Zena Nebab


Гео и язык канала: Эфиопия, Амхарский
Категория: Новости и СМИ


ትኩስ የሃገር ውስጥ እና የውጪ ዜናዎችን ከታማኝ ምንጭ የሚያገኙበት ቻናል
Keepup with the world, find information, get the headlines, be one step ahead, get the news in one place.
📩 @All_Input

Связанные каналы

Гео и язык канала
Эфиопия, Амхарский
Категория
Новости и СМИ
Статистика
Фильтр публикаций




የሰላም ሚኒስቴር ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል ከአውሮፓ ህብረት የአፍሪካ ቀንድ ልዩ ተወካይ አኔቴ ዌበር ጋር ተወያዩ።

በውይይቱ ሚኒስትሯ በሀገሪቱ ወቅታዊ ሁኔታና ቀጠናዊ ጉዳዮች ላይ ማብራሪያ ሰጥተዋል።

የአውሮፓ ህብረት ለሀገሪቱ ልማት በተለያዩ መስኮች እያደረገ ለሚገኘውን ድጋፍ ማመስገናቸውን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ አመላክቷል።

አኔቴ ዌበር በበኩላቸው የአውሮፓ ህብረት ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር ለረጅም ዘመናት የቆየውን መልካም የዲፕሎማሲያዊና የልማት ትብብር ለመቀጠል ያለውን ጠንካራ ፍላጎት መግለፃቸውን ሚኒስቴር መስሪያቤቱ አስታውቋል።


በኢትዮጲያ የኢንሹራንስ ማቋቋሚያ ካፒታል መጠን ሊጨምር ነው በሚል ስለወጣው መረጃ አላውቅም ሲል የኢትዮጲያ ብሄራዊ ባንክ ገለጸ፡፡

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ ምክትል ገዢ አቶ ሰለሞን ደስታ የኢንሹራንስ ኢንዱስትሪ ማቋቋሚያ ካፒታል መጠን ሊጨምር ነው በሚል በአንድ መገናኛ ብዙሃን ላይ ስለወጣው ዘገባ ምንም አይነት መረጃ የለኝም ሲሉ ለአሃዱ ገልጸዋል፡፡

በባንኩ አሰራር መሰረት አዲስ ለሚመሰረቱ የኢንሹራንስ ኩባንያዎች የማቋቋሚያ ካፒታል አሁን በስራ ላይ ከሚገኘው የካፒታል መጠን ጭማሪ ቢደረግ እንኳን ከውሳኔ ሳይደረስ ጭማሪ ሊደረግ ነው ተብሎ ለህዝብ ይፋ አይደረግም ያሉት የባንኩ ምክትል ገዢ አቶ ሰለሞን አሁን ላይ ዝርዝር ሁኔታውን ለማስረዳት የሚያስችል መረጃ የለኝም ሲሉም ተናግረዋል፡፡

አሁን በስራ ላይ ባለው የኢትዮጲያ ብሄራዊ ባንክ መመሪያ መሰረት የኢንሹራንስ ኩባንያዎች ማቋቋሚያ ካፒታል 65 ሚሊየን ብር መሆኑ ይታወቃል፡፡

አሐዱ ራድዮ


የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ንግድ ቢሮ ፥ "የዳቦ ዋጋን ተመን ለማውጣት የሚፈቅድ አሰራር የለንም" አለ።

ቢሮ ይህን ያለው ለአሀዱ ኤፍ ኤም 94.3 ሬድዮ ጣቢያ ነው።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ንግድ ቢሮ የህዝብ ግንኙነት ሀላፊ አቶ ዳንኤል ሚኤሳ በሰጡት ቃል ፥ በመዲናዋ በርካታ ነዋሪዎች የዳቦ ዋጋ በእጅጉ መጨመሩን እንዲሁም የዳቦው መጠንና ዋጋው እንደማይመጣጠን ተደጋጋሚ ቅሬታ ያቀርባሉ ብለዋል።

በመዲናዋ ያሉ ከ 2 ሺህ በላይ ዳቦ ቤቶች ካለፈው 1 አመት ወዲህ ከንግድ ቢሮው ጋር የነበራቸውን ትስስር ያቋረጡ በመሆኑ አሁን ላይ ቢሮው የዋጋ ተመንን ለማውጣት የሚፈቅድ አሰራር እንደሌለው ተናግረዋል፡፡

መንግስት የስንዴ ድጎማውን ማቋረጡን ተከትሎም በመዲናዋ ያሉ ከ 2ሺ በላይ ዳቦ ቤቶች ትስስራቸውን ማቋረጣቸውንም አስረድተዋል፡፡

አቶ ዳንኤል ፥ "ምንም እንኳን በርካታ የመዲናዋ ነዋሪዎች ቅሬታ ቢያቀርቡም አሁን ባለው የቢሮው አሰራር ዳቦ ቤቶቹ ባስቀመጡት የዳቦ ግራም እና ዋጋ በትክክል እየሸጡ መሆን አለመሆኑን ቁጥጥር ይደረጋል እንጂ ዋጋ በመተመን በገበያው ጣልቃ መግባት አይቻልም" ሲሉ ተናግረዋል፡፡

አክለው በተያዘው አመት ባስቀመጡት የዳቦ ግራም መጠን ዋጋ ሲሸጡ ያልተገኙ ወደ 24 የሚጠጉ ዳቦ ቤቶች ላይ እርምጃ መወሰዱን ገልጸዋል፡፡
አሀዱ ኤፍ ሬድዮ


የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በሱዳን አብዬ ግዛት በሰላም ማስከበር ላይ የሚገኙ የኢትዮጵያ ወታደሮችን በሌላ ለመተካት መስማማቱን የአገሩ ሹማምንት መናገራቸውን ሱዳን ትሪቡን ዘግቧል፡፡

ከኢትዮጵያ ጋር በድንበር ፍጥጫ ውስጥ የምትገኘው ሱዳን በአወዛጋቢው የአብዬ ግዛት ውስጥ በሠላም አስከባሪነት የተሰማራው የኢትዮጵያ ሠራዊት በሌላ አገር ጦር እንዲተካ ከሦስት ወራት በፊት በውጭ ጉዳይ ሚኒስትሯ በኩል መጠየቋ መነገሩ ይታወሳል፡፡

እንደ ሱዳን ትሪቡን ዘገባ ከሆነ የአገሪቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር መርየም አል መሕዲ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የምሥራቅ አፍሪካ ልዩ መልእክተኛ ከሆኑት ፐርፋይት ኦናንጋ አንያንጋ እና ሌሎች የሰላም አስከባሪው ሹምምንት ጋር ካደረጉት የበይነ መረብ ውይይት በኋላ የመንግስታቱ ድርጅት የኢትዮጵያ ወታደሮች የአብዬ ግዛትን ለቀው እንዲወጡ ከስምምነት ተደርሷል፡፡

የአብዬ ግዛትን ይለቃሉ የተባሉት የኢትዮጵያ ወታደሮች፣ ከሥፍራው እንዲወጡ ከስምምነት የተደረሰው በቀጣይ ሦስት ወራት ጊዜ ውስጥ መሆኑም ተጠቅሷል፡፡

የተባበሩት መንግሥታት መረጃ እንደሚያመለክተው ከ3 ሺሕ 300 በላይ የኢትዮጵያ ሠራዊት አባላት በድርጅቱ ዕዝ ስር በአብዬ ግዛት ውስጥ ተሰማርተው የሠላም ማስከበር ተግባር እያከናወኑ ይገኛሉ።


በቦሌ ክፍለ ከተማ በሚገኝ አንድ ፔንሲዮን የተደበቁ 20 ክላሽን-ኮቭ ጠመንጃዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የአዲስ አበባ ፖሊስ ገለፀ፡፡

በወንጀሉ የተጠረጠሩ ሁለት ግለሰቦች ተይዘው ምርመራ እየተጣራባቸው እንደሚገኝም ፖሊስ አስታውቋል፡፡

ትናንት ምሽት በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ አራት ልዩ ቦታው ውሃ ልማት ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በሚገኘው አምባሳደር ፔንሲዮን ውስጥ የመኝታ አገልግሎት ፈልገው አልጋ ለመከራየት የገቡ ሁለት ግለሰቦች በማዳበሪያ የተጠቀለለ ለጊዜው ምንነቱ ያልታወቀ ነገር ይዘው ስለመግባታቸው በክትትል ተደርሶባቸዋል፡፡

የብሄራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ጥብቅ ጥናትና ክትትል ሲያደርግ ከቆየ በኋላ ከአዲስ አበባ ፖሊስ ጋር በመቀናጀትና አስፈላጊውን ህጋዊ ሂደት በመከተል በፔንሲዮኑ ውስጥ ባደረገው ብርበራ በጨርቅ እና በማዳበሪያ የተጠቀለሉ አስር ባለሰደፍ እና አስር ታጣፊ ክላሽን-ኮቭ ጠብመንጃዎችን እንዲሁም 17 የክላሽንኮቭ ጥይት ካርታዎችን በመኝታ ክፍል ውስጥ ተደብቀው መገኘታቸውንና በቁጥጥር ስር ማዋሉን ፖሊስ ገልጿል፡፡

ከውስጥ እና ከውጪ ፀረ- ሰላም ሃይሎች ጋር ተጣምረው ሃገራችንን ለማፍረስ እየሰሩ የሚገኙት የሽብር ቡድኖች ተልዕኳቸውን ለማሳካት የተለያዩ መንገዶችን ሊጠቀሙ እንደሚችሉ ተጠቅሷል፡፡

በተጨማሪም አስፈላጊውን ቅድመ ጥንቃቄ ለማድረግ አልጋ የሚያከራዩ ሆቴሎች፣ ፔንሲዮኖች እና መሰል አገልግሎት የሚሰጡ የንግድ ተቋማት እንዲሁም የመኖሪያ ቤት የሚያከራዩ ግለሰቦች የተከራዮችን ማንነት በደንብ ማረጋገጥ እና አጠራጣሪ ነገሮች ሲያጋጥሙ ለፀጥታ አካላት ጥቆማ በመስጠት እንዲተባበር የአዲስ አበባ ፖሊስ አሳስቧል፡፡


በትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ሰራተኞ የታዘዙ ቼኮች እንዳይመነዘሩ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ለቅርጫፎቹ በደብዳቤ ማሳወቁን ዋዜማ ራዲዮ ከደብዳቤው ቅጂ ተረድቻለሁ ብሎ ዘግቧል፡፡

ንግድ ባንክ ትእዛዙን ያስተላለፈው የፌዴራል መንግስት በተናጠል አውጄዋለሁ ያለውን የተኩስ አቁም ተከትሎ መቀመጫውን አዲስ አበባ ካደረገው የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ደረሰኝ ባለው ደብዳቤ ላይ ተመስርቶ እንደሆነ ገልጿል።

በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በ‹‹ሽብርተኛ›› ድርጅትነት የተፈረጀው ሕወሓት ከፌዴራል መንግስት ጋር የገጠመውን ጦርነት ተከትሎ በትግራይ ክልል ያሉ የባንክ ሂሳቦች እንደታገዱ ደብዳቤው አስታውሷል።

