አብዛኛዎቻችሁ አልገባችሁም ጭራሽ ምን እንደሆነም አታቁም ለማንኛውም እስኪ ላብራራላችሁ!
ይህ ነገር የሊቨርፑል ደጋፊዎች "Mo Salah Christmas Curse" ብለው ይጠሩታል እናም ትርጉሙ የሞ ሳላህ የገና በአል እርግማን እንደማለት ነው! ይህ Curse በአለም አቀፍ የሊቨርፑል ደጋፊዎች የሚታመንበት እና የሊቨርፑል ደጋፊዎች በጣም የሚፈሩት ነው።
ጉዳዩ ምንድነው መሰላችሁ ሳላህ ክሪስማስን ካከበረ አልያም ክሪስማስን እንዳከበረ የሚያሳይ ምስል ፖስት ካደረገ ከዛ በኋላ የሊቨርፑል አቋም ማሽቆልቆል ይጀምራል። ሊቨርፑል እና ሳላ ትልቅ የአቋም መውረድ ይገጥማቸዋል። ይህ ነው እርግማኑ። በዚህ እርግማን 100% የውጪ የሊቨርፑል ደጋፊዎች ያምናሉ እናም ሳምንቱን ሙሉ ሳላ ክሪስማስ እንዳያከበር በየ ሶሻል ሚዲያው ሲማፀኑት ነበር። የሚገርመው ደሞ የዚህ እርግማን ሳላህ ባከበረ ቁጥር የእውነትም መፈጠሩ ነው...
በ2020 ሳላህ ክሪስማስ እያከበረ ምስል ለቆ ነበር ከዛ በኋላ የተፈጠረው በጣም ከባድ ነበር ለሊቨርፑል በታሪኩ ተሰምቶ በማይታወቅ ሁኔታ በተከታታይ 8 ጨዋታዎች በሜዳው አላሸነፈም ነበር። ምስቅልቅሉ ወቶ ነበር በዛን አመት ሳላህ ይህን በአል ካከበረ በኋላ።
ሳላህ በ2021 በአሉ ሲመጣም እንደዚህ ከቤተሰቡ ጋር እያከበረ ፎቶ ለቆ ነበር ከዛም በቀጣይ ጨዋታ ሳላ ፔናሊቲ ስቶ ሊቨርፑል በሌስተር ተሸነፈ። እናም የሳላህ አቋም በጣም ወርዶ ነበር የአፍሪካ ዋንጫንም በሴኔጋል ተነጠቀ። ሊቨርፑል የሊጉን ዋንጫ ለሲቲ አሳልፎም ሰጠ። ቻምፒየንስ ሊግ ፍፃሜ ላይም አቻ የሚያደርጋቸውን ያለቀለት ኳስ ስቶ ሊቨርፑል የUCL ዋንጫ ተነጠቀ።
ባለፈው አመትም እንዲሁ የምታውቁት ነው ሊቨርፑል ሊጉን በ5 ነጥብ ልዩነት እየመራ ነበር ቀጥሎ የተፈጠረውን አለም ያውቀዋል።
እናም እርግማኑ በአጠቃላይ ይህ ነው እንጂ እናንተ እንዳላችሁት ሙስሊም ስለሆነ አይደለም በነገራችን ላይ ይህ የዘመነ መለወጫ መንደርደሪያ ነው አዲሱን ዘመን ለመቀበል ዋዜማ ነው ለነሱ ነው በአውሮፓውያን ዘመን ቀመር የሚጠቀም ሁሉም ሀይማኖት ሙስሊምም ሆነ ክርስቲያን ሁሉም ዘመኑን የሚለውጠው አዲሱን ዘመን ለመቀበል የሚዘጋቸው ከክሪስማስ ጀምሮ በዚህ ቀን ነው ለዛም ነው ሳላህ የሚያከብረው...ምን ታስባላችሁ ያው እግርኳስን ረጅም አመት የተመለከተ ሰው በCurse ማመኑ አይቀርም ብዙ ጊዜ ተመልክተናል ሲፈጠር ብዙ ነገሮች ሲሰሩ...
ሳላህ ዘንድሮ በአሉን አክብሮ እርግማኑ ይቀጥላል ወይስ ሳላህ የሊቨርፑል ደጋፊዎችን ተማፅኖ ሰምቶ በአሉን ሳያከብር ያልፋል?
@ZENA_ARSENAL @ZENA_ARSENAL