The Home of all የሁሉም ቤት


Гео и язык канала: Эфиопия, Амхарский
Категория: Познавательное


Well come to the home of all in this channel all things about human being life post every day
* Motivate for free
* learn for free
* earn more for free
Buy ads: https://telega.io/c/+LiBy-b_3bjIyMjk0
══════❁✿❁═════════

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Гео и язык канала
Эфиопия, Амхарский
Статистика
Фильтр публикаций


❤️
ባል ሚስቱን ወደ ስጦታ መሸጫ ይዟት ይሄድና
❤️"የኔ ማር ለእናቴ የምሰጣት ቆንጆ ስጦታ ምረጭልኝ አላት።😊

እሷም በጣም ስለቀናች ርካሽ ስጦታ መረጠች
ባልም ስጦታውን አስጠቅልሎ ወደ እናቱ ቤት
እንደሚሄድ ነግሯት ተለያዩ።

ግን ማታ ላይ የመረጠችውን ስጦታ አምጥቶ ሰጣት።ዉዴ ምርጫሽን ሳላውቅ ቀርቼ ሳይሆን ሰርፕራይዝ ላደርግሽ አስቤ ነው "ስጦታው ለአንቺ ነው"አላት።
ሚስትም በስራዋ አዘነች።ሌላውን እንደራሷ ብትወድ ኖሮ ስጦታዋ ያማረ እንደሚሆን ተረዳች።
***
መልካምነት ለራስ ነው የሚባለው ለዚህ ነው


>> ስትቀርበው ለራቀ አትጨነቅ
ምክንያቱም:- ውድ ነገር ያለቦታው ርካሽ ነውና፥

>>ሥታምነው ለከዳህ አትጨነቅ
>>ምክንያቱም:-ታማኝ በመሆንህ አሸንፈሃልና፥

>> ሥትፈልገው ባጣኽው ነገር አትጨነቅ
>>ምክንያቱም:-እሱ አንተን ሲፈልግ ታገኘዋለህና፥

>>ሥትወደው ለጠላህ አትጨነቅ
>>ምክንያቱም:-ሥንት ምርጥ ሠዎች አንተን የሚወዱ አሉና፥

>>ሥላልሆነው ነገር አትጨነቅ
>>ምክንያቱም:-ገና ከዚህ በኋላ የሚሆኑ ነገሮች አሉና፥

>> አጣዋለሁ ብለህ ያላሠብከውን ብታጣ አትጨነቅ
>>ምክንያቱም:-አገኘዋለሁ ብለህ ያላሠብከውን ታገኘዋለህና፥

>> ያሠብከው ሳይሆን ቢቀር >>አትጨነቅ
>>ምክንያቱም:-ፈጣሪ ያላሠብከውን ይሠጥሃልና፥

>> ፍቅር ሥትሰጠው ፍቅር ለማይሠጥክ  አትጨነቅ
>>ምክንያቱም:-ምንአልባት ፈጣሪ ምርጥና ደሥ የሚል የፍቅር ታሪክ እየፃፈልክ ይሆናልና፥

እናልክ ወዳጄ አትጨነቅ!!

>>አንተ ለሁሉም ተፈጠርክ እንጅ ሁሉም ላንተ አልተፈጠረም!
>> ፈጣሪ ላንተ የሚያሥፈልግክን ያውቃል ያሠብከውን አሥጥሎክ ያላሠብከውን ይሠጥካል!

>>ሥላለፈው ብዙም አታሠላሥል፣
>>ሥለ ወደፊቱም አብዝተህ አትጨነቅ፣
>>ከዚህ ይልቅ ዛሬን ጠበቅ አድርግ፤

   አትጨነቅ!

