በዛሬው እለት በተለያዩ በማህበራዊ ድረ ገጾች ላይ “መንግስት 200,000 የመቃብር ቦታዎችን እንዲዘጋጁ አዘዘ” የሚል የሀሰት መረጃ እየተዛመተ ይገኛል። ይህ ፍጹም ከእውነት የራቀ ከመሆኑም በላይ ህዝባችንን ለማደናገር ሆን ተብሎ የተደረገ አሳዛኝ የተንኮል ተግባር በመሆኑ በጥብቅ ሊወገዝ ይገባል። ይህን የሀሰት መረጃ በማመን ህብረተሰባችን እንዳይደናገጥና እንዳይደናገር እያሳስብን በዚሁ አጋጣሚ ማሕበረሰቡ ትክክለኛ የመረጃ ምንጭ የሆኑትን የጤና ሚኒስቴርና የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የሚሰጡትን ወቅታዊ እና ትክክለኛ መረጃ በመከተል እና በመጠቀም በሽታውን ለመከላከል እና ለመቆጣጠር የሚደረገውን ጥረት በተረጋጋ አካሄድ እንዲያግዝ ጥሪያችንን እናቀርባለን።
Ministry of Health,Ethiopia
@zena24now
Ministry of Health,Ethiopia
@zena24now