የፌዴራል መንግስት ጦር መቀሌን ጨምሮ መላው የትግራይ ክልል ለወራት ከተቆጣጠረ በኋላ ክልሉን ለቆ ሲወጣ ክልሉን ሲያስተዳድሩ የቆዩት የጊዜያዊ አስተዳደሩ አባላት ወደ አዲሰ አበባ እንደተሰደዱ ይታወሳል።

በትግራይ ያሉ የባንክ ሂሳቦች የታገዱ ቢሆንም በጊዜያዊ አስተዳደሩ ከክልሉ የተለያዩ የባንክ ሂሳቦች (ሙያተኞቹ B እና Z አካውንቶች ከሚሏቸው) ወጭ እንዲሆን ያዘዙት ቼክ ስላለ ይሄንንም ቼክ በተለያዩ መንገዶች ለመመንዘር ጥረት ሊደረግ ስለሚችል ሁሉም የንግድ ባንክ ቅርንጫፎች ጥንቃቄን እንዲያደርጉና ቼኩን እንዳይመነዝሩ ከንግድ ባንኩ ፕሬዝዳንት ትእዛዝ እንደተላለፈላቸው ደብዳቤው ገልጿል።

የታዘዙ ቼኮችን ለመመንዘር የሚደረጉ ጥረቶች ካሉ የንግድ ባንኩ ሰራተኞች ለሚመለከተው አካል የሚያሳውቁባቸው ስልክ ቁጥሮችም በደብዳቤው ተዘርዝረዋል። ሆኖም እግዱ የተላለፈበት ትክክለኛ ምክንያት በደብዳቤው ላይ አልተገለጸም።

መንግስት ባለፉት ቀናት የሕወሓት የገንዘብ ምንጭ ይሆናሉ ብሎ ባሰባቸው የገንዘብ እንቅስቃሴዎች ላይ ተከታታይ እርምጃን መውሰዱ የሚታወቅ ነው። ንግድ ባንኮች በማስያዣ ብድር መስጠት እንዲያቆሙ፣ በህገወጥ ሀዋላ ላይ መወሰድ የጀመረው አሰሳ፣ እንዲሁም የንብረት በተለይ የቤት ሽያጭ ላይ የተላለፉት እገዳዎች የዚሁ አካል መሆናቸው ይታወቃል።


ኤርትራ በጦር መሪዋ ላይ አሜሪካ የጣለችውን ማዕቀብ ውድቅ አደረገች


ኤርትራ ከትግራይ ጦርነት ጋር በተገናኘ በጦር መሪዋ ጄነራል ፊሊጶስ ወልደዮሐንስ ላይ በአሜሪካ የጣለችውን ማዕቀብ መሠረተ ቢስ ነው ብላዋለች፡፡

ኤርትራ መሠረተ ቢስ ያለችውን የአሜሪካን የማዕቀብ እርምጃ በተመለከተ በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴሯ በኩል መግለጫ አውጥታለች።

የአሜሪካ አስተዳደር በጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ጄነራል ፊሊጶስ ወልደዮሐንስ ላይ ተቀባይነት የሌላቸውን ክሶች ሰንዝሯል ያለው መግለጫው፣ የኤርትራ መንግስት የተቃጣበትን መሠረተ ቢስ ውንጀላ እና ክስ በደብዳቤም ሆነ በመንፈስ እንደማይቀበል አስታውቋል።

የአሜሪካ አስተዳደር እንዲህ ዐይነት መሠረተ ቢስ የውንጀላ ዘመቻዎችን በኤርትራ ላይ ሲያደርግ የመጀመሪያው እንዳልሆነም ለአገሪቱ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት ኃላፊ አንቶንዮ ብሊንክን የተሰጠውን መልስ አስታውሷል፡፡

ኤርትራ ምክንያታዊ ያልሆኑ ያለቻቸው ተደጋጋሚ ክሶችን በዝምታ ልታልፍ እንደማትችልም መግለጫው ይጠቁማል።

ሐሰተኛ ያለው ውንጀላ ሊጣራ የሚችል ነገር ካለው በገለልተኛ አካል እንዲጣራም ለአሜሪካ አስተዳደር ጥሪ አቅርቧል።

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የጸጥታው ምክር ቤት ተደጋጋሚ የዓለም አቀፍ ህግጋትና የሃገራትን የሉዓላዊነት ጥሰቶች በመግታት እና መፈትሔ በመፈለግ ረገድ ኃላፊነቱን እንዲወጣም አሳስቧል።

በትግራይ ጦርነት የሚመሩት ጦር የተለያዩ ሰብዓዊ ጥሰቶችንና ግድያዎችን ፈጽሟል ያለው የአሜሪካ ፌዴራል ግምጃ ቤት፣ ጄነራል ፊሊጶስ በአሜሪካ አላቸው ያለውን ሐብት እንዳያንቀሳቅሱ ማገዱን ማስታወቁ የሚታወስ ነው።


