የፍቅር ቴሌግራም ❤️‍🔥™


Гео и язык канала: Эфиопия, Амхарский


𝐖𝐞𝐥𝐜𝐨𝐦𝐞 t̑̈ȏ̈ የፍቅር ቴሌግራም™ ❤
💙በዚ 𝐂𝐡𝐚𝐧𝐧𝐞𝐥 ላይ
💜ድርሰቶች
💚የፍቅር ግጥሞች
💛ጣፋጭ ታሪኮች
❤️ምክሮች ...
አልፎ አልፎ ቀልዶች ይለቀቁበታል 😂

Since 2016 e.c
❤️ከናተ ሚጠበቀው 𝐉𝐨𝐢𝐧 to request በማረግ ብቻ መከታተል ነው ❤️
👇👇👇

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Гео и язык канала
Эфиопия, Амхарский
Статистика
Фильтр публикаций


ከBETTING ውርርድ እንዴት ብዙ ገንዘብ ማግኘት እንደሚችሉ ማወቅ ይፈልጋሉ? በወር ከ100,000 እስከ 1,000,000 ብር! አው ከሆነ መልስህ/ሽ Join✅
የምትለውን በመንካት ይቀላቀሉን! ህይወትህን አሁኑኑ ቀይር ❗️✅


Репост из: Ei Du 💃
🥰ለፕሮፋይል የሚሆኑ ገራሚ ገራሚ ፎቶዎችን ለማግኘት ከስር ጆይን ያድርጉ የፈለጉትን አይነት ያገኛሉ ይ🀄️ላ🀄️ሉን!👇

https://t.me/+UqU8zCoHqyw2NzQ0


      🔸🔸🔺🔺🔹🔸

      
❤️ የፍቅር ጥግ ❤️

ልብ አንጠልጣይ እውነተኛ  ታሪክ
❤️

ፀሀፊ
✍️ ማኔ


                        ክፍል  
3️⃣7️⃣


እንዴት በድጋሜ ሰው አምናለሁ እያል መብሰልሰል ጀመርኩ   ትንሽ ቆይታ ልእልት መጥታ በር አንኳኳች እራት እንብላና ወደቤቴ ልሂድ አለች፡፡
እናንተ ብሉና ሂጂ እኔ አልመጣም አልኳት፡፡
በር ላይ ቆማ ለረጅም ሰአት ከለመነችኝ ቡሀላ እሺ ደና ደር ብላኝ ሄደች።

ምሽቱን ሙሉ ብቻዬን ስነሳ ስቀመጥ ዝም ብዬ ክፍሉ ውስጥ ስንጎራደድ አራት ሰአት አካባቢ ሆነ የዛኔ መተኛትም ማሰብም አልቻልኩም የማስበው ግራ ገባኝ ጭንቅላቴ ውስጥ ጭጭጭጭ የሚል ድምፅ ብቻ ይሰማኝ ጀመር።
ተነስቼ ከክፍሌ ወጣሁና ወደ እዮብጋ ሄድኩ ቤት ውስጥ የለም ዞር ዞር ብዬ አየሁትና ወደ ውጭ ወጣሁ ቀጥጥጥ ብሎ ቆሞ ሰማይ ሰማይ እያየ ፈገግ ይላል እግሩ ስር ቢያንስ አራት አምስት የተጨሰ ሲጋራ ተጥሏል።

አየሁትና አጠገቡ ሄጄ ምን እንደሆነ ጠየኩት።
ዝም ብሎ ፈገግ ብሎ እያየኝ ምንም አልሆንኩም አንተ ለምን መጣህ አለኝ። ቤት ስለጨነቀኝ ወክ እንድናደርግ ጠየኩት እሺ አለኝ ቤቱን እንኳን ሳንዘጋው የውጭውን በር ብቻ ቆልፈን ወጣን።

ሰፈሩ ጭር ብሏል እኛ ዝም ብለን መራመዳችንን ቀጥለናል ሁለታችንም ዝም ብለን እስከ አስፋልት ደረስን ወዴት እንሂድ ወደቀኝ ወንስ ወደግራ ተባብለን ወደቀኝ ጉዞ ጀመርን በመሀል እኔ ቅድም ለምን ነበር ብቻህን ፈገግ ስትል የነበረው አልኩት።
ልእልትን እያሰብኩ ነበር አለኝ።

በጥያቄ አይን እያየሁት ከምርህን ነው እሷን አስበ በጥያቄ አይን እያየሁት ከምርህን ነው እሷን አስበህ ፈገግ አልክ አልኩት፡፡ አዎ ፈጣሪ እንደማይወደኝ የገባኝ እሷን ከረፈደ ቡሀላ ባንተ በኩል አድርጎ ወደኔ ሲያመጣት ነው አለኝ፡፡ እንዴት????

በቃ አሁን ላይኮ ሁሉም እረፍዷል አብቅቷል ህይወት ለኔ በሯን በዘጋችብኝ ሰአት የሷ መምጣት ልክ አደለም ለዛውም አንተን አፍቅራ ስትከተልህ እኔ እሷን መተዋወቄ ልክ አደለም፡፡ እንዳዲስ እንድኖር እያጓጓችኝ ነው፡፡
ዝም ብዬ በማንኛውም ሰአት እሷን ማየት እሷ ወዳለችበት መሄድ ነው ምፈልገው አለኝ። እኔ እንደዛ ሲለኝ ውስጤ ላይ የነበረው ስሜት ምን እንደሆነ ግራ ገባኝ ብቻ ዝም ብዬ ባፌ መለፍለፍ ጀመርኩ፡፡ አረፈደምኮ አሁንም አብራችሁ መኖር ትትችላላችሁ፡፡

ይሄኔኮ እሷም ትወድህ ይሆናል በቃ እሱን ሊያፅናና ይችላል የምላቸውን ቃላቶች መደርደር ጀመርኩ፡፡ እዮብ ግን በአባቱ እየማለ መቼም ቢሆን ልእልትን የራሱ እንደማያደርጋት ነገረኝ፡፡ ከዛ ሁለታችንም መሀል ፀጥታ ሰፈነና ዝም ብለን እየተጓዝን የተከራየንበት ሰፈር ስንደርስ ዝም ብለን ገብተን ተኛን። የእናቴ ሙት አመት አለፈ። ሙት አመቷ ቀን ሁሉም ከንፈሩን እየመጠጠ መቃብሯን ከበው ቆመው ነበር ።እኔ ማንም ሰው ሳያየኝ ከሩቅ አይቻቸው ተመለስኩ።

ልክ በነጋታው ግን ሁሉም ያነሱት ሀሳብ ስለቤቱ ነበር ሁሉም ነገር በልእልት ስም እንደሆነ ሲያውቁ ሊገሏት ምንም አልቀራቸውም ሙሉ እንደጠላት ነበር ያዩዋት ቤቱን ለመውረስ ብላ ልጁን የሆነ ነገር አድርጋው ነው እንጂ በህይወት ቢኖር ኖሮ እኛ እናየው ነበር ይጣራልን ወንጀለኛ ነች ብለው ከሰሷት።

እኔ በአካል ፍርድ ቤት ቀርቤ ወድጄና ፈቅጄ ይሄንን እንዳደረኩ ግልፅ መረጃ ሰጠሁ፡፡
አክስቶቼ ከአመት ቡሀላ ያ የሚያቁት መልኬ ሳቄ ጠፍቶ ሲያዩኝ ምነው ከሳህ ምነው ጠቆርክ አላሉኝም
የሁሉም ጥያቄ ተመሳሳይ ነበር ለማንም ባዳ አሳልፈህ ከምትሰጠው እኛ እህቶቿ ብንጠቀምበት አይሻልም ነበር ያሉኝ። ላያቸውም ስላልፈለኩ ትቻቸው ሄድኩ፡፡
እኔና እዮብ አንዴ ቤት አንዴ የኪራዩ ቤት እያደርን ጊዜያቶች መሄድ ጀመሩ፡፡
ልእልትም ብትሆን የመመረቂያ ጊዜዋ ተቃርቧል።

እዮብ እንዴት እንደምናስመርቃት እያሰበ ብቻውን ይደሳሰታል። ሁኔታውን ሳየው ግራ ይገባኛልም ያሳዝነኛልም፡፡
በአጋጣሚ ሌላ ቦታ ሄደን ከልእልትጋ
ሳንገናኝ ከዋልን ። ከአፉ የሷ ስም አይጠፋም ሳልፈልግ ስለሷ እንዳስብ ያደርገኛል።

እሷ እያየችው ማጨስ አይፈልግም እሷ ፊት መቃም መጠጣት ነውር መስሎ ነው ሚታየው።
ከአስር አመት ቡሀላ ለመጀመሪያ ጊዜ ፊቱን በመስታወት ያየው ልእልትን ከተዋወቃት ቡሀላ ነው።

የመጀመሪያ ቀን መስታወት ፊት ቆሞ እራሱን አየና አየህ አደል ባህራን ጊዜ ሲጥልህ ሁሉም ይተውሀል መልክህ...



