🙏ኦርቶዶክሳዊ ዝማሬ🙏


Гео и язык канала: Эфиопия, Амхарский
Категория: Эзотерика


ገና እንዘምራለን እንደ መላእክቱ
ብርሃንን ለብሰን ገና እንዘምራለን
የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክርሰቲያን አሰተምሮ ና ሰርአት የጠበቁ
✥👉መንፈሳዊ ትምህርቶች
✥👉መንፈሳዊ መዝሙሮች
✥👉መንፈሳዊ ንግሰ እናሳዉቃለን
✥👉መንፈሳዊ ምክር ነክ ፁሁፍ
✥👉መንፈሳዊ ታሪኮች
ለማስታወቂያ ሥራ👉 @mane_tekel21

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Гео и язык канала
Эфиопия, Амхарский
Категория
Эзотерика
Статистика
Фильтр публикаций


✞ በመከራ ጽና ✞

በመከራ ጽና በመከራ ጽና በፈተና ጽና
ለጊዜው ነው እንጂ ሁሉም ያልፋልና /፪/


              አዝ ========

ኢዮብ ተጨነቀ በጣም ተማረረ
በመከራው ብዛት ትዕግስትን ተማረ
ልጅ የሌለው ሆነ እጣንብረቱን
በመከራ ጸና አልካደም አምላኩን

              አዝ ========

መፈተን መልካም ነው ያነጣል እንደወርቅ
በመጨረሻው ቀን በክብር እንደትደምቅ
አንዱን ሳትሻገር ሌላው ቢገጥም
በሕይወት ዘመንህ መከራው ያንተው ነው

              አዝ ========

ከአምላክህ ተስማማ እራስህን አዋርድ
በቃሉ ተመራ እንደፈቃዱ ሂድ
ዋጋህ ከአምላክ ዘንድ በሠማይ አለና
በርታ ክርስቲያን ሆይ በመከራ ጽና

ዘማሪት ፋሲካ መኮንን

✝️ከወደዱት✝️ሼር ያድርጉት↗️

✨✨✨✨✨✨✨
✝️#ኦርቶዶክሳዊ_ዝማሬ✝️
✨✨✨✨✨✨✨


👏ከሰው_ጋር_ሳይሆን_ከፈጣሪ
               
#ጋር_ሂድ   
       
🏃‍➡️ ከሰዎች ጋር ሮጠህ ያልደረስክበት ነገር ካለ ወደ ተነሳህበት ተመልሰህ ከፈጣሪህ ጋር መሮጥ ጀምር፣ ያኔ ካሰብክበት ሳይሆን ካሰበልህ ቦታ ትደርሳለህ፡፡

✝️ከወደዱት✝️ሼር ያድርት↗️

✨✨✨✨✨✨✨
✝️#ኦርቶዶክሳዊ_ዝማሬ✝️
✨✨✨✨✨✨✨


Репост из: 🎤✨ድምፀ ተዋህዶ✨🎤
የምስራች ከሀገር ውጪ ለምትኖሩ!

የግእዝ (የአብነት) ትምህርት በስልኮ መጣሎት።


ማንኛውም ምዕመን ውዳሴ ማርያምና መዝሙረ ዳዊትን መጸለይ እንደሚገባው ያውቃሉ ?

በተጨማሪም ገድላትን ለማንበብ ወይም ጸሎትዎን 
#በልሳነ_ግዕዝ ለማድረግ ከፈለጉ  የግድ #ንባብ መማር ያስፈልግዎታል።

ከሀገር ውጪ እየኖሩ ማንኛውንም
#የንባብ_ትምህርት#ቅኔ  እንዲሁም #ቅዳሴ በቀላሉ መማር ከፈለጉ ያግኙን።

በጉባኤም ኾነ በግል ሰዓት ይዘን እናስተምራለን።

ስልክ +251934104451
Tg @lealem16


የምንሰጣቼው ትምህርቶች በጥቂቱ፦
፩) ንባብ ቤት

ሀ) የቃል ትምህርት በሙሉ (ከጸሎት ዘዘወትር እስከ መልክአ ኢየሱስ)

ለ) ምንባብ  (ወንጌለ ዮሐንስና መዝሙረ ዳዊት፣ በተጨማሪም ስንክሳርን ጨምሮ ገድላትና ድርሳናት እንዲሁም ሐዲስ ኪዳን ብሉይ ኪዳን ንባብ)

፪) ቅኔ ቤት
ቅኔ ነገራ፣ ቅኔ ዘረፋ፣ ግስ፣ አገባብ...