ኢትዮጵያ በቀጣዩ ዓመት ለሶስት ጎረቤት አገራት 1 ነጥብ 6 ቢሊዮን ኪሎ ዋት ኤሌክትሪክ እንደምትሸጥ አስታወቀች።
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሀይል በድረገጹ ባወጣው መግለጫ ተቋሙ በሚቀጥለው ዓመት ከኃይል ኤክስፖርት ከ138 ሚሊዮን ዶላር በላይ ገቢ ለማግኘት አቅዷል።
በተቋሙ የማርኬቲንግና ቢዝነሰ ደቨሎፕመንት መምሪያ ሥራ አስኪያጅ አቶ ሚኒሊክ ጌታሁን እንዳሉት በተያዘው የበጀት ዓመት ለሱዳን፣ ለጅቡቲ እና ኬንያ ከ1 ነጥብ 63 ቢሊዮን ኪሎ ዋት ሠዓት በላይ የኤሌክትሪክ ኃይል በማቅረብ 138 ነጥብ 25 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር ገቢ ለማግኘት ታቅዷል፡፡
ገቢውን ለመሰብሰብ ለሱዳን 1 ነጥብ 1 ቢሊዮን ኪሎ ዋት ሠዓት ኤሌክትሪክ በማቅረብ 55 ነጥብ 48 ሚሊዮን ዶላር እንዲሁም ለጅቡቲ 527 ነጥብ 4 ሚሊዮን ኪሎ ዋት ሠዓት ኤሌክትሪክ በማቅረብ 34 ነጥብ 1 ሚሊዮን ዶላር ለማግኘት መታሰቡንም ሥራ አስኪያጁ ተናግረዋል፡፡
እስካሁን የኢነርጂ ኤክስፖርት ወዳልተጀመረበት ኬኒያ ወደ 695 ኪሎ ዋት ሰዓት የኤሌክትሪክ ኃይል ለማቅረብና 48 ነጥብ 65 ሚሊዮን ዶላር ለማግኘት ዕቅድ መያዙንም ስራ አስኪያጁ ገልጸዋል፡፡
በኢትዮጵያ በኩል የኢትዮ- ኬንያ ከፍተኛ የኤሌክትሪክ ኃይል ማስተላለፊያ መስመር በመጠናቀቁና የኬንያም ተጠናቆ አገልግሎት መስጠት እንደሚጀምር ታሳቢ ተደርጎ ከጥር 2014 ዓ.ም ጀምሮ ለመጀመሪያ ጊዜ ወደ ኬንያ የኤሌክትሪክ ኃይል ኤክስፖርት ለማድረግ እቅድ ተይዟል ተብሏል፡፡
በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ለኬንያ 695 ሚሊዮን ኪሎ ዋት ሰዓት የኤሌክትሪክ ኃይል በማቅረብ 48 ነጥብ 6 ሚሊዮን ዶላር ገቢ ለመሰብሰብ ታቅዶ የነበረ ቢሆንም በኬንያ በኩል እየተገነባ ያለው የኢትዮ- ኬንያ የማስተላለፊያ መስመር ፕሮጀክት ግንባታ ባለመጠናቀቁ ለኬንያ የኤሌክትሪክ ኃይል ማቅረብ እንዳልተቻለ መዘገባችን ይታወሳል፡፡
ኢትዮጵያ ከሦስቱ ሀገራት በተጨማሪ በቀጣይ ከሶማሌ ላንድ፣ ከታንዛኒያ እና ደቡብ ሱዳን እና ከሌሎች የአፍሪካ ሀገራት ጋር የኤሌክትሪክ ኃይል ትስስር ለመፍጠር የሁለትዮሽ ግንኙነት በማድረግ ላይ ትገኛለች፡፡
ኢትዮጵያ በቀጣዮቹ 10 ዓመታት 71 የኤሌክትሪክ ሀይል ማመንጫ ጣቢያዎችን ለመገንባት ማቀዷን መግለጿ የሚታወስ ነው።


ምርጫ ባልተካሄደባቸው ምርጫ ክልሎች የፊታችን መስከረም 20 ድምፅ ይሰጣል ተባለ

ሰኔ 14 ምርጫ ባልተካሄደባቸው ምርጫ ክልሎች የፊታችን መስከረም 20 ድምፅ እንዲሰጥ መወሰኑን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አስታወቀ።
ቦርዱ ምርጫ ባልተደረገባቸው ምርጫ ክልሎች ከሚወዳደሩ ፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር ውይይት በማድረግ ድምፅ መስጫ ቀኑ መወሰኑን አስታውቋል።
ሁሉም የቦርዱ አመራሮች በተገኙበት የምክክር መድረክ በቦርዱ ዋና ሰብሳቢ ብርቱካን ሚደቅሳ አማካኝነት ቦርዱ ሲሰራቸው የቆያቸው ስራዎች የተመለከተ ሪፓርት ለፓርቲዎች የቀረበ ሲሆን ቀጣዩን የምርጫ ሂደት ከአካባቢዎቹ አጠቃላይ ሰላምና ተጨባጭ ሁኔታ ጋር በማገናዘብ ዝርዝር መረጃ ተሰጥቶ ውይይት ተደርጓል።
በዚህም ምርጫው በመጪው መስከረም 20ቀን 2014 ዓ/ም እንዲካሄድ ስምምነት ላይ ተደርሷል።
ድምፅ አሰጣጡ በሶማሌ፣ በሐረሪ ክልል እና በደቡብ ብሔር ብሔረሰቦች እና ህዝቦች ክልል የሚከናወን ሲሆን የደቡብ ምእራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ህዝበ ውሳኔም በተመሳሳይ ቀን መስከረም 20 ቀን 2014 ዓ.ም እንደሚከናወን ቦርዱ አስታውቋል።

አል ዐይን


በሱዳን ጎርፍ ባስከተለው አደጋ ከ50 በላይ ሰዎች ህይወት ማለፉን ተከትሎ ግብጽ ሃዘኗን ገልጻለች፡፡

በጎርፍ አደጋው እናትና ልጅን ጨምሮ የ52 ዜጎች ህይወት ማለፉን የሀገሪቱ የሲቪል መከላከያ ብሔራዊ ምክር ቤትቃል አቀባይ አብደል ጋሊል አብደል ራሂም መናገራቸውን ኢጂብት ቱዴይ ዘግቧል።

