✍ "ድኻ ወርቅ አይግዛ"🔍
የመጨረሻው ክፍል
(ካለፈው የቀጠለ)
😘ይባስ ብሎ ቀበሌ አዳራሽ ልጆቹን ሰብስቦ ‹ታዋቂው ደራሲ› የሚል ፖስተር ለጥፎ ልምድ አካፍላለሁ ይላቸዋል፡፡ ‹እርሟን ጠምቃ፣ ሰጠች ጠልቃ› አሉ፡፡
አንበሳ ተኝቶ ፍየል ዘለለችው
ንቆ ቢያሳልፋት ሞኝ አደረገችው› አለ የሀገሬ ሰው፡፡ በብጥሌ ወረቀት አላሳተምንም እንጂ ስንት ግጥም ነበረንኮ፡፡
መቶ ታምሳ ዜማ የሚሰማብሽ
ድኻ ባለጠጋ የማይጠፋብሽ
ፀሐይ እንደ እንግሊዝ የማይጠልቅብሽ
የሁሉ እኩል ሀገር አራት ኪሎ ነሽ› ብሎ እንደመግጠም ‹አራት ኪሎ ኪሎ፣ የድንጋይ አሎሎ› ብሎ አሎሎ የሚያህል ግጥም የጻፈን ልጅ ልምድ አካፍላቸው ማለት በአሎሎ ደብድባቸው እንደ ማለት ነው፡፡› ሳቅና ጭብጨባ አጀባቸው፡፡ ድኻ ወርቅ አያግኝ ማለት ይኼ ነው፡፡ አሁን እኛን የቸገረን እንዲህ እንደ አዲሴ የሚባርቅባቸው ድኾች ናቸው፡፡ ሥልጣን አይቶ ለማያውቀው ሥልጣን ትሰጡትና ይባርቅበታል፡፡ የቢሮውን መኪና በሠፈራችን እያፈጠነ ካላሳየን ሞቶ ይገኛል፡፡ በታክሲ ሲሰቃይ ለከረመ ሰው ቪ ኤይት መኪና መስጠት በውኃ ጥም ለከረመ ሰው ቅቤ አቅልጦ እንደማጠጣት ነው፡፡ ሁለቱም ጤና አይሆናቸውም፡፡ አበሉ፣ ስብሰባው፣ ግብዣው፣ ፊርማው፣ ብርቅ ይሆንበታል፡፡ ቀበሌውና ክፍለ ከተማው የግል ንብረቱ ይመስለዋል፡፡ እኛም አሽከሮቹ እንመስለዋለን፡፡ የተሾመ ሰሞን ብርቅ ስለሚሆንበት ያገኘውን ገንዘብና መሬት ይጠበጥበዋል፡፡ ያልራሰ መሬት ማለትኮ ነው፡፡ ምን ውኃ ይመጥነዋል፡፡ ‹አይቶ አያውቅ ዳቦ ፍሪዳው ነው› ይባላል፡፡ አንድ ስብሰባ ላይ አንዲት እንግሊዝኛ የሰማ ዕለት እኛን ሰብስቦ እርሷን ካልተናገረ ይሞታል፡፡ ውጭ ሀገር ሄዶ አንዲት ነገር ካየ፣ ብርቅ ስለምትሆንበት ‹ቻይና ሳለሁ፣ ኮርያ ሳለሁ› እያለ መከራ ያሳየናል፡፡ ድኻ ወርቅ አይግዛ የተባለውኮ ለዚህ ነው፡፡
አላያችሁም እንዴ በድንገት ሀብታም የሆነን ሰው፡፡ ሳይነግራችሁ ታውቁታላችሁኮ፡፡ የውሻ ማሠሪያ የሚያህል የአንገት ወርቅ፣ ክብደት መለኪያ የሚሆን የእጅ ሰዓት፣ የሚታይ ከናቴራ፣ ከከናቴራው ላይ አዲስ ሸሚዝ፣ በሸሚዙ ላይ አዲስ ሹራብ፣ በሹራቡ ላይ አዲስ ኮት፣ በኮቱ ላይ አዲስ የውጭ ካፖርት፣ በካፖርቱ ላይ ስካርፕ ደርቦ ታዩታላችሁ፡፡ ይህን ስታዩ ‹ድኻ ወርቅ አይግዛ› በሉና ሽሹ፡፡ መኪና ከገዛማ አይጣልባችሁ፡፡ በግራ እጁ መሪ ይዞ፣ ወንበሩን ወደ ኋላ ስቦ፣ ልጥጥ እያለ፣ የአስፓልት ውኃ እየረጨባችሁ ያልፋል፡፡
እና አዲሴ ተይን እባክሽ፣ አንቺ ዛሬ ወርቅ ስትገዥ የችግራችን ሁሉ መፍቻ ወርቅ መሰለሽ፡፡ የክፉ ሐኪም ምክር አትምከሪን፡፡ ክፉ ሐኪም ሥጋው የገጠጠ በሽተኛ በቀበሌ ደብዳቤ በነጻ እየታከመ እያየ ከምግብ በፊትና ከምግብ በኋላ ሦስት ጊዜ የሚዋጥ መድኃኒት ያዛል፡፡ ይህ ማለትኮ ሰውዬውን አትድንም ተስፋ ቁረጥ ማለቱ ነው፡፡ መድኃኒቱንስ በነጻ አገኘ፡፡ ምግቡን ማን ይሰጠዋል? አሁን ያስቸገሩን እንዳንቺ ያሉት ናቸው፡፡ ሲበሉ የበላን፣ ቤት ሲሠሩ የሠራን፣ አበል ሲከፈላቸው የተከፈለን፣ ሲሾሙ የተሾምን፣ የእነርሱ ችግር ሲፈታ የእኛ የተፈታ የሚመስላቸው የአእምሮ ድኾች፡፡ ድኃ ወርቅ አይግዛ ከገዛም ይጥፋበት የተባለውም ለዚህ ነው፡፡ ወርቁ ጠፍቶባቸው ከሥልጣን ሲወርዱ፣ ከሀብት ሲናዱ ምን እንደሚመስሉ አይተናቸዋላ፡፡
ሞቅ አድርገን አጨበጨብንላቸው፡፡ ራሷ ሰብሳቢያችን አጨበጨበች፡፡ እኔም ከእርሷ ወስጄ ‹ድኻ ወርቅ አይግዛ ከገዛም ይጥፋበት› እላለሁ:: አሉኝ የምንዳየ እናት አባዬ፡፡
አለቀ፡፡፡፡፡
አስተያየትዎን ያድርሱን @E5683
ያነበባቹ #like and #share
እንዳትረሱ፡፡
@yesakal