፫) ቅዳሴ ቤት
ግብረ ዲቁና፣ ፲፬ቱ ቅዳሴያት፣ ሰዓታት


ለበለጠ መረጃ፦
ቻናላችንን ይቀላቀሉ።
@beteyared21
@beteyared21
@beteyared21


✞ ቸር_አገልጋይ_ማነው

ቸር አገልጋይ ማነው ለንጉስ የታመነ
መክሊቱን ያልቀበረ አትርፎ የከበረ


ባለ አምስቱ መክሊት መልካም ያደረገው
በመውጣት በመውረድ አትርፎ መጥቶ ነው
በጥቂቱ ታምኖ በብዙ የተሾመው
ባለ አምስቱ መክሊት ሊቀ ጳጳሱ ነው
      
አዝ----------------

ሣይሠለች የተጋ ባለሁለት መክሊት
የታመነ እረኛ በፍቅር እና በእምነት
ግባ የተባለው ወደ ጌታው ደስታ
አጥምቆ ያቆርባል ካህኑ የጌታ
      
አዝ----------------

ለሚበልጠው ፀጋ ተጠርቶ የነበረ
መክሊቱን ደብቆ ቆፍሮ የቀበረ
ሰነፍ ባሪያ ተብሎ ወደ ፍርድ ተጣለ
ማኔ ቴቄል ፋሬስ በአምላክ ፊት ቀለለ
      
አዝ----------------

ፈቃድህን ማድረግ ነፍሱ ለምትወደው
ወንጌልህን መግለፅ የየዕለት ግብሩ ነው
ህግህ ለዘለዓለም ተፅፎ ይኖራል
በታላቅ ጉባኤ ፅድቅህ ይነገራል

                  ዘማሪ
         ዲያቆን ቀዳሚ_ጸጋ


✝️ለባለ ማህተቦች✝️ሼር ያድርጉ↗️

✨✨✨✨✨✨✨
✝️#ኦርቶዶክሳዊ_ዝማሬ✝️
✨✨✨✨✨✨✨


ቅዱሳኑን ያዳነ ቅዱስ መልአክ እኛንም ያድነን ዘንድ እንደ አባቶቻችን "አድኅነኒ ዘአድኃንኮሙ በአክናፊከ ምንትው:: አመ ውስተ እሳት ተወድዩ ሠለስቱ እደው::" እያልን እንለምነው::

     (መልክዐ ገብርኤል)

"በአምላኬም በእግዚአብሔር ፊት ስለ ተቀደሰው ስለ አምላኬ ተራራ ስለምን: ገናም በጸሎት ስናገር አስቀድሜ በራእይ አይቼው የነበረው ሰው ገብርኤል እነሆ እየበረረ መጣ:: በማታም መሥዋዕት ጊዜ ዳሰሰኝ:: አስተማረኝም ." †

       (ዳን. ፱፥፳)

† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †

#አቤቱ የሆነብንን አስብ

#አቤቱ ህዝብህን አድን ርስትህንም ባርክ ጌታ ሆይ ማራቸው  ከፍ  ከፍ አድርጋቸው።

7.9k 1 12 1 149

 #ሰላም_ለኪ ✝️መልክአ ኪዳነ ምህረት ✝️

✝️እመቤቴ ኪዳነ ምሕረት ሆይ፤ እንደ ቃል ኪዳንሽ ምስጋናሽ የሚነገርበትን ቤተ ክርስቲያን በስምሽ ያሳነፀውን መታሰቢያሽን ያደረገውን በስምሽ የጸለየውን ከበረከትሽ ታሳትፊውና ይቅር ባይ ከሚሆን ልጅሽ ይቅርታን ታሰጭው ዘንድ ሰላም እያልኩ ከፊትሽ ወድቄ በቃል ኪዳንሽ እማፀንሻለሁ፡፡

   ✝️እመቤቴ_ማርያም_ሆይ፤ በክፉ ሰዎች እጅ ከመውደቅ በቃል ኪዳንሽ ጠብቂኝ፡፡ በልዩ ጠላት በዲያብሎስ ወይም በሰይጣን ኃይል ተይዞ ከመቀጥቀጥ በእግረ አጋንንት ከመረገጥና ከመጠቅጠቅ አድኚኝ ለዘላለሙ አሜን🤲