ሱዳን አና ግብጽ ከኢትዮጵያ ታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ጋር ተያይዞ የውሃ እጥረት ያጋጥማል በማለት ተደጋጋሚ ቅሬታ እንደሚያቀርቡ ይታወቃል፡፡

በአንጻሩ በቀጠናው በቂ የውሃ አቅርቦት መኖሩን ተከትሎ ሱዳን በተደጋጋሚ ለጎርፍ አደጋ እየተጋለጠች መሆኑን መረጃዎች ያመላክታሉ፡፡


በአሜሪካ የሚገኙ ሕፃናት በዴልታ ኮቪድ 19 ቫይረስ እየተጠቁ መሆኑ ተጠቆመ፡፡የአሜሪካ ፔዲያትሪክስ አካዳሚ እና የሕፃናት ሆስፒታል ማሕበር ባወጡት ሪፖርት÷ ባሳለፍነው ሳምንት ብቻ በሀገሪቱ ወደ 94 ሺህ የሚጠጉ ሕፃናት በቫይረሱ ተጠቅተዋል ፡፡

ሉዚያና እና ፍሎሪዳ በርካታ በኮቪድ 19 ቫይረስ የተጠቁ ሕፃናት ሪፖርት የተደረገባቸው አካባቢዎች እንደሆኑም ተመላክቷል፡፡

በኒው ኦርሊያንስ የሕፃናት ሆስፒታል ውስጥ የሚሰራ ዶክተር ማርክ ክላይን ÷ በሆስፒታላቸው ውስጥ በኮሮና ቫይረስ ተጠቅተው ሊታከሙ ከሚሄዱ ሕፃናት ግማሽ ያህሉ እድሜያቸው ከ 2 ዓመት በታች ነው ብሏል፡፡

የተቀሩት በቫይረሱ የተጠቁና በሆስፒታሉ ለሕክምና የተገኙ ሕፃናት ደግሞ እድሜያቸው ከ 5 እስከ 10 ባለው ክልል ውስጥ የሚገኙ መሆናቸውን ጠቁመው፥ በጣም ሕፃናት በመሆናቸው ክትባት ለመስጠት አስቸጋሪ እንዳደረገው ዶክተሩ ገልፀዋል፡፡

ወረርሽኙ ከተከሰተ ወዲህ እስካሁን ወደ 4 ነጥብ 3 ሚሊየን የሚሆኑ ሕፃናት ቫይረሱ እንደተገኘባቸውና ቁጥሩም ከጊዜ ወደ ጊዜ እያሻቀበ መሆኑን ነው ከሲጂቲ ኤን ያገኘነው መረጃ የሚያመላክተው፡፡


በኢትዮጵያ 3ኛው የኮቪድ 19 ወረርሽኝ መከሰቱን የሚያሳዩ ምልክቶች መታየታቸው ተገለጸ

On Aug 24, 2021  227

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 18፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ሶስተኛው የኮቪድ 19 ወረርሽኝ በኢትዮጵያ መከሰቱን የሚያሳይ ምልክት መታየቱን የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ ገለጹ።

 

ዶክተር ሊያ ጉዳዩን አስመልክተው ዛሬ በሰጡት መግለጫ ÷ በኢትዮጵያ ባሳለፍነው ሳምንት ብቻ 5 ሺህ 547 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸውን ተናግረዋል፡፡

 

በአንድ ቀን ውስጥ ከ1 ሺህ በላይ ሰዎች መያዛቸውን የገለጹት ሚኒስትሯ÷ የወረርሽኙ መጠን ከዚህ በፊት ካለው በእጅጉ መጨመሩን ተናግረዋል።

 

የኮቪድ 19 ወረርሽኝ በአሁኑ ሰዓት ቫይረሱ የሚገኝበት ሰው ቁጥር ምጣኔ በእጅጉ መጨመርም ሶስተኛው የኮቪድ 19 ወረርሽኝ በኢትዮጵያ መከሰቱን የሚያመላክት መሆኑን ጠቁመዋል፡፡

 

ማህበረሰቡም ከዚህ በፊት የሚያደርገውን ጥንቃቄ አጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት ሚኒስትሯ አሳስበዋል፡፡

 

በቅድስት ተስፋዬ


ዕድሜያቸው ከ35 በላይ ለሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎች የኮቪድ 19 ክትባት በመንግስት ጤና ጣቢያዎች ሊሰጥ መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮ አስታወቀ፡፡

የጤና ቢሮው ኃላፊ ዶክተር ዮሐንስ ጫላ የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ካለፉት 4 ሳምንት ጀምሮ በአዲስ አበባ በኮቪድ 19 የመያዝ መጠን ፤ በጽኑ የሚታመሙ ሰዎች ፤ እንዲሁም በበሽታዉ ምክኒያት ህይወታቸዉን ያጡ ሰዎች ቁጥር ከፍተኛ ጭማሪ አሳይቷል : :

ይህም በበርካታ የአፍሪካ ሀገራት የታየውን የወረርሽኙ 3ኛዉ ማአበል በከተማችን የመታይት አዝማሚያ ያሳያል ብለዋል : :

