🌹 ፍቅሬን በ ግጥም 🌷


Гео и язык канала: Эфиопия, Амхарский


♥️ይህ ነው ለእኔ ፍቅር 💟 ማለት፤
➣ ያለምላሽ ወዶ መገኘት፤
➣ በንፁህ ልብ ጠልቆ መዋኘት፤
➣ ይህ ነው ለእኔ ፍቅር ማለት💟
ҒϴᏞᏞϴᏔ ϴΝ ҒᎪᏟᎬᏴϴϴᏦ = https://www.facebook.com/fikrenbegtm
ᶠᵒʳ ᵃⁿʸ ᵖʳᵒᵐᵒᵗⁱᵒⁿ
= +251931374891
= t.me/Abate_Hiwote

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Гео и язык канала
Эфиопия, Амхарский
Статистика
Фильтр публикаций


መቼ ትመጣለህ...?

እኔ አንተን ስጠብቅ ዘመናት ነጎዱ፣
ወራት አመታቶች እንደዘበት ሄዱ፣

በተስፋህ ታስሬ መምጫህን እያየሁ፣
በናፍቆትህ ታመምኩ በትዝታህ ከሳሁ።

አንተ ሳትመጣ ሃገር በለፀገች፣
በሰው የደም ዋጋ ዲምላይት አስተከለች፣

እልፎች ተቀነሱ በመደመር ስሌት፣
ብዙዎች ታ*ረዱ አንድ ሃገር ለማጽናት።

አንተ ሳትመጣ...!
እንደ ሙሴ ያለ ታላቅ መሪ አገኜን፣
መርከብ እየሰራ ባህር የሚዶለን።

ሀገሬም አልፎላት ገንዘብ አበደረች፣
የተራበ ልጇን ፆም እያሳደረች

አንተ ሳትመጣ...!
ከንቲባም አገኜን ከእናት የበለጠች፣
የስንቱን ምስጉን ልጅ ከጎዳና ጣለች።

አንተ ሳትመጣ...!
ህፃናትን መግ*ደል እንደጽድቅ ተቆጥሯል፣
ዘንባባ መግጨት ግን በጥብቅ ያሳስራል።

ይሄን ሁሉ ችዬ...!
መች እንደምትመጣ ቀናቱን ባላውቅም፣
እጠብቅሃለሁ በሰጠኸኝ አቅም።

@hiwot1252 ✍️

━━━━━━✦✗✦━━━━━━━
ምርጫዎ ስለሆነ እናመሰግናለን 🙏

Join us 👇👇👇
https://t.me/joinchat/AAAAAE-H14mYFGMHTdYugA

4.4k 0 44 12 89

⚠️ ማሳሰቢያ !!  ይድረስ ለቻናሉ አባላት በሙሉ

➲ በአዲሱ የቴሌግራም ፖሊሲ መሠረት ይህን  ከታች unmute ሚለው ላይ የሚያደርጉ አባላት ቻናሉ ላይ እንደሌሉ ይቆጠራሉ ፡፡ ይህንን ማድረግ የሚፖሰቱትን መረጃዎች
#VIEW ይቀንሰዋል።

ምንም እንኳን የምንፖስተውን እየተመለከቱ ቢሆንም ቻናሉ ላይ እንዳሉም አይቆጠርም ፤ ስለዚህ...