✝️ለባለ ማህተቦች✝️ሼር ያድርጉ↗️
✨✨✨✨✨✨✨
✝️#ኦርቶዶክሳዊ_ዝማሬ✝️
✨✨✨✨✨✨✨


​​📣ነገ ወር በገባ በ 13 መልአኩ ቅዱስ ሩፋኤል ነው 📣

📣 ትርጉሙ እንዲህ ነው ፣ በልሳነ ዕብራይስጥ ሩፋ ማለት ጤና ፣ ፈውስ ፣ መድሃኒት ሲሆን ኤል ማለት ደሞ አምላክ ፣ እግዚአብሔር ማለትነው።
♨️አምጻኤ ዓለማት እግዚአ መላዕክት እግዚአብሔር በነገደ መላዕክት አለቆች ይኾኑ ሰብዓቱን ሹሟል ። ቅዱስ ሩፋኤልን ከሊቃነ ነገደ መላዕክት ቅዱስ ሚካኤልና ቅዱስ ገብርኤል በመቀጠል በማዕርግ ሶስተኛ ኾኖ የተሾመው  ሊቀመላዕክት ነው ፣ ዮሃንስ ወንጌላዊ ቀደም ብሎ ተናግረዋል እንዲህ ይላል ርኢኩ ሰብዓተ መላዕክተ እለ ይቀውሙ ቅድመ እግዚአብሔር ራእ 8:21 ቅዱስ ሩፋኤል የሴቶችን ማህጸን ይፈታ ዘንድ ሥልጣን ተሰጥቶታል ። መላኩ ሩፋኤል በ 23 ነገደ መላዕክት መናብርት ተብለው የሚጠሩት የተሾመው ብርሃናዊ መላክ ነው ። የነገድ ስማቸውን እንዲህ ነው ፣ አጋእዝት ፣ ሓይላት ፣ ሥልጣናት ፣ ሊቃናትና መናብርት ፣ መኳንንትና አርባብና ፣ ኪሩቤልና ሱራፌል አዕላፍም ፣ ድርገታትም ተብለው ይታወቃሉ ። አለቆቻቸውም ዓስር ናቸው ። እሊኽም፣ ቅዱስ ሚካኤል ፣ ቅዱስ ገብርኤል ፣ ቅዱስ ሩፋኤል ፣ ቅዱስ ፋኑኤል ፣ ቅዱስ ራጉኤል ፣ ቅዱስ ኡራኤል ፣ ቅዱስ ሱርያል ፣ ቅዱስ ሰዳክያል ፣ ቅዱስ ሰላትያል ፣ ቅዱስ አናንኤል ናቸው ።

✝️እሊኽ ነገደ መላዕክትም ለዘለዓለም በሰማያት ሕያዋን ኹነው ይኖሩ ዘንድ እግዚአብሔር ወሰናቸው ። ነገር ግን እግዚአብሔር ግን በጠራቸው ግዜ ፈቃዱን ለመፈጸም እሊኽ መላዕክት እስከ ጽርሃ አርያም ይወጣሉ ። በላካችውም ግዜ የፍጥረተ ሁሉ ወሰን እስከኾነችው ጨላማይቱ የባርባሮስ ሥፍራ ድረስ ይወርዳሉ ። ተመልሰውም ብቻውን የነበረው ያለና የሚኖር በአገዛዝ ላይም ሁሉ ሥልጣን ያለው እርሱን ከማመስገን በቀር በሽታም ሞትም ቢሆን ሓዘንም ቢሆን ወደሌለባቸው ቦታቸው ይገባሉ ። እግዚአብሔር ከሊቃነ መላዕክት ሩፋኤል ሠራዊት መርጦ በመንበሩ ዙርያ አቆማቸው ፣ ከእሳት ወርቅ የተሰራ ጽናዎችምና የሚያንጸባርቅ የብርሃን አክሊል አንጓቸው ብርሃን የሆነ ዘንግንም ሰጣቸው ።

መልኩ መብረቅ የሆነ የክህነት ልብስን አለበሳቸው ። ከማዕጠንታቸውም ምስጋና የተሞላ መዓዛውም ደስ የሚያሰኝ ዕጣን ይወጣል ፣ እግዚአብሔርም በማዕጠንታችሁ የቅዱሳን ሁሉ ጸሎት ወደኔ ይቀርብ ዘንድ ይደረግላችሁ አላቸው ። አዎ ወደ ፈጣሪያቸውን እግዚአብሔርም ሳያቋርጡ ዘወትር ስለሰው ልጆች ይለምናሉ ፣ በሰማያት የሚኖር የአብም ገጽ  ዘወትር ያያሉ ፣ ንስሐ ስለሚገባው አንድ ሓጥእም በእግዚአብሔር መላዕክት ታላቅ ደስታ ይደረጋል ፣ እግዚአብሔር ቅዱሳን መላዕክት ሁሉ ስለዚህ ነገር ፈጥራችኋል ። አዎ ከእግዚአብሔር በስተቀር የመላዕክትን ተፈጥሮ የሚያውቅ ማንም ማንም የለም ። ኩፋሌ 2:7
ቅዱስ ሩፋኤል ቅዱሳን ጻድቃን በገድላቸውም የሚረዳቸው ፣ የምያጽናናቸው ፣ የሚደግፋቸው እርሱ ነው ፣ ፈታሄ ማህጸን ፣ ዐቃቤ ሆህት ፣ ሰዳዴ አጋንንት ፣ ከሣቴ ዕውራን ፣ ፈዋሴ ዱያን ተብሎ በመሆኑ ይታወቃል ።
ሄኖክ 6:3 ዘፍ 3:24