የኮቪድ 19 ክትባትን መስጠት ወረርሽኙን ለመከላከል ትልቅ አስተዋጽኦ የሚያደርግ ሲሆን÷ በኮቫክስ ፋሲሊቲ አማካይነት ወደ ሀገራችን የሚገቡትን ክትባቶች በየደረጃዉ ላሉ በስራ ባህሪያቸዉ ለቫይረሱ ይበልጥ ተጋለጭ ለሆኑ የጤና ባለሙያወች ፤ እድሜቸዉ ከ65 አመት በላይ ለሆኑ እና እድሜቸዉ ከ 55 – 64 የሆኑና ተጓዳኝ የጤና ችግር ላለባቸዉ ብቻ ቅድሚያ እንዲያገኙ ሲደረግ መቆቱን ጠቅሰዋል፡፡

በአሁኑ ወቅትም በለጋሽ ሀገራት እገዛ የተለያዩ ክትባቶች ወደ ሀገራችን እየገቡ እንደሚገኙና እስካሁንም አስትራዜኒካ ፤ ሲኖፋርምና ጆንሰን ጆንሰን የሚባሉ ክትባቶች አገልግሎት ላይ እየዋሉ ይገኛሉ ብለዋል : :

የክትባቶቹ መጠሪያ የተለያየ ቢሆንም በደህንነታቸዉና ፍቱንነታቸዉ፣ የወረርሽኙን ስርጭት ከመቆጣጠርና በወረርሽኙ ሊደርስ የሚችለዉን የከፋ ህመምና ሞት ከመከላከል አንጻር ሁሉም ክትባቶች ተመሳሳይ ዉጤት ያላቸዉ መሆኑን አንስተዋል፡፡

በዚህም ማህበረሰቡ ያለምንም ስጋት ወደ መንግስት ጤና ጣቢያዎች በመሄድ ክትባቱን በነፃ ያለምንም ክፍያ በመዉሰድ ራሱንና ቤተሰቡን ከአስከፊ ወረርሽኝ እንዲጠብቅም ዶክተር ዮሐንስ ማሳሰባቸውን ከቢሮው ያገኘነው መረጃ ያመለክታል: :

በዚህ ዙር የሚሰጠው ክትባት ከዚህ በፊት ክትባቱን ያልወሰዱ ከ1ሚሊየን በላይ የህብረተሰብ ክፍሎች እንደሆኑ ገልፀው÷ እድሜቸዉ 35 ዓመት የሆኑ: እድሜቸዉ ከ 18 አመት በላይ የሆኑና ተጓዳኝ በሽታ ላለባቸዉ ሰዎች ክትባቱን ለመስጠት ታስቧል፡፡

በተጨማሪም በስራ ባህሪያቸዉ ተጋላጭ ናቸዉ ተብለዉ የተለዩ ከ105 በላይ ለሚሆኑ የመንግስትና የግል ተቋማት ክትባቱን ለመስጠት መታቀዱንም ገልጸዋል : :

በተጨማሪም ኃላፊው ክትባቱን መዉሰድ ወረርሽኙን ለመከላከል አንዱ ዘዴ ቢሆንም የኮቪድ 19 ወረርሽኝ መከላከያ ዘዴዎችን መተግበር አስፈላጊ መሆኑንም ገልጸዋል : :

ህብረተሰቡ ክትባቱ የሚሰጠዉ በነፃ መሆኑን አዉቆ ምንም አይነት ክፍያ የሚጠይቅ አካል ካለ ለጤና ተቛሙ ሀላፊዎች ወይም በአቅራቢያዉ ለሚገኝ የህግ አካላት ጥቆማ እንዲሰጡ አሳስበው ቢሮው ጉዳዩን ተከታትሎ እርምጃ የሚወስድ መሆኑን ተናግረዋል : :


የጸጥታ ጥበቃው ምክር ቤት በመጪው ሐሙስ በትግራይ ጉዳይ እንደሚመክር ተሰማ !


የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የጸጥታ ጥበቃው ምክር ቤት፤ በኢትዮጵያ በትግራይ ክልል ባለው ነባራዊ ሁኔታ ላይ በመጪው ሐሙስ በዝግ ሊመክር መሆኑ ተሰምቷል፡፡ ምክር ቤቱ በትግራይ ክልል ውጊያ ከተቀሰቀሰ ወዲህ በጉዳዩ ላይ ሲወያይ የሐሙሱ ለስምንተኛ ጊዜ ነው።


የትግራይ ሁኔታን በተመለከተ የጸጥታው ምክር ቤት ስብሰባ እንዲያደርግ የጠየቁት ስድስት ሀገራት መሆናቸው የተነገረው ሲሆን፣ እነዚህ አገራት አየርላንድ፣ ኢስቶኒያ፣ ፈረንሳይ፣ ኖርዌይ፣ ብሪታኒያ እና አሜሪካ ናቸው፡፡


ስድስቱ ሀገራት ስብሰባው እንዲካሄድ የጠየቁት፤ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ጸሐፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ በኢትዮጵያ የተኩስ አቁም እንዲደረግ ጥሪ ማቅረባቸውን ተከትሎ ስለመሆኑም ተዘግቧል፡፡


ጉተሬዝ በሐሙሱ ስብሰባ ላይ ተገኝተው በጉዳዩ ላይ ማብራሪያ ይሰጣሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ጉዳዩን በቅርብ የሚያውቁ የዲፕሎማቲክ ምንጮች ነግረውኛል ብሎ ኢትዮጵያ ኢንሳይደር ድረ ገጽ ጽፏል፡፡


ከተመድ ዋና ጸሐፊ በተጨማሪ በቅርቡ ወደ ኢትዮጵያ በተጓዙበት ወቅት ትግራይን ጎብኝተው የተመለሱት የድርጅቱ የሰብዓዊ እና የአስቸኳይ እርዳታ አስተባባሪ ማርቲን ግሪፊትዝም በስብሰባው ላይ እንደሚሳተፉ ነው የተነገረው፡፡


