TGStat
TGStat
Введите текст для поиска
Расширенный поиск каналов
  • flag Russian
    Язык сайта
    flag Russian flag English flag Uzbek
  • Вход на сайт
  • Каталог
    Каталог каналов и чатов Поиск каналов
    Добавить канал/чат
  • Рейтинги
    Рейтинг каналов Рейтинг чатов Рейтинг публикаций
    Рейтинги брендов и персон
  • Аналитика
  • Поиск по публикациям
  • Мониторинг Telegram
ፍኖተ የሀ

24 Nov 2017, 22:44

Открыть в Telegram Поделиться Пожаловаться

የሀ
የሀ ከተማ ስትታይ ከጭቃ ቤቶች በቀር ለዓይን የሚገባ ቤት
እንደሌለባት ስትታይ "ፊተኞች ኋለኞች ይሆናሉ" የሚለው
ብሂል ትዝ ይለናል "ከሀገር የሀ ከፊደል ሀ ይቀድማሉ"
ሚለውም ይታወሰናል አቧራ ያጠለቃትን ይህች ጥንታዊ
ከተማ አቋርጠን ስንጓዝ ከክርስቶስ ልደት በፊት ያለው ዘመን
ላይ ምንገኝ ይመስለናል።
እንደ አርኪዮሎጂስቶችና ታሪክ ፀሀፊዎች ምስክርነት የሀ
የተቆረቆረችው ከክርስቶስ ልደት በፊት ስምንት ምዕት
አመታት ቀደም ብላ ነው። የፑንት ከተማ - የዳእማት ማማ።
ከባቢሎን ውድመት በኋላ የኩሽና የሴም ዘሮች እንደገና
በዘርና በቋንቋ ተቀላቅለው ፣ ዘራቸውን አግአዝያን ፣
ቋንቋቸውን ግዕዝ ያደረጉባት የኢትዮጲስ የተቀበረባት
የኢትዮጵያ ሀሁ መሠረት የሀ። የመጀመርያዋ የኢትዮጵያ ዋና
ከተማ። ዙርያዋ የከበቧት ተራሮች ላይ የዋልያ አርማ
የነበረው የዳእማት ባንዲራ ሲርገበገብ በምናባችን እንየው
ኩሽና ሴም ያሁኗን ኢትዮጵያ ተነስተው ቢመለከቱ ምን ይሉ
ይሆን? 'ተቀላቅለን ሳለ እንደገና ለምን ተለያያችሁ?
ማንኛችሁ ናችሁ ንፁህ ሴም? ማንኛችሁ ናችሁ ንፁህ ኩሽ?'
የሚሉን አይመስላችሁም ማን ይሆን ታሪካችንን አዳፍኖ ሙጃ
የተከለበት? አንዳቸው ተነስተው ታሪኩ ተቀብሮበት ኮምፓሱ
እንደጠፋበት መርከብ ያለ አቅጣጫ ለሚንሳፈፈው ትውልድ
ሁሉንም ቢነግሩት እንዴት ጥሩ ነበር። ከተማውን ሰንጥቆ
የሚያልፈውን ማይ መኾለ ሚባለውን ወንዝ እንሻገረውና ወደ
ኮረብታው እንውጣና ከተማዋን ቁልቁል ተኮፍሶ የሚያየውን
የየሀን ህንፃ እንመልከት በአሥራ ስድስተኛውና በአሥራ
ሰባተኛው ክፍለ ዘመን እነ ጀምስ ብሩስና ፍራንሲስኮ አልቫሬዝ
የመሳሳሉ አሳሾች አይተው የተገረሙበት ይህ ጥንታዊ ህንፃ
ከአክሱም በፊት ከመታነፁም በተጨማሪ ህንፃው
የተገነባባቸው ግዙፍ ጥርብ ድንጋዮች ያለ አርማታ ተያይዘው
ከሦስት ሺህ አመታት በላይ መቆየታቸው ማንንም
የሚያስደንቅ ነው።
ምንጭ google

4.6k 0 2
Каталог
Каталог каналов и чатов Подборки каналов Поиск каналов Добавить канал/чат
Рейтинги
Рейтинг каналов Telegram Рейтинг чатов Telegram Рейтинг публикаций Рейтинги брендов и персон
API
API статистики API поиска публикаций API Callback
Наши каналы
@TGStat @TGStat_Chat @telepulse @TGStatAPI
Почитать
Академия TGStat Исследование Telegram 2019 Исследование Telegram 2021 Исследование Telegram 2023
Контакты
Справочный центр Поддержка Почта Вакансии
Всякая всячина
Пользовательское соглашение Политика конфиденциальности Публичная оферта
Наши боты
@TGStat_Bot @SearcheeBot @TGAlertsBot @tg_analytics_bot @TGStatChatBot