የአእላፋት ዝማሬ | Melody of Myriads


Гео и язык канала: Эфиопия, Амхарский
Категория: Религия


እንዳልዘምር የሚከለክለኝ ምንድን ነው?

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Гео и язык канала
Эфиопия, Амхарский
Категория
Религия
Статистика
Фильтр публикаций


በድሬዳዋ የመጀመሪያው የአእላፋት ዝማሬ ተካሔደ

| ጃንደረባው ሚዲያ | ታኅሣሥ 28 2017 ዓ.ም.|
ድሬዳዋ ኢትዮጵያ

ከጥቅምት 5-2017 ዓ.ም ጀምሮ በኢትዮጵያዊው ጃንደረባ ትውልድ ይፋ የተደረገው የአእላፋት ዝማሬ ከሦስት ወራት የመዝሙር ጥናትና የማኅበራዊ ሚድያ ዘመቻ በኋላ አእላፋት በተገኙበት በእግዚአብሔር ቸርነት በድሬዳዋ የመጀመሪያው ዙር የአእላፋት ዝማሬ በድሬዳዋ ምድር ባቡር ለገሃር አደባባይ በድምቀት ተካሔደ::

ከቀኑ 10:00 ሰዓት ላይ በድሬዳዋ ሀገረ ስብከት ሊቀጳጳስ ብፁዕ አቡነ በርተሎሜዎስ ፣ የሀገረ ስብከቱ ሥራ አስኪያጅ እና የመምሪያ ኃላፊዎች እንዲሁም በሀገረ ስብከቱ የሚገኙ የሁሉም አድባራት እና ገዳማት አስተዳዳሪዎች እና ሰ/መ/ጉ/ጽ/ቤት አባላ ተገኝተዋል:: በኢጃት ጃን እስጢፋኖስ ሥር በሚያገለግሉ 12 ዲያቆናት ባካሔዱት በመሐረነ አብ እና በምሕላ ጸሎት ጉባኤው የተጀመረ ሲሆን በጸሎቱ ፍጻሜም በብፁዕ አቡነ በርተሎሜዎስ የድሬዳዋ ሀገረ ስብከት ሊቀጳጳስ ጸሎተ ወንጌልና ኪዳን ደርሶአል::

በዕለቱም ምእመናን 60 ካሬ ስክሪኖች በአራት አቅጣጫ እየተመለከቱ አብረው የዘመሩ ሲሆን ፍጹም በተረጋጋ መንፈሳዊ ድባብ የመድኃኔ ዓለም ክርስቶስን ልደት በአእላፋት ዝማሬ አክብረዋል:: የኢትዮጵያዊው ጃንደረባ ትውልድ ወጣቶች ለወራት በብዙ ጸሎትና ትጋት የደከሙበት ይህ የዝማሬ ማዕድ በእግዚአብሔር ጥበቃ ባማረ ሁኔታ ተከናውኖአል:: አእላፋት በዕንባና በተመሥጦ ሆነው እየዘመሩ የመድኃኒታቸውን ልደት በመንፈስ አክብረዋል:


የአእላፋት ዝማሬ ለፓሪስ ኦሎምፒክ ጸያፍ ትርዒት ምላሽ ሠጠ
| ጃንደረባው ሚድያ | ታኅሣሥ 2017 |
አዲስ አበባ - ኢትዮጵያ

የ2017 ዓ.ም. የአእላፋት ዝማሬ ላይ "የገና መልእክት ከኢትዮጵያውያ ሰዎች ወደ ኦሎምፒከኞች" (A Christmas Message from Myriads to Olympiads) በሚል ርእስ የሁለት ደቂቃ አኒሜሽን ታየ:: የዚህ መልእክትም ዋነኛ ሃሳብ ከአራት ወራት በፊት በፓሪስ ኦሎምፒክ መክፈቻ ላይ የጸሎተ ሐሙስ ሥዕል ላይ ጸያፍ መልእክቶችን በማስተላለፍ የተደረገውን ተሳልቆ ለጸሎተ ሐሙስ ሥዕልና ለከበረው የክርስቶስ ደም ክብር የምትሠጠው የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያንን ምን ያህል እንዳስቆጣ ለማሳየት ነው:: "እነርሱ በስሙ ሲዘብቱ ኢትዮጵያ ግን ዳግመኛ እጆችዋን ወደ እግዚአብሔር ትዘረጋለች" (When they mock his name in vain, Ethiopia lifts her hands to God again) የሚል መልእክት ያለው ይህ ቪድዮ የፓሪስ ኦሎምፒክ አዘጋጆችን ድርጊት በክርስቶስ ላይ የጥላቻ ጦር ከሰበቀው ከንጉሥ ሔሮድስ ድርጊት ጋር በማመሳሰል የተሠራ መሆኑን የአኒሜሽኑ ዳይሬክተር ወ/ሪት ቅድስት ፍስሓ ገልጻለች::

