎጂም በባህልም የበለፀገ ከተማ እንገንባ የሚል
ሃሳብ ያለው ነው" ይላሉ በአማራ ክልል የኢንቨስትመንት
ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ ጌታሁን መኮንን።
ሀብ ሲቲ ላይቭ የቴክኖሎጂ ከተማውን ዋካንዳን ካሊፎርኒያ
ውስጥ ለመገንባት የቀደመ ሃሳብ ቢኖረውም፤ እውነተኛ
ዋካንዳ ግን አፍሪካ ለዚያውም ኢትዮጵያ ውስጥ ነው መሆን
ያለበት በሚል በደቡብ ፣ በኦሮሚያ እንዲሁም በባህርዳር
የሚገኙ ቦታዎችን ሲያስስ መቆየቱን የሚናገሩት ደግሞ
በሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ሚንስትር ዲዔታ የሆኑት
ዶክተር ሹመቴ ግዛው ናቸው።
በመጨረሻም በአማራ ክልል የሚገኘው ጢስ አባይ በፊልሙ
በምናብ ከተሳለው የቴክኖሎጂ ከተማው (ዋካንዳ) ጋር
ተመሳስሎ በማግኘታቸው የክልሉን መንግስት ጋር ንግግር
እንደተጀመረ ይገልፃሉ።
ከክልሉ መንግስት ይሁንታ ከተገኘ በኋላ ሃሳቡ የቴክኖሎጂ
ከተማን መገንባት በመሆኑ ድርጅቱ ከሳይንስና ቴክኖሎጂ
ሚኒስቴር ጋር መወያየት እንደጀመረ ዶክተር ሹመቴ
ይናገራሉ።
ፕሮጀክቱ ቴክኖሎጂን ከማሳደግ፣ቱሪዝምን ከማስፋፋት፣
ኢንቨስትመንትን ከማበረታታቱ የሚኖረውን አስተዋጽኦ
በማለም ሃሳቡን ወደዱት፤ የመጀመሪያው የምክክር
መድረክም በሚኒስቴር መስሪያቤቱ ተካሄደ።
በቅርቡ በባህር ዳር ከተማ ሁለተኛው ውይይት ይደረጋልም
ብለዋል።
ተፈጥሮውን ከመጠበቅ ጋር የሚጋጭ ነገር እንደሌለ
የሚናገሩት ኮሚሽነር ጌታሁን መኮንን "ሌሎች የሐይድሮ
ኤሌክትሪክ ማመንጫ በመዘየድ የጢስ አባይ ፏፏቴ ወደ
ቀድሞው ግርማው መመለሱ የፕሮጀክቱ አካል ነው" ሲሉ
ይገልፃሉ።
ይቀጥላል.....
@yaltenegeru_mistroch
@yaltenegeru_mistroch
@yaltenegeru_mistroch


############
ሌላው እና አነጋጋሪዉ
ቢል ጌትስ ኮሮናቫይረስን
ለመዋጋት ማይክሮchip implants ን ለመጠቀም አቅዶ
ነበር የሚባሉ ሚዲያዎች ሐሠት መሆናቸውን ተናግረዋል
ቢል ጌትስ የኮሮናቫይረስ በሽታን ለመዋጋት ማይክሮchip
implants በመጠቀም እንደሚሰራ በማኅበራዊ ሚዲያ
ላይ የቫይረስ ጥያቄ አቀረበ ፡፡ አብዛኛዎቹ ልጥፎች ጌትስ
“ለኮሮኔቫቫይረስ የተፈተነ እና የክትባት ማን እንደሆነ
የሚያሳዩ 'በሰው ሰራሽ ሊመስሉ የሚችሉ ካፕተሮችን“
ዲጂታል ሰርቲፊኬቶች ”ያነሳሉ ይላሉ ፡፡
############

ምንጭ
https://www.reuters.com/article/uk-factcheck-coronavirus-bill-gates-micr/false-claim-bill-gates-planning-to-use-microchip-implants-to-fight-coronavirus-idUSKBN21I3EC
ከላይ ያሳየዋችሁን መረጃዎች ሳያቸዉ አንድ ነገር አሰብኩኝ።
ምን አሰብክ ብትሉ ጅራፍ እራሱን ገርፎ እንደሚጮህ ሁሉ እነሱም በኋላ ሰው አልቀበልም እንዳይላቸው እያለማመዱት ይመስለኛል ።
እንዳሉት ውሸት ከሆነ አሰየው ሆኖም መጠንቀቁ አይከፋም
ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ሕዝበቿን ይባርክ!!!
@yaltenegeru_mistroch
@yaltenegeru_mistroch
@yaltenegeru_mistroch