➲ ከታች
#MUTE የሚለው ላይ ከሆነ ምንም አይንኩት ነገር ግን

#UNMUTE ላይ ከሆነ 1 ግዜ በመንካት MUTE የሚለው ላይ አድርጉት

🙏 ስለ ትብብርዎ እናመሰግናለን 🙏

https://t.me/joinchat/AAAAAE-H14mYFGMHTdYugA


~~~~~~ በስልክ ስሰማህ ~~~~~

ካአድማስ ማዶ ሁኘ ድምፅህን ስሰማ
ቁጭ ብየ ሳነባ ሁሌ በጨለማ
ስልኬን አቅፊ ማንም ሰው ሳይሰማ

እንባየ ይወርዳል ናፍቀህኝ ነው እና
ወይም እንዳልመጣ ጠፍቶብኝ ጎዳና
እብሰለሰል አለው በሀሳብ ጎዳና
ፍቅርህ በሰው ሀገር ሁኖብኝ ፈተና

ግን እኮ ውዴ
ግን እኮ ጨካኝ ነህ እውነቴን ልንገርህ
ምንም አታዝንልኝ ሁሌም ትመጣለህ
ወይ እንዳልዳልስስህ በአካል አይደለህ
ለምን ለብቻየ ታሰቃየኝ አለህ
ድምፅህን ስሰማ ስርበተበትልህ
አንድም ደንታ አይሰጥህ መውደዴ ጨካኝ ነህ
ለሊት ለሊት በእልሜ ለምን ትመጣለህ
እኔን አሰቃይተህ ምን ትጠቀም አለህ

እህል እንዳልበላ ሰውነቴ ከስቷል
ድምፅህን ከሰማ ምግብ መች ያምረዋል
የምሆነው ሁሉ መላው ይጠፋኛል
እንባየ በመንታው ጉንጨን ያርሰኛል
አላርም ስሰማ ግራው ይገባኛል
አንተ እየመሰልከኝ ይደናገረኛል
የእሩቅ እራብተኛህ እንዴት ይሻለኝል


━━━━━━✦✗✦━━━━━━━
ምርጫዎ ስለሆነ እናመሰግናለን 🙏

Join us 👇👇👇
https://t.me/joinchat/AAAAAE-H14mYFGMHTdYugA


​​💛 ሳፈቅርሽ ኖራለው 💛

የትም ብትሆኚ ከአጠገቤም እሩቅ
አፍቃሪሽ ልቤ ነው መውደዱ የማያልቅ
ብትጠይኝ ብትወጂኝ መውደዴ አይቀንስ
አንቺን ገና ሳይሽ መንፈሴ የሚታደስ
ፍቅር ትሩፋቴ መላ እንነቴ
ያንቺው ነው ብያለው ተረጂልኝ እቴ

የልቤ ምት እንኳን ስላንቺ ሲመቱ
ብታዳምጪልኝ ምን ነበረ እቱ!

የመውደዴን ምላሽ ካንቺ ሳልጠብቀው
ባታፈቅሪኝ እንኳን ሳፈቅርሽ ኖራለው።

#ሼር_አደራ_ህይወቴዎች😘🙏

@Fkren_begtim ,,,📩 @Abate_hiwote

━━━━━━━✦🌹✿🌹✦━━━━━━━


✍️ አስታወሰኝ ረጋሳ

መዳፍ ማንበብ ትችያለሽ ?


ድሮ ለታ የጨበጥሽኝ ቀኝ መዳፌን አሳከከኝ፣
ለእርግማን ነው ብየ ፈራሁ በልቶኝ መቼም አይባርከኝ፤

እስኪ እይልኝ እባክሽን የሚበላኝ የት ድረስ ነው ?
እኔስ ቁስሌን ሳባብለው የምኖረው እስከ የት ነው ?

መዳፍ ማንበብ ትችያለሽ?

አበባ አለ ከ ዕጣዬ ጋር አይተሽዋል ቅጠል ግንዱን፣
መርገፍ ሊሆን የነገ ዕጣው እንዴት ይኑር ሰው የግዱን፤

ወይንስ

ባጭር እሆናለሁ ያልኩት ተስፋ አጓጉቶ ያንቋጠጠኝ፣
በእፍኝ ተድላ ሊቀጨኝ ነው የእስከ ዛሬን ቀን የሰጠኝ፤

አንችስ... አንችስ...

አንችስ ብሞት ትመጫለሽ ?
በድኔን አፈር ታለብሻለሽ ?
በ እንባሽ ሽቶ ታብሻለሽ  ?

ብቻ ተይው

መዳፍ ማንበብ ትችያለሽ ?
ነገን ገልጠሽ ባታሳይው ከህመሙ ባትፈውሺው፣
ለእድሌ እንደሁ ግድ የለኝም እስኪ በዛው የናፍቆቴን አንዴ ብቻ እጄን ዳብሽው።