ይችም ቀን ታልፍና ድሮ ትባላለች!
ሠአቷ ታልቅና ታሪክ ትባላለች!
ሥለዚህ አትጨነቅ በደሥታ እለፋት!
ነገም ሌላ ቀን ነው፣ህይወትህ ተሥፋ አላት።


Sherak


በዓለማችን ላይ ታዋቂነትንና ዝናን ያተረፈው ተወዳጁ Sherak የተሰኘው አኒሜሽን ፊልም ላይ ያለው ዋናው ገፀባህርይ መልክና የሰውነት ቅርፅ የተወሰደው ከ ፈረንሳዊው ማውሪስ ከተባለ በ 1950ዎቹ አካባቢ ላይ የትግል ተወዳዳሪ ከነበረው ሰው ነበር።


​​😂😂😂ወዳጄ__ሳቅ !😁😁😁


😁ሳቅ ማንነትን ደብቆ ከሰው ጋር መኖር
ያስችላል ፣ እድሜ ይጨምራል

😁ሳቅ ትካዜን ቀይሮ ደስተኛ ያረጋል
ፊትን ያጠራል

😁ሳቅ ኩርፊያን አስጥሎ ህሊናን ያድሳል የፊት መጨማተርን ያስወግዳል

😁ሳቅ~የቁጣን ሀይል ወደ ፈገግታ ይቀይራል ለሰው መጥፎ እንዳናስብ ያደርጋል

😁ሳቅ የውስጥን ጨለማ በፈገግታ ያደምቃል

😁ሳቅ~የልብን ስብራት በጥርስ ይደብቃል

😁ሳቅ የደስታን ስሜት በነብስ ውስጥ ያኖራል::

😂የህይወት ውጣ ውረድ ብዙ እና አድካሚ ቢሆንም ባገኛችሁት አጋጣሚ ሁሉ #ለመሳቅ ሞክሩ😁

😁ለሳቅ ለጨዋታ የምታባክኑት ጊዜ አይፀፅታችሁ ይቺ አለም እንደ ኪራይ ቤት ናት!!

😁😁ስለዚህ ስቀህ እለፋት!!😁😁

✔️""ሳቅ የደስታ ምንጭ ነው ""


ጥምቀት እንደኔ እቤት ተኝታችሁ እያሳለፋችሁ ያላችሁ እስኪ እቺን 👍 አድርጓት

930 0 1 11 42

ፒያሳ መብራት ሃይል ህንፃን ተሻግሮ ከአላፊ አግዳሚው ብር የሚለምኑ ልጆች ነበሩ። አለማመናቸው ትንሽ ፈጠራ የታከለበት ነው። ካርቶንና ምናምን በሚነድበት ምድጃ ላይ በሆነች የብረት ድስት ሽሮ ወጥ ጥደው ይንተከተካል። ህፃን ያቀፉ ሴቶች በሚያሳዝን ሁኔታ ድስቷን ዓይን ዓይን እያዮ አይጠፉም! እና አላፊ አግዳሚውን ወደወጡ እየጠቆሙ "ጋሸ ወጥ ሰርተን እንጀራ መግዣ አጥተን ነው ያለህን በእግዚአብሔር..." ይላሉ! ያው የሆነ የሚያሳዝን ነገር አለው። ሰወች ግማሽ መንገድ ደክመው ግማሹን እርዳን ሲሉ ትብብር እንጂ ልመና አይመስልም።

በተለይ አንዷ ቀይ ሸራፋ ልጅ በቃ በተደጋጋሚ ነው የምታጋጥመኝ። አንድ ቀን በዛው በተጣደው ወጥ አጠገብ አልፈን፣ የእንጀራ መግዣም ተጠይቀን ገዳም ሰፈር አካባቢ ወደነበረች ምግብ ቤት ሄድን። ምሳ አዘን ስንበላ ያች ቀይ ሸራፋ ልጅና አንድ ጎረምሳ ከች አሉ። "ፈጠን ያለ ጥብስና ቅቅል" አለች እሷ። ሁለት ሲንግል አለ ወንዱ! ከዚያ በኋላ ፒያሳን የምታዘወትሩ ሁሉ እንደምታውቁት ያች ድስት ከምድጃ ሳትወጣ እኔ ከአገር ወጣሁ😀 እና ምን ልል ነበር ...? ሰሞኑን የማስበው ነገር ሁሉ መሃል ላይ እየጠፋብኝ ተቸግሪያለሁ...! አወ አንዳንድ ነገሮች ይጣዳሉ እንጅ አይበስሉም! ምክንያት? አለመብሰላቸው የገቢ ምንጭ ነው!! የሆነ ሆኖ ፒያሳ ሲፈርስ ያች ድስት የት ተጥዳ ይሆን?