*በአሁኑ ጊዜ በጣም ሰፊ እና አነጋጋሪ የሆኑ ስለ corona virus እናወራለን*
የማይክሮሶፍት መስራች እና ቢሊየነር የበጎ አድራጎት ስራ ሠሩ
ቢል ጌትስ መሰረታቸው ሰባት ተስፋ ሰጪ የኮሮና ቫይረስ ክትባቶችን የሚያመርቱ ፋብሪካዎችን
ለመገንባት የገንዘብ ድጋፍ እያደረገ ነው ብለዋል ፡፡
ኮሮና ቫይረስ በዓለም ዙሪያ መስፋፋቱን በመጥቀስ
ቢል እና ሜሊንዳ ጌትስ ፋውንዴሽን
ባወጣው ቅንጭብ ቪዲዮ ላይ እንደተናገሩት ፣
ቢል እና ሜሊንዳ ጌትስ ፋውንዴሽን መሰረቱን ለመቆጠብ
ለሰባት ክትባት እጩዎች የማምረቻ አቅም በመገንባት
ወደፊት እየገሰገሰ ነው ብለዋል ፡፡
@yaltenegeru_mistroch
@yaltenegeru_mistroch
@yaltenegeru_mistroch

ምንጭ
https://thehill.com/changing-america/well-being/prevention-cures/491006-bill-gates-is-funding-factories-for-7-potential


