ያሲን ኑሩ️️ YASIN NURU


Гео и язык канала: Эфиопия, Амхарский
Категория: Блоги


የ ያሲን ኑሩ ሐዲሶች
Yasin Nuru
"ወደ መልካም ነገር ያመላከተ ሰው የሰራውን ሰው ያህል አጅር ያገኛል" ረሱል (ﷺ)
"የበጎ ስራ ምላሹ በጎ እንጂ ሌላ አይደለም "  
የብናኝ ክብደት ያክልም መልካምን የሰራ ሰው ያገኘዋል :>> { አል -ዘልዘለህ 7}
This is not official
ለአስተያየት👇👇
@Hasabbbbot

ሀዲሶችን ከፈለጋችሁ👇👇
@yasin_nuru_hadis

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Гео и язык канала
Эфиопия, Амхарский
Категория
Блоги
Статистика
Фильтр публикаций


የነብዩን ስም ሲሰሙ እንዲሸማቀቁ ነው የምናደርጋቸው አለ ኣ ሰውዮው🤔

ፊዳከ አቢ ወኡሚ ወሩሂ ያረሱለሏህ 😍

ለአንተ/ቺ ረሱል ምንህ/ሽ ናቸው እስኪ ንገሯቸው!

@yasin_nuru @yasin_nuru

3.9k 0 9 126 313

" ይህ በአደባባይ የተላለፈ የጥላቻ ንግግርና ሀይማኖታዊ ትንኮሳ በህዝበ ሙስሊሙ ላይ የፈጠረውን ህመም በአግባቡ በመረዳት የሚመለከታቸው የፀጥታና የህግ አካላት ተጨማሪ ጥፋት ከመከተሉ በፊት እርምጃ ይውሰዱ " - ጠቅላይ ም/ቤቱ

ከሰሞኑን በማህበራዊ ሚዲያዎች በተለይ ደግሞ በቲክቶክ ላይ አንድ ግለሰብ ነብዩ ሙሀመድ " ﷺ " እና እስልምናን መዝለፉ በርከቶችን አስቆጥቷል።

ጉዳዩን በተመለከተም የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ም/ቤት መግለጫ ልኮልናል።

በዚህም መግለጫው የጥላቻ ንግግር በማድረግ ግጭት ለመፍጠር የሚንቀሳቀሱ አካላት ተጠያቂ እንዲሆኑ አጥብቆ አሳስቧል።

የእስልምናን መልካም እሴቶች እና የነብዩ ሙሀመድን (ሰ.ዐ.ወ) ክብር በመዳፈር ህዝበ ሙስሊሙን የሚያስቆጡ የጥላቻ ንግግሮች በስፋት እየተሰራጩ መሆናቸውን የገለጸው  ጠቅላይ ም/ቤቱ እነዚህ አካላት ከዛሬ ነገ ህጋዊ እርምጃ ተወስዶባቸው ከጥፋታቸው ይታረማሉ በሚል ቀና እሳቤ ጉዳዩን በትዕግስት ሲከታተል እንደቆየ ገልጿል።

ይሁን እንጂ ችግሩን ከዚህ በላይ በትዕግስት መመልከት ውጤቱ የከፋ መሆኑን ጠቁሟል።

የኢስላምንና የነብዩ ሙሀመድን (ሰ.ዐ.ወ) ክብር የሚነኩ አካላት በህግ ተጠያቂ እንዲሆኑ ለማድረግ ከየትኛው አይነት ተግባር ቅድሚያ ሰጥቶ እንደሚሰራም አሳውቋል።

በመሆኑም በተደጋጋሚ ተከስቶ በቸልታ እየታለፈ ያለው የኢስላምንና የነብዩ ሙሀመድን (ሰ.ዐ.ወ) ክብር የሚነካ የጥላቻ ንግግር ያደረጉ ግለሰቦች አስተማሪ ቅጣት እንዲያገኙ ጉዳዩ በቀጥታ የሚመለከታቸው የፍትህ፣ የፀጥታና የደህንነት አካላት የህግ ተጠያቂነትን ለማምጣትና መሰል ጥፋቶች እንዳይደገሙ ከመቼውም ጊዜ በላይ በልዩ ትኩረት እንዲሰሩ ም/ቤቱ አሳስቧል።

ጠቅላይ ምክር ቤቱ ፦

➡️ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ጉዳዩ ከዚህ በላይ ከመካረሩ በፊት የጋራ አቋም በመያዝ አፋጣኝ መፍትሄ እንዲያገኝ አስቸኳይ ውሳኔ እንዲወስን፤

➡️ ይህ በአደባባይ የተላለፈ የጥላቻ ንግግርና ሀይማኖታዊ ትንኮሳ በህዝበ ሙስሊሙ ላይ የፈጠረውን ህመም በአግባቡ በመረዳት የሚመለከታቸው የፀጥታና የህግ አካላት ተጨማሪ ጥፋት ከመከተሉ በፊት አስቸኳይ እርምጃ እንዲወስዱ፤

➡️ የሰሞኑ የጥላቻ ንግግር ምንጩ የተራ ግለሰብ ቢመስልም ከጀርባ የአጀንዳና የሃሳብ ተጋሪዎች ያሉት በመሆኑ ህዝባዊ ቁጣ ከመቀስቀሱ በፊት የሀገርና የህዝብ ጉዳይ ያገባናል የሚሉ ሁሉ ከጠቅላይ ም/ቤቱ ጋር በመቆም ትንኮሳውን እንዲያወግዙ፤

➡️ ወቅቱ በሙስሊሞችና በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ አማኞች የጾም ወቅት እንደመሆኑ እንዲህ አይነት ከሀይማኖትና ከኢትዮጵያዊነት እሴት ያፈነገጡ የጥላቻ ንግግሮች የሚገሰፁበትና የሚታረሙበት የፅሞና ወቅት እንዲሆን ም/ቤቱ ጥሪ አቅርቧል።

@yasin_nuru @yasin_nuru

4.9k 0 7 21 128

የአላህን እዝነት ተመልከቱ!!