✝️የቅዱስ ሩፋኤል በረከት ፣ የዕልፍ አዕላፍ ነገደ መላዕክት ረድኤት ፣ አማላጅነት ፣ የእግዚአብሄር በጎ ቸርነትና  ምህረት ዛሬም ዘወትርም ከኛ ጋር ይሁን

✝️ለባለ ማህተቦች✝️ሼር ያድርጉ↗️

✨✨✨✨✨✨✨
✝️#ኦርቶዶክሳዊ_ዝማሬ✝️
✨✨✨✨✨✨✨


✝️የኔ መሃሪ ✝️

የኔ መሀሪ ሁሉን መርሻዬ
ሁሉን መርሻዬ
እንደ ህልም አልፏል ትናንትናዬ
ባንተ ጌታዬ...(2)

አዝ.....
      አዳፋው ልብሴ ከነፃ
      ከእዳ ከፈታኝ በነፃ
      የፅድቁ ባሪያው ሆኛለው
      ሳገለግለው ኖራለው።
                የእንባ ዘለላን ያቀፈው
                አይኔም እልልታ ተረፈው
                ደልዳዩ መዳፍ ደርሶሎኝ
                ተራራው ሜዳ ሆነልኝ።
አዝ.....
     አይኖቼን ከጉድ ጋርዶልኝ
     ክንዶቼን በእጁ ይዞልኝ
     ከእግሬ በታች ነው ወጀቡ
     አሁን ታይቶኛል ወደቡ።
                   ሰላም ይነፍሳል ዙሪያዬ
                   እረፍት ሆኖልኝ ጌታዬ
                   የባረከኝን ባርኬ
                   ተለወጠልኝ ታሪኬ።
አዝ.....
   ብርሃንህ ገፏል ድቅድቁን
   በልቤ ተክሏል ሰንደቁን
   ተቆጣጥሮኛል መውደዱ
   መንገዴ ሆኗል መንገዱ።
                    ያበቃው ነገር ቀጥሏል
                   ጭንቄ በሞቱ ተሰቅሏል
                    የእየሱስ ሆኜ ምን አጣሁ
                    ሁሉን በስሙ ተወጣሁ።
አዝ.....
       እንደኔ ማንን ታግሷል
       ይቅርታ ፍቅሩን አልብሷል
      ማይገባኝን አድርጎ
       ያሳለፈልኝ ሸሽጎ።
               መልካም ነው ለኔስ መልካም
               ፀጋው ያገዘኝ ስደክም
               ሞትኩኝ ስል ምህረት ደርቦ
               አቆመኝ በህይወት አስዉቦ።

ዘማሪ ገ/አምላክህ ደሳለኝ

✝️ለባለ ማህተቦች✝️ሼር ያድርጉ↗️

✨✨✨✨✨✨✨
✝️#ኦርቶዶክሳዊ_ዝማሬ✝️
✨✨✨✨✨✨✨


‼️‼️‼️‼️‼️‼️‼️‼️‼️
ሁሉም ክርስቲያን ፖስት ያድርገው አሁኑኑ 
እዚህ page ላይ የምትገቡ ሁሉ ይህንን ሳታዮ እንዳታልፉ!!

‼️‼️‼️‼️‼️‼️‼️‼️‼️

በምስሉ ላይ የምትመለከቱት ግለሰብ በቲክቶክ ስሙ ሳላህ በትክክለኛው ስሙ ቶፊቅ በመባል የሚታወቅ ሲሆን ቪዲዮ ላይ እንዳያችሁት ከሆነ በመጽሐፍ ነው ያለማስረጃ አናወራም የክርስትናን መጽሐፍ እኛ እናውቅላችዃለን በማለት መጽሐፍቶቻችንን እና አስተምህሮታችንን በመዘባበት  ፈጣሪያችንን በመሳደብ ለፈጣሪያችን የማይገባ ከአስተምህሮታችን ውጪ የሆነ አፀያፊ ቃልን በማድረግ ተማሪዎችን የሚያሰለጥኑ ኡስታዞች በፈለግ በመከተል እንግዲ በዚህ መልኩ ለኃልዎተ እግዚአብሔር በማይገባ በማይመጥን አማርኛ ቃል በመሰንጠቅ እና በማጣመም ሲሳለቅ ሲሳደብ የሚያሳይ አሳዛኝ ምስል ነው።