እግዚአብሔር ለምን መቅሰፍት ያመጣል?
(አባ ገብረኪዳን)
በልብ መታሰቡ በቃል መነገሩ ስሙ ይክበርና ቸሩ አምላካችን እግዚአብሔር ፍጥረቱን ለመጥቀም ስለ ሦስት ነገር መቅሰፍትን ያመጣል።
፩. " ከመ መቃብር ክሡት ጎራዒቶሙ - ጉረሯቸው እንደተከፈተ መቃብር ነው " ለሚላቸው ሰዎች። ማለት መቃብር ቢቀብሩበት ቢቀብሩበት
በቃኝ እንደማይል ኃጢአትን በቃኝ ለማይሉ ፥ መመለስን ለማያስቡ መመለስንም ለማይፈልጉ ሲል መቅሰፍትን ያመጣል። ሰው ኃጢአትን
ከመደጋገሙ የተነሳ ኃጢአት ወደ ልማድ ይለወጣል። በልማድ ከመታሰሩ የተነሳ ልቡ ይደነድናል። ልቡ ከመደንደኑ የተነሳ ጽድቅን ይጠላል ፥
ኃጢአት ይጣፍጠዋል ። ከዚህ በኋላ ጽድቅን ሁሉ ይቃወማል። " እስመ ግዘፈ ልብ ዘልፈ ይትቃዎሞ ለጽድቀ እግዚአብሔር - የደነደነ ልቡና
ዘወትር የእግዚአብሔርን እውነት ይቃወማል " እንዲል ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ። ከዚህ ሲያልፍ ምሕረት እንኳ ያስጠላዋል። መጨረሻ ላይ
ለማይረባ አዕምሮ ተላልፎ ይሰጣል ። ከዚህ ወዲያ በግብሩ አውሬ ወይም ሰይጣን ይሆናል ። አንድ ሰው በዚህ ግብር ለመያዙ የደዌው
ምልክት ምንድን ነው ቢሉ በኃጢአት አለማፈር ና በግፍ መደሰት ፤ ከዚህም አልፎ በግፍ መኩራት ይታይበታል። ቀደም ብለን እንዳነሣነው
እጁጉን በሽታው እንደጸናበት የፍጻሜ ምልክቱ ደግሞ ምሕረትን መስማትም አለመፈለግ ነው ። እንዲህ አይነት ሰው ደግ መሥራትቱስ
ይቅርና ሃይማኖቱን እንኳ እስከማጣት ይደርሳል። "የሌለውን ያንኑ ይወስዱበታል " የተባለው ይኸው ነው።
ሊቁም " ኢይትከሃሎ ለብእሲ ለእመ ኢያግኀሰ ርእሶ እምግዕዘ ልማድ - ሰው ከፈቃደ ልማድ ማእሰር ራሱን ካላራቀ ሃይማኖታዊ ምእመን
መሆን አይቻለውም " ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ትርጓሜ እብራውያን ፳፪
መመለስን ለማይሻ ፣ ምሕረት ለማይፈልግ ፣ ልቡ ለደነደነ ፣ አዕምሮው ለተነሣው ፣ ሕሊናው ለከዳው " እሰማው ዘንድ እግዚአብሔር ማን
ነው " በሚል እንቢተኛ ልብ ለጸና ሰው መቅሰፍት ይታዘዝልታል ። ለምን ቢሉ ምሕረተ እግዚአብሔርን ላልተጠቀመባት ሰው ፍትሑ
ትፈርድበታለችና።
ይህ ሰው ሞቱ ሁለት ጥቅም አለው። መጀመሪያ "ወባሕቱ በአምጣነ ኢትኔስሕ ትዘግብ መቅሰፍት ለርእስከ - ነገር ግን ንስሐ
እንዳለመግባትህ ለራስህ ፍዳን ታከማቻለህ " እንዳለው ሐዋርያው ቆይቶ ፍዳን ከሚጨምር መሄዱ ይሻለዋልና ስለዚህ ነገር
እግዚአብሔር ይቀስፈዋል። ሌላው ደግሞ ንስሐ ለመግባት ያለቀውን የተሰጠውን ዘመንና ትምህርት ላልተጠቀመበት ሰው መቆየቱ
ለሌላው ስቃይ እንዳይሆን ስለዚህም ይቀስፈዋል። አስር ምክር ተሰጥቶት ላልተመለሰ ፈርዖን ቢቆይ በሕዝበ በእስራኤል ላይ ስቃይ
ከመጨመር በቀር እርሱ እንደማይመለስ ባወቀ ገንዘብ እግዚአብሔር በባሕር ውስጥ እንዳሰጠመው ማለት ነው። እኛንም " ወይእዜኒ አመ
ሰማዕክሙ ቃሎ ኢታጽንዑ ልበክሙ - አሁንም ቃሉን ብትሰሙ ልባችሁን አታጽኑ " ያለን ዕድል ፈንታችን ጽዋ ተርታችን እንዲህ እንዳይሆን
ነው።
፪. ሁለተኛ መቅሰፍት የሚመጣው " ቅን ልቡና ላላቸው ፣ የተንኮል ጥበብ ለሌለባቸው ፣ እግዚአብሔርን ለማይሸነግሉ ፣ በብልጠት
መጽደቅ ለማይፈልጉ ፣ በቅን መንገድ ሆነው ፣ ድካማቸውን ተረድተው " ኢታብአነ እግዚኦ ወስተንሱት - አቤቱ ወደ የፈተና አታግባን "
ለሚሉ ሰዎች እግዚአብሔር ደዌውን ሞትን ያመጣል። የፈተና ቀን ምንድን ነው ቢሉ መከራ ፈርተው ክርስቶስን የሚክዱባት ቀን ናት ይላሉ
አበው። ስለዚህ በጭንቅ ቀን የእምነት ትጥቃችን እንዳይላላ በክንፈ ርድኤትህ ከልለን ፤ ለሚሉና
"አማን መነኑ ሰማዕት ጣዕማ ለ ዛ ዓለም ወከአዉ ደሞሙ በእንተ እግዚአብሔር ፥ ወተዐገሡ ሞተ መሪር በእንተ መንግሥተ ሰማያት
ተሣሃለነ በከመ ዕበየ ሣሕልከ - ሰማዕታት በእውነት የዚህችን ዓለም ጣዕም ናቁ ። እግዚአብሔርን ስለ መውደድም ሰውነታቸውን
ለሕማም ለሞት አሳልፈው ሰጡ ደማቸውንም አፈሰሱ። ስለ ጣዕመ መንግሥተ ሰማያትም መራራ ሞትን ታገሡ። አቤቱ እኛ ግን እንደ
ሰማዕታት እሳቱን ስዕለቱን ፥ እንደ ባሕታውያን ድምፀ አራዊቱን ጸብዓ አጋንንቱን ፥ እንደ መነኮሳት ዕፀብ ገዳሙን ፣ ፍትወታት ርኩሳት
ኃጣውእ ርኩሳቱን ታግሠን መጽደቅ አትቻለንምና እንደ ምሕረትህ መጠን ማረን " እያሉ የሚለምኑትን እግዚአብሔር በመከራ ጽናት
እንዳይናወጹ በጊዜው ይወስዳቸው ዘንድ መቅሰፍትን ያመጣል። ይህን የሚያደርገው መቆየታቸው ያለቻቸውን ጥቂት ምግባር
እንዳያሳጣቸው ሃይማኖታቸውን እንዳያስክዳቸው ነው።
ከኢትዮጵያውያን ጻድቃን እንዷ እናታችን ቅደስት ወለተ ጴጥሮስ ይህንን አድርጋለች። በሚቀጥሉት ጊዜያት መከራ እንደሚመጣ በጸጋ አውቃ
ከመንፈሳዊ ልጆቿም ጥቂቶቹ በድካማቸው ካሉበት መንፈሳዊ ሕይወት መከራው እንዲያናውጻቸው በተረዳች ጊዜ ፤ አርድእቶቿን በሞት
እንዲወስድላት እግዚአብሔርን ለምና እንዲሞቱ አድርጋለች። ቆይተው በመከራው ተናውጸው ሲኦል ከሚወርዱ ያለቻቸውን በጎ ሕይወት
ይዘው የምድሩ እድሜ ቀርቶባቸው ዘለዓለም ቢኖሩ የተገባ ነውና ። እግዚአብሔርንም እንዲህ በሚለው የቅዱስ ዳዊት መዝሙር ነበር
የለመነችው " እስመ ይኄይስ እምኀይው ሣሕልከ - አቤቱ ከሕይወት ቸርነትህ ይሻላል "። ይህ ማለት በምድር ኃጢአት ሊጨምሩ ከመኖር
የምድሩ እድሜ ቀርቶ አጥሮ በቸርነትህ የዘለዓለም ሕይወትን መውረስ ይሻላልና ማለት ነው ። ነቢዩ በሌላም ስፍራ " አቤቱ በኃጥኣን
ድንኳን ከመኖር ይልቅ በአንተ ቤት መጣል ይሻላል " ። በዚህ ዓለም ቆይተን ኃጢአትን ጨምረን ኪፈረድብን በሞት ተጥለን ዘለዓለም
ብንኖር በእውነት ይሻለናልና ። ይህንን ማድረግ የሚቻለው ግን እርሱ ባለቤቱ ሕያው እግዚአብሔር እንጅ ማንም አይደለም ። ራሱን የፈጠረ
ሰው እንደሌለ ማንም ራሱን ቢገድል ራሱን ጣዖት ማድረጉ ነው።
፫. ሦስተኛው ደግሞ እግዚአብሔር በሚያመጣው መቅሰፍት የሚጠቀሙ ሰዎች እድሜ ለንስሐ የተሰጣቸው ናቸው ። ክብር ይግባው ስሙ
ይመስገንና አቡሃ ለምሕረት እግዚአብሔር ካልዘራበት አያጭድም ካልበተነበት አይሰበስብም ። ማለት ሳያስተምር አይፈርድም። ስለዚህ
ሰውን በብዙ መንገድ ለድኅነት ይጠራል ። መምህራንን ለሚሰማ በመምሕራን ፥ በትሑት ሰብእና በቅን ልቡና በበጎ ሕሊና ሆነው
ሊሚፈልጉት በመጻሕፍት ፥ ይህ ሁሉ ላልተሳካላቸው በሥነ ፍጥረት " ወኩሉ ዘተፈጥረ ለመፍቅደ ነባብያን ቦ እምኔሆሙ ለምሕሮ ወቦ
እምኔሆሙ ለአንክሮ ወቦ እምኔሆሙ ለተዘክሮ - የተፈጠረው ፍጥረት ሁሉ በነፍስ ለባውያን ነባብያን ሕታዋን ሆነው ለተፈጠሩ ለሰዎች
የተፈጠረ ነው። ከተፈጠሩትም ፍጥረታት ለትምህርት የተፈጠሩ አሉ። ለአድናቆት የተፈጠሩ አሉ ፤ እግዚአብሔርን ለማሰብ የተፈጠሩ አሉ "።
እንዳለ አረጋዊ መንፈሳዊ
በስነፍጥረት ላልተማረም በአዕምሮ ጠባይዕ ያስተምራል ። በዚህ ሁሉ ለላልተመለሰም በተአምራት ያስተምረዋል ።
ይህንን ሁሉ አልፎ ወደ እግዚአብሔር ያልተመለሰ ሰው በመቅሰፍት ይማራል ። ፈጣሪ የለም የሚል ሰነፍ ልቡ እንኳን ቢሆን በመቅሰፍት
እግዚአብሔር እንዳለ ያውቃል። ለሚጨነቁት የማያዝኑ ሲጨንቃቸው ርኅራኄን ይለምዳሉ ። ፍርድ የጎደለው ድኻ ተበደለ የማይሉ
ባለሥልጣናት ፈራጅ እንዳለ ያውቁ ዘን መቅሰፍት ይመጣል። ክንደ ብርቱ ነን ብለው ቋንጃ የሚቆርጡ ፥ ደም የሚያፈሱ ........
..... ቤት የሚተኩሱ ፦ ከእግዚአብሔር ጸባዖት - ከአሸናፊው የሠራዊት ጌታ ከሕያው እግዚአብሔር ክንድ በታች ሥር መሆናቸውን
ተረድተው ይመለሱ ዘንድ መቅሰፍት ይመጣል ።
@yaltenegeru_mistroch
@yaltenegeru_mistroch
@yaltenegeru_mistroch