🍂ከቁርኣን አንድ ሀርፍ የቀራ ሰው 10 አጅር ያገኛል። «አሊፍ፣ ላም፣ ሚም» ያለ ሰው 30 አጅር ያገኛል።

🍂«ቁል ሁወ‘ላሁ አሀድ»ን የቀራ ሰው የቁራኣንን 1/3 እንደቀራ ይፃፍለታል።

🍂ሰላሳ አያዎችን ያላትን «ሱረቱል ሙልክ»ን የቀራ ሰው… ታማልድለታለች፣ ወንጀሉም ይማራል።

🍃አላህን ሚያስታውስ ሰው አላህ ያስታውሰዋል።

🍃በአላህ መንገድ ከመግደልና ከመገደል በላይ ዚክር ማድረግ በላጭ ነው።

🌴ሱብሀነላህ፣ አልሀምዱሊላህ፣ ክኢላሀ ኢለላህ፣ አላሁ አክበር… ፀሀይ ከወጣባቸው ቦታዎች ባጠቃላይ በላጭ ናቸው። የጀነት ተክሎችም ናቸው።

🍃100 ጊዜ ሱብሀነላሂ ወቢሀምዲሂ ያለ ሰው… ወንጀሉ የበህር አረፋ ቢያህል እንኳን ይማርለታል።

🍃100 ጊዜ ‘ላ ኢላሀ ኢለላህ ወህደሁ ላ ሸሪከ ለሁ ለሁል ሙልኩ ወለሁል ሀምዱ ወሁወ አላ ኩሊ ሸይዒን ቀዲር’ ያለ ሰው… 10 ባሪያ ነፃ እንዳወጣ ይያዝለታል። 100 ወንጀል ይማርለታል፣ 100 ምንዳ ያገኛል፣ ከሸይጣን ይጠበቃል፣ ማንም የሱን ያህል ምንዳ አያገኝም እሱ ያለውን ያህል ያለ ወይም ከሱ በላይ ያለ ሰው ሲቀር።

🌴‘ላሀውለ ወላ ቁወተ ኢላ ቢላህ’ የጀነት ተክል ነው።
በነቢዩ ላይ አንዲትን ሰለዋት ያወረድ አላህ በሱ ላይ 10 ያወርዳበታል።

🌼ውዱእን አስውቦ ያደረገ ሰው ወንጀሉ ይማርለታል። ፊቱን ሲታጠብ በአይኑ ያየው ወንጀሉ ይገርፋል። እጁን ሲታጠብ በጁ የሰራው ይወጣል፣ እግሩን ሲታጠብ በእግሩ ወደ ወንጀል የሄደበት ወንጀሉ ይጠራል። (ከወንጀል ጠርቶ እስኪወጣ ድረስ።)

🌼ቤቱ ውድዕ አድርጎ ወደ መስጂድ የሚሄድ ሰው በአንድኛው እርምጃው ወንጀሉ ይታበሳል፣ በሌላኛው አጅር ይፃፍለታል።
ውዱኧን፣ ኩሹኧን፣ ሩኩኣን አስተካክሎ ዋጂብ ሰላትን የሰገደ ሰው ያለፈው ወንጀሉ እንዳለ ይማርለታል። (ከባኢሮች ሲቀሩ።)

🌼ውዱእ ሳይፈታ እዛው የሰገደበት ቦታ ላይ የዘወተረ ሰው… መላኢካዎች ምህረትን ይጠይቁለታል። ‘አላህ ሆይ! ማረው፣ አላህ ሆይ! እዘንለት!’ ይላሉ።

🌼ኢሻን በጀመኣ የሰገደ ሰው ሌሉትን ግማሽ እንደቆመ ይፃፍለታል፣ ፈጅርን በጀመኣ የሰገደ ደግሞ ሌሊቱን በሙሉ እንደሰገደ ይፃፍለታል።
በፈጅርና በኢሻ ውስጥ ያለን ምንዳ ሰዎች ቢያውቁ ኖሮ በእንብርክካቸውም ቢሆን ይመጡ ነበር።

🌼የፈጅር ሱና ከዱንያን ውስጡ ካለው ነገር ባጠቃላይ በላጭ ናት።

🌼በአላህ ላይ ምንዳውን ተሳስቦ ለይልን የቆመ ሰው ያለፈው ወንጀሉ እንዳል ይሰረያል።

⚡️ፆመኛን ያስፈጠረ ሰው… የፆሚን ምንዳ ያገኛል።

@yasin_nuru @yasin_nuru

5.3k 0 96 12 79

🖐 كلام اعجبني ..................
ካስገረሙኝ ንግግሮች 🖐

🔲 عندما تولد لا تعلم
من الذي أخرجك من بطن أمك
🔲በምትወለድበት ጊዜ ከእናትህ ሆድ ያወጣህን ፈፅሞ አታውቅም።

🔳 وعندما تموت لا تعلم
من الذي أدخلك إلى قبرك
🔳 በምትሞትበት ጊዜ ማን ወደ ቀብርህ እንዳስገባህ ፈፅሞ አታውቅም።

*🔲 عجبا لك ياابن آدم*
*🔲 የአደም ልጅ ሆይ! ትገርማለህ።*

🔳 عندما ولدت تغسل وتنظف
🔳 በተወለድክ ጊዜ ትታጠባለህ፣ ትፀዳለህ።

🔲 وعندما تموت تغسل وتنظف
🔲 በምትሞትበት ጊዜ ትታጠባለህ፣ ትፀዳለህ።
*🔳 عجبا لك ياابن آدم*
*🔳 የአደም ልጅ ሆይ! ትገርማለህ።*