በጣም የማዝነው ከሚመለከታቸው አካላት ዝምታ ብቻ ሳይሆን ህዝቡ በፍቅር አክብሮ ወደ ዝና ማማ ያወጣቸው ግለሰቦች ናቸው።

የሚሰደበው ፈጣሪያችሁ አይደለምን ⁉️

ካለመኖር ወደ መኖር አምጥቶ እድሜ ጤና ሰጥቶ የሰው ፍቅር እና መውደድን ጨምሮ ጨማምሮ በነገራችሁ ሁሉ ያልተለየ አምላካችሁ በአደባባይ መሳለቂ ሲሆን እያያችሁ እንዴትስ ልባችሁ እሺ አለ⁉️

እንዴትስ አእምሮቹ ፈቀደ⁉️

“ከጥፊው በላይ የወዳጄ ዝምታ ልቤን አደማው “ አለ ባለቅኔው።

😭😭😭😭😭😔😔😔😔😔
እፎይ እና ጰልድዮስ እውነት አላቸው

@Efoyewnetalew
@Efoyewnetalew

#ድምፀ_ተዋህዶ
#ኦርቶዶክሳዊ_ዝማሬ


Видео недоступно для предпросмотра
Смотреть в Telegram
በጣም አስደንጋጭ መረጃ አስቸኳይ መረጃ ‼️


ይድረስ ለጠቅላይ ቤተ ክህነት ይድረስ ለማህበረ ቅዱሳ ይድረስ ለሰንበት ትምህርት ቤት ማዳረጃ እና መምሪያ።

እስከመቼ ዝምታ ነገሩ ከእቅበት እምነት ሳይሆን በቤተክርስቲያናችን በሀገረ እና በዘር ላይ ያነጣጠረ ጭፍን ጥላቻ ሲሰበክ በአደባባይ እንዴት ዝም ይባላል?

አሁንም እንደዚህ አይነት ዘርን እና ሃይማኖትን ያነጣጠረ ጠብ እና አመጽ ቀስቃሽ አደገኛ የሆነ መልእክት እየተላለፈ አሁን ሁሉም የሚመለከት አካላት ይድረስልን ይህ በማሕበረሰባችን ያለውን ትስስር አደጋ ላይ የሚጥል ጸያፍ እና አስደንጋጭ የሆነ መልእክት ልትቃወሙት ይገባል። በሃይማኖት ሰበብ የጥላቻን እና የህዝብን ሉዐላዊነት አደጋ ላይ የሚጋርጥ መልእክት የምታዮት ሰዎች በሙሉ ይህ የቤተ ክርስቲያን ጉዳይ በሀገራችነ‍እ ሉዓላዊነት ለዘመናት ተከባብረው ዜጎች የሚኖሩባት ሀገረን አደጋ ላይ የሚጥ አፀያፊ ጽንፈኛ አስተሳሰብነ‍እ ሁሉም የሃይማኖት አባቶች ሁሉም የእምነት ተቋማት እና የህግና የመንግስት አካላት ልታወግዙ እና ልታስቆሙ ይገባል ።

ስለዚህ ይህንን መልእክት የምታዩት ቢያንስ ለ20 ሰው ሼር በማረግ ለመንግስት እና የህግ አካላት ተጨማሪም ሀይማኖቶች ጉባኤ እንድታደርሱልን ስንል እንጠይቃለን !!!

እፎይ እና ጰልድዮስ እውነት አላቸው።
ትክለኛ የቴሌግራም ቻናላቸው ነው ተቀላቀል አንተ ባለማህተብ ክርስቲያን የሆንክ
👇👇👇👇
@Efoyewnetalew
@Efoyewnetalew

#ኦርቶዶክሳዊ_ዝማሬ


ወንድማችን እፎይ የ63+ ሚሊዮን ኦርቶዶክሳዊያን አደራ ነው ይህ ይሰመርበት !!

ጌታ ኢየሱስ ይጠብቀው ጸልዩለት፣ ብዙኀናችን አብሮነታችንን እናሳየው !!


✝️ለባለ ማህተቦች✝️ሼር ያድርጉ↗️

✨✨✨✨✨✨✨
✝️#ኦርቶዶክሳዊ_ዝማሬ✝️
✨✨✨✨✨✨✨


➖ይሁዳ ክርስቶስን አንድ ቀን ፫ ጊዜ ብቻ ካደው።➖

እኔ የዘመኑ ይሁዳ ግን ስንት ጊዜ ካድኩት ? ስንት ግዜ አሳልፌ ሰጠሁት ? ስንት ግዜ በንዋይ ቀየርኩት?