ይቀጥላል...



🔻ክፍል3️⃣8️⃣1️⃣5️⃣0️⃣ like በዃላ ይቀጥላል...  ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ Like💝 ማድረግ አይርሱ።
🔺🔺🔺🔺🔺😀😀😀😀😀

      ‌‌‌‌‌‌‌      ይ 🀄️ላ🀄️ሉን!
😀

💔 https://t.me/yefikirtelegramet 💔


ሰላም ሰላም ቤተሰብ የፍቅር ጥግ ክፍል 37 ሊለቀቅ ነው አላችሁ ወይ?


      🔸🔸🔺🔺🔹🔸

      
❤️ የፍቅር ጥግ ❤️

ልብ አንጠልጣይ እውነተኛ  ታሪክ
❤️

ፀሀፊ
✍️ ማኔ


                        ክፍል  
3️⃣6️⃣

ይውሰዱት አልኳት።
ሁለቱም ተናደዱብኝ ልእልት ተስፋ በመቁረጥ አይን ተመለከተችኝ፡፡
ተነስቼ ልወጣ ስል እዮብ አስቆመኝና እንግዳኮ ነኝ ለቤቱ ትተኸኝ ልትወጣ ነው እንዴ ብሎ አስቆመኝ፡፡

ተመልሼ ቁጭ አልቁ ስለቤቱ እርእስ ማንሳት አልፈለኩም እነሱም ሁኔታዬ ስለገባቸው ዝምታን መረጡ፡፡
ቀኑ እየመሸ ሲሄድ ልእልት ቤት ደርሼ ሸውጄ እወጣለሁ ካልሆነ እናቴ ትገለኛለች ብላ ተነስታ ወጣች፡፡
ትንሽ ቆይቶ በር ተንኳኳ ተመልሳ እንደመጣች አስበን እዮብ በር ከፈተ ግን እሷ አልነበረችም ከሱቅ ሳጥን ቢራ የያዘ ሰው በር ላይ ቆማል እኔ ደረጃው ላይ ቆሜ ስለነበር እዮብ ግራ ገብቶት ማነው ያዘዘው ማእዶት ናት የላከችው እያለ ነው አለኝ።ግራ ገብቶኝ እኔጃ ማናት ማእዶት አልኩት ሰውዬው ቀበል አድርጎ እዚህ ጎረቤታችሁ ናታ ቆንጅዬዋ ድምፕል ያላት ፀጉረ ረጅሟ ልጅ አለ፡፡

ስለማን እያወራ እንደሆነ ስለገባን ተቀብለነው ወደውስጥ አስገባነው ልእልት እስክትመጣ እዮብ እኔ አልጋ ላይ የነበረውን ፍራሽ ሳሎን አነጣጠፈና ና ዱቅ እንበል አለኝ፡፡ ለአይን ያዝ ያዝ ሲያደረግ ልእልት በድጋሜ በር አንኳኳች ከፍተን አስገባናት እዮቤ ገና ከበር አንቺ ማእዶት ነው እንዴ ስምሽ አላት። አዎ እኔኮ ብዙ ስም ነው ያለኝ ይሄኔ በስሜ ልክ ብር ቢኖረኝ እኔ ነበርኩ ሀብታም ብላ እየቀላለደች ፍራሹ ላይ ቁጭ አለች።

እስክመጣ እንድትጠጡኮ ነው ቀድሜ መጠጡን የላኩላችሁ አጠጡም እንዴ አለችን።
እዮብ አብራን ከጠጣች ብለን እየጠበቅናት እንደሆነ ነገራት፡፡

ታውቁ የለ እንደማልጠጣ እናንተ ጠጡ አለችን ተጀመረ ሞቅታው ሲጀምርን እርስ በርስ መተራረብና ከጣራ በላይ መሳቁን ተያያዝነው፡፡ ልእልት ሁኔታችን ግራ ገብቷት ድምፅ እንድንቀንስ አጥብቃ እየጠየቀችን እንደነበር አስታውሳለሁ፡፡

ልክ መጠጡ ድንዝዝ ማድረጉን ሲቀጥል ልእልት እንድናቆም ነገረችን እኔ አሻፈረኝ አልኩኝ የእናቴን ፎቶ እያየሁ ድፍት ብዬ እዬዬ ማለት ጀመርኩ ልእልትና እዮብ እንደምንም አስነስተው አስገብተው አስተኙኝ።
ጠዋት አረፋፍጄ ተነሳሁ እዮብ ብቻውን ነው ያለው ፡፡ቁርስ ላቅርብ ተነስና ታጠብ አለኝ።

ተጣጥቤ ቁርስ እየበላን እዮብ አንድ ሀሳብ አቀረበልኝ አሁን አንተ ለዚህ ቤት በብርቱ አላማ የመታገል ሀሳብ ከሌለለህ ለምን ቤቱን በልእልት ስም አታረገውም ቢያንስ ዘመድ ጎረቤት ፊቱን ሲያዞርብህ አንድ ያልተወችህ ሰው እሷ ናት ።

እናትህም ለሷ ነው አደራ የሰጠችህ።
እንደምታያት ጎበዝና ጠንካራ ልጅ ናት በምንም አይነት ሁኔታ ውስጥ አትተውህም ስለዚህ አሁኑኑ ፕሮሰሱን እንጀምርና በሷ ስም አድርግላት አለኝ።

እሺ ማለትም መቃወምም አልፈለኩም።
ዝም አልኩት፡፡እዮብ ቁጭ አድርጎ ብዙ ነገሮችን ነገረኝ መከረኝ ። ያው በሰአቱ ለምንም ነገር ፍላጎት ስላልነበረኝ ዝም ብዬ እሺ እሺ አልኩት።

እስከ ምሳ ሰአት አንዴ ስንጠጣ አንዴ ስናጨስ ከቤት ግቢ ውስጥ ከግቢ እቤት ስንመላለስ ምሳ ሰአት ደረሰ። ልእልት መጣች ትምህርት ቤት እንደሚሄድ ሰው ለባብሳ
ነበር፡፡እዮብ እንዳያት ሄዶ ጥምጥም አለባት።
እኔ ዝም ብዬ ቁጭ አልኩ።
አጠገቤ መጥታ ቁጭ አለችና ዛሬ እቴቴ መቃብርጋ አትሄድም አደል ይኸው ቤቱም ምኑም የሷ ፎቶ ስለሆነ እዚህ እሷን ማየት ትችላለህ ።
ስትወጣ ስትገባ እያዩህ እንዳይረብሹህ ብዬ ነው አለችኝ፡፡ በሀሳቧ ተስማማሁ እዮብ ገና ከመቀመጧ ቤቱን ባንቺ ስም ሊያደርግልሽ ነው አላት።

ደነገጠች አረ አይሆንም በስማም እኔ አልፈልግም ይሄ ቤትኮ እቴቴ ነፍሷን ያጣችበት ቤት ነው ለሱ ደሞ ምን ማለት እንደሆነ ያቀዋል አለች።
እኔ ሀሳብ አልሰጥም ወሳኝም ፈራጅም ሁለቱ ሆነው ቁጭ አሉ።እዮብ ከነምክንያቱ እትትት እያለ ያስረዳት ጀመር።

በመሀል እዮብ ለልእልት በዛውምኮ ይሄ ቤት በስምሽ ከሆነ መቼም ቢሆን ተለያይታችሁ አትለያዩም አናቱን ባሰ ቁጥር ቤቱን ያስባል ቤቱን ባሰበ ቁጥር ደሞ አንቺን ያስብሻል አላት። ትንሽ አንገራገረችና እሺ አለች።
የዛን ቀን ልእልትና እዮብ ባንድ ነጠላ ካላስቀደስን እያሉ አብረው ቤት ሲያፀዱ አብረው ምግብ ሲሰሩ ቀኑ አለፈ። በነጋታው ልእልት ከቤቷ እስክትመጣ ጠብቀን አብረን ወደሚመለከተው አካል ሄድን ።

