የልጆች ትምህርትን የመያዝ አቅም ይለያያል። በቁርኣን፣ በኪታብ፣ በትምህርት፣ በሙያ አንዳንዶች ጎበዝ ሆነው እንደሚያስደስቱን ሁሉ አንዳንዶች ደግሞ ቀዝቀዝ ያሉ ሊሆኑ ይችላሉ። ሁሉም ልጆች አንድ አይነት አቅም ሊኖራቸው አይችልም። ስለዚህ በሌሎች ተሰጥኦ ባላቸው ልጆች እየለኩ ታዳጊዎችን ከአቅማቸው በላይ ማስጨነቅ፣ ስነ ልቦናቸውን መጉዳት አይገባም።
ከነ ጭራሹ አርግፈን እንተዋቸው ማለቴ አይደለም። ማገዝ፣ ማበረታታት፣ እንዲጥሩ መምከር፣ ሲዘናጉ መቆጣት፣ ማኩረፍ፣ እንዳስፈላጊነቱ መቅጣት ድረስ ልንሄድ እንችላለን። አንዳንዶቹ ልጆች እምቅ አቅም እያላቸው ያልታወቀላቸው ወይም እነሱም ራሳቸውን የማያውቁ ሊሆኑ ይችላሉ። አንዳንዶቹ በሂደት የሚለወጡ ይሆናሉ።
እንዳ'ጠቃላይ ደካማም ሆኑ ጠንካራ የሚጥሩ እና የማይጥሩ ፍሬያቸው አንድ አይደለም። አእምሮ ማለት ልክ እንደ ጡንቻ በጣረ እና በሰራ ቁጥር የሚጠነክር፣ ስራ ፈቶ ሲቆይ የሚደክም አካል ነው። ስለዚህ ልጆች ላይ ትኩረት ልናደርግ የሚገባው መጣርን፣ መታገልን ልማዳቸው፣ ባህላቸው እንዲያደርጉ እንጂ በውጤት ብቻ ልንለካቸው አይገባም። የሚጠበቅበትን አድርጎ አመርቂ ውጤት ያላመጣን ልጅ ማስተዋሉ ካለን ደካማ ጎኑን ነቅሶ በማሳየት ውጤታማ የሚሆንበትን መንገድ ማሳየት እንጂ ማሸማቀቅ አይገባም። ብዙም ሳይጥር ውጤታማ የሚሆነውንም እንዲሁ በውጤቱ ብቻ ከመቦረቅ በጊዜ ሂደት ነገሮች በተለያዩ ምክንያቶች ሊለዋወጡ እንደሚችሉ በማስታወስ ጥረትን ልምዱ እንዲያደርግ መምከር ያስፈልጋል።
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://t.me/IbnuMunewor