@Fkren_begtim ,, 📩 @Abate_hiwote

━━━━━━━✦🌹✿🌹✦━━━━━━━


😘

12.1k 0 147 4 120

​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​▓▓▓▓▓▓  ግጥም  ▓▓▓▓▓▓

#ካወራሽው_ላውራው 

ሌላ ወደድኩኝ ብል ፥ በአፌ ደጋግሜ፣
ለቃል ፍጆታ ነው ፥አትመኚ አለሜ።
ስምሽን አረሳም፥ፍቅርሽን አላወጣም፣
በንግግር መሃል፥ያንቺን ስም አላጣም።

ያቺን የዛሬ ሴት፥ገላ አረማመዷን፣
ድንቅ አለባበሷን፥ቀሚስና ጉርዷን፣
ገፅታ ስሜቷን፥ማኩረፍና ሳቋን፣
የጉንጯን ስርጉዳት፣ ከንፈርና ጥርሷን፣
በማየት መካከል፣አንቺን መስላኝ እንጅ፣
ካንቺ የበለጠ፥ማን አለኝ ወዳጅ።

እኔም እንዳቺው ነኝ፥ስምሽ ያመልጠኛል፣
ማሬ ፍቅሬ ማለት፥ሁሌም ይቀናኛል።
እናም ሳንጨርሰው፥የፈታነው ፍቅር፣
ዛሬ ናፍቀነዋል፥ልመለስ ጥል ይቅር።
ያምቺንም ሰማሁት፥የኔውም ይሄው ነው፥
ተራርቆ ፍቅር ፥ቢቀርብን ምነው?

@Gtmwustie

━━━━━━
✦✗✦━━━━━━━
ምርጫዎ ስለሆነ እናመሰግናለን 🙏

Join us 👇👇👇
https://t.
me/joinchat/AAAAAE-H14mYFGMHTdYugA


​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​▓▓▓▓▓▓  ግጥM  ▓▓▓▓▓▓

#ተጣልተናል_እኮ
.
እንደማንመለስ ምለን በታቦቱ፣
ንግግር ካቆምን አልፈዋል ወራቱ፣
ኧረምን ወራቱ አመታቱም ነጉዷል፣
ሌላ ወድጃለው እሱም ሌላ ወዷል፣

ግና....
ቁልምጫ በሚሉት እዳ ተለክፌ፣
ሙሉ ስሙን መጥራት አለመደም ኣፌ፣
ተጣብቆብኝ አንዴ የቁልምጫው ነገር፣
ስለሱ ስጠየቅ ለሰዎች ስናገር፣
ውዴ፡ ማሬ፡ ፍቅር፡ ላለማለት ስጥር፣
ይቀድመኛል ኣፌ ባስታዎስኩት ቁጥር።

#ኤዶምገነት_ፃፈችው
@arifgtmbcha

━━━━━━✦✗✦━━━━━━━
ምርጫዎ ስለሆነ እናመሰግናለን 🙏

Join us 👇👇👇
https://t.me/joinchat/AAAAAE-H14mYFGMHTdYugA


​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​▓▓▓▓▓▓  ግጥም  ▓▓▓▓▓▓


♥️🤍 አባ አንተ ማለት 🤍♥️

የውበት አክሊሌ ክብርና ኩራቴ
መኖሬ ትርጉም የምድር ገነቴ
ስምህ ስሜን ሲከተል ሆኖ ወደኋላ
ልጁናት ተብዬ በስምህ ስጠራ
እንኳንስ አቀበት እንኳንስ  ተራራ
ድቅድቅ ያለ ጽልመት ጨለማም አልፈራ

ጀግና ማነው ብለው ሰወች ቢጠይቁኝ
ጎበዝ እነ ደፋር ብለው  ቢጠይቁኝ
ካንተ ውጪ ሌላ ማነው እላለሁኝ

ጓደኛየ ሆነህ ሚስጥር ምትጋራ
አባቴም እየሆንክ መንገድ የምትመራ
ያንተ ልጅ እኮነኝ አባ እንዴት አልኮራ
የፍቅህን ዋጋ አምላክ ይክፈልልኝ
የበደልኩህ ካለም እሱ ይካስልኝ

እንጂማ በእኔ አቅም ካለው የምችለው
ነፍሴንም አልሳሳ ስላንተ ብከፍለው😍😍


(ብሩክ ጻባ)✨✍