🔲   عندما تولد لاتعلم من فرح واستبشر بك
🔲 በተወለድክ ጊዜ በውልደት ማን እንደተደሰተ እና እንደተበረሰ አታውቅም።

🔳 وعندما تموت لاتعلم من بكى عليك وحزن
🔳 በሞት ጊዜ በመሞትህ ማን እንዳለቀና እንደአዘነ አታውቅም።


*🔲   عجبا لك ياابن آدم*
*🔲 የአደም ልጅ ሆይ! ትገርማለህ*

🔳 في بطن أمك كنت في مكان ضيق ومظلم
🔳 በእናትህ ሆድ ውስጥ በጠባብ ቦታና በጨለማ ውስጥ ነበርክ።

🔲 وعندما تموت تكون في مكان ضيق ومظلم
🔲 በምትሞትበት ጊዜ በጠባብ ቦታና በጨለማ ውስጥ ትሆናለህ።

*🔳 عجبا لك ياابن آدم*
*🔳 የአደም ልጅ ሆይ! ትገርማለህ*

🔲 عندما ولدت تغطى بالقماش ليستروك
🔲 ስትወለድ በጨርቅ ትጠቀለላህ ሊሸፍኑህ!

🔳 وعندما تموت تكفن بالقماش ليستروك
🔳 ስትሞት በከፈን ይጠቀልሉሃል ሊሸፍኑህ!

🔲 عجبا لك ياابن آدم
🔲 የአደም ልጅ ሆይ! ትገርማለህ

🔳 عندما ولدت وكبرت يسألك الناس
عن شهادتك وخبراتك
🔳 በተወለድክና በአደግክ ጊዜ ሰዎች ስለምስክር (ወረቀትህና) ስለሙያህ ይጠይቁሃክ።

🔲 وعندما تموت تسألك الملائكة عن عملك الصالح
🔲 በሞትክም ጊዜ መልዓይኮች ስለመልካም ስራህ ይጠይቁሃል።

*🔳 فماذا أعددت لآخرتك  ؟*
*🔳  ለመጨረሻው ሃገርህ ምን አዘጋጀህ?*

🔲 جرب تقولها من قلب :
آشهد آن لآ آله آلآ آلله
واشهد آن محمد رسول آلله
🔲   ከልብህ ይህችን (ቃል) ለመናገር ሞክር! ።ከአላህ ሌላ በፍፁም የሚመለክ አምላክ እንደሌለ መስክር። እንዲሁም ሙሃመድ የአላህ መልክተኛ መሆናቸውን መስክር።

🔳 مستحيل تقرآها بدون ما ترسلها
🔳    (ይህን መልእክት) በፍፁም ሳታነባድ እንዳትልካት!!

                    & & &
‏        بسم الله الرحمن الرحیم
*{ قل هو الله أحد * الله الصمد * لم يلد ولم يولد * ولم يكن له كفواً أحد }*


*ﺑﺴﻢ ﺍﻟﻠﻪ ﺍﻟﺮﺣﻤﻦ ﺍﻟﺮﺣﻴﻢ*
*{ በል! እርሱ አላህ አንድ ነው።አላህ (የሁሉ) መጠጊያ ነው። አልወለደም፤ አልተወለደምም። ለእርሱም አንድም ብጤ የለውም።}*


@yasin_nuru    @yasin_nuru           

6.7k 0 163 31 233



Видео недоступно для предпросмотра
Смотреть в Telegram
በጥጋቧ ጊዜ አብሬ አልኖርም!!😁😁 የትዳር ሳይንስ አጠር ያለምክር!

በኡስታዝ ያሲን ኑሩ
🥰🥰

ያ አላህ እስከ መጨረሻው ስሙት የነብያችንን ፍቅር☺️☺️ ሰሉ አላ ነብይና መሀመድ😘😘

JOIN: @yasin_nuru   
JOIN: @yasin_nuru 

7.2k 0 60 22 162

﴿إِنَّ اللهَ وَمَلَائِكَتَهُ يُصَلُّونَ عَلَى النَّبِيِّ يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا صَلُّوا عَلَيْهِ وَسَلِّمُوا تَسْلِيمًا﴾ (الأحزاب ٥٦)

"አላህና መላእክቱ በነቢዩ ላይ የአክብሮት እዝነትን ያወርዳሉ፡፡ እናንተ ያመናችሁ ሆይ! በእርሱ ላይ የአክብሮት እዝነትን አውርዱ፡፡ የማክበርንም ሰላምታ ሰላም በሉ፡፡" (አል-አህዛብ 56)

اللهم صل على محمد وعلى ال محمد كما صليت على ابراهيم وعلى ال ابراهيم وبارك على محمد وعلى ال محمد كما باركت على ابراهيم وعلى ال ابراهيم انك حميد مجيد

@yasin_nuru @yasin_nuru

8.3k 0 19 42 145

እኔ በምሰግድበት መስጅድ ሁለት ጉዳዮች ለኔ የታዩኝ
1) ልጆችን ስርዓት ማስተማር ለታላላቆች ክብር መስጠትን እና መስጂድ ውስጥ ፀጥታ ማስከበር  ሰላት እየተሰገድ ገበያ እንኳ በዚ ልክ ረብሻ ያለ አይመስለኝም ቢያንስ መስጅድ እንደ መስጅድነቱ ቢከበር።
2) ቁኑት ባይረዝም አብዛኛው ሰው ነጋዴ እና የቀን ሰራተኛ ነው ቢያንስ ሰላቱ እንዳይሰለች ቁኑት አጠር ብሎ ቢመጠን ባይ ነኝ።
ጀሞ ራህማ መስጅድ።

