ዓለምን ማዳን አይጠበቅብህም!! ቢያንስ አንድ ሰው ማዳን ግን ትችላለህ!!
እውነት ነው ብዙዎቻችን ቤታችን ራሱ ስፋቱ ሁለት የአዋቂ እርምጃ ነው። ለስድስት እንኖርባት ይሆናል።…… ስድስታችንም ከቤት ውጪ ከተጠነቀቅን ስድስታችንም ሰላም አልሆንም? አይበለውና ቤተኞችህን ማዳን አልቻልክም። እኔ ከሞትኩ ሰርዶ አይብቀል ካላልክ ጎረቤትህስ ቢተርፍበት? ነውስ እኔን ከያዘኝማ ሌላው ለምን ይዳን ነው?
ደግሞስ በቤተኞቻችን ማመኻኘት የማንችል ምን ያህል ወንደላጤና ሴተላጤዎች አለን? ግንሳ ጥንቃቄዎቹን እየተገበርን ነው?
በሽታው ለኢትዮጵያ አኗኗር የሚሆን አይደለም እያሉ ከጥንቃቄ መራቅ ኋላ ዋጋ እንዳያስከፍለን እፈራለሁ።
እኔ ብጠነቀቅ ምን ዋጋ አለው ሌላው እየተዝረከረከ ነው እያሉ መዘናጋት ኋላ እንዳያስለቅሰን እፈራለሁ።
እንደማናችሁም በሽታው ሀገሬን ቢያልፋት ደስታዬ ጥግ የለውም። ግን እፈራለሁ።…… ከልግጫችን እጅጉን የላቀ ለቅሶ እንዳናለቅስ እፈራለሁ።
ቀልዳችንን ገታ አድርገን ጥንቃቄያችንን እናብዛ!!!