━━━━━━✦✗✦━━━━━━━
ምርጫዎ ስለሆነ እናመሰግናለን 🙏

Join us 👇👇👇

https://t.me/joinchat
/AAAAAE-H14mYFGMHTdYugA

13.5k 0 185 8 121

    🔹🔹 💎 ማኅተም ንቅሳቴ 💎 🔹🔹

በጅምር የቀሩ፡ ብዙ ጽሑፎች አሉ፣
ሐረግ የሆኑብኝ፡ አልሆን ያሉኝ ሙሉ።
...
ኃያል የሆነባት፡ የልክነት ምሥጢር፤
እንኳን ዓይን ላለው: ይታያል ለዕውር።
...
ከዚም ከዚያም: ተከባ በወዳጅ፣
ፍቅር ያስችራት ዘንድ፡ ሆኖበታል ግዳጅ።
...
ከአርያም በታች፡ አቻ ባስስላት፤
ልኳን የሚለካ፡ አኳያ አጣኹላት።
...
አድርጌ የሾምኳት: ማኅተም ንቅሳቴ፣
የተቸረኝ ከላይ: ኅቡዕ ሽልማቴ፤
እንደ አንገት ማዕተብ: አጥብቄ የያዝኳት፣
እንደ ክቡር ንጉሥ: ዙፋን የሰጠዃት፤
ቆሜ እምቀርላት: እንደ ሐውልተ አክሱም፤
ምንም አይንካብኝ በጠናም በስሱም።
...
ወርቅ አልሰጣት፡ ዕይቁ ምኗ ለ'ሷ፣
አላስጌጣት፡ ጌጥ በጌጥ ቀሚሷ፤
ከብራ ትቆይልኝ በሥጋዋ፣ ወደፊት በነፍሷ።
...
መሠረቴ እሷ ናት፡ ያለ እሷ ማን አለኝ!
እናቴ ከሌለች፡ እኔም ሕይወት የለኝ!
            ያለ እሷ ማን አለኝ 😍

❤️እናቴ ❤️እማዬ❤️❤️

✍️ Mekuriya Murashe 🔸 ዘአበው


━━━━━━━━✦🔵✦━━━━━━━━
ምርጫዎ ስለሆነ እናመሰግናለን 👍

𝚓𝚘𝚒𝚗 𝚞𝚜  👇👇👇

https://t.me/joinchat/AAAAAE-H14mYFGMHTdYugA

ለእናቶቻችሁ አንብቡላቸው 🔥🔥🔥

15.4k 0 140 3 132

✍አራቱ ሚስቶቻችን

ይነበብ እና ሼር ማድረግም አይርሱ

አራት ሚስቶች የነበሩት አንድ ሀብታም ነጋዴ
ነበር፡፡ አራተኛ ሚስቱን ከሌሎች አብልጦ በእጅጉ
ይወዳታል፡፡ ስለሚወዳትም ጥሩውን ሁሉ ለእርሷ
በመስጠት ይንከባከባታል፤ያስደስታታል፡፡ ሦስተኛ
ሚስቱን መውደድም ብቻ አደለም ይኮራባታል፣
ይመካባታልም ጭምር፡፡ ይዟት በአደባባይም
ለመታየት ይፈልጋል ነገር ግን ጥላው እንዳትሄድ
በጣሙን ይሰጋል፡፡ ሁለተኛ ሚስቱንም እንዲሁ
ይወዳታል፡፡ ይች ሁለተኛ ሚስቱ በነገሮች
አስተዋይና ብልህ ታጋሽም በመሆኗ ይመካባታል፡፡
ነጋዴው አንዳች እክል የገጠመው እንደሁ ችግሩን
ታቅፎ እሚያመራው ወደ ሁለተኛ ሚስቱ ነው ፡፡
እሷም በአስቸጋሪው ሰዓት ከጭንቀቱ
ትገላግለዋለች፡፡ የመጀመሪያ ሚስቱ በጣም
ታማኝ አጋሩ ናት፡፡ ቤቱንና ንግዱን የምትመራለትና
የምታስተዳድርለት እሷው ነች፡፡ እሷ በጣም
የምታፍቅረው ቢሆንም እሱ ግን ስለማያፈቅራት
አንድም ቀን በትውስታው ውስጥ ቦታ ሰጥቷት
አያውቅም ነበር፡፡
ታዲያ አንድ ቀን ህመም ተሰማውና ማለፉን ባሰበ
ጊዜ የተድላ ዓለሙን እያስታወሰ እንዲህ አሰበ
“አራት ሚስቶችና የተትረፈረፈ ሀብት አለኝ ነግር
ግን በሞት ጊዜ ብቻየን እሆናለሁ፡፡ እንዴት ብቻየን እሆናለሁ?” በማለት አራቱንም ሚስቶች
በማስጠራት ጥያቄ አቀረበላቸው፡፡