የሚያስፈልገውን ሁሉንም ፕሮሰስ ጠየቅን ነገሩን ያን ያህል ከባድ አልነበረም ፕሮሰሱን ጀመርን ሙሉ ያለኝ ነገር የቀረኝ አንድ ሀብት ቤታችንን በልእልት ስም አደረግነው አክስቶቼ ቤቱን ሊጠይቁ ሲመጡ በሷ ስም እንደሆነ ሲያውቁ የሚሰማቸውን ስሜት እያሰብኩ ደስታ ተሰምቶኝ ነበር።

ብቻ በዛን ሰአት ልክ ቤቱን በስሟ አድርገን ስንመለስ ፏ ብዬ ለብሼ ፀጉሬን ተስተካክዬ ነበር ምክንያቱም እዛ ቦታ ላይ ከንግግር በላይ የለበስነው ልብስ ዋጋ አለው፡፡

መንገድ ላይ ልእልትና እዮብ ተያይዘው እየሄዱ እኔ ከኋላቸው ብቻዬን እጄን ኪሴ ከትቼ እየተራመድኩ እነሱን እየተመለከትኩ ነበር ሁሉም ሰው አይኑ እነሱ ላይ ነው ሲመስለኝ እዮብና እሶ ፍቅረኛሞች መስለዋቸው ሳይሆን
አይቀርም። ቤት ገባን አሪፍ ጊዜ እንዲያሳልፉ ነግሪያቸው መኝታ ቤቴ ገብቼ ቆለፍኩና ጋደም አልኩ።
ጭንቅላቴ እረፍት አጣ ልእልት የምር ምትታመን ሰው ናት ከፋኖስ ቡሀላ መመማር መቻል ነበረብኝ እንዴት በድጋሜ......







ይቀጥላል...



🔻ክፍል3️⃣7️⃣1️⃣5️⃣0️⃣ like በዃላ ይቀጥላል...  ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ Like💝 ማድረግ አይርሱ።
🔺🔺🔺🔺🔺😀😀😀😀😀

      ‌‌‌‌‌‌‌      ይ 🀄️ላ🀄️ሉን!
😀

💔 https://t.me/yefikirtelegramet 💔


ሰላም ሰላም ቤተሰብ የፍቅር ጥግ ክፍል 36 ሊለቀቅ ነው አላችሁ ወይ?


Репост из: Info Tech
📣Guys  Getgems ላይ  1 caps NFT  70Ton   እየተሸጠ ነው  

💠ይሄ Game በ24hour ውስጥ 1.5M ደንበኛ አፍርተዋል

💠ከ6 ቀን በዃላ ያለውን ሙሉ መረጃ ያደርሱናል   በ multi acount ጀምራችሁ ጠብቁ 

💠ለጊዜው ሁለት Task ብቻ ነው ያለው 

Start here
👇👇👇👇👇
https://t.me/DurovCapsBot/caps?startapp=414781528


      🔸🔸🔺🔺🔹🔸

      
❤️ የፍቅር ጥግ ❤️

ልብ አንጠልጣይ እውነተኛ  ታሪክ
❤️

ፀሀፊ
✍️ ማኔ


                        ክፍል  
3️⃣5️⃣

ግን መቆየት አልቻልኩም ምራቄን እራሱ ለመዋጥ አቃተኝ ደሞ ጠረኗ ደስ ይላል።

አስራ ምናምን ደቂቃዎችን ታገልኩና እጆቼን ከላይዋ ላይ አንስቼ ፊቴን ላዞር ስል በማርያም ትንሽ ደቂቃ ብቻ እቀፈኝ በእቴቴ ይዤሀለሁ አለችኝ።አልተኛሽም እንዴ አልኳት።ተኝቼ ነበር ግን ስነሳ እዚህ ሁኔታ ውስጥ እራሴን ሳገኘው መተኛትን መረጥኩ አለችኝ።ስለዚህ አንቺም እኔም እያስመሰልን ነበር አልኳት። አዎ ለደቂቃዎች ከራስጋ ስትታገል እያየሁ ነበር እኔ ደሞ አቅፈኸኝ ትንሽ ደቂቃ እንድትቆይ እየፀለይኩ ነበር አለችኝ።

ይሄን ዋጋ አለው እንዴ እኔ አንቺን ማቀፌ ብዬ ጠየኳት፡፡ ምናልባትም አንተ ከምታስበው በላይ ለኔ ዋጋ አለው እኔ ደሞ በተፈጥሮዬ መታቀፍን ምወድ ሰው ነው የሆነ ሰው ሲያቅፈኝ ሰላሜን እየሰጠኝ ይመስለኛል።
በምወደው ሰው መታቀፍ ደሞ ለኔ ህልም ነው አለችኝ፡፡ ዝም ብያት ተነሳሁና ቆምኩ ትገርማለህ በእቴቴ
ይዤሀለሁ እያልኩህ ለማንኛውም እሺ ብላ ፊቷን አዙራ ተኛች።

ስታኮርፍ በራሱ ሌላ ውበት አላት ከፊት ለፊቷ ቆምኩና እሺ ነይ ተነሽ አቅፌ ሳሎን ልውሰድሽ አልኳት ዘለለች መጥታ ተጠመጠመችብኝ ደረቴ ላይ እንደህፃን ልጅ ልጥፍ ብላ አንገቴ ስር ውሽቅ አለች። በሁኔታዋ ፈገግ እያልኩ ወደሳሎን አቅፌ ወሰድኳት ሶፋ ላይ ውረጂ ብላት አሎርድም አለች በእጇ አጥብቃ ከመያዟ የተነሳ አንገቴን ህመም ተሰምቶኝ ነበር።

አረ ደከመኝ ብዬ እንድትወርድልኝ አደረኩና እኔ ቁጭ ከልኩ። እሷ ወደስልኳ ሄደች በስማም ስንቴ እንደተደወለ መጣሁ ቆይ እናቴን ላውራት ብላ ወደውጭ ወጣች።
ብዙም ሳትቆይ እዮብን ይዛው ወደውስጥ ገባች፡፡ እንዳየኝ መጣና ሰላም አለኝ።
እኔ ፊቴን እንደጣልኩት ዝም ብዬ ቁጭ አልኩ ልእልት አውሩ በሉ እኔ ምግብ ልስራ አለችና ወደውስጥ ገባች፡፡

እዮብ ሁሉንም ነገር አስረዳኝ ገና ጎዳና ላይ ብዙ አመት ስትቆይ ምትለምደው ብዙ ነገር አለ።ፊት ለፊትህ ሰው ሲታረድ እያየህ ባላየ ልታልፍ ትችላለህ ምንም የማያውቁ ህፃናት የሰቆቃ ድምፃቸውን እያሰሙ እየለመኗቸው ያለምንም ርህራሄ ሚደፍሩ ብዙ የጎዳና ልጆች አሉ አለኝ፡፡ ትንሽ ተረጋጋሁ እዮብ መረጋጋቴን ሲመለከት ዞር ዞር እያለ ቤታችንን ማደናነቅ ጀመረ፡፡

ቀጠል አድርጎ ወደ ልእልትጋ ገባና አብረው እየተሳሳቁ ምግም መስራት ጀመሩ እኔ ላጨስ ወጣሁ ውጭ ላይ ቁጭ ብዬ ሳብ ሳብ አደረኩና ሲጋራውን ጣልኩት፡፡ ትንሽ ቆይታ ልእልት መጣችና አስደነገጥከኝኮ ና ምሳ ደርሷል አለችኝ ተከትያት ገባሁ ከምሳ ቡሀላ ልእልት ልታወራኝ ምትፈልገው ጉዳይ እንዳለ ነገረችኝ።
ምን እንደሆነ ጠየኳት።


ምን እንደሆነ ጠየኳት። አሁን የእቴቴ ሙት አመት እየደረሰ ነው እና ዘመዶቻችሁ እሱ እየደገሱላት ነው።

ልክ ሙት አመት ፕሮግራሙ እንዳለፈ ግን ይዠየዚህን ቤት ጉዳይ ወደፍርድ ቤት ሊወስዱት አስበዋል። አንተ ቤት ውስጥ ስለማትኖርና አልፈልግም ብለህ ሀገር ጥለኽ ስለጠፋህ ቤቱ ተዘግቶ ከሚኖር እነሱ ቢጠቀሙበት እንደሚሻል አውርተው ጨርሰዋል።

ባለፈው አክስትህ መጥታ ነበር እና ሁሉንም የነገረችኝ እሷ ናት ከቻልክ ይሄ ቤት እቴቴ ላንተ የተወችልህ ትልቁ የህይወት አደራ ስለሆነ የሆነ መፍትሄ እንድትፈልግ ነው እንደኔ እንደኔ እንደምንም ብለህ ተመልሰህ እዚህ ቤት መኖር አለብህ አለችኝ



ይቀጥላል...