#ኤረር_ተራራ
በአለማችን ላይ ድብቅና ምስጢራዊ ተብለው ከሚነሱ ታላላቅ ስፍራዎች መካከል አንዱና የቀዳሚነት ደረጃ ይዞ የሚገኘው ኤረር ተራራ ነው፡፡ ምንም እንኳን ይህ ተራራ ከአዲስ አበባ በቅርብ ርቀት የሚገኝ ቢሆንም አብዛኛው ሰው እንዲሁ እንደዘበት ስለዚህ ተራራ የሚነገሩ ንግርቶችን ከማድመጥ በዘለለ ስለዚህ ታላቅ ስፍራ የሚያውቀው ነገር የለውም፡፡
ለማንኛውም ኤረር ተራራ
1. የአዳም ርስት ሀገር ማዕከላዊ ስፍራ
2. የመጨረሻውን ዘመን መምጣት አብሳሪ የሆነው የቅዱስ ሩፋኤል መቀመጫ ስፍራ
3. የታላቁ የሊቀ ካህን መልከጸዲቅ ስድስቱ የክብር ዕቃዎችን መጠበቂያ ስፍራ
4. የማዕከለ ሰብዕ መሰብሰቢያ ስፍራ
5. የእነዚህ ህዝቦች መጓጓዣ የሆኑት ክንፍ ያላቸው ፈረሶች መገኛ ስፍራ
6. የታላቁ የስውራን መንፈስ መውጫ ስፍራ
7. የኢትዮጵያ የዳግም ትንሳኤ ሀሳብ መነሻ ስፍራ
8. #የህይወት_መፀሀፍ (መፀሀፈ ራዚኤል)አባታችን አዳም ከገነት ከወጣ ቡሀላ ቅዱሳን መላእክት ያስተማሩት የሰማያተ ሰማይ ብሎም የምድራዊ ሰማያት ሚስጥራትን ጥበባትን ለልጆቹ #ለኢትዮጵያን ማስተማርያ ይሆን ዘንድ በ እግዜብሔር ፍቃድ በድንጋይ ላይ በግእዝ ቋንቋ ፅፎ አስቀመጠላቸው ይህ መፀሀፍ መፃፈ ራዚኤል ብለን የምንጠራው ነው።ይህም መፀሀፍ በዚ በኤረር ተራዎች ከመሬት በታች በሆነው ስውሩ ስፍራ ይገኛል።ኢትዮጵያ ድሮ ታልቅ የሆነችበት ሚስጥር ይሔን መፀሀፍ በመጠቀሟ ነው።