“ሁላችሁንም በጣም እወዳችኋለሁ:: የሚያምሩ
አልባሳትንም እያለበስኩ ሳስጌጣችሁ ኖርኩ፡፡
አሁን ግን ልሞትናውና ከብቸኝነቴ ታድኑኝ ዘንድ
ተከተሉኝ” አላቸው፡፡ አራተኛው ሚስቱ “በፍጹም
አይሆንም” ስትል መልሱን ሰጥታው ከአካባቢው
ተሰወረች፡፡ ነጋዴው በሰማው ምላሽ ልቡ ተነካ፡፡
ለሦስተኛዋ ሚስቱ “በሕይዎቴ ሙሉ ስወድሽ
ኑሪያለሁ አሁን አብረሽኝ ልትሆኝና ወደምሄድበት
ልትከተይኝ ትፈቅጃለሽ?” አላት በአዘኔታ ሁኖ
መልስ ሲጠባበቅ “አይሆንም ሕይዎት
አትጠገብም ፡፡ እዚህ መኖር መልካም ነው፡፡
እናም ከአንተ ሞት በኋላ አግብቸ መኖር እሻለሁ”
አለችው፡፡ ይህ ሀብታም ነጋዴ ልቡ ዝቅ ሲልና ወደ
ቀዝቃዛነት ሲለወጥ ተሰማው፡፡ አሁንም በተስፋ
መቁረጥ ሁኖ “በሕይዎቴ ሙሉ እርዳታን ስፈልግ
ወደ አንች ስመላለስ ኑሪያለሁ፡፡ ስትረጅኝም
ነበር፡፡ አሁንም እርዳታሽን ፈልጊያለሁና እርጅኝ”
ሲል ሁለተኛ ሚስቱን ጠየቃት፡፡ “በዚህ ሰዓት
ልረዳህ ባለመቻሌ አዝናለሁ፡፡ ማድረግ
የምችለው አንተን ወደ መቃብርህ መሸኘት ብቻ
ነው” ስትለው መብርቅ የመታው ያህል ክው አለ፡፡
በድንጋጤ ስሜት ተውጦ እያለ “የትም ብትሄድ እከተልሃለሁ፤ አንተጋ እሆናለሁ!” የሚል ድምጽ
ሲያስተጋባ ተሰማው ዓይኑን ሲያነሳ የተጎሳቆለ
እይታ ያላት የመጀመሪያ ሚስቱ ነበረች ነጋዴው
ሳግ እየተናነቀው “ሲኖረኝና ስችል ልንከባከብሽ
ይገባኝ ነበረ” በማለት እቅፍ አድርጎ ወደሰውነቱ
አስጠጋት፡፡
በመሠረቱ ሁላችንም በሕይዎታችን አራት
ሚስቶችን አኑረን ይሆናልና የእኛም ታሪክ ሊሆን
ይችላል፡፡
1. አራተኛው ሚስታችን ፈራሹ ስጋችን ነው፡፡
ለምቾቱና ለውበቱ ተጨንቀን ብንደክምም ቀሪ
እንጅ ተከትሎን አይሄድም፡፡
2. ሦስተኛው ሚስታችን አለን የምንለው ነገር
ንብረት፣ ሀብትና ክብራችን ነው፡፡ ይሄም እኛ
ስንሞት ወደሌሎች የሚተላለፍ ነው፡፡
3. ሁለተኛው ሚስታችን ቤተሰቦቻችንና ጓደኞቻችን
ናቸው፡፡ በሕይወት ዘመናችን የቱንም ያህል
ቀረቤታና ቁርኝት ቢኖረንም ማድረግ የሚችሉት
እስከ መቃብር መሸኘት ብቻ ነው፡፡
4. የመጀመሪያዎ ሚስታችን ሕያው ነፍሳችን ናት፡፡
ቁስና ሀብት ስናሳድድ ወደ ጎን ገፍተናት ቢሆንም
አብራን የምትሆነው እሷው ነችና በመጨረሻው
ሰዓት ሳይሆን አሁኑኑ እንድናለመልማት ያስፈልጋል
ነው የታሪኩ ጭብጥ፡፡


🙏መልካሙን ሁሉ የምንሰማበት  ያርግልን🙏

@Fkren_begtim ,,,📩 @Abate_hiwote

━━━━━━━
✦🌹✿🌹✦━━━━━━━

17.1k 0 207 8 221

♥️♥️ #ሁሌም_ታማሚ_ነኝ 😞😞

አንተ የኔ ፍቅር ውጋቴ ህመሜ
ሳወጣ ሳወርድ ሳልምህ ከርሜ
እረፍት አገኘው ስል ለአመታት ድካሜ
ትልቁ ድብ እዳ መለየት መጣና
ፍቅርን ያህል ነገር አደረገው መና
       ቅስሜ ተሰበረ የማደርገው ጠፋኝ
እሬት እሬት አለኝ መኖርም ሰለቸኝ
እንደህልም ቢሆንም መለየትህ ከኔ
ወይኔ እኔ ብዬ ባለቅስ  ደም ቢያነባ አይኔ