🔻ክፍል3️⃣6️⃣1️⃣5️⃣0️⃣ like በዃላ ይቀጥላል...  ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ Like💝 ማድረግ አይርሱ።
🔺🔺🔺🔺🔺😀😀😀😀😀

      ‌‌‌‌‌‌‌      ይ 🀄️ላ🀄️ሉን!
😀

💔 https://t.me/yefikirtelegramet 💔

4.3k 0 14 2 264

ሰላም ሰላም ቤተሰብ የፍቅር ጥግ ክፍል 35  ሊለቀቅ ነው አላችሁ ወይ?


አንበሳውን ይከተሉ

ዝሆን ትልቅ ነው; ቀጭኔ ረጅም, ቀበሮው ጥበበኛ ሲሆን አቦሸማኔ ደግሞ በጣም ፈጣኑ እንስሳ ነው፡፡ ሆኖም ግን አንበሳ ምንም ልዩ መገለጫ ነገር ባይኖረውም የጫካው
ንጉስ ነው፡፡ ምክንያቱም አንበሳ ደፋር ነው፡፡ በልበ ሙሉነት ማንኛውንም ነገር ይከውናል ፈጽሞ አይፈራም።
° አንበሳ አንዳችም ሀይል ሊያቆመው እንደማይችል ያምናል።
° አንበሳ ማንኛውም እንስሳ ለእሱ ምግብነት በበረከት የቀረቡለት መሆኑን ውስጡ ይነግረዋል አንበሳ ማንኛውንም እድል መሞከር ጠቃሚ ነው ብሎ ስለሚያምን ከመሻት ባለፈ በድርጊትም ያሳያል፡፡
በመሆኑም ጥበበኛ መሆን አላስፈለገውም ብልህ መሆንም አላሻውበጣም ብሩህ መሆንንም እንደዛው እናም ወዳጄ! የሚያስፈልግህ ድፍረት ነው፣
የሚያስፈልግህ መሞከር ፍላጎት ነው፣ የሚያስፈልግህ እምነት ነው፡፡ የሚያስፈልግህ በራስህ መተማመን ነው፣ ይቻላል መንፈስን በውስጥ አስርጽ። አንበሳ 20 ሰአታት
ይተኛል ለ 4 ሰአታት ይሰራል በስተመጨረሻም ስጋ ይመገባል። ዝሆን ለ 24 ሰአት ይሰራል ሆኖም እጽዋት ነው ምግቡ፡፡

የእርስዎ ሀሳብ ምንድነው?

✍ተሰማ




https://t.me/yefikirtelegramet


      🔸🔸🔺🔺🔹🔸

      
❤️ የፍቅር ጥግ ❤️

ልብ አንጠልጣይ እውነተኛ  ታሪክ
❤️

ፀሀፊ
✍️ ማኔ


                        ክፍል  
3️⃣4️⃣


እኔም ተነስቼ እግሬ ወደመራኝ ተጓዝኩ ቁርስም
ስላልበላሁ ስራመድ አቅም እያነሰኝ ሲመጣ taxi ይዤ ወደናቴ መቃብርጋ ጉዞ ጀመርኩ ።

አጠገቤ የተቀመጠችው ልጅ እኔ ከጎና ስለተቀመጥኩ ክብሯን ያጣች ያህል እንደተሰማት ተመለከትኩ በአይኗ ገላምጣ ጨረሰችኝ መኪናው ትንሽ ሲንገጫገጭ ሰውነቴ ከሰውነቷ ሲነካካ እንዴት ፅይፍ እንዳለችኝ ተመለከትኩና ከtaxi ወረድኩላት ብቻዬን አይ ባህራን እውነት ግን እኔ እራሴ ነኝ መሞት በስንት ጣሙ ብዬ እያወራሁ በሌላ taxi ወደናቴጋ ሄድኩ። የእናቴ መቃብርጋ ቁጭ አልኩና አይ እማ እንደዛ ለማቀፍ ምትናፍቂው ልጅሽ ዛሬ ሰዎች ለመንካት ሚፀየፉት ሰው እንደሆነ ብታይ ግን ምን ይሰማሽ ይሆን አልኳት፡፡ ትንሽ ቁጭ ካልኩ ቡሀላ ልሄድ ስል ልእልት መጣች እንዳየችኝ አቀፈችኝ፡፡
ዝም ብዬ አየኋት።

የት ጠፍተህ ነው ግን ሌሊቱን ሙሉ ምን ሆኖ ይሆን ብዬ እያሰብኩ አይኔ እንደፈጠጠ ነው የነጋልኝ አየሁ አይኔ እንዴት እንዳበጠ አለችኝ፡፡
አሳዘነችኝ ። ግን ካፌ ምንም ቃል አላወጣሁም ዛሬ ቀኑን ሙሉ እዚህ ቁጭ ብዬ ልጠብቅህ ነበር የመጣሁት አለችኝ። ዝም ብዬ አይን አይኗን ነው ማያት ሁኔታዬ ግራ ገብቷት ምነው ባህራን ደና አደለህም እንዴ አለችኝ።

በድጋሜ መልሴ ዝምታ ብቻ ነበር።
ወደቤት ሄደን እንድናወራ ጠየቀችኝ እሺ አልኳት። ሰፈር ላይ ኮፍያህን አድርገህ ማንም ሳያይህ ግባ ከዛ ሳንኳኳ ቶሎ ክፈትልኝ የሰፈር ሰው እንዳያየን አለችኝ፡፡

እሺ ብዬ ቁልፉን ተቀብያት ወደውስጥ ገባሁ ብዙም ሳትቆይ አንኳኳች ከፍቼ ወደውስጥ አስገባኋት፡፡ ቤት ገብቼ ቁጭ አልኩ እጄን በደረት አድርጌ ጭብጥ ብዬ ቁጭ አልኩ የሆነ ሰው ቤት ለእንግድነት የሄድኩ እንጂ ተወልጄ ያደኩበት ቤት አልመስልህ አለኝ።

ልእልት ተሯሩጣ ገብታ ገዛዝታ በመጣችው ቆንጆ ቁርስ ሰራችና አብረን በላን እርቦኝ ስለነበር እንዴት እንደበላሁ እራሱ አላቅም ብቻ በልተን እንደጨረስን።
ልእልት ቡና አፈላችና ጠጣን ከሱ መልስ ቁጭ ብለን ማውራት አለብን አለችኝ ካጠገቤ መጥታ እየተቀመጠች፡፡ ዝም ብዬ ማዳመጥ ጀመርኩ።

ምን እንደተፈጠረ እዮብ ነግሮኛል ማወቅ ያለብህ እዮብ በዛን ሰአት ላንተ ባያስብ አንተን እንድትሄድ ትቶህ ወደቤቱ መመለስ ይችላልኮ አደል እሱ ላንተ ብሎ ነው አንዳንዴ መጋፈጥ ማትችለውን ነገር መጋፈጥ አደጋው የከፋ ነው አለችኝ።

ዝም አልኳት በቃ ዝም ማለት ነው የፈለኩት የማወጣው ቃላት እራሱ ጥቅሙ አልታይህ አለኝ።ልእልት ቀጥላ ደሞ አያርገውና ያቺ ሴት እቴቴ ብትሆን አሰብከው አንዳንዴ ሞት እረፍት የሚሆንበት አጋጣሚ አለኮ አለችኝ።

ያቺ ቃል ከጭንቅላቴ አልጠፋ አለች ሌላ ወሬ እያወራች ደጋግማ ምታቃጭልብኝ ቃል ግን ሞት እረፍት ሚሆንበት ያለቻት ቃላት ናት፡፡

አሰብኩት በዛች ሴትዮ ቦታ እማ ብትሆን ሚለውን ነገር አሰብኩና ሰውነቴን ነዘረኝ እንደዛ ከምትሆንማ እንኳን በሰላም አረፈች እኝኳኝ በክብር ተቀበረች አልኩኝ። ልእልት ብዙ ነገር ነግራኝ ስትጨርስ በቃ ገላህን ታጥበህ እረፍት አድርግ ትንሽ ተኛና ማወራህ ትልቅ ጉዳይ አለ አለችኝ፡፡