- Aslame aleykume werhmtulahi webrkatu yegna mesjid ye aned gelseb menoriya bet nbr enam sewyew endisegdbte neyetole enam be ahune seate eytsegedbt nw gn ye gelsbu batesboche batu endishet yeflgalu ke remdan buhala endaysegdebt tedrgole enam mesjedu bezu jemaoche afertole enam yeh jema endaybetn be allahe sem erdata entyklen akemu yechal sew endigzalen kalhonem yechalachuten endtagezun be duame bihone sefru ajamba ye mesjdu sem bilale mesjde

-አሠላሙአለይኩም ወራህመቱላሂ ወበረካቱ..  እኔ የምፅፍላችሁ ከአአ ነው እና ሠፈራችን አፍንጮ በር አካባቢ አንድ መሥጊድ አለ በዚህ መሥጊድ ውሥጥ አይነሥውራን ወገኖቸች ልክ እንደ ሌሎቹ ቁርአንን ከመደርደርያ አንሥተው ይቀራሉ.. አይነሥውራንና መሥማት የተሣናቸው ቁርአን የሚቀሩበት እሥፔሻል ክፍልም አላቸው እናም ሌሎችም ለአካል ጉዳተኞች ትኩረት ቢሠጡ ለማለት ያክል ነው

ኬንተሪ ሰላም መስጅድ ሰላት እየተሰገደ አኳርጦ መሄድ፤ ተሰግዶ እንዳለቀ ለመውጣት ግፋያ ነው ቢስተካከል

- ጅማ ፈቲ መስጅድ ስለ ቂያማ አስፈሪነት ስለ ጀሀነም ምንም ደእዋ አይደረግ ስለ ጡሩ ጥሩ ነገር እንጂ እሄ ቢስተካከል የሚል ሀሳብ አለኝ

- ማማ መስጂድ የሴቶች ሽንትቤት ይቆለፋል እና ኡዱ ማድረጊያውም አብሮነው ስለዚህ ለመስገድ ሄደን ቁልፍ ስለሆነ ሳንሰግድ እንመለሳለን አድራሻ ኬንቴሪ(አለምገና)

-አሸዋ ሚዳ ሃዋ መስጅድ ኢሻ ሰላት በጊዜ አይሰገድም በጣም ይቆያሉ

- ወራቤ ዱና ኡስማን መስጂ ተራዊህ ስሰገድ ያለምንም አረፍት ነውና የምያልቀው ከሁለት ተስሊም ቦኃላ ትንሽ እረፍት የዉሃ መጠጫ ሳት ብሰጡን መልካም ነው

-አዲሱ ገበያ ኑር ሁሴን መስጅድ ምንጣፉ ቢቀየር


-አንዋር መስጅድ የውጭ መብራት ይስተካከል

ኑር መስጅድ ወንዶች አስፓልት ላይ የሚሰግዱ ወደፊት ቢጠጉ በመሃላቸው ከምናልፍ በጀርባ በኩል እንድናልፍ ቢደረግ

9.9k 0 12 19 130

መስጅዳችሁ ውስጥ ቢስተካከል የምትሉት ነገር ካለ አጠር አርጋችሁ በዚ ቦት ላኩልን @Hasabbbbot እዚህ ላይ መልሰን ስለምንለቀው የአንድ መስጅድ ኮሜቴ እንኳ አይቶ ሊያስተካክሉት ይችላሉ!

#የመስጅዳችሁን #ስም እና #ሰፈር አብራችሁ ፃፉልን እና መልሰን እዚህ ላይ እንፖስተዋለን!

@Hasabbbbot


የነብዩ ዱዓዎች


1.በለሊት የመጨረሻዎቹ  ሰዓታት ላይ አማኞች በዱዓእ እንዲበረቱ ያዙ ነበር፡፡


2. ምእመናን በሱጁዳቸው ውስጥ በዱዓእ እንዲበራቱ ይጠቁሙ ነበር፡፡

3. እጃቸውን ከፍ አድርገውና ተናንሰው አላህን ይለምናሉ፡፡

4. አንድን ሰው ያስታወሱ እንደሆነ ዱዓእ ያደርጉለታል፡፡

5. አጠቃላይ /ጃሚዕ/ የሆኑ ዱዓኦችን ይጠቀሙ ነበር፡፡

6. ዱዓ ሲያደርጉ ሶስት ሶስት ጊዜ ዱዓእ ያደርጋሉ፡፡

7.ሶስት ሶስት ጊዜ ከአላህ (ሱ.ወ.) ምህረትን ይለምናሉ /ኢስቲግፋር ያደርጋሉ/፡፡

8. በራስ ላይ፣ በልጆች ላይ፣ በአገልጋዮች ላይና በሀብት ንብረት ላይ በመቅሰፍትና በእርግማን ዱዓእ እንዳይደረግ  ይከለክሉ ነበር፡፡