አላውቅህም ብዬ በሰው ፊት የምክድህ እኔ በደምምህ የዋጀኸኝ ብላቴና ነኝ።
ወደ ቤትህ መልሰኝ የደነደነህ ልቤን መልስልኝ፤ ይቅር በለኝ።

✝️ለባለ ማህተቦች✝️ሼር ያድርጉ↗️

✨✨✨✨✨✨✨
✝️#ኦርቶዶክሳዊ_ዝማሬ✝️
✨✨✨✨✨✨✨


❓በዐብይ ጾም ፫ኛ ሳምንት ስያሜ ምን ይባላል❓
Опрос
  •   ደብረዘይት
  •   ምኩራብ
  •   ኒቆዲሞስ
  •   መፃጉ
3237 голосов


☦️አቤት የዚያን ጊዜ☦️

አቤት የዚያን ጊዜ ክርስቶስ ሲመጣ (፪)
ትንሹም ትልቁም (፫) መድረሻውን ሲያጣ


ከምስራቅ ከምዕራብ ከሰሜን ከደቡብ (፪)
አየራት/መላእክት/ ሲላኩ (፫) መአትን ለማዝነብ፤
ሰማይና ምድር በአንድ ሲዋሐዱ (፪)
የት ይሆን መድረሻው(፫) የት ይሆን መንገዱ
      አዝ= = = = =
ጻድቃን በቀኝ በኩል ኃጥአን በግራ (፪)
ሲነፋ መለከት (፫) ሲደለቅም ዕንዚራ
ምድር ቀውጢ ስትሆን አጽም ሲሰበሰብ (፪)
ሐፍረት ይይዘዋል (፫) ሰው ለፍርድ ሲቀርብ
     አዝ= = = = =
ጩኸት ሲበረታ የማይጠቅም ለቅሶ (፪)
እንደ ቍራ ጠቁሮ(፫) ጽልመትን ተላብሶ
ገነትን ሲያገኙ ጻድቃን በስራቸው (፪)
ኃጥአን ወደ ሲኦል(፫) ተፈረደባቸው።

            መዝሙር
   ኪነጥበብ ወልደቂርቆስ


"አምላካችን ይመጣል ዝምም አይልም፤ እሳት በፊት ይቃጠላል"
             መዝ ፶፥፫


✝️ለባለ ማህተቦች✝️ሼር ያድርጉ↗️

✨✨✨✨✨✨✨
✝️#ኦርቶዶክሳዊ_ዝማሬ✝️
✨✨✨✨✨✨✨


🗓የምጽዋት ብዛት

የምጽዋት ብዛት የሚመዘነው በሚሰ’ጠው ገንዘብ ቁጥር ሳይኾን ስጦታውን በሚሰጥ የልብ ስፋት ነው፡፡ አንዲት ድኻ ሴት ያላትን ጥቂት እንጀራ ምንም ከሌላት ከሌላ ሴት ጋር ተካፍላ የምትበላ ከኾነ፥ ወርቅን በሙዳዬ ምጽዋት ከሚጨምር ባለጸጋ ሰው እጅግ ትበልጣለች፡፡

ነገር ግን ምንም እንኳን ይህ እውነት እንደ ኾነ ብዙ ክርስቲያኖች ቢያውቁም፥ ምስጋና የሚሰጡት ወርቅ ለሰጠው ነው፡፡

☦️☦️☦️☦️☦️☦️☦️
አንድ ባለጸጋ ጠቀም ያለ ገንዘብ ለቤተ ክርስቲያን ቢሰጥ እጅግ ያመሰግኑታል፤ ካለው የሀብት ብዛት የተነሣ ያንን በመስጠቱ ምንም ባይጎድልበትም እንኳ፥ በሰዎች ዘንድ እጅግ ቸር እንደ ኾነ ተደርጎ ይንቆለጳጰሳል፡፡ ድኻው ጥቂት ገንዘብ ቢሰጥ ግን ሰዎች ስለ እርሱ ምንም ትንፍሽ አይሉም፡፡ ምናልባት ያቺ የሰጣት ገንዘብ’ኮ በኋላ እርስዋን በማጣቱ ምክንያት ተርቦ እንዲያድር ልታደርገው የምትችል ትኾን ይኾናል፤ ነገር ግን ይህን በማድረጉ የሚያመሰግነው አንድ ሰውስ እንኳ አይገኝም፡፡ በእውነት ያለ ሐሰት ምንም ሳይጎድልበት የሰጠውን ባለጸጋውን አመስግኖ ያለውን ኹሉ የሰጠውን ድኻ ሳያመሰግኑ ከሚቀሩ ከእነ ጭራሹ ምስጋና ባይኖር ይሻል ነበር፡፡