ተነስቼ ሻወር ቤት ገባሁና ገላዬን ታጠብቁ ከቁም ሳጥን ቱታዬን አውጥታ ሰጠችኝና ለባበስኩ ።ወደመኝታ ቤት ገብቼ አልጋዬ ላይ ቁጭ አልኩ ልእልት መጣችና ለባብሰህ ተኛ ሞቅ ሲልህ ቶሎ ነው እንቅልፍ ሚወስድህ ለጭንቅላትህም እረፍት ስጠው እንጂ ብላ አለባበሰችኝ እኔ ጋደም ስል እሷ ለመውጣት ተዘጋጀች ፡፡

እንዴት ካፌ እንዳመለጠኝ አላቅም ግን አንቺስ ሌሊቱን አልተኛሁም ብለሽ የለ ለምን አተኝም ነይ አብረን እንተኛ አልኳት። ፊቷ ፍክትክት እያለ እሺ ብላ ከጀርባዬ ጥቅልል ብላ ተኛች።አውነት ለመናገር ከዛ ክፍል ትታኝ ስትወጣ ቤቱ
ሚበላኝም መስሎኝ ነበር።

ጠዋት አካባቢ ተኝተን ከሰአት ነው የነቃነው ስነቃ ልእልት በሁለት እጄ ጥብቅ አድርጌ አቅፊያት እሷ ደሞ ደረቴ ውስጥ ገብታ ውሽቅ ብላ እጇን ከወገቤ ላይ ጣል አድርጋ የለበስኩትን ቲሸርት ጥብቅ አድርጋ ይዛው ነበር፡፡

በሰአቱ በጣም ደንግጫለሁ ሂጂ ከዚህ ተነሽ ብዬ ላባርራትም ፈልጊያለሁ ግን እንዴት እንደሆነ አላቅም ግን እንደዛ ሆኜ መቆየትም ፈልጌ ስለነበር አውቄ እንቅልፍ እንደወሰደው ሰው መልሼ አይኔን ጨፈንኩ



ይቀጥላል...



🔻ክፍል3️⃣5️⃣1️⃣5️⃣0️⃣ like በዃላ ይቀጥላል...  ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ Like💝 ማድረግ አይርሱ።
🔺🔺🔺🔺🔺😀😀😀😀😀

      ‌‌‌‌‌‌‌      ይ 🀄️ላ🀄️ሉን!
😀

💔 https://t.me/yefikirtelegramet 💔

4.4k 0 16 1 243

ሰላም ሰላም ቤተሰብ የፍቅር ጥግ ክፍል 34  ሊለቀቅ ነው አላችሁ ወይ?


      🔸🔸🔺🔺🔹🔸

      
❤️ የፍቅር ጥግ ❤️

ልብ አንጠልጣይ እውነተኛ  ታሪክ
❤️

ፀሀፊ
✍️ ማኔ


                        ክፍል  
3️⃣3️⃣

እዛ ቦታ ላይ ማታ ብቻዋን ስትደፈር የስምንት ጎረምሳ ወንዶች ስሜት ማብረጃ ስትሆን ያ ሁላ ወጠጤ እጁን ሲያሳርፍባት ሁሉም የሞቀ ቤቱ ውስጥ ተኝቶ ነበር፡፡ ልክ እሷ ደክማ ለሞት ስትዳረግ ግን ሁሉም ሰው ከንፈሩን እየመጠጠ ተሰብስቦ እሷን ለማየት ይጋፋል።

ህይወት በራሷ ምንም የማትጨበጥ ናት፡፡
ሁሉም ሰው ከቤት ወጣ እዮብም ቢሆን አብሮኝ አልነበረም ያንን አጋጣሚ ተጠቅሜ ከቤት ወጣሁ በድጋሜ ወደ እዮብጋ ላለመመለስ ለራሴ ቃል እየገባሁ ነበር ከዛ ሰፈር የወጣሁት ድጋሜ ላላገኘው ላላየው አጠገቡ ላልደርስ የሰው ነፍስ ሲጠፋ ቆም የሚመለከት ጨካኝ ሰው አድርጌ ነበር የቆጠርኩት።
መሄጃ ባይኖረኝም መሄዱን ስለፈለኩት ዝም ብዬ መጓዝ ጀመርኩ።

መጀመሪያ እናቴ ሄድኩና የተፈጠረውን እንዳለ ነገርኳት እንባዬ መቆም አልቻለም ነበር።
መቃብር ቦታው ላይ ትንሽ ከቆየሁ ቡሀላ ተመልሼ ወደሌላ ቦታ መጓዝ ጀመርኩ ኪሴ ውስጥ አምስት ብር ነው ያለው፡፡

እዮብ ተደጋጋሚ ጊዜ ሲደውልልኝ ሲሙን አውጥቼ ወርውሬ ስልኩን ብቻ ያዝኩት።
ሰአቱ ስምንት ሰአት አካባቢ ሲሆን በጣም እራበኝ እኔ ደሞ ተመላሽ እንኳን እንዴት እንደሚጠየቅ አላውቅም፡፡

ጨጓራዬ ሆዴ ውስጥ ያሉ ሁሉንሜ አካሎቼን ሳይበላቸው በፊት እኔ ምግብ መብላት እንዳለብኝ ሲገባኝ ስልኬን አውጥቼ ለመሸጥ ወደስልክ ቤት ይዣት ሄድኩ።

150 ብር ልግዛህ አለኝ። እሺ አልኩት ብሬን ተቀብዬ ሄድኩና በላሁ።
የቀረችውን ብሬን ኪሴ ከትቼ ስንከራተት ቀኑ መሸ ዝም ብዬ የሆኑ ጎዳና ተዳዳሪዎችን ሳይ ተጠግቼ ካጠገባቸው ቁጭ አልኩ።

ቼክ አላረጉኝም ሁሉም የየራሱን በላ እንቅልፍ እስኪወስዳቸው ዘፈናቸውን ዘፋፈኑና ተደራርበው ለማለት በሚያስችል ሁኔታ ውስጥ ተኙ። እኔ ጥጌን ይዤ ግድግዳውን ተደግፌ ቁጭ አልኩ፡፡

ዝም ብዬ አስፋልቱ ላይ አይኔን ተክዬ እየተመለከትኩ እማ ሳመሽ እንደዛ ምትጨነቀው ግን ምን እንዳልሆን ነበር ዛሬስ እንደዚህ ሌትና ቀኑ እንደተምታታብኝ ብታይ ምን ትል ይሆን እያልኩ እንደለመድኩት ማልቀስ ጀመርኩ ሳለቅስ ቶሎ ይደክመኛል መሰለኝ እዛው በተደገፍኩበት እንቅልፍ ወሰደኝ።

ሌሊት ላይ ብንን ስል ዝም ብዬ መራመድ ጀመርኩ ሰፈሩን ባላቀውም እግሬ ወደመራኝ ስጓዝ አንድ ሰፈር ደረስኩ ሰፈሩ ቀውጢ ነው በዛን ሰአት ተቃቅፎ ወክ ሚያደርግ አለ።

ዘፈኑ ለጉድ ነው በየክለቡ በር ላይ የተቀቀለ እንቁላልና ችብስ የሚሸጡ ብዙ ሰዎች አሉ ግማሹ እራቃኑን ሚያስንቅ አለባበስ ለብሶ ግማሹ ደሞ ገና በለጋ እድሜው ሲጋራ ለኩሶ እያንቦገቦገ ተመለከትኩ ዞር ስል እድሜዋ ከአስራዎቹ የማይዘል ልጅ ቦርጩ ብቻ 9ዐኪሎ ከሚመዝን ሰውዬ መኪና ውስጥ ቁጭ ብላ ጭኗን ሲደባብስ አየሁ።

ቁጭ ብሎ እንቁላል እየሸጠ ወደነበረው ሰውዬ ጠጋ አልኩና ስንት ሰአት ነው ብዬ ጠየኩት 9:3ዐ አለኝ፡ የቀኑ ይሁን የሌሊቱ እንጃ ብቻ ግር ግሩ የሌለ ነው ከዛ እዚህ ከዚህ እዛ ሚራወጡ ሴቶች ብዛታቸውን ሳይ ገረመኝና አይ ፈጣሪ እዚሁ ኢትዮጵያ ውስጥም ቀንና ሌሊቱ ይለያያል ማለት ነው ብኔ ጥጌን ይዤ ዝም ብዬ ሁሉንም መመልከት ጀመርኩ ።

አላስተዋልኩትም እኔ ትልቁ ችግሬ ለካ ብቻዬን መሆን አለመቻሌ ነው ትንሽ ደቂቃ ብቻዬን ስሆን እያበድኩም እየሞትኩም ይመስለኛል።

እንደዚህ ቁጭ ብዬ ደሞ የሰዎችን ግርግር ስመለከት ትንሽ ጭንቅላቴ አረፍ ይላል።
የማይነጋ የለም ነጋ ልክ ቀኑ ወገግ እያለ ሲሄድ ሰፈሩም ጭር እያለ ሄደ እንቅስቃሴ ቆመ ዘፈኖቹ ፀጥ እረጭ አሉ።

ይቀጥላል...