9. ሲነጋ አላህን በማውሳት ቀናቸውን ይጀምራሉ፤ ሲመሽም ዱዓእ ያደርጋሉ፡፡

10. ከቤት ሲወጡ ‹ቢስሚላህ ተወከልቱ ዐለላህ ወላ ሐውለ ወላ ቁወተ ኢልላ ቢልላሂ› ይላሉ፡፡

11.      ዝናብ ባዩ ጊዜ ‹አላሁምመ ሰዪበን ናፊዐን ..› በማለት  ይደጋግማሉ፡፡

12.  የመብረቅ ድምጽ የሰሙ እንደሆን ‹አልላሁምመ ላ ተቅቱልና ቢገዶቢከ› ይሉ ነበር፡፡

13. የምግብ ማዕድ ሲነሳ  ‹አልሐምዱ ሊላሂ-ልለዚ አጥዐመና ወሰቃና ወአዋና ወጀዐለና  ሙስሊሚን› ይላሉ፡፡

14. ንፋስ በነፈሰ ጊዜ ከያዘችው መልካም ነገር ይለምናሉ፡፡ በውስጧ ካለ መጥፎ ነገርም በአላህ ይጠበቃሉ፡፡

15. በአንድ ነገር ላይ መወሰን የከበዳቸው እንደሆን ‹አላህ ሆይ ምረጥልኝ፡፡›ይላሉ፡፡

16. ከድካም፣ ከስንፍና፣ ከፍርሃት፣ ከመጃጃት፣ ከስስት፣ ከመቃብር ቅጣት አላህ እንዲጠብቃቸው ለምነዋል፡፡

17.  አላህን ከማይፈራ ቀልብ፣ ተሰሚነት ከሌለው ዱዓእ፣ ከማትጠግብ ነፍስ፣ ከማይጠቅም ዕውቀትም በአላህ ተጠብቀዋል፡፡

18. አላህ (ሱ.ወ.) የለገሳቸውን ፀጋ እንዳይወስድባቸው፣ ጤናቸውን እንዳያቃውስባቸው፣ ደንገተኛ ቁጣ እንዳያወርድባቸው ጠብቀኝ ብለዋል፡፡

19. ከድህነት፣ ከውርደት፣ ከክህደት፣ ሰውን ከመበደልና በሰዎችም ከመበደል አላህ እንዲጠብቃቸው ለምነዋል፡፡

20. በዚህች ዓለምም ሆነ በመጨረሻው ዓለም አላህ መልካምን ነገር እንዲሰጣቸው ይለምኑ ነበር፡፡

ምንጭ ፡ 500 የነቢዩ ባህርያት
ነጃሺ ማተሚያ ቤት
ትርጉም በሙሐመድ ሰዒድ

@yasin_nuru   @yasin_nuru

11.2k 0 103 29 149

አስተማሪና መሳጭ ታሪክ!

በስዑዲ የሚኖር አንድ የመኒ ነው፡፡ በአንድ ወቅት ያጋጠመውን ታሪክ እንዲህ ይተርከዋል፡፡
ከፊሌ የዘካ ገንዘብ ሊያከፋፍል ፈልጎ ከሱ ጋር ወጣሁ፡፡ የድሃ መንደሮች ወዳሉባቸው ጠረፍ አካባቢ ሄድን፡፡ የዘካው ገንዘቦች በፖስታ የታሸጉ ነበሩ፡፡ እያንዳንዱ ፖስታ በውስጡ 5000 ሪያል ይዟል፡፡ ከአንዱ መንደር ወጥተን የጂዳን-ጂዛን መስመር ስንይዝ አንድ የ70 አመት አካባቢ ሽማግሌ አገኘን፡፡ ሽማግሌው ብርቱና ጤናማ ነው፡፡ ጎዳናውን ይዞ ይጓዛል፡፡
ወዳጄ “ይሄ ደግሞ በዚህ ሰዓት በዚህ በረሃ ምን ይሰራል?” አለኝ፡፡

ሹፌሩ “ህገ ወጥ የመኒ ነው” አለ፡፡
ካጠገቡ ደርሰን ቆምንና ሰላም አልነው፡፡
“ከየት ነው ወንድም?”
“ከየመን”
“የት ነው የምትሄደው?”
“የአላህን ቤት ናፍቄያለሁ”
“ህጋዊ ነህ?”
“አይደለሁም”
“ለምን ህጋዊ አልሆንክም?”
“ለዋስትና 2000 ሪያል ማስያዝ ይጠበቅብኛል፡፡ እኔ ያለኝ 200 ብቻ ነው፡፡ በመቶዋ ተሳፈርኩባት፡፡ የቀረኝ መቶ ብቻ ነው” አለ፡፡
“እሺ አጎቴ! በጉዞ ላይ ምን ያክል ሆነህ?” አለው ጓደኛየ፡፡
“ስድስት ቀን!”
“እየፆምክ አይደለም?”
“አይ ፆመኛ ነኝ፡፡”
“ጥሩ፡፡ አንተ ከ 5 በላይ የፍተሸ ኬላዎችን አልፈሃል፡፡ እንዴት ነበር የምታልፋቸው?” ሲለው
“ከሱ በስተቀር እውነተኛ አምላክ በሌለው አላህ እምላለሁ! የማልፈው በነሱው ዘንድ ነው፡፡ ግን አንድም ያናገረኝ የለም!!” አለ፡፡
“ለስራ ነው አመጣጥህ?”
“በጭራሽ ወላሂ! እኔ የአላህን ቤት ናፍቄ ነው የመጣሁት፡፡ ዑምራ ማድረግ ነው የምፈልገው፡፡ ወደ መካ ነው የምጓዘው፡፡”
“በአስፋልት ላይ ስትጓዝ ተዘዋዋሪ ዘቦች /ፓትሮል/ አልያዙህም?”

