እንኳን ለመጋቢት ወር ዜና ገዳማት መርሐግብር አደረሳችሁ ፡፡ በወሩ የመጀመሪያው ቀን ነገ መጋቢት 1 የወሩ የመጀመሪያው ማክሰኞ ወርኃዊ የዜና ገዳማት መርሐግብራችን መሰናዶዋን አጠናቃ ትጠብቃችኋለች፡፡ በ2 ትልልቅ ገዳማት ሊቃነ ጳጳሳት የተገኙበት የገዳማውያ አባቶች የልምድ ልውውጥ መርሐግብር፣ ወደ ታላቁ ገዳም ዲማ ቅዱስ ጊዮርጊስ የተደረገ ፍኖተ ገዳማት ጉዞ ፣የታላቁ ገዳም የደብረሊባኖስ ደቀ መዛሙርት ምርቃት በዜና ገዳማት ይዳሰሳሉ ፡፡ የዐቢየእግዚእ ኪዳነምህረት የመጻሕፍተ ብሉያት ት/ቤት በትኩረት አቅጣጫ ይቀርባል፡፡ የማኅበረ ቅዱሳን የበገና ዘማርያን ታላቁን የዐቢይ ጾም በማስመለከት የበገና ዝማሬ ያቀርባሉ ፣ በሊቃውንተ ቤተክርስቲያን ትምህርት ይሰጣል፡፡መጋቢት 1 ማክሰኞ 11፡30 -1፡30 በማኅበረ ቅዱሳን ህንጻ 3ኛ ፎቅ ተጋብዘዋል፡፡ ለሌሎችም መልእክቱን በማጋራት የመርሐግብሩ ተሳታፊ እንዲሆኑ ኃላፊነትዎን ይወጡ፡፡ ሃሳብና አስተያየትዎን በ @zenagedam ይላኩልን፡፡