ስለዚህ እውነተኛ ምጽዋት የሚባለው የባለጸጋውም ይኹን የድኻው በአግባቡና በሥርዓቱ ልናውቀው ይገባናል፡፡ ማመስገን የሚገባንም ከዚያ በኋላ ነው፡፡ በሌላ አነጋገር የምስጋናችን ስጦታም ሰዎች ከልባቸው ከሚሰጡት ገንዘብ ብዛት አንጻር ሊኾን ይገባል፡፡

ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ:

✝️ለባለ ማህተቦች✝️ሼር ያድርጉ↗️

✨✨✨✨✨✨✨
✝️#ኦርቶዶክሳዊ_ዝማሬ✝️
✨✨✨✨✨✨✨


በጌቴ ሰማኔ

በጌቴ ሴማኔ በአታክልቱ ቦታ 2×
ለኛ ሲል ጌታችን (በአለም ተንገላታ 2×

አዳምና ሔዋን ባጠፉት ጥፋት 2×
እኛም ነበረብን(የዘላለም ሞት 2×

መስቀል ተሸክሞ ሲወጣ ተራራ(2×
ይገርፉት ነበረ (ሁሉም በየተራ(2×

ድንግል አልቻለችም እንባዋን ልትገታ(2×
እያየች በመስቀል( ልጇ ሲንገላታ( 2×

በአምላክነቱ ሳይፈርድባቸው(2×
እንዲ ሲል ፀለየ (አባት ሆይ ማራቸው(2×

በረቂቅ ስልጣኑ ሁሉን የፈጠረ
በረቂቅ ጥበቡ ሁሉን የፈጠረ
በሰው እጅ ተገሎ( ሞተ ተቀበረ(2×

ፍቅሩን የገለፀው ተወልዶ በስጋ(2×
ኢየሱስ ጌታ ነው (አልፋና ኦሜጋ(2×

በመስቀል ተሰቅሎ እንዲያ እየቃተተ(2×
አለምን ለማዳን (የማይሞተው ሞተ(2×

ከሞት ሊታደገን በመጣልን ፈጥኖ(2×
መስቀል አሸከሙት( ውለታው ይህ ሆኖ(2×

መከራውን ሳስብ ሳስታውስ ቀኑን(2×
ይቆስላል ይደማል (ልቤ በሀዘኔ(2×

መች ለራሱ ነበር ይህ ሁሉ መከራ(2×
መስቀል ተሸክሞ( የወጣ ተራራ(2×

ሲያጎሩሱት ሚናከስ ሰው ክፉ ነውና
እውሩን ቢያበራ ጎባጣን ቢያቀና
ጌታዬን ሰቀሉት (አይሁድ ጨከኑና(2×

ምነው አያሳዝን የአይሁድ ክፋት (2×
የዝናቡን ጌታ( ውሀ ሲነፍጉት(2×

በተንኮል በሀጢአት ቀሩ እንደሰከሩ(2×
ሙታን ከመቃብር( ተነስተው ሲያስተምሩ(2×

እናታችን ሔዋን ወየው በይ አልቅሺ
የአንቺን ህመም ታሞ ከሞት ሊያድንሺ
የህያዋን ጌታ (ተሰቀለልሽ(2×

አዬ ጉድ አዬ ጉድ አለም የኋላሽ(2×
መዳኒት ክርስቶስ (በግፍ ሞተብሽ(2×

በመስቀል ተሰቅሎ ስጋውን ሲቆርስ
በችንካር ተወግቶ ደሙንም ሲያፈስ
ዋለች በመከራ ድንግል ስታለቅስ
                    እናት ስታለቅስ

ሰውነትሽ ራደ ሀዘን ከበበሽ
ስቃይ ከመከራውም ዳግም ፀናብሽ
ተሰቅሎ ስታይው (አንድ አምላክ ልጅሽ (2×

ቢፈስም እንባዬ ሆኖ መንታ መንታ
መች ዋጋ ይሆናል ለአንዲቱ ጠብታ
ላለቀሽው ለቅሶ (ድንግል የዛ ለታ(2×

ባለቅስሽው ለቅሶ በልጅሽ ህመም (2×
ከሀጢያት ነፃሁኝ ዳንኩኝ ከገሃነም(2×

✝️ለባለ ማህተቦች✝️ሼር ያድርጉ↗️

✨✨✨✨✨✨✨
✝️#ኦርቶዶክሳዊ_ዝማሬ✝️
✨✨✨✨✨✨✨


✝️ጾም የተቀደሰ የእግዚአብሔር መንገድ መጀመሪያ ነው እና የመልካም ምግባራት አጋር ነው። ጾም በመንፈሳዊ ጦርነቱ መጀመሪያ ላይ በጎነትን ይመራል እና ንፅህናን ይጠብቃል። ጾም የጸሎት አባት፣ የመረጋጋት ምንጭ፣ የዝምታ አስተማሪ፣ የአዕምሮ ብርሃን ነው። የአንደበት ጾም ከአፍ ጾም ይሻላል፣ የልብም ጾም ከሁለቱም ይበልጣል። ከኃጢአትና ከምኞቱ ጋር የሚደረግ ትግል ሁሉ መጀመሪያ በጾም መጀመር አለበት። ልክ እንደ ጋለሞታ ስለ ንጽህና እንደምትናገር ወይም ሰውነታቸውን ሲወድ መንፈሳዊ ጉዳዮችን ሲፈልግ ነው።


[ቅዱስ ይስሐቅ ሶርያዊ]
መልካም የጾም ሳምንት ይኹንላችሁ!