“ከግማሽ ሰዓት በፊት በ 50 ኪ. ሜ. ርቀት ላይ ይዘውኝ ነበር፡፡ እዚህ ከመድረሴ አንድ ኪ. ሜ. ቀደም ብሎ ድረስ እነሱ ናቸው ያመጡኝ፡፡ የት እንደምሄድ ሲይቁኝ በአላህ ምየ የአላህን ቤት እንደምፈልግ ስነግራቸው ለቀቁኝ” አለ፡፡
“ሱብሓነላህ! ጭራሽ እስከዚህ ቦታ በፍጥነት እንዲያደርሱህ አላህ ፓትሮሎችን አመቻቸልህ” አልኩኝ በውስጤ፡፡

ወዳጄ ሁለት ፖስታዎችን እየሰጠው “እነዚህን ያዝ፡፡ ዘካ ነው” አለው፡፡
እየተቀበለ “ጀዛኩሙላህ ኸይር” አለ፡፡
በፖስታዎቹ ያለው ገንዘብ መጠኑ ምን ያክል እንደሆነ አያውቅም፡፡
“የሰዑዲን ብር ታውቃለህ?” አልኩት፡፡
“አዎ!” አለ፡፡
“ጥሩ፡፡ ፖስታውን ክፈትና እንዳይጠፋብህ ገንዘቡን በቀበቶህ (በሒዛምህ) ውስጥ ደብቅ” አልኩት፡፡
ሲከፍተው 10 ሺህ ሪያል!!
“ይህ ሁሉ ለኔ ነው?” አለ፡፡
“አዎ ላንተ ነው” አልነው፡፡
ከመኪናው ላይ ወደቀ፡፡ እራሱን ሳተ፡፡ ከመኪናው ወርደን በላዩ ላይ ውሃ መርጨት ያዝን፡፡ “ይህ ሁሉ ገንዘብ ለኔ ነው? ይህ ሁሉ ገንዘብ ለኔ ነው?” እያለ መጮህ ያዘ፡፡ ቁጭ ብሎ ማልቀስ ቀጠለ፡፡

ወዳጄ፡ “ከኛ ጋር ትንሽ ወደ ፊት እንውሰደው” አለ፡፡ ከኛ ጋር መኪና ላይ ወጣ፡፡ ትንሽ ሲረጋጋ ጠየቅኩት፡

“ምንድን ነው ይህ ሁሉ ለቅሶ?” አልኩት፡፡
“እኔ የመን ውስጥ ከቤቴ ጎን ቦታ አለችኝ፡፡ ለአላህ ሰጥቻታለሁ፡፡ እኔና ቤተሰቦቼ በሷ ላይ በጭቃና በድንጋይ አድርገን መስጅድ ገንብተንባታል፡፡ ግንባታው ቢጠናቀቅም ምንጣፍና ጥቂት ነገሮች ቀርተውት ነበር፡፡ ለዚህ መስጂድ እንዴት ምንጣፍ እንደማገኝ ተቀምጬ አስብ ነበር” አለ፡፡

ይህን ሲል የእውነት ሁላችንም አለቀስን፡፡ “አሳቡ ኣኺራ የሆነ ሰው ዱንያ እንዳለች ትመጣለታለች” የሚለውና “አሳቡ ኣኺራ የሆነ ሰው አላህ መብቃቃቱን ከልቡ ውስጥ ያደርግለታል፡፡ ነገሩንም ይሰበስብለታል፡፡ ዱንያ በግዷ ወደሱ ትመጣለች፡፡ አሳቡ ዱንያ የሆነ ደግሞ አላህ ድህነቱን በአይኖቹ መሀል ያደርግበታል፡፡ ነገሩንም ይበትንበታል፡፡ ከዱንያም የተወሰነለት ብቻ እንጂ አይመጣለትም” የሚለው የነብዩ ﷺ ንግግር ትዝ አለኝ፡፡

በዚህን ጊዜ ወዳጄን ለሰውየው እንዲጨምረው ጠየቅኩት፡፡ ተጨማሪ 2 እሽግ ፖስታ ሰጠው፡፡ በድምሩ 20 ሺ ሪያል አገኘ ሰውየው፡፡ ሰውየው ከመኪናው ከመውረዱ በፊት እያለቀሰ ያጉተመትምና ዱዓ ያደርግ ነበር፡፡

“በአላህ ላይ እውነተኛ የሆነውን መመካት ብትመኩ ኖሮ ልክ ወፍን እንደሚረዝቀው ይረዝቃችሁ ነበር፡፡ ተርባ ወጥታ ጠግባ ትመለሳለች” የሚለው የነብዩ ﷺ ሐዲሥ መጣብኝ፡፡

@yasin_nuru    @yasin_nuru         

11.4k 0 112 38 311

መሳኪኖችንም እያስፈጠርን!

9.7k 0 3 25 229

🍂ዕረፍት

☞ስንቅ የፈለገ አላህን መፍራት ይበቃዋል።

◾️ልዕልና የፈለገ እስልምና ይበቃዋል።

☞ፍትህን የፈለገ የአላህ ፍርድ ይበቃዋል።

◾️አጫዋች የፈለገ አላህን ማስታወስ ይበቃዋል።

☞መካሪን የፈለገ ሞት ይበቃዋል።

◾️ሐብትን የፈለገ መተናነስ ይበቃዋል።

☞ጌጥን የፈለገ እውቀት ይበቃዋል።

◾️ቁንጅናን የፈለገ ጥሩ ፀባይ ይበቃዋል።

☞ዕረፍትን የፈለገ አኺራ ይበቃዋል።
"ይህ ሁሉ ያልበቃው እሳት ይበቃዋል"

@yasin_nuru @yasin_nuru

12.8k 0 104 33 294

የረመዷን ተናፋቂ ወርን በተሻለ የኢማን ከፍታ እና አንድነታችን በሚያጎላ መንፈሳዊ ክዋኔ ለመፆም «ቁርዓን የእውቀት እና የሰላም ምንጭ» በሚል መሪ ቃል መጋቢት 07/2017 በአብዮት አደባባይ ከኢፍጣራችን ጋር ከፍተኛ የመንግስት ሀላፊዎች፣ የአገር ሽማግዎች፣ ድፕሎማቶች፣ ጥሪ የተደረገላቸው የክብር እንግዶች እና የተከበረው ህዝባችን በተገኙበት በድምቀት ለማከናወን እየተዘጋጀን እንደሆነ መግለፃችን ይታወቃል።