🔻ክፍል3️⃣4️⃣1️⃣5️⃣0️⃣ like በዃላ ይቀጥላል...  ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ Like💝 ማድረግ አይርሱ።
🔺🔺🔺🔺🔺😀😀😀😀😀

      ‌‌‌‌‌‌‌      ይ 🀄️ላ🀄️ሉን!
😀

💔 https://t.me/yefikirtelegramet 💔


ሰላም ሰላም ቤተሰብ የፍቅር ጥግ ክፍል 33 ሊለቀቅ ነው አላችሁ ወይ?


      🔸🔸🔺🔺🔹🔸

      
❤️ የፍቅር ጥግ ❤️

ልብ አንጠልጣይ እውነተኛ  ታሪክ
❤️

ፀሀፊ
✍️ ማኔ


                        ክፍል  
3️⃣2️⃣


እኔ እናቴ ከሞተች ቡሀላ አንድ ቦታ ተረጋግቶ መቆየት አልችልም ሰላም አይሰጠኝም፡፡
የኔ አልበቃ ብሎ እዮብንም ቀኑን ሙሉ ሳዞረው ዋልኩ ልእልትም ክላስ ስለነበራት እሷን አድርሰናት።
ከክላስ ከወጣች ቡሀላም አብራን አመሸችና ወደቤት ሄደች ስትሄድ ለእዮብ በግድ ብር ሰጥታው ስለነበር እናጥፋት ተባብለን እየጠጣን አመሸን።ብራችን ሲያልቅ ከመጠጥ ቤቱ እስከቤት በእግራችን መራመድ ጀመርን ።ሁለታችንም ዝም ብለን ነው ምንራመደው እዮብ የጥሞና ጊዜ ይለዋል ወክ ስናደርግ ከማንምጋ መነጋገር አይፈልግም ከራሱጋ ብቻ እያወራ መሄድ ሚፈልገው፡፡

ወደሰፈር እየገባን አስፋልቱ መታጠፊያጋ ስንደርስ የሚጮህ ድምፅ ሰምተን ወደኋላ ተመለሰን ድምፁ ከየት እንደሚመጣ ተምታታብን ወደቀኝም ወደግራም አየን የሰቆቃ ድምፅ ነው ሚሰማን እየሮጥን ወደታችኛው አስፋልት ተሻገርን ወደ ድምፁ እየቀረብኩ ስመጣ ውስጤ መረበሽ ጀመረ ድምፁን ወደሰማንበትጋ መሮጥ ጀመርን ከአስፋልቱ በታች ደልድይ አለ ድምፁ ከድልድዩ ስር ነው ሚወጣው። ሁለታችንም እኩል አይናችንን ከድልድዩ ስር ላክነው።

በግምት 7 ወይ ስምንት ይሆናል ክብ ሰርተው አንዷን ሴት እየተፈራረቁ ይደፍሯታል አንድ ድምፅ ባወጣች ቁጥር አንድ ዱላ ያርፍባታል አንዱ እስኪጨርስ አንዱ ሱሪውን ለማውለቅ አሰፍስፎ ይጠብቃል።
ያንን ሳይ አልቻልኩም በድልድዩ ለመዝለል የማይተሰብ ስለሆነ ወደነሱጋ ለመውረድ መሮጥ ጀመርኩ፡፡ እዮብ ተከተለኝና ያዘኝ ምን ሆነሀል ለምንድነው
ምትይዘኝ አልኩት።

ወዴት ነው አለኝ።አታይም እንዴ እየተደፈረችኮ ነው ሄደን እናድናት እንጂ አልኩት።ተረጋጋ ባህራን አንተ ስፓይደር ማን ወይ ደሞ የፊልም አክተር አደለሁም ብቻህን ሄደህ ለስምንት ምትፋለመው አታያቸውም እንዴ እነሱኮ ብዙ ናቸው በዛ ላይ የጎዳና ልጆች ናቸው አብዛኛው የጎዳና ልጅ ደሞ ተስፋ የቆረጠ ነው ቢሞትም ቢገልም ግዴለውም አለኝ።

እኔ ለመኖር መች ፈለኩ አልኩት እሱ ጥብቅ አድርጎ ይዞ አለቅም አለኝ፡፡ ለመታገል እራሱ አቅም ሳጣ ድምፄን ጮክ አድርጌ አይቼሀለሁ ፖሊስ ፖሊስ እያልኩ መጮህ ጀመርኩ። ከመቅፅበት ከነዛ ሁላ ልጆች ወደኛ የድንጋይ መአት ይወረወር ጀመር እዮብ በምትወዳት እናትህ ይዤሀለሁ ባህራን እንሩጥ በቃ ካሁን ቡሀላ ስለሚፈሩ መልሰው አይደፍሯትም በእርግጠኝነት ከስምንቱ አምስቱ ጩቤ ይዘዋል አለኝ።

ድንጋዩና የእዮብ ልመና ሲበረታብኝ መሮጥ ጀመርኩ እየሮጥን ወደቤታችን ገባን። አንዳንድ ሌሊቶች ያመት ያህል እረጅም ናቸው አይነጉም ሰአቱ አይሄድም ሌሊቱ ለኔ ምድራዊ ሲኦል ነበር በፍፁም አልገፋ አለኝ፡፡ እንዲሁ ስገላበጥ አድሬ ሰው ሲነቃ እኔ እንቅልፍ ጣለኝ ። ትንሽ ቆይቼ እዮብ ቀሰቀሰኝና ተነሳሁ።ቀጥታ ፊቱን ነበር የተመለከትኩት ምነው ምን ተፈጠረ አልኩት።

ናማ ተነስና እንውጣ ማታ የተደፈረችው ሴትዮኮ ሞታ ተገኘች እዛው ቦታ ላይ ነው አስክሬኗ ያለው አለኝ።
ደነገጥኩ እየተርበተበትኩ ተነሳሁ ምን አልክ ምን አልክ በጥያቄ አጣደፍኩት አዎ ባህራን ደሞ እእ ማለቴ ያቺ ትናት ጠዋት አብራን የበላችው እብዷ ሴትዮ ናትኮ እንደዛ የደፈሯት አሁን ሞታ ተገኘች አለኝ።

የሆነ ህይወት በራሱ ምንድነው መኖር ጥቅሙ ምንድነው እስከመች ነው ምንኖረው ለምን ለማን እንጃ ግን ውስጤ ድብልቅልቅ አለ፡፡

ሁሌ ቀና ልንል ነው ስንል ድንገት ሰብሮ ሚያስቀረን ነገር በህይወታችን ይፈጠራል ለምን እንደሆነ ፈጣሪ ይወቀው ትናት እናቴ ደረስኩልሽ ያለቻትን ልጇን በሞት ነጠቋት ዛሬ ደሞ ደና ነኝ ተሽሎኛል ጤናዬ ተመልሷል ብላ ገና አውርታ ካፏ ሳትጨርስ የራሷን የናቷን ህይወት ነጠኩት፡፡

በዛን ሰአት ወንድነቴ አስጠላኝ ስሜት ሚባለው ነገር ለምን ተፈጠረ ብዬ እስካስብ ድረስ ጨነቀኝ ዝም ብዬ እዮብ ላይ መጮህ ጀመርኩ አየህ በዛን ሰአት ደርሰን ሀኪም ቤት ብንወስዳትኮ ትድን ነበር እኛ ነን የሷ ገዳዮች እያልኩ መለፍለፍ ጀመርኩ እዮብ በንዴት ውስጥ ሆኖ ይሄኔ እኛ እዛ ቦታ ላይ ተገኝተን ቢሆን ሶስት አስክሬን ነበር ከዛ ቦታ ሚነሳው አለኝ።
እኔ ግን እሱ ሚያወራውን ከቁም ነገር አልቆጠርኩትም በቃ የሷ ገዳይ እኔ ነኝ ብዬ መቀበልን መረጥኩ

ይቀጥላል...