✝️ለባለ ማህተቦች✝️ሼር ያድርጉ↗️

✨✨✨✨✨✨✨
✝️#ኦርቶዶክሳዊ_ዝማሬ✝️
✨✨✨✨✨✨✨


በአብይ ፆም የመጀመሪያው ሳምንት እስከ ስንት ሰዓት መጾም ይጠበቅብናል❓(ኢትዮጲያ አቆጣጠር)
Опрос
  •   ሀ. እስከ ፱ ሰአት
  •   ለ. እስከ ፲፪ ሰአት
  •   ሐ. እስከ ፲፩ ሰአት
  •   መ. እስከ ፩ ሰአት
2598 голосов


✝️​​ተመከር ሰው ሆይ

ተመከር ሰው ሆይ ተመከር
እባክህ ተመከር (፪)
የዛሬ አበባ የነገው አፈር(፪)


መላ ሰውነትህን አስገዛ ለእግዚአብሔር



ተመከር ሰው ሆይ ተመከር
እባክህ ተመከር (፪)
የዛሬ አበባ የነገው አፈር (፪)


እጅና እግርህ ታስሮ ሳትወርድ ወደ መቃብር

ተመከር ሰው ሆይ ተመከር
እባክህ ተመከር (፪)
የዛሬ አበባ የነገው አፈር (፪)


ተሰብከዋል እና በዓለም ቅዱሳት መጻህፍት ለአንተ ለመመስከር

ተመከር ሰው ሆይ ተመከር 
እባክህ ተመከር (፪)
የዛሬ አበባ የነገው አፈር (፪)


የእግዚአብሔር ሕጉን በአንዱ ጆሮ ሰምተህ በአንዱ ማፍሰስ ይቅር

ተመከር ሰው ሆይ ተመከር
እባክህ ተመከር (፪)
የዛሬ አበባ የነገው አፈር(፪)


                 መዝሙር
                ቀሲስ አበበ


✝️ለባለ ማህተቦች✝️ሼር ያድርጉ↗️

✨✨✨✨✨✨✨
✝️#ኦርቶዶክሳዊ_ዝማሬ✝️
✨✨✨✨✨✨✨

          


አትቁረጡ_ተስፋ 

አትቁረጡ ተስፋ የእግዚአብሔር ልጆቹ/2
ከናንተ አይለዩም የፍቅር አይኖቹ/2/
ምድርና መላዋ ናት እና የእግዚአብሔር
በሰማያት አለ በቀላይ በባህር

በጥልቁ እንኳን ቢሆን ከናንተ ጋራ ነው
ወገኖቼ አትስጉ ሰልፉ የእግዚአብሔር ነው
ጌታ አይረሳም እና የእጆቹን ስራ
ይኸው በልጆቹ አይተናል ሲስራ

አዝ✝️✝️✝️✝️

እንደ ጠላት ቢሆን እንደሱ ጉልበት
ማነበር የሚኖር ዛሬ በሂወት
የሚያኖር ጌታ ነው የሚገልም ጌታ
ብርቱ እሱ ብቻ ነው በሀይል የበረታ

አዝ✝️✝️✝️✝️

በምስጋና ትጉ ፅኑ በፀሎት
በስሙ ታመኑ ቁሙ በእምነት
ለናንተ የምትሆን እግዚአብሔር ቀን አለው
አትቁረጡ ተስፋ ሁሉም አላፊ ነው

አዝ✝️✝️✝️✝️

ብትሆኑም ከ ጉርጓድ እሱ የያቹዃል
በማዳኑ ጥላ ይጎበኛቹዃል
ገና ያበዛቹዃል ከዚህም በላይ
ሁሉ ይቻለዋል ነውና አዶናይ

    ሊቀ-መዘምራን ቴድሮስ ዮሴፍ

✝️ለባለ ማህተቦች✝️ሼር ያድርጉ↗️

✨✨✨✨✨✨✨
✝️#ኦርቶዶክሳዊ_ዝማሬ✝️
✨✨✨✨✨✨✨

Показано 20 последних публикаций.