9. በስተመጨረሻም የሰው ወገኖች ሁሉ መሰብሰቢያ ስፍራ ነው፡፡

እነዚህ እኛ የጠቀስናቸውን እና አሁን ልንጠቅሳቸው ያልፈለግናቸውን ምስጢራት ኤረር ተራራ ይዞ ይገኛል፡፡ እኛም በዘመናችን ስለዚህ ስፍራ በተገለጠልን እና በተረዳነው መጠን እነዚህ ምስጢራት በዚህ ዘመን የሚገኝ የሰው ልጅ እንዲያገኛቸውና እንዲጠቀምባቸው ለማድረግ በዚህ ስፍራ ላይ ሙሉ ጊዚያችንን ሰጥተን እየሰራን እንገኛለን፡፡ ከእነዚህም ስራዎቻችን መካከል ከዚህ ታላቅ ተራራ በአራት አቅጣጫ ከሚፈልቁት ምንጮች መካካል አንደኛውን በተገለጠን እና በተሰጠን ጥበብ መጠን ለሰው ልጆች አገልግሎት እንዲሰጥ አድርገናል፡፡
ምንጭ፡ጤንነት ሰጠኝ
@yaltenegeru_mistroch
@yaltenegeru_mistroch
@yaltenegeru_mistroch




ውድ የኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነት ተከታዮች በሙሉ በያላችሁበት
ሰላማችሁ ይብዛ፡፡ እንግዲህ እኔ ለማለት የፈለግኩት÷
# ከታች በምስሉ እንደምትመለከቱት የመስቀል ምልክት ያለበት
ሽንት ቤት(በተለይ በወንዶች ውሃ-ሽንት ቤት) በየኮሌጆች;
ዩኒቨርሲቲ; ማሰልጠኛ ተቋማት; ሆቴል-ምግብ ቤቶች
ወዘተ..መስቀሉን እዬተሸናበት ስለሆነ ባገኘነው ኣጋጣሚ # ሼር
በማድረግ ያላወቀን እያሳወቅን የሃይማኖት ግዴታችንን እንወጣ፡፡
መስቀል ኃይላችን ነው ፣ኃይላችን መስቀል ነው ፣ የሚያፀናን
መስቀል ነው ፣ መስቀል ቤዛችን ነው ፣ መስቀል የነፋሳችን መዳኛ
ነው፡፡
ስለሆነም ሼር በማድረግ ኣደራችንን እንወጣ፡፡
እግዚኣብሄር ህዝቡን ይባርክ ፥ መስቀልን ለሚደፋሩ ኣእምሮ
ይስጣቸው፡፡ እመ ብርሃን ቅድስት ድንግል ማርያም በምልጃዋ
ትርዳን፡፡ አሜን አሜን ኣሜን
@yaltenegeru_mistroch
@yaltenegeru_mistroch
@yaltenegeru_mistroch