ሻጥ ብትልብኝ ልቤ ከለቃዬ
ለማን አቤት ልበል ለማን ልንገር ጭንቄን
ሁሌም ታማሚ ነኝ "ዋ" ካላገኘው አንተን

       ገጣሚ እሌኒ
ግጥም ለመላክ 👉
@Abate_hiwote

        @Fk
ren_begtim ,,,📩 @Abate_hiwote

━━━━
━━━✦🌹✿🌹✦━━━━━━━


. . .  #ውሸቴን_ነው_ለካ . . .

አቅሙ እንዳለው ሰው በመርሳት ልረካ
እረሳሁህ ያልኩት ውሸቴን ነው ለካ!

ብዙ’ኮ አፍቃሪ አለ . . .
እውነቱን በልቡ ባፉ ውሸት ይዞ
እረስቼዋለው እያለ ሚያወራ በሽንፈት ተክዞ

ምስልህን ልቤ ላይ አትሜው ካይኖቼ
ፎቶህን ብቀደው ካለበት አውጥቼ

እረሳውህ ብዬ ላስታውስህ ነገር
ከዚህ የበለጠስ ምን ሽንፈት ሊፈጠር

ስልክህ ከስልኬ ላይ እንዳይቀር ማጥፋቴ
ለካስ ውሸት ነበር አወይ ጅሉ እምነቴ

በቃሌ ሸምድጄው ልረሳህ ብለፋ
ትርጉም ይሰጣል ወይ? ቁጥርህን ባጠፋ

እናማ ሲገባኝ . . .
ለካስ ውሸቱን ነው መሸነፉን አምኖ ላለመባለ ፈሪ
እረስቻለሁ እያለ ሚያወራው አብዛኛው አፈቃሪ ፡፡
             
             
@Fkren_begtim ,,,📩 @Abate_hiwote

━━━━━━━
✦🌹✿🌹✦━━━━━━━

17.9k 0 154 14 91

CROWN DOOR ክራዉን በር

ከእንጨት ፋይበር የተሠራ በር

ዘላቂነት፡- ክራዉን ኢንጂነሪድ የእንጨት ላምኔትድ በሮች ከባህላዊ የእንጨት በሮች የበለጠ ረጅም ጊዜ እንዲቆዩ በማድረግ ከከፍተኛ እርጥበት እስከ ከፍተኛ የሙቀት ለውጥ ድረስ እንዲቋቋም ተደርገው የተነደፉ ናቸው።

የ25% ቅናሽ ዋጋ በካሬ 9850 ብር ኢንክ ቫት ጀምሮ ለተወሰነ ጊዜ ብቻ

ባለ 800mm በር ከ16,540 ብር ኢንክ ቫት

ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥራችን ፡-

0993050914/0993053021

https://t.me/crowndoor

@crowndoor1

Email: crowndoor101@gmail.com

የማሳያ ሾዉ ሩም አድራሻ፡-

ብስራት ገብርኤል ቦራን ኮምፕሌክስ ህንፃ 2ኛ ፎቅ አዲስ አበባ


​​​🌹።።።።።🌹የፍቅር ጅማሮ🌹።።።።🌹


አዳምና ሄዋን ፍቅራቸው ሲጀመር
ታሪኩ እንዲህ ነበር

ሄዋን ፍቅር ይዟት ተጨንቃ ተጠባ
ስትል ፈራ ተባ
ቆይታ ቆይታ
እንደዚ አለችው አዳምን ተጣርታ

"ምን ብዬ ልንገርህ
አዳም የኔ ፍቅር
ፍቅርህን እሻለሁ
በጣም እወድሃለሁ
መልሥህን ንገረኝ እባክህ በሞቴ
ፍቅሬን ተቀበለኝ አዳም አካላቴ"

በማለት ጠይቃው ልቧ ሲንሠፈሠፍ
"ምን አማራጭ አለኝ!" አላትና እርፍ

ከዚያን ጊዜ ወዲህ ምን በፍቅር ብታልቅ
ከሡ ይምጣ እንጂ እሷ ጠይቃ አታውቅ!

  

@Fkren_begtim ,,,📩 @Abate_hiwote
━━━━━━━✦
🌹✿🌹✦━━━━━━━

14.1k 0 209 4 141


Показано 16 последних публикаций.