ውደድሩ የክልል እስልምና ጉዳዮች ክልላቸውን ወክሎ የሚወዳደረውን ተወዳዳሪ  የሚያቀርቡበት ሂደት ስለሆነ  ምዝገባም ሆነ የማጣሪያ ውድድር የሚካሄደው  በክልሎችና በከተማ አስተዳደር እንደሆነ በመረዳት በመርከዝ ደረጃም ሆነ በግል ለመወዳደር የምትፈልጉ በየክልላችሁ ወይም በከተማ አስተዳደር ተወዳድራችሁ በውጤታችሁ መሰረት ለአሸናፊዎች አሸናፊ ወደ ፌደራል እስልምና ጉዳይ በውጤታችሁ መሰረት የምትመጡ ይሆናል። 
አንድ ክልል ወይም ከተማ አስተዳደር አወዳድሮ የሚልከው በክልሉ ወይም ከተማ አስተዳደሩ በወንድ 1ኛ እና 2ኛ የወጣውን ሲሆን በሴት 1ኛ የወጣችውን በድምሩ 3 ተወዳዳሪ በመላክ  የአሸናፊዎች አሸናፊ ውድድር ላይ እንዲወዳደር ይደረጋል። 

አዲስ አበባ ላይ  በሚደረገው የአሸናፊዎች አሸናፊ ውድድር ላይ መጨረሻ ለሚኖሩት አሸናፊዎች፡-
·    
👉በሁለቱም ፆታ 1ኛ ለሚወጡ ተወዳዳሪዎች የመኪና ሽልማት፤
·      
👉ውድድሩን በ2ኛ ደረጃነት ለሚያጠናቅቅ ወንድ ተወዳዳሪ የሐጅ ዕድል እንዲሁም ለሴት ተወዳዳሪ ብር 500,000.00 (አምስት መቶ ሺህ ብር)፤
·      
👉3ኛ ደረጃ የሚወጡ ወንድም ሴትም ተወዳዳሪዎች ለእያንዳዳቸው ብር 300,000.00 (ሶስት መቶ ሺ ብር) ሽልማት ያገኛሉ። 

እድሜና እና ፆታ በማይወስነው በዚህ የቁርዓን ውድድር ላይ በክልላችሁ ወይም ከተማ አስተዳደር የእስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት አማካኝነት ተጨማሪ መረጃዎችን የምናሳውቅ ሲሆን  በዚህ ወር ከቁርአን በላይ ቅድሚያ የሚሰጠው ነገር ባለመኖሩ እሁድ መጋቢት 7 ከቀኑ 8፡00 ጀምሮ በአብዮት አደባይ በመገኘት የዝግጅቱ ታዳሚ እንድትሆኑ ተጋብዛችኋል።

@yasin_nuru @yasin_nuru

12.7k 0 18 10 137

የባህርዳር፣አሶሳ፣ሻሸመኔ፣መቀሌ፣ሐረር፣ጅግጅጋ፣መቱ፣ጅማ፣አዲስ_አበባ፣ድሬዳዋ የረመዳን ወር የሰላት ሰዓት

@yasin_nuru @yasin_nuru

9.2k 0 11 18 61

ጾመኛ ሆነህ ያለ አግባብ ሊያልፉህ የማይገቡ ③ ወቅቶች‼
=================================

①) የቀኑ የመጀመሪያ → ከፈጅር ሶላት በኋላ፦

በርግጥ ሌሊት ተነስቶ ሰሑር የበላና ተሃጁድ የሰገደ ሰው ከፈጅር በኋላ ከባድ እንቅልፍ የሚያስቸግረው ቢሆንም፤ ግና ያንን ወቅት ጸሐይ እስክትወጣ ድረስ እንደምንም ተቋቁሞ በዚክርና በዒባዳህ ማሳለፍ ወሳኝ ነው።

አል-ኢማም አ-ን'ነወዊይ (አላህ ይዘንላቸውና) በ"አልአዝካር" ኪታባቸው ላይ «በቀኑ ክፍለ ጊዜ እጅግ በጣም በላጩ የዚክር ወቅት ከፈጅር በኋላ ያለው ነው!» ብለዋል።

«የፈጅርን ሶላት በጀማዓህ የሰገደ፣ ከዚያም ጸሐይ እስክትወጣ ድረስ አላህን እያወሳ የተቀመጠ፣ ከዚያም 2 ረከዓህ የሰገደ ሐጅና ዑምራ እንዳደረገ ነው!» የሚል ሐዲሥ አለ።


አስበው ደግሞ ምንዳ እጥፍ ድርብ በሚደረግበት የረመዿን ወቅት ሲሆን!
*
②) የቀኑ የመጨረሻ ጊዜ → ከመጝሪብ በፊት፦
ለኢፍጣር በምንዘጋጅበት በዚህ ወቅት አላህን መለመን ዱዓእን ተቀባይ ያደርገዋል።
*
③) በሰሑር ወቅት → ከፈጅር በፊት፦
ይህ ወቅት አላህ ወደ ዱንያ ሰማይ ወርዶ «ማነው ምህረትን የሚጠይቀኝ → የምምረው፣ ማነው የሚለምነኝ ልመናውን የምቀበለው …» የሚልበት ወቅት ስለሆነ ይህን ወቅት በአግባቡ መጠቀም ያስደልጋል።


ታዲያ ያውም በረመዿን ምን ትጠብቃለህ ያ ዐብደ-ል'ሏህ⁉️

አላህ ያግራልን!