"ዓለም አቀፍ መክፈቻ ሥነ ሥርዓቶችና ምርቃቶች በተካሔዱ ቁጥር በክርስትና መቀለድና ሰይጣናዊ ትርዒቶችን ማሳየት እየተለመደ መጥቶአል" ያሉት የአኒሜሽኑ ክሪኤቲቭ ዳይሬክተር ዲ/ን ሄኖክ ኃይሌ በበኩላቸው "ዓለም አቀፍ ሚድያዎች ከፍተኛ ሽፋን እየሠጡት ባለው በአእላፋት ዝማሬ ላይ ለዓለም አቀፉ ተመልካች የሚሆን መልእክት ለማስተላለፍ አጋጣሚውን ተጠቅመንበታል" ብለዋል::


ሁለተኛው የአእላፋት ዝማሬ በቦሌ ደብረ ሳሌም መድኃኔዓለም በድምቀት ተካሔደ::

| ጃንደረባው ሚድያ | ታኅሣሥ 29 2017 ዓ.ም.|
አዲስ አበባ - ኢትዮጵያ

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በጠቅላይ ቤተ ክህነት በማኅበራት ምዝገባና ክትትል መምሪያ በኢትዮጵያዊው ጃንደረባ ትውልድ የተዘጋጀው የአእላፋት ዝማሬ ለሁለተኛ ጊዜ በድምቀት ተካሔደ:: ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክን ጨምሮ ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት ብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ የትግራይ ማይጨውና የማኅበራት መምሪያ ሊቀ ጳጳስ ፣ ብፁዕ አቡነ ሄኖክ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ፣ ብፁዕ አቡነ መቃርዮስ የምዕራብ ካናዳ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ፣ ብፁዕ አቡነ ቶማስ የአዊ ዞን ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ፣ ብፁዕ አቡነ ኤልሳዕ የሱማሌ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ፣ አቡነ መቃሪዮስ የምዕራብ ካናዳ ሃገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ፣ አቡነ ኤጲፋንዮስ የምሥራቅ ጉራጌ ሀገረ ስብከት ጳጳስ
የመምሪያ ኃላፊዎችና የአኃት አብያተ ክርስቲያናት ልዑካን ፣ አንጋፋ ዘማርያን በተገኙበት በዚህ የአእላፋት ዝማሬ ላይ ከአምናው በቁጥር እጅግ የበዛና ቅጽረ ቤተ ክርስቲያኑን አልፎ መንገዱን እስከ መዝጋት የደረሰ ሕዝበ ክርስቲያን በዝማሬው ላይ ታድሞ አምሽቶአል::

በመምህር ጳውሎስ መልክዓ ሥላሴ መሪነት በተካሔደው በዚህ ጉባኤ በተያዘው መርሐ ግብር መሠረት ከቀኑ ዐሥር ሰዓት ላይ ስለ ሀገራችን ሰላምና የተፈጥሮ አደጋዎች ጸሎተ ምሕላ በማድረግ የተጀመረ ሲሆን በቅዱስነታቸው መሪነት ጸሎተ ወንጌልና ኪዳን ደርሶ ተጀምሮአል:: በማስከተል የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ሄኖክ የእንኳን አደረሳችሁ መልእክት አቅርበዋል:: በማስከተል የአእላፋት ዝማሬ የማብሠሪያ መዝሙር በቅዱስነታቸው ፊት ከተዘመረ በኋላ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ የልደት በዓልን አስመልክቶ ትምህርተ ወንጌል ሠጥተው የአእላፋት ዝማሬን ማኅቶት ባርከው በመለኮስ አስጀምረው ዝማሬውን ባርከው ወደ መንበራቸው ተመልሰዋል:: የአእላፋት ዝማሬ ከአምናው በተለየ ዝግጅት የመድረኩን ቅርጽ በጥንታዊ ኢትዮጵያዊ ሥዕላት ያጌጡ ሲሆን ከመድረኩ ግርጌም ኢትዮጵያ ሁለቱን ኪዳናት እንደተቀበለች በሚያሳይ መንገድ ታቦተ ጽዮንና የጃንደረባው ሠረገላ ለእይታ ቀርበዋል::