🔻ክፍል3️⃣3️⃣1️⃣5️⃣0️⃣ like በዃላ ይቀጥላል...  ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ Like💝 ማድረግ አይርሱ።
🔺🔺🔺🔺🔺😀😀😀😀😀

      ‌‌‌‌‌‌‌      ይ 🀄️ላ🀄️ሉን!
😀

💔 https://t.me/yefikirtelegramet 💔


እንዴት ናችሁ ቤተሰቦች ሰው ሲጠፋ አትፈልጉም ወይ? ሰሞኑን በስራ ምክንያት ስላልተመቸን በየቀኑ እየለቀቅንላችሁ ባለመሆኑ ዛሬም ይቅርታ እንጠይቃለን

የፍቅር ጥግ ክፍል 32 ሊለቀቅ ነው አላችሁ ወይ
?


      🔸🔸🔺🔺🔹🔸

      
❤️ የፍቅር ጥግ ❤️

ልብ አንጠልጣይ እውነተኛ  ታሪክ
❤️

ፀሀፊ
✍️ ማኔ


                        ክፍል  
3️⃣1️⃣

የሆነ ቀን ላይ ከእዮብጋ ቁጭ ብለን እያወራን ቢያንስ አንዴ እንኳን ስትስቅ ማየት እፈልጋለሁ ምን ላድርግ አለኝ። እኔ መሳቅ እንደማልፈልግ ነገርኩት ዝም አለኝ።

ማታ ላይ ዝም ብለን እየተራመድን ና አዲስ ነቃ ሚያደርገን ነገር ተገኝቷል እንሞክረው አለኝ አልተቃወምኩትም ሞከርኩት ምሽቱን እንደ እብድ ብቻዬን ስስቅ አመሸሁ አሁን የቢራ ጠርሙስ ምኑ ያስቃል አየሁ ጠርሙሱ ምን አይነት ቅርፅ እንዳለው ብዬ ክትክት ብዬ እስቃለሁ አረ ምን እሱ ብቻ ጠረጴዛው እራሱ አራት እግር እንዳለው ሳይ አስቆኝ ነበር ብቻ እዮብ እንደህፃን ልጅ ፈገግ ብሎ እያየኝ ምሽታችን አለቀና ወደቤት ገብተን ነጋ።ጠዋት እንደተነሳሁ እዮብ ተነስቶ ቁጭ ብሎ ነበር ስነሳ አይን አይኔን ሲያየኝ የተፈጠረ ነገር አለ ወይ ብዬ ጠየኩት።

እሱም ፊቱን እንደጣለው ቁጭ ብሎ ታቃለሁ ግን ይሄ ሱስ ሚባል ነገር የስንቱን ፈገግታ እንዳጨለመ ምናለ እዚህ ምድር ላይ ተስፋ መቁረጥ ሚባለው ነገር ባይኖር ማታ ስትስቅ ሳይህ ልቤ ሞቅ ነው ያለው እንኳን ሴትን ወንድ ልጅን የሚያፈዝ ውበትኮ ነው ያለህ ይሄ ፀባይህ ይሄ አቋምህ ይሄ መልክህ ለሱስ ሲገበር ያስጠላል በቃ ባህራን ግዴለህም አንተ እንኳን ተቀየር እኔ አንዴ አልፎብኛል የፈሰሰ ውሀ ማለት ነኝ አለ፡፡

ገና ተቀየር የሚለውን ቃል ስሰማ ተነስቼ ወጣሁ በለበስኩት ሹራብ ፊቴን ጠረግ ጠረግ አድርጌ ከግቢ ወጥቼ መራመድ ስጀምር እዮብ ደርሶብኝ አብረን እንጓዝ መዳረሻችንን ፈጣሪ ያቀዋል አለኝ፡፡

እየተጓዝን ሁልጊዜ ከመገዳችን ማናጣትን አሮጊት እብድ አገኘናት ከወትሮው በተለየ እዮቤ ደና ነህ ባክህ ዛሬ በጠዋቱ እሮብኛል ቁርስ በላችሁ እንዴ አሁን ደሞ ተመላሽ


እንዳልጠይቅ አይኖርም አለችው አልበላንም ነይ እንብላ እኔጋ ሳንቲም አለ ብሎ ቁርስ ልንበላ ገባን እንደዛ አስፋልት ላስፋልት ስትሯሯጥ ትንሹንም ትልቁንም ካልደበደብኩ እያለች የማያት ሴትዮ እንደዛ ተረጋግታ ቁርስ ስትበላ ሳያት ገረመኝና አይኔን ከሷ ላይ መንቀል አቃተኝ፡፡
በልታ ስትጨርስ እዮቤ የማታ እንጀራ ይስጥህ መቼም ቢሆን መቋቋም ከምትችለው ሀዘን ፈጣሪ ይሰውርህ አሁን ደና ነኝ ፈጣሪ ከፈቀደ በቅርቡ ደም በጣም ጤነኛ እሆናለሁ ብላን ወጣች።

ገና ከመውጣቷ እዮብን ጠየኩት ይቺ ሴትዮ ግን ምን ሆና ነው ሁሌ ሳያት ታሳዝነኛለች አልኩት። ውይ በጣም ነው ምታሳዝነው የሚገርምህ አንድ ልጅ ነበረቻት እንዴት እንደምታምር ልነግርህ አልችልም ፡

እንዴት አርጋ እንዳሳደገቻት ስታወራ እንባ ነው ሚቀድምህ ለልጇ ስትል ሌላ ባል ልጅ ሳያምራት እሷ አንገቷን እየደፋች የልጅቷን አንገት ቀና አድርጋ ነው ያኖረቻት ልጅቷን ብታያት እንኳን ሰው ሴጣን ይደነግጥባታል እናትየው ካመት አመት አንድ ልብስ ነው ምትለብሰው ልጅቷ ግን ዛሬ የለበሰችውን ነገ አትደግመውም ብቻ ምናለፋህ እድሜዋን በሙሉ ለልጇ ኖረች::

ልጅቷም አዲስ አበባ ዩንቨርስቲ ነበር ምትማረው አምስት አመት ሙሉ ለፍታ ተምራ እናቷን ደረስኩልሽ ስትላት እንደነገ ምርቃቷ ተደግሶ እንደዛሬ አንዱ አፍቃሪሽ ነኝ ባይ ለምን ጠይቂያት እንቢ አለችኝ ብሎ የቤቷ በር ቀጩቤ ቀዲት ሄደ ለምርቃቷ የተደገሰው ለለቅሶዋ ሆነ እናትየውም ሳትቀብራት እንኮን ገና ሞቷን እንደሰማች በቃ አበደች አበደች አለኝ።

አሳዘነችኝ የሁላችንም ህይወት ውስጥ እኛን ለመጥፎ ህይወት የዳረገን አንድ መጥፎ ሰው አለ አደል አልኩት፡፡ድሮ አባቴ የሰው ልጅ አዳኙም አጥፊውም እራሱ ሰው ነው።

ሰው አንዳንድ ቦታ መዳኒት ይሆንሀል አንዳንድ ቦታ ደሞ ያጠፋሀል እያለ ነበር ያሳደገኝ አሁን ላይ ግን የገባኝ የሰው ልጅ አጥፊ እንጂ አዳኝ መሆን አይችልም አለኝና ተነስተን
ወጣን።


ይቀጥላል...



🔻ክፍል3️⃣2️⃣1️⃣5️⃣0️⃣ like በዃላ ይቀጥላል...  ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ Like💝 ማድረግ አይርሱ።
🔺🔺🔺🔺🔺😀😀😀😀😀

      ‌‌‌‌‌‌‌      ይ 🀄️ላ🀄️ሉን!
😀

💔 https://t.me/yefikirtelegramet 💔

7k 0 11 2 272

እንኳን አደረሳችሁ ቤተሰብ የፍቅር ጥግ ክፍል 31 ሊለቀቅ ነው አላችሁ ወይ?