Alex Abraham


ለ ቻነላችን ኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮች በሙሉ መልካም የጥምቀት በዓል ይሁንላችሁ

እንኳን አደረሳችሁ


ለ በዓል ፀጉራችሁ እንዴት ተሰራችሁት😂


ለጥምቀት ያልሆነ ወግ...
(በእውቀቱ ስዩም)

ዓመት በአል በመጣ ቁጥር እልል ያልሁ አማኝ ነኝ፤ ጥምቀትንማ ከልደቴ በላይ ነው የማከብረው፤ ጎረምሳ ሳለሁ እኔና ይሁኔ በላይ አብረን ጥምቀት እንሄድና የጊዮርጊስን ታቦት እናጅባለን፤ ከዚያ የሎሚ ውርወራ ክፍለጊዜ ይቀጥላል ፤

ሎሚ ውርወራን የፈለሰፈው ኢትዮጵያዊ ደብተራ ግን ምንኛ ደንቅ ሰው ነው! ለምሳሌ የስፔን ሕዝብ በአል የሚያከብረው ቲማቲም በመወራወር ነው፤ አንድ ክፍለከተማ የሚመግብ ቲማቲም ሲወራወር ይውልና ፥ ሲመሽ ቀይ ወጥ ውስጥ የዋኘ ይመስል፥ ተጨመላልቆ ወደ ቤቱ ይገባል፤ እኔ ራሴ ባለፈው ዓመት ተሳትፍያለሁ፤ ቱሪስት ነው ብለው ሳይራሩልኝ፥ ያልታጠበ የድግስ ድስት አስመሰለው ለቀቁኝ ! በአልንስ አበሻ ያክብራት!

በጉብዝናየ ወራት፥ የጥምቀት ቀን ፥ ከይሁኔ በላይ ጋራ ሰንተራ ሜዳ ላይ እንሰማራለን፤ እኔ ከትርንጎ ጋራ የተዳቀለ ጠንካራ ሎሚ ታጥቄ ቆነጃጅቱን አማትራለሁ፤ ይሁኔ በላይ እንደኔ የሀብታም ልጅ ስላልበረ፥ ሎሚ afford ስለማያረግ እምቧይ ይወረውራል፤
ከዝያ “ ወርወሬ መታሁት ፥ ጥላሽን በእንቧይ”ብሎ ያንጎራጉራል፤

“ጥላዋን ከመታኸው እንደ ጥላ ስትከተልህ ትኖራለች “ የሚል ፈሊጥ ነበረው’

ሎሚ የምወረውርላቸው ሴቶች ባብዛኛው ይሽኮረመማሉ፤ ትዳር እንኳ ባይሆን ፈገግታ ይለግሱኛል፤ አንደኛዋ ግን ሎሚ ስወረውርላት “ አላማ አለኝ “ አለችና በእግሯ መልሳ ብትለጋው ግንባሬ ላይ ግልገል አናናስ የሚያህል እጢ በቀለ፤

ቅድም፥ ይህንን እያስታወስኩ፥ ሀያሁለት ማዞርያ ላይ፥ ቆሜ አላፊ አግዳሚውን እመለከታለሁ፤የለበስኩት ቲሸርት ከፊትለፊቱ የፋሲል ግንብ ተስሎበታል፤ ከሁዋላ ደግሞ የመጥምቁ ዮሀንስን ምሰል ይዟል፤