ተ ቱ ቲ ታ ቴ ት ትርጉም እንመለከታለን። በግዕዝ ቋንቋ መሰረት የተ ፊደል ዘሮች ጠልሰማዊና ፊደላዊ ፍች አላቸው። ፍቻቸውም ምድራዊ ብቻ ሳይሆን ሰማያዊም ጭምር ነው::
1ኛ) ጠልሰማዊ ፍች፦
ተ ማለት ምዕራብ ምስራቅ ሰሜን ደቡብ፣ ቅርፀ አዳም፣ ማዕከላዊ: መስቀል: በሁሉ ላይ የተሾመ ማለት ነው::
ቱ ማለት "አዳም ብቻውን እንዳይሆን ከግራ ጎኑ ሰው እንፍጠርለት" ማለትን ያመለክታል:: ከአንድ ሁለት መሆንን ያሳያል::
ቲ ማለት ዲያቢሎስ በቀኝ የነበረውን አዳም በግራ ሊያደርገው መንቀሳቀሱን ማለትም የሄዋንን መሳሳት የሚጠቁም ነው::
ታ ማለት የአዳም እና የሄዋን በሰሩት ሃጢያት መፀፀትና ወደ ፈጣሪያቸው መመልከታቸውን: ከግራ ወደ ቀኝ እንዲመልሳቸው መማፀናቸውን ያሳያል::
ቴ ጠልሰም እጅግ ትልቅ ሚስጥርን የያዘ ነው:: ለአምስት ሺህ አምስት መቶ ዘመን በሲኦል በዳቢሎስ ቀንበር ሲማቅቅ የነበረን ነፍስ ሁሉ ለማዳን 'ቴ' ኢየሱስ ክርስቶስ ወደ ሲኦል መውረዱን የሚያመላክት ነው:: ይህ 'ቴ' በተዓምረ ኡራኤል ላይ የሚነበብ ነው:: ይህ ጠልሰም ጌታችን ለአዳም የገባለትን ከ5500 ዘመን በኃላ የሚፈፀመውን ከላይ የተገለፀውን የምህረት ስራ ከርቀት የሚያሳይ ነው::
ት ማለት ትህትና ነው:: ጌታችን አዳምን ሁሉ ሊያድነው በቀራንዮ መሰቀሉን ያመለክታል:: ትዕግስትም ነው:: እንዲሁም በ ታ የተጸጸተው አዳም ከታች ወደ ላይ መነሳቱንና በቴ መዳኑን ያሳያል።
ቶ ማለት ክርስቶስ ተነስቷል በአባቱም ቀኝ ተቀምጧል:: አዳም ዳግም ወደ ክብሩ ተመልሷል:: በስሙ ለሚያምኑት ለተጠሩት ልጅነትን ከኃይል ጋር ሰጣቸው:: የሰማይናንና የምድርንም መክፈቻ ቁልፍ ሰጣቸው:: በማለት አባቶች ያመሰጥሩታል::
2ኛ) ፊደላዊ ፍች፦
ተ ማለት ተሰብአ ወተሠገወ እማርያም እምቅድስት ድንግል ማለት ነው፡፡
ቱ ማለት መዝራዕቱ ለአብ ማለት ነው፡፡
ቲ ማለት ተአኳቲ ለእግዚአብሔር ማለት ነው፡፡
ታ ማለት ታው ትጉህ እግዚአብሔር ማለት ነው፡፡
ቴ ማለት ከሣቴ ብርሃን ማለት ነው፡፡
ት ማለት ትፍሥሕት ወሐሤት ማለት ነው፡፡
ቶ ማለት ነአምን ልደቶ ለክርስቶስ ማለት ነው፡
@yaltenegeru_mistroch
@yaltenegeru_mistroch
@yaltenegeru_mistroch