የሽብር ቡድኖቹን እንቅስቃሴ ለመግታት ዝግጅት ማድረጉን የኦሮሞ ብሄረሰብ ልዩ ዞን አስታወቀ
************************

የህወሓትና ሸኔ የሽብር ቡድኖችን እንቅስቃሴ ለመግታት በቂ ዝግጅት ማድረጉን በአማራ ክልል የኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር ልዩ ዞን አስታወቀ፡፡

የፌደራል፣ የክልልና የኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር ልዩ ዞን የመንግስት የስራ ሃላፊዎች በባቲ ግንባር የተሰማራውን ሚሊሻ የስራ እንቅስቃሴ ጎብኝተዋል፡፡

የልዩ ዞኑ ወረዳዎች፣ ከደቡብ ወሎና የአፋር ክልል የሚዋሰኑባቸው ቦታዎች ላይ የተሰማራው ሚሊሻ የሽብር ቡድኖቹ ሰርገው መግባት የሚችሉበትን መንገድ ሙሉ ለሙሉ ዘግተናል ብሏል፡፡

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ አህመዲን መሐመድ (ዶ/ር) የፖለቲካ አመራሩ፣ የሀገር ሽማግሌዎችና የፀጥታ ሃይሉ የሽብር ቡድኖቹን ለመመከት ያደረጉትን ዝግጅት አድንቀዋል፡፡

መተባበር ከቻልን አንዳች ሃይል አይደፍረንም ያሉት ሚኒስትር ዴኤታው የስጋት ቦታዎችን ሁሉ በመድፈን ህዝባችንን ከስጋት ነፃ ማድረግ አለብን ብለዋል፡፡

በአማራ ክልል የኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር ልዩ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ አህመድ ሐሰን የህዝባችን ጠላት የሆኑትን የህወሓትና የሸኔ ቡድኖችን የሰርጎ ገብ እንቅስቃሴ ለመግታት ሚሊሻው በአስተማማኝ ቁመና ላይ መሆኑን ተናግረዋል።

የአማራ ክልል ገቢዎች ቢሮ ምክትል ኃላፊ ፍቅረማርያም ደጀኔ የኢትዮጵያውያን ሁሉ ጠላት የሆኑትን ቡድኖች ለመመከት ትብብር ወሳኝ መሆኑን አንስተዋል፡፡


የተሻሻለው የታሪፍ ደንብ የጦር መሣሪያዎችን በነጻ ማስገባት የሚፈቅድ መሆኑ ተገለጸ

አዲስ የተሻሻለው የታሪፍ ደንብ የወታደራዊ (ሚሊተሪ) ከባድ የጦር መሣሪያዎችን ማለትም እንደ ጠመንጃ፣ ሮኬት፣ ላውንቸር እና እሳት የሚተፉ መሣሪያዎችን ከቀረጥ ነጻ እንዲገቡ የሚፈቅድ መሆኑ ተገለጸ።
የአገር መከላከያ ሚኒስቴር፣ የፌዴራል እና የክልል ፖሊስ ተቋሞች፣ የሕዝብ ደሕንነት ተቋሞች ወደ አገር የሚያስገቧቸዉ የመከላከያና የሕዝብ ደህንነት መሣሪያዎች፣ ለነዚሁ አገልግሎት የሚዉሉ ክፍሎችና እና ቁሳቁሶች (አክሰሰሪዎች) በነጻ እንዲገቡ ማሻሻያው ይፈቅዳል።


የኢትዮጵያ ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ጌዲዮን ጢሞቴዎስ (ዶ/ር) ከቢቢሲ ሀርድቶክ ፕሮግራም ጋር ሰኞ ዕለት ቆይታ አድርገው በትግራይ ከተከሰተው ጦርነት ጋር በተያያዘ ለተነሱላቸው ጥያቄዎች ምላሽ ሰጥተዋል።

ትግራይ ውስጥ ተጀምሮ ሌሎች ክልሎች ስለተስፋፋው ጦርነት ፣ በትግራይ ስለተቋረጡት መሰረታዊ አገልግሎቶች፣ ሰለሰብአዊ መብት ጥሰቶች፣ ስለእርዳታ አቅርቦት እና ተያያዥ ጉዳዮች ጠቅላይ ዐቃቤ ሕጉ ከስቴፈን ሳከር ተወያይተዋል።

ዶ/ር ጌዲዮን በምን ጉዳዮች ላይ ምላሽ ሰጡ ?
- የሰብዓዊ እርዳታ ጉዳይ
- ሰላማዊ መፍትሔ
- የትግራይ ተወላጆች እስር
- የሰብዓዊ መብት ጥሰት ክሶች
- ስለመሠረታዊ አገልግሎቶች ... ሌሎችም።

ያንብቡ : telegra.ph/BBC-HardTalk-08-24 / ጥሩ የሆነ የኢንተርኔት ግንኙነት ማግኘት ከቻላችሁም ከላይ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

Credit : BBC Amharic Service

©tikvahethiopia


ቦርዱ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝበ ውሳኔ መስከረም 20 እንዲካሄድ ወሰነ


የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ጳጉሜ 1፣ 2013 ይካሄዳል ተብሎ ቀጠሮ የያዘለትን የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝበ ውሳኔ በአዲስ ዓመት መስከረም 20 እንዲካሄድ ውሳኔ አሳልፏል፡፡


ምርጫ ቦርድ ለሁለት ጊዜያት ያራዘመው ሕዝበ ውሳኔ፣ በከፋ፣ በዳውሮ፣ ቤንች ሸኮ፣ ምዕራብ ኦሞና የሸካ ዞኖች እንዲሁም የኮንታ ልዩ ወረዳን የሚያሣትፍ ነው፡፡