ዘናጭ ሴቶች በፊቴ እያለፉ ነው፤

ከሴቶች ጋራ ማውራት ያምረኛል ፤ ግን እንዴት እንደምጀምር ግራ ይገባኛል፤
አንዲቱ አጠገቤ ስትደርስ፥
“ ይቅርታ” ብየ ጀመርሁ፥

“ ምንም አይደል “ ብላኝ መንገድዋን ቀጠለች፤

ቀጣይዋ ከፊቴ ብቅ ስትል፥

“ እናት !” ስላት፥

“ አገር “ አለችኝ፥

ምን አይነቱን ከይሲ ትውልድ ነው ፈትቶ የለቀቀብን ብየ፥ ተስፋ ቆርጨ በማየት ብቻ ተወሰንኩ ፤ ሶስተኛይቱ ባጠገቤ ስታልፍ ዞር ብላ ፈገግ ያለችልኝ መሰለኝ ፤

“ እንኩዋን አደረሰሽ “ አልኳት፤

“ የጆቭሀ ምስክር ነኝ “

እንኳን አደረሳችሁ ❤️❤️❤️


አንዱ የዶርሜ ልጅ ነው ቅድም ለቤተሰብ ስልክ ሲያወራ የሰማሁት

የካፌ ምግብ መብላት አልቻልኩም፣ ጨጓራ ይዞኝ የግቢው ክልኒክ ስሄድ መድሀኒት ግቢውስጥ የለም ውጪ ግዛ ብለውኝ ውጪ ስጠይቅ ውድ ሁኖብኝ በህመም እየተሰቃየሁ ነው

ብሎ ሰክሶ ብር አስላከ ወዮ ለጥምቀት ጃምቦ ሊጠጣበት ነው😜😜

Join us @yehulum_bet


በተለያየ ግዜ በብዓል ቀን የፖሰትናቸው ፖስቶች እናቀርባለን ይከታተሉን እናመሰግናለን

👇👇👇


በዓል እንዴት ነው😂


ድሮ ድሮ ከቤት ሳንወጣ ለጥምቀት ልብስ ካልተገዛ አይዋልም ነበር አሁን ራሳችን ስንችል ግን ልብስ ማብዛት አስፈላጊ አይደለም ብለናል በ Budget ምክንያት 🤔


ለጥምቀት ልብስ ገዛችሁ?


ከተራ loading ......