የኢትዮጵያዊው ጃንደረባ ትውልድ ጃን አጋፋሪ የሴኪውሪቲ ኃላፊ ወ/ሪት ትዕሲት "ከተጠበቀው በላይ የምእመናን ቁጥር በዝማሬው ላይ በመገኘታቸው ምክንያት የፍተሻና የመስተንግዶ ሒደቱን ከአቅም በላይ ያደረገው ቢሆንም ምእመናን በትዕግሥትና በታዛዥነት የአእላፋት ዝማሬን ያማረ እንዲሆን ስላደረጉ ከፍ ያለ ምስጋና እናቀርባለን" ያሉ ሲሆን "በቀጣይ ዓመት ከዘንድሮው በተሻለ መንገድ ለማካሔድ ከወዲሁ ዝግጅት እንደምንጀምር ቃል እንገባለን" ብለዋል::

የአእላፋት ዝማሬን በአካልና በኦንላይን ሚልዮኖች የታደሙበት ሲሆን የዘንድሮው አእላፋት ከአምናው በተለየ በርካታ ምእመናን በቦሌ ደብረ ሳሌም ቆይተው በማስቀደስ በቅዳሴ እንዲያጠናቅቁ መመሪያ የተሠጠበት ነበረ:: በዚህም መሠረት በርካታ ምእመናን እዚያው ቆይተው ያስቀደሱ ሲሆን ቤተ መቅደሱ ከሞላ የደረሱ ምእመናን ደግሞ በስክሪን ቅዳሴውን ተከታትለዋል:: የኢጃት ጃን ቅዳሴ ሰብሳቢ መምህር ኃይለ ኢየሱስ "ለ2018 ዓ.ም. የአእላፋት ዝማሬን ሙሉ በሙሉ ወደ አእላፋት ቅዳሴ ለማሸጋጋር በቅርብ ቀን የቅዳሴ ተሰጥኦ ትምህርት በጃንደረባው ሚድያ ስለምንጀምር ምእመናን ለመማር ዝግጁ ሆነው ይጠብቁን" ብለዋል:: የአእላፋት ዝማሬ በበርካታ ሀገር በቀልና ዓለም አቀፍ ሚድያዎች ሽፋን አግኝቶአል::


ወደ አእላፋት ዝማሬ ሲመጡ እስከ 10 ጧፍ ይዘው እንዲመጡ ጥሪ ቀርቧል። ሦስቱ ጧፎች የአእላፋት ዝማሬ እስኪጠናቀቅ የሚበሩ ሲሆን የቀሩትን ለደብሩ በመባ መልክ ያስረክቡ። በደብሩ በኩልም ለገጠር አብያተ ክርስትያናት ድጋፍ ይደረጋል።


የ2017 ዓ.ም የአእላፋት ዝማሬ ጋዜጣዊ መግለጫ ዛሬ ከቀኑ 10:30 በጃንደረባው ሚድያ የዩቲዩብ ቻናል ላይ ይጠብቁን

https://www.youtube.com/watch?v=PNV6TxWJonw




'ወዳንቺ የመጣው | ሊቀ መዘምራን ይልማ ኃይሉ' የመዝሙር ቪዲዮ ተለቀቀ ሙሉ ቪዲዮውን በጃንደረባው ሚዲያ የYouTube channel ላይ ያግኙ

https://youtu.be/PXF7Y8ME42Y



Показано 8 последних публикаций.