🌺🌸🌺🌸 ትርታዬ 🌺🌸🌺🌸
🌼🌼🌼 ክፍለ አንድ (3) 🌼🌼🌼
🌻ልብ አንጠልጣይ እና አስተማሪ ታሪክ🌻
ከለታት አንድ ቀን። መቅደስ ብቻዋን ካፌ ቁጭ ብላ እያለ ዮናስ የሚባል ልጅ መቶ አጠገቧ ቁጭ አለ ።ይቅርታ የኔ ወንድም ወንበሩ ሰው አለው አለችው ታዲያ ምን ችግር አለው ሲመጣ እነሳለኹ አላት እሺ አለችውና ስልኳን አውጥታ መነካካት ጀመረች ከዛም መቅዲ አላት ድንግጥ ብላ የት ታውቀኛለህ አለችው ዮናስም ሳቅ ብሎ እዚ ግቢ አንቺን የማያውቅ አለ እንዴ አላትና እኔን ካላወቅሽኝ ዮናስ እባላለሁ ግን ደስ እንዲለኝ ዮኒ በዪኝ አላት።መቅደስም ፈገግ ብላ በዝና የማውቅህ መሰለኝ በሚገባ አላት።
.....ዮናስ ማለት በጣም ቆንጆ ለውበቱ ከምንም በላይ ቦታ የሚሰጥ የግቢው አማላይ ወንድ እሱ ነው ቆንጆ የተባለች ሴት አታመልጠውም መምህራኖቹ በስንፍናው ከመናደዳቸው የተነሳ አንተ በጭንቅላትክ ሳይሆን በልብስህ ነው የምታስበው ብለውታል ባለባበሱ በቁንጅናው ያልተማረከችበት ሳታደንቀው ያለፈች ሴት አለች ቢባል ዘበት ነው።አሁን ደግሞ ተራው የመቅደስ ነው ከብዙ ጓደኞቹ ተወራርዶባታል......
በወሬ ድሰማ እኮ መላእክ ነበር የመሰልከኝ እና እንደጠበቅሽኝ አላገኘሽኝም አላት እሷም አይ ምንም አትልም አለችው።ብቻ በወሬ ወሬ ከዮናስ ጋር እየተጫወቱ እየተሳሳቁ እዛው ካፌ ውስጥ እያሉ አጋጣሚ ሆነና ጌዲዮ በዚያው ሲያልፍ ከመቅደስ ጋር አይን ላይን ተፋጠጡ መቅደስም ከመቀመጫዋ ተነስታ ቆመች.........
.......መቅደስ ከመቀመጫዋ ተነሳች ጌዲዮም በነበረበት ቆሞ እሷን እያየ ጭንቅላቱን ያዘ መቅደስ በድንጋጤ ሙክክ ብላለች እንደው አይተው ሲገምቷት ባሏ ከሌላ ወንድ ጋር የያዛትን ሴት ነው የምትመስለው ጌዲዮ ሰውነቱን እንደማንቀጥቀጥ አደረገው ይህን ጊዜ ሊያመው እንደሆነ አወቀች መቼም መቅደስ የግቢው ቅፅል ስሟ የጌዲዮ የግል ነርስ ሆኗል በፍጥነት እየተንቀጠቀጠች ቦርሳዋን ከፈተች..... ዮናስ ምንም እንዳልተፈጠረ ምን ሆነሽ ነው እንኳን አላላትም ምክንያቱም ጌድዮን አይቶታል መቅደስም ቦርሳዋን ጠረንቤዛው ላይ ዘረገፈችው ይህን ጊዜ ዮናስ ብዙ ሴቶች ወደሱ እያዩ ስለነበር ሼም ያዘው ለመነሳትም አቃጣው መቅደስም በሚርበተበተው አንደበቷ ማማማ ማን ነበር ያያያ..ልከኝ...አ..ው..ዮ.ናስ.እእ..ባክህ..ክርቢት..ካካ..ለህ ይዤ ነነ.በር እ..ኮ.ጠፍኝ አለችው ዮናስም ከቦርሳዋ ከዘረገፈችው እቃ ወደ ክርቢቱ እያመለከተ ያውልሽ አላት መቅደስም ክርቢቱን ልታነሳ ስትቸኩል የብርጭቆውን ጁስ ዮናስ ላይ ደፋችበት ዮናስ በጣም ጮኸ ግን አልሰማችውም ይቅርታም ሳትለው ክርቢቱን ይዛ ወደ ጌዲዮ በረረች........