በሰርግህ ቀን የሙሽሪት ቤተሰብ በደንብ እየጨፈሩ ካየህ እመነኝ ወንድሜ የቤታቸውን ችግር ነው ያገባኸው😂

ቆይ ግን አሁን ላይ የምትጋቡ ሰዎች መጀመርያ ግን የትዳር ትምህርት Course A++++ ነው ያመጣችሁት🤔🤔


ይነበብ  ጠቃሚ ነው ‼️‼️‼️💯

ዛሬ ስለ ቃልኪዳን ላውራቹ ደሞ ቃልኪዳን ስላቹ የሰፈራቹ ልጅ እንዳትመስላቹ😁
ወደ ገደለው ስገባ በድሮ ጊዜ አንድ ንጉስ ለማደን ከወታደሮቹ ጋር ወደ ጫካ ይሄዳል እየሄደም ሳለ የአየር ሁኔታው ተቀይሮ ለመመለስ ይገደዳል ወደ ቤተ መንግስቱ ሲመለስ አንድ የቤተ መንግስቱን ጠባቂን ስስ ልብስ ለብሶ ይመለከተዋል በዚ ሰአት ለምን እንደዚ አይነት ልብስ ትለብሳለክ ብሎ ይጠይቀዋል ጠባቂውም ለንጉሱ ልብስ እንደሌለው ደሀም እንደሆነ ግን አንተን መጠበቅ ግዴታዬ ነው ብርዱንም ለምጄዋለው ይለዋል ንጉሱም በማዘን ከጥጥ የተሰራ ወፍራም ጃኬት እንደሚልክለት ቃል ይገባለትና ወደ ውስጥ ይገባል ነገር ግን እንደገባ  ልብሱን መላኩን ችላ ብሎት እሳት መሞቅ ይጀምራል ጠባቂው በጣም ተስፋ አርጎ መጠባበቅ ይጀምራል ብርዱም ሲበረታ ጠባቂውም ሲደክም እኩለ ለሊት ይሆናል ብርዱም በሀይል ጠባቂውን አቅም ያሳጣው ጀመር በመጨረሻም ጠባቂም ለንጉሱ ደብዳቤ ፅፎ አቅም አንሶት ይሞታል ጠዋት ብዙ ሰዎች ተሰብስበው ይመለከታል ንጉሡም ከቤተ መንግስቱ ወቶ ሲመለከት ቃል የገባለት ጠባቂው ነበር የሞተው እጁ ላይም ወረቀት ያያል ልክ ሲያነበው ከአይኑ እንባ ይፈስ ጀመረ ጠባቂም እንዲ ነበር  የፃፈው "ታላቅ ንጉስ ሆይ ቃል የገባህልኝን ስጠብቅ ብርዱ በርትቶብኝ አቅሜን አሳቶኝ ህይወቴንም እንዳያሳጣኝ ፈራሁ ከዚ በፊት ከአሁኑ የበለጡ ለሊቶችን አሳልፌ ነበር ግን እነሱ አልከበዱኝም ያልከበዱኝ ምክንያት ምንም ተስፋ የማረግበት ነገር ስለሌለ እበረታ ነበር ዛሬ ግን አንተን ተስፋ እያረኩ መጠበቄ አቅሜን አጥቼ እንዳልሞት ሰጋሁ ቃል የገባከውን ስጠብቅ ብርዱ በረታብኝ ብሎ ነበር የፃፈው"

👉👉 ቃል ስንገባ የምናደርገው ይሁን ምክንያቱም ሰው ከኛ ብዙ ሊጠብቁ ይችላሉና ካልቻላችሁት ቃል አትግቡ ቃል ኪዳን ከባድ ነውና መልካም ምሽት ።🙏🙏


ሰርጉ ላይ ካሜራ ማኑ አስር ግዜ ፈገግ በል ሲለው...
:
#ወንድሜ_እያገባው_እኮ_ነው እየተፋታው መሰለህ እንዴ😡
🤣😂😜

⚠️በነገራችን ላይ ለአዳዲስ ሙሽሮች
መልካም የትዳር ዘመን ወቅቱ የሰርግ አደል😜🙏


♥️💔❤️‍🔥❤️‍🔥
ሲጋራ #አጨሳለሁ ላንች ስል ላንች ስል
ከጭሱ መካከል አገኝሽ ይመስል”😔💔
ብሎ ቢል አጫሹ… 🚬🚬


እኔ ጠጬ ደግሞ…🍻🍺
“መጠጥ እጠጣለሁ ላንች ስል ላንች ስል
አልኮል እጋታለሁ ላንች ስል ላንች ስል
ሌሊት ሲያስመልሰኝ🤮
ካንጀቴ አስወጥቼ እጥልሽ ይመስል”😞

መልካም ቀን🙏🙏🙏🙏


MSI Katana 17 Gaming Laptop 2025, 17.3" 144Hz FHD
Display, Intel 10-Cores i7-13620H, GeForce RTX 4060, 64GB
DDR5, 2TB SSD, USB-Type C,
Win 11 Pro, with Cleaning Kit

አዲስ Gaming Laptop ለምትፈልጉ
በተመጣጣኝ ዋጋ
contact @freew24

Показано 20 последних публикаций.