@yasin_nuru @yasin_nuru

10.6k 0 90 31 213

በምናፈጥር ጊዜ የሚባል ዱአ

ﺫﻫﺐ ﺍﻟﻈﻤﺄ ﻭ ﺍﺑﺘﻠﺖِ ﺍﻟﻌﺮﻭﻕ ﻭﺛﺒﺖ ﺍﻷﺟﺮ ﺇﻥ ﺷﺎﺀ ﺍﻟﻠﻪ
ጥም ተወገደ፣ ጉሮሮዎችም (የደም ስሮች) ረጠቡ፣ በአሏህ ፍቃድ አጅሩም ፀደቀ።"

📚 ﺻﺤﻴﺢ ﺍﻟﺠﺎمع) [(4678)

@yasin_nuru @yasin_nuru

10.3k 0 72 13 211

ለጾመኛ ሰው የሚወደዱ 40 ተግባራት‼️
=============================

1) ለሙስሊሙ ኡማ ዱዓ ማብዛት
2) ሰላምታን ማብዛት
3) ዝምድናን መቀጠል
4) መልካም ነገርን ማብዛት
5) ሶደቃ ማብዛት
6) ወንድምን በፈገግታ መገናኘት
7) ለጎረቤት መልካም መዋል
8) ለሚስኪኖች፣ ለአቅመ ደካሞችና ለየቲሞች መልካም መዋል
9) መልካም ንግግርን መናገር
10) አላህን ማውሳት (ዚክር) ማብዛት
11) ወደ አላህ መመለስን፣ ኢስቲጝፋርን ማብዛት
12) ኢማንን ማደስ፣ "ላ ኢላሃ ኢለልሏህ!" የሚለውን ቃል ማብዛት
13) "ላ ሐውለ ወላ ቁወተ ኢላ ቢልላህ!" የሚለውን ቃል ማብዛት
14) "ሱብሐነልላህ ወቢ ሐምዲህ፣ ሱብሐነልሏሂል ዓዚም!" የሚለውን ቃል ማብዛት
15) በነብያችን ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ላይ ሶለዋት ማብዛት
16) እውቀትን ፍለጋ ማብዛት
17) ወደ አላህ መጣራትን ማብዛት
18) ለቤተሰብ ስጦታ መስጠት
19) ውዱዕን መጠበቅ (ቂርኣትና ሶላት ላይ ባንሆንም በስራ ቦታ ሁሉ ብንሆንም)
20) ሲዋክ መጠቀም
21) ጥሩ ሽታ መኖር (ንጽህናን መጠበቅ)
22) ከመጝሪብ በፊት ሁለት ረከዓ መስገድ
23) በሱንና ሶላቶች ላይ መበራታት
24) ቤት ውስጥ የትርፍ ሶላቶችን ማብዛት
25) ወደ አወለ ስሶፍ (የመጀመሪያው ረድፍ) መጣደፍ
26) ከአንድ ሶላት በኋላ ቀጣዩን ሶላት በጉጉት መጠበቅ
27) በጁሙዓ ቀን በወቅቱ መገኘት
28) የሌሊት ሶላትንና ግዜን መጠበቅ
29) መስጅድ ውስጥ መቆየት ማብዛት
30) አላህን ከሚያወሱ መልካም ሰዎች ጋር መቀመጥ ማብዛት
31) የጧትና የማታ አዝካሮችን መጠበቅ
32) ቁርኣንን መማር፣ መቅራት፣ ድምጽ በማሳመር መቅራት፣ ሱጁዱ ቲላዋ መውረድ፣ ቁርኣንን ለማኽተም መጓጓት፣ ሲያኸትሙ ዱዓ ማድረግ
33) ዛሂድ መሆን
34)  ስናፈጥር መቸኮል
35) ሌላን ሰው ማስፈጠር
36) ሱሕር መመገብ፣ ሱሕርን ማዘግየት (ባይሆን ወቅቱ እንዳያልፍ)
37) የታመመን መጠየቅ
38) ቀብርን መዘየር (ለወንድ)
39) አኺራን፣ ሞትን፣ ጀነትንና እሳትን ማስታወስ
40) የአላህ ታዕምሮችን እያስተዋሉ ማስተንተን

እና ሌሎችም መልካም ተግባራት!!

*
አላህ ያግራልን።
||
[ከሸይኽ ሙሐመድ ኢብኑ ዐብዱል ወህ'ሃብ አል-ወስ'ሷቢይ ሐፊዘሁልሏህ

11.4k 0 131 6 143


9k 0 23 4 59

ፆም የሚያበላሹ ነገሮች
~
1- የግብረ ስጋ ግንኙነት መፈፀም፣

2- የዘር ፈሳሽን ሆን ብሎ ማውጣት፣

3- መብላትና መጠጣት፣

4- በአፍ መድሃኒት መዋጥ፣

5- ሲጋራና መሰል ነገሮችን ማጨስ፣

6- የወር አበባ ወይም የወሊድ ደም መምጣት፣

7- ፆምን የማቋረጥ ቁርጠኛ ውሳኔ ላይ መድረስ (ባይበላም ባይጠጣም)

እነዚህ ነገሮችን ፆምን የሚያበላሹት የሚያፈርሱ እንደሆነ እያወቀ፣ አስታውሶ እና በምርጫው በቀኑ ክፍለ ጊዜ ከፈፀማቸው ነው።

* የሚያፈርሱ መሆናቸውን ሳያውቅ ቢፈፅም ፆሙ አይበላሽም። ልክ እንደዚሁ ያልነጋ መስሎት ወይም ፀሐይ የገባ መስሎት ቢፈፅምም ፆሙ አይበላሻም።

* የሚያፈርሱ መሆናቸውን እያወቀ ነገር ግን ረስቶ ቢፈፅም ፆሙ አይበላሽም።

* የሚያፈርሱ መሆናቸውን እየወቀ ግን ተገዶ ቢፈፅም ፆሙ አይበላሽም።

@yasin_nuru @yasin_nuru

10.1k 0 63 19 236
Показано 20 последних публикаций.