      🔸🔸🔺🔺🔹🔸

      
❤️ የፍቅር ጥግ ❤️

ልብ አንጠልጣይ እውነተኛ  ታሪክ
❤️

ፀሀፊ
✍️ ማኔ


                        ክፍል  
3️⃣0️⃣


ጠዋት እዮብ ቀሰቀሰኝና አንተ ሰላቢ መቼ መተህ ነው
አለኝ።

ዝም አልኩት እንዳኮረፍኩ ገብቶታል መሰለኝ እሱም ቀለል አድርጎ አይ ልእልት ደውላ ስትነግረኝኮ ደንግጬ ነው አለኝ። ዝም እንዳልኩ ተነስቼ ወጥቼ ቁጭ አልኩ።
በጣም አምሮብሀል ባክህ አለኝ።
ዝም ብቻ ሆነ መልሴ ማታ ለሰከንድ የሳኩት ሳቅ ትልቅ ሀጥያት መስሎ ተሰማኝ በድጋሜ ልእልትን ላለማግኘትም ወሰንኩ ለእዮብም አስረግጬ ነገርኩት፡፡
በድጋሜ ልእልት እኛጋ ስትመጣ እኔ መሸሸ ጀመርኩ እሱ ክላስ ሊያደርሳት ሲሄድ እኔ ጫት እየቃምኩ እጠብቀዋለሁ፡፡

ትንሽ ሰንበት እንዳልን ግን ልእልት በድጋሜ ክላስ አቆመች እዮብ ልመና በሚመስል መልኩ ከልእልት ፍቅር እንደያዘውና እሷ ስትጎዳ ማየት እንደማይችል ዘንድሮ ተመራቂ ስለሆነች እስክትመረቅ እንኳን እንድታገስ ለመነኝ የሱ ነገር ስለሆነብኝ እሺ አልኩት፡

ድጋሜ እሷን እስከ ክላስ መሸኘት መመለሱን ተያያዝነው ልክ ወደክላስ ልናደርሳት ስንሄድ እዮብ ጭንቅላቱን እየነቀነቀ አይገርምህም ግን የልእልት ልብኮ ይለያል እኛ እንደዚህ ተንቦርክከን እሷ እንደዛ ዘንጣ ከጎኗ ስንሄድ ምንም አይመስላትም ለሰው አትጨነቅም እራሷን ሆኖ ምትኖር ሰው ናት ንፁህ ልብ ነው ያላት ምናለ ቀደም ብዬ ባመኳት ብዬ ምመኛት አይነት ሴት ናት አለኝ።
አሁንም እንዳልረፈደና እድል እንዳለው ነግሬ አፅናናሁት ፡፡

አሁንም እንዳልረፈደና እድል እንዳለው ነግሬ አፅናናሁት ፡፡ የሆነ ቀን ላይ እኔም እዮብም ምንም ብር አጥተን ተፋጠን ቁጭ ብለናል።

ልእልት የሰጠችንን ብር ትናት ባንጠጣበትኮ ለዛሬ ይሆነን ነበር አሁን ምን እናድርግ አለኝ።
በቃ ወተን አንዱ ላይ እንፍረድና እንመለስ አልኩት።ተያይዘን ወጣን ሁለታችንም የየራሳችንን አቅጣጫ ይዘን ጥግ ጥጋችን ይዘን ቆምን ።

ኮፍያ ያለው ሹራብ አድርግን ነው ከቤት ምንወጣው ኮፍያውን ድፍት አድርገን መሬት መሬት እናያለንስለምንሰርቀው ሰውዬ ምንነት እንኳን አናቅምስለምንሰርቀው እቃ እንጂ ...እኔም ባጠገቤ ጥቁር ጃኬት አድርጎ እያለፈ ጆሮው ላይ ስልክ የያዘውን ሰውዬ አነጣጥሬ አየሁና ተከተልኩት ከመቅፅበት ከጆሮው ላይ ነጥቄው መሮጡን ተያያዝኩት ሳይጮህም ምንም ሳይል ባህራን ባህራን እያለ በስሜ ጠራኝ ድምፁን አቀዋለሁ ስልኩን ውሰደው አንተ ብቻ አናግረኝ ሲል ማን እንደሆነ ገባኝ አለቃዬ ነው ቀጥ ብዬ ቆምኩኝና ፊቴን ወደሱ አዞርኩት፡፡


ቤት ስገባ ልእልትና እዮብ ቤቱን ፏፏ አድርገው
አሰማምረው ጠበቁኝ ሌሎቹ ልጆችም ነበሩ ዛሬ ምን አለ በአል ነው እንዴ አልኳቸው እዮብ ወደኔ እያየ በአል ካልሆነ እንደዚህ አታድርጉ ያለው ማነው አለኝ፡፡ ዝም ብዬ እንደቆዘምኩ ገብቼ ተቀመጥኩ፡፡
ልእልት_ የሆንከው ነገር አለ እንዴ ፊትህ ልክ አደለም አለችኝ።

ዝም አልኳት አልፊያቸው ገብቼ ዝም ብዬ መሬቱ ላይ ተኛሁ የለበስኩትን ሹራብ አውልቄ ፊቴን አለበስኩትና ስቅስቅ ብዬ አለቀስኩ ምናለ ፈጣሪ ያለኝን ነገር በሙሉ ወስደህ እናቴን ብትተውልኝ ቢያንስኮ ለሷ ስል እኖር ነበር አልኩት፡፡

ሁሉም ዝም አሉኝ በዛው እያለቀስኩም እያሰብኩም እንቅልፍ ወሰደኝ። ስነሳ ልእልት ብቻ ናት ካጠገቤ ቁጭ ያለችው፡፡
አይኔን ስገልጥ ተመለከትኳት ተነሳህ እንዴ እንዳንረብሽህ ብለንኮ ነው ዝም ያልነው ትንሽ ይተኛ ብሎ እዮብም ልጆቹን ሰብስቧቸው ነው የወጣው አለችኝ።

ዝም ብያት ተነሳሁና ሹራቤን ለብሼ ወደውጭ ወጣሁ ተከተለችኝ ዛሬ እቴቴጋ አሌድክማ ለምን አኔድም አለችኝ፡፡

የእናቴ ነገር ስለሆነ እሺ አልኳት ሄድንና ቁጭ አልን እንደሌላ ጊዜው እናቴን የማወራት ነገር እራሱ አልነበረም፡፡

ዝም ብዬ ተመለከትኳት አይኔን ከመቃብሯ ላይ ሳላነሳ የተወሰኑ ደቂቃዎች ከቆየሁ ቡሀላ ተነስቼ መራመድ ጀመርኩ ልእልት ተከተለችኝና ከፈለክ የሚሰማህን አውራኝ እየሰማሁህ ነው አለችኝ።

በሰአቱ ሚሰማኝ ሰው ነበር የፈለኩት ና መለፍለፍ ጀመርኩ አለቃዬ ያለኝንና ያደረገልኝን ነገርኳት አሁን ላይ ዝም ብሎ ማልቀስ ነው ሚያምረኝ ዝም ብሎ ሆድ ይብሰኛል መብላት በራሱ ያስጠላኛል ማታ ማታ ስተኛ ከዚህ አለም እንዲገላግለኝ ፀልዬ ነው ምተኛው ጠዋት ስነቃ እራሴን እየተነፈስኩ ሳገኘው በራሱ እናደዳለሁ አልኳት፡፡

አይዞህ ይሄም ያልፋል ታቃለህ በከባባድ ፈተናዎች ውስጥ የሚወለዱ በጣም ብዙ መልካም ነገሮች አሉ እኛ ሁሌም መከራውን ስለምናይ ነው እንጂ ከባድ ፈተና ከባድ ደስታይን ሰቶን ነው ሚያለፈው አለችኝ።
ሁሌም ስለምታዳምጪኝ አመሰግናለሁ አልኳት።

ፊቷ ፍክት ብሎ እያየችኝ አሁን ግን የምር አትጠላኝም አደል አለችኝ፡፡ገላምጫት ዝም አልኩ፡፡ ቤቷ ልትሄድ ስለነበር ሸኝቻት ተመለስኩ።


ይቀጥላል...



🔻ክፍል3️⃣1️⃣1️⃣5️⃣0️⃣ like በዃላ ይቀጥላል...  ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ Like💝 ማድረግ አይርሱ።
🔺🔺🔺🔺🔺😀😀😀😀😀

      ‌‌‌‌‌‌‌      ይ 🀄️ላ🀄️ሉን!
😀

💔 https://t.me/yefikirtelegramet 💔

8.3k 0 19 5 267

ቤተሰብ በጣም ይቅርታ መጣን 5 ደቂቃ ብቻ ጠብቁን

Показано 20 последних публикаций.