......ከዛም ህመሙ ሳይብስበት ክርቢቱን አጫጭሳ ሰውነቱን አረጋግታ ደግፋ ከወንዶች ማደሪያ በር ላይ አድርሳው ተመለሰች ስትመለስ ዮናስም ወደማደሪያው እየሄደ ተገጣጠሙ ከዛም በጣም ይቅርታ አለችው በርግጥ በሰአቱ ስትደፋበት ብዙ ሴቶች ቢስቁም የለበሰውን ቲሸርት ሲያወልቀው ግን እንኳን ደፋችበት ያሉት በዝተዋል የዮናስ ደረት ላይን ያሳሳል ለነገሩ ምን አለበት ከትምርቱ ይልቅ ለሰውነቱ ቅርፅ ሲል እስፓርትን ነው የሚወደው እናም ይቅርታ እንዳደረገላት ነግሯት በሌላ ጊዜም ተገናኝተው እንድትክሰው ቃል አስገብቷት ተለያዩ።
...ቦርሳዋንም አስተናጋጇ አስተካክላ ስለጠበቀቻት ይዛ ወደዶርሟ ሄደች ግራ የገባት ግን የሷ መደንገጥ ሳይሆን የጌዲዮ እሷን ከሌላ ጋር ስላያት የህመሙ መቀስቀስ ነው እውነት ይወደኝ ይሆን ብላ አሰበች ደግማም አረ አይመስለኝም እያለች በሁለት ሀሳብ ተይዛ ብቻዋን ታወራ ጀመር።
......ጌዲዮም እንደልማዱ መፅሀፉን ይዞ ጋደም ብሎ በሀሳብ ተውጧል የዶርም ጓደኞቹም አንድ ላይ ቁጭ ብለው እያወሩ ነበር ጌዲዮም ከተለምዶ ውጪ ጮክ ብሎ አንድን ሴት ከሌላ ወንድ ጋር ስላየሀት ምን ያናድዳል ብሎ ጠየቃቸው ሁሉም በድንጋጤ ወደሱ ዞሩ ቀልዱን ነው እንዳይሉ ጌዲዮ እንኳን ሊቃለዳቸው የግዜር ሰላምታንም ሰቷቸው አያውቅም ከምሩንም ነው እንዳይሉ እሱ ስለሴት ከመቼ ወዲ ሲያስበው ነው ብለው ወደራሳቸው ሲመለሱ አሁንም መልሱልኛ አላቸው የሚመልሱት ጠፋቸው ከዛም አንድኛው ፎንቃ ይሆናላ አለው ጌዲዮም ምን ማለት ነው አለው ከዛም እንደምንም ተደፋፍሮ ፍቅር ይዞህ ይሆናል ታዲያ ፍቅር ያናድዳል እንዴ ሲላቸው እየውልህ ጌዲ አንተን ስለፍቅር ለማስረዳት ከሀ መጀመር አለብን ሲለው አንድኛው ጓደኛቸው እንደመሳቅ ብሎ ዝም ለማስባል በቁንጥጫ መዠለገው ልጁም ዝም አለ ጌዲዮም
....
#ክፍል 4 ይቀጥላል
ክፍል 2 ይቀጥላል ..........
ለሀሳብ አስተያየት 👉 @Dinomu
ለመቀላቀል 👉 @mazngna