የ "ቶ"መስቀል ምስጢር
***
# ETHIOPIA | “ቶ” የግዕዝ ሠባተኛዋ ፊደል ነች፡፡ ሠባት ቁጥር ትልቅ ትርጉም ያላት ነች ፍፁምነትን የምታመለክት ነች፡፡ ሠባተኛው ዙፋን የጌታ እንደሆነ፣ ሠባተኛው ቀን ሠንበት እንደሆነች፣ 7 ቁጥር ብዙ ሚስጥር አላት፡፡ “ቶ” ሠባተኛዋ ቁጥር በመሆኗ ፍፁምነትን የምታመለክት ነች፡፡ ክርስቶስን የምትወክል ነች፡፡ ክርስቶስ ለኛ ሲል በቀራኒዮ መስቀል ላይ ራቁቱን መሠቀሉን የምታመለክት ነች። ትልቁ ከዚህ በላይ ያለው ሚስጥር አባቶቻችን ከመፅሐፍ ቅዱስ ትርጔሜ ሲተነትኑ በሰማይ መላዕክት ዘንድ ውጊያ ሆነ ቅዱስ ሚካኤል ቅዱስ ገብርኤል ከሣጥናኤል ጋር ሲዋጉ ሁለት ጊዜ ተሸንፈዋል፡ በሶስተኛው እንዲያሸንፉ ሲልካቸው ይህን ቀስተደመና ቀርፆ፣ ይህን ምልክት የኮከቡን ቅርፅ የ“ቶ” ቅርፅ ያለው መስቀል በየክንፋቸው ቀርፆላቸዋል። "ኤል"የሚለውንም ሚስጢራዊ ስም አትሞባቸዋል።ይህን ካደረገላቸው በኋላ ተመልሰው ወደ ውጊያው ቢሄዱ ሳጥናኤል ሀይላቸውን ሊቋቋመው አልቻለም ውድቀቱ ፈጠነ ሽንፈቱ የከፋ ሆነበት ፅልመትን አልብሰው ወደ በርባኖስ ውስጥ ጥልቅ ጨለማ ላይ ወረወሩት። የአምላክ ክንድ ፅኑ መሆኗን ሳጥናኤል ያውቃልና በመፅሐፍ ቅዱስ ውስጥ ስላሴን ስሉስ ቅዱስ እያለ እየተንቀጠቀጠ ይገዛል ይላል። ሆኖም ምግባር ስለሌለው ፅድቅን አያያትም። ሰወች "ቶ"ን የህይወት ምልክት አድርገዉ
የሚወስዱት ለኢትዮጵያዉያን ብቻ ነዉ::የሚገርመዉ ደግሞ ይህ ምልክት አገልግሎት ላይ የዋለዉ ከክርስቶስ ልደት በፊት 3000 አመታት ቀደም ብሎ ጥንት ግብፃዉያን ቶርኔተር (የፑንት ምድር) ብለዉ በሚጠሯት ሀገር ነዉ:: ግብፃዉያን እንደሚሉት የፒራሚድ ግንባታ ጥበብን የተማሩት ከቶርኔተር (የአሁኗ ኢትዮጵያ) ሰወችና አማልክቶች ነዉ:: በ670 አ.አ በኢትዮጵያ ነግሶ የነበረዉ ንጉስ ቲርሀቅ እየሩሳሌም የኦሶር ንጉስ በሆነዉ በሰናክሬም ስትወረር
ለእየሩሳሌም መከታ ሆኖ ሲዘምት ሀያላን ከሚባሉ ወታደሮች ጋሻ ላይ የ "ቶ" ምልክት እንደተቀረፀና ንጉሱም በ"ቶ" ቅርፅ የተሰራ መስቀል ማሰሩን የሚያስረዱ የድንጋይ ላይ ፅሁፎች ተገኝተዋል:: .
የ"ቶ" ምልክት የተፈጠረዉ በቅርብ ግዜ ነዉ ለሚሉ ሰወች "ቶ "የተፈጠረዉ አለም ሲፈጠር ነዉ ብል እዉነት እንጅ ዉሸት አይሆንም::ለዚህ ማስረጃየ ደግሞ የሰዉ ልጅ የተፈጠረዉ በ"ቶ" ቀመር መሆኑ ነዉ:: . ይህ ምልክት ግብፅ በሚገኙ የዋሻ ስእሎች ላይ የህይወትን ገፀ ባህሪ ይዞ እንደነበር የሚያስረዳ ሲሆን ይህ
ምልክት አገልግሎት የጀመረዉ ኢትዮጵያ ላይ ከሆነ ግብፅ ላይ እንዴት ተገኘ? ብሎ ለሚጠይቅ ግብፅ ላይ የነገሱት 18 ኢትዮጵያዊ ንጉሶች ተጠቃሽ ናቸዉ:: ሜምኖን የተባለዉ ኢትዮጵያዊ የግብፅ ንጉስ ከ1320 አ.አ እስከ ሴፕዩምስኬኩረስ 170 አ.ም የቆመ ሀዉልት እንደነበረዉና ሀዉልቱም ጠዋት ጠዋት ፀሀይ ሲያርፍበት የክራር ድምፅ ያሰማ እንደነበር ሄሮዱተስ በፓፒረስ ወረቀት ላይ አስፍሮት ይገኛል::ክራር ደግሞ የኢትዮጵያ የባህል መሳሪያ መሆኑ አጀብ ያስብላል:: በሳባዉያን የዋሻ ላይ ስእሎችና ማህተሞች ላይ "ቶ" ተመስሎ ጣቱን የቀሰረ ምስል እንዳለ (አስቻለዉ ከበደ የተባለ ፀሀፊ ከርከቤዴል ሳዶፍ) በሚል መፅሀፉ አስፍሮታል::ሳባዉያን ሰዉን ለመሳል "ቶ"ን መጠቀማቸዉ ይታወሳል፡፡