በሌላ በኩል ሰኔ 14፣ 2013 ምርጫ ባልተካሄደባቸው ምርጫ ክልሎች የድምጽ መስጫ ቀን በተመሳሳይ መስከረም 20፣ 2014 እንዲሆን መወሰኑን ምርጫ ቦርድ አስታውቋል፡፡

በጉዳዩ ላይ ነሐሴ 13፣ 2013 ምርጫ ባልተደረገባቸው የምርጫ ክልሎች ከሚወዳደሩ ፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር ውይይት ማድረጉን ያስታወቀው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ፣ ከፓርቲ ተወካዮቹ ሀገሪቱ አሁን ካለችበት ሁኔታ አንጻር ምርጫ ማድረጉ ተገቢ አይደለም የሚል አስተያየት የሰጡ መኖራቸውን፣ በአንጻሩ ደግሞ ሰኔ 14፣ 2013 የተደረገውም ምርጫ የተደረገው በተመሳሳይ የፀጥታ ችግር በነበረበት ሁኔታ፤ አንጻራዊ ሰላም ያለባቸው አካባቢዎች ተለይተው እንደተካሄደ ጠቅሰው፤ አሁን የሚካሄደው ምርጫም እንደቀደመው ሁሉ የተሻለ ፀጥታ ያለባቸውን አካባቢዎች በመለየት ማካሄድ እንደሚቻል አስተያየት ተሰጥቷል መባሉንም ገልጧል፡፡

በመጨረሻም መስከረም 20 ድምፅ አሰጣጡ ይከናወን ያለው ቦርዱ፣ ምርጫው የሚከናወነው በሶማሌ፣ በሐረሪ እና በደቡብ ክልሎች መሆኑንም አስታውቋል፡፡
©AmbaDigMedia


የኢትዮጵያ የሀገር መከላከያ ሰራዊት በአማራ ክልል ደቡብ ጎንደር ዞን በህወሓት ተይዘው የነበሩ ቦታዎች ማስለቀቁን አስታወቀ።

#Ethiopia : መከላከያ ሰራዊት ከአማራ ልዩ ኃይል እና የአማራ ሚሊሻ ጋር በመሆን በወሰደው እርምጃ ፦ ጋሳይ፣ ክምር ድንጋይ፣ ጎብጎብ፣ ሳሊና ንፋስ መውጫ ነፃ ማውጣቱን ገልጿል።

የንፋስ መውጫ ከተማ ነዋሪዎች ህወሓት በንፋስ መውጫ ከተማ ንፁሃንን መግደሉንና በርካታ ውድመት ማድረሱን የተናገሩ ሲሆን ሀገር መከላከያ ሰራዊት ወደከተማቸው ሲገባ አቀባበል አድርገዋል።

በሀገር መከላከያ ሰራዊት የሰሜን ምዕራብ ዕዝ አንደኛ ኮር አዛዥ ብርጋዴር ጄነራል ብርሃኑ ጥላሁን ፤ ከሰሞኑን ህወሓት ህዝቡን በጣም እንደጎዳው ፤ የቀረ ነገር ሳይኖር ዘርፊያ እንደፈፀመ ገልፀው ፥ "ህዝባችን እንዲህ ያለ ወራዳ ተግባር ማየቱ የሚያሳዝን ነው፤ ነገር ግን አሁን ላይ ቡድኑ ዋጋውን እያገኘ ነው" ብለዋል።
ብርጋዴር ጄነራል ብርሃኑ ጥላሁን ፥ ህወሓት በወረራ የያዛቸውን ቦታዎች በሙሉ የማስለቀቅ እና የማፅዳት ስራ እየተሰራ ነው ያሉ ሲሆን አሁን ላይ ከመኪና ወርዶ እየተበታተነ ነው እሱን የመልቀም ስራ እየተሰራ ነው፤ የሚሸሽበትም መንገድ ተዘግቷል፤ ትግራይ ውስጥ ያየውን ጉድ እዚህም ያየዋል፤ እዚህ ገብቶ መውጣት የሚባል ነገር እንደሌለ ያየዋል" ብለዋል።
አዛዡ ፤ ህወሃት ስርዓት መቀየር ነው ፍላጎቴ ይላል እንጂ ተግባሩ ሀገር ማፍረስ እና ሀገር ማውደም ነው ፣ ኢትዮጵያን ማፍረስ ነው የማፍረስ ምልክቱም ህዝቡን ምን እያረገው እንዳለ ማየት በቂ ነው ፤ የከተማውን ህዝብ ጠይቁ ምን አድርጓቸው እንደሄደ ፤ እነሱ የስርዓት አራማጅ አይደሉም ፤ ድሆች ናቸው ፤ ከድሆቹ አፍ ነጥቆ ሽሮ ሳይቀር እየጫነ እየወሰደ ያለው" ሲሉ አስረድተዋል።

"በአጠቃላይ ቡድኑ ስርዓት መቀየር ብቻ ሳይሆን ሀገር ማጥፋት ስለሆነ በዚህ ሀገር አጥፊ ኃይል ላይ ማንም ትዕግስት ሊኖረው አይገባም ኢትዮጵያን ወዳታለሁ የሚል ሁሉ መሰለፍ አለበት" ብለዋል። ይህ ደግሞ ለማንም ሳይሆን እራስን እና ሀገርን ለመከላከል እና ሀገርን ለማዳን ነው" ሲሉ ተናግረዋል።
©Natnael Mekonen

Показано 20 последних публикаций.

2 431

подписчиков
Статистика канала