ይቆየን

@yaltenegeru_mistroch
@yaltenegeru_mistroch
@yaltenegeru_mistroch


በሽታ በቅርቡ እንደሚጠፋ ታምናለህ?
በዲ/ን አቤል ኃይሉ(ዶ/ር)

አንድ ወቅት በጠዋቱ ወደ አንድ ክሊኒክ ለሥራ እየሄድኩ ሳለ መንገድ ላይ ሁለት ሰዎች አስቁመውኝ ስለመጽሐፍ ቅዱስ እናውራ ተባልኩ፡፡ እሺ ብዬ ቆምኩኝ፡፡ ‹‹በሽታ በቅርቡ እንደሚጠፋ ታምናለህ?›› አሉኝ፡፡ የእኔ መልስ የነበረው ‹‹ለምንድነው የሚጠፋው?›› ነበር፡፡ ትንሽ ገረማቸው፡፡ በሽታ እንዲጠፋ የማይፈልግ ይህ ደግሞ ማነው? ሳይሉ አልቀሩም!

ቀጠሉ፡፡ ‹‹ዓለም በበሽታ ተጨንቃላች፡፡ ስለዚህ እግዚአብሔር ከምድር ላይ በሽታን ያጠፋልና ‹‹እንድትጽናና›› ፈልገን ነው አሉኝ፡፡ የሚቀጥለውን ምክር አዘል ቃል ተናገርኩኝ፡፡ ‹‹በሽታ ይጠፋል፤ ፍጹም ሰላም ይመጣል፡፡ ለጥ ብላችሁ ትተኛላችሁ …ወዘተ ›› እያላችሁ ሰዉን አታስንፉት፡፡ ‹‹ለምን ይጠፋል?›› እንዲህ ብዬ የመለስኩት በበሽታ መኖር ደስተኛ ሆኜ አይደለም፤ ሀሳባችው ግን አጥፊ ስለሆነ ነው፡፡ በመቀጠልም ጌታ በወንጌል ለይ ያስተማረውን ቃል አስቀመጥኩላቸው፡፡‹‹በዓለም ሳላችሁ መከራ አለባችሁ፡፡ነገር ግን አይዟችሁ፡፡ እኔ ዓለምን አሸንፌዋለው፡፡›› ዮሐ 16÷30

ይሄ እውነት እስከጌታ ምጽአት ድረስ ይቀጥላል፡፡ ጌታ ቃል የገባልን እንዳሸነፍኩት ታሸንፋላችሁ ነው እንጂ በሽታ ፣ስቃይ አይኖርባችሁም አላለንም፡፡ ሰዎችንም ዘወትር ልናስተምራቸው የሚገባው እንዴት ማሸነፍ እንደሚችሉ ነው እንጂ በቅርቡ በሽታ ይጠፋል ብለን ላያገባት አገባሸለው ብሎ ያልሆነ ተስፋ እንደተሰጣት ሴትዮ እንዳያደርጉን ልንጠነቀቅ ይገባል፡፡

@yaltenegeru_mistroch
@yaltenegeru_mistroch
@yaltenegeru_mistroch


የመንፈሳዊ ሕይወትዎን ማሰደግ ይፈልጋሉ?

መጸለይ እንዳለቦት ያውቃሉ። ግን እንዴት ወደ ጸሎት ሕይወት መግባት እንደሚችሉ ግራ ተጋብተዋል?

ወደ መልካሚ መንገድ ለመሄድ ግልጽ በሆነ አቀራረብ የተዘጋጀውን የመንፈሳዊ ሕይወት ማሻሻያ ጽሁፍ ለማግኘት ይህን ቻናል ይቀላቀሉ።

@zebisrat
@zebisrat
@zebisrat
@zebisrat

Показано 20 последних публикаций.

462

подписчиков
Статистика канала