🌺🌸🌺🌸 ትርታዬ 🌺🌸🌺🌸
🌼🌼🌼 ክፍለ አስራ አራት (14) 🌼🌼🌼
🌻ልብ አንጠልጣይ እና አስተማሪ ታሪክ🌻
.....
#ሸርርርር ማድረግ አይረሳ
...ዮናስም ደሙ ፈልቶ ስማ አንተ ደነዝ እንድትመክረኝ ሳይሆን እንድትጠነቀቅ ነው ያስቆምኩህ አሻፈረኝ ካልክ ግን በነብስህ ፍረድ ሲለው ጌዲዮ ከበፊቱም በላይ በመኮሳተር
........አንተ የፍቅር ትርጉሙ አልገባህም መኖር ካለብኝ ለፍቅር ነው ፍቅር ማለት ደግሞ ስለሌላ መኖር ነው አየህ በዚች ምድር ላይ ለሁለት ነገሮች ነው የምኖረው አንድ ለናቴ ዛሬ ደግሞ ለሁለተኛዋ እናቴ ለፍቅሬ በነዚ ሁለት ነገሮች ለመጣብኝ ከነብስ በላይም ካለ አሳልፌ ለመስጠት ዝግጁ ነኝ ዙሪያ ጥምጥም ከምትሄድ ፊትለፊት ሞክረኝ ደግሞ አትርሳ መቅዲ የማታውቃቸው ያንተ ድብቅ ሚስጥሮች እንዳሉ እናም ወንድም ከኔ በላይ አንተ ፍራ እሺ ብሎት እየተውረገረገ መንገዱን ቀጠለ ዮናስ በጓደኞቹ ፊት አፈረ እነሱም እሱን ለማባበል ይሄ በሽተኛ ፋራ ቆይ እንሰራለታለን ይሄ ገገማ እያሉ የስድብ ናዳ አወረዱበት።
.......አሁን ጌዲዮ አንድ ነገር ገባው መቅደስና ዮናስ የፍቅር ግንኙነት እንደሌላቸው የባለፈው ውሳኔውም ትክክል እንዳልነበር ተረዳ ግን አሁንም መቅደስ እሱን እንደምታፈቅረው ማወቅ ቢፈልግም ግልፅ አልሆነለትም
.......መቅደስና ጓደኞቿ ከመመገቢያ ክፍል እየወጡ ሳለ ጌዲ ደግሞ ገና ሊበላ እየገባ ፊትለፊት ተገናኙ መቼስ ጅብ በቀደደው ውሻ ይሾልክበታል ነው ውሻ በቀደደው ጅብ ይሾልክበታል የሚባለው ብቻ የሆነው ሆኖ እንደተገናኙ ብርሀን ሀይ ጌዲ ሰላም ነው አለችው ከዛም መቅደስ በከፈተችው መንገድ ሁሉም ሰላም አሉት የሚሄድበትን እያዩ የሚያወሩት ሲያጡ የት እየሄድክ ነው ብለው ጠየቁት እሱም ምሳ ልበላ አላቸው እሺ መልካም ምሳ ብለውት ከመለያየታቸው ጌዲዮ አዙሮ ጣለው መቅደስ እየሮጠች ወደሱ መጣች በጣም እየተወራጨ ነበር እንደምንም ብላ አረጋጋችው ከግማሽ ሰአት ቡሀላ እግሮቿ ላይ አስተኝታ ባፍ ባፍንጫው የደፈቀውን አረፋ በገዛ ልብሷ እየጠረገችለት ነቃ ገና ከመንቃቱም አናግሯት የማያውቀውን ከግሮቿ ሳይነሳ መቅዲ አላት እሷም እራሱን እየደባበሰች ወዬ ጌዲ አለችው
የእውነት ፈተንሽኝ ታውቂያለሽ ከዚ በፊት ወድቄ ስነቃ አለሜ ጨልማ ሂወት ጠቁራብኝ ተስፋዬ ተሟጦ ነበር አሁን ግን እንዲህ ሲላት ታይቶ የማይታወቅ ምንም እንኳ ባይስቅ ፈገግታ ፊቱ ላይ ይነበብ ነበር አሁን ግን ምን አለችው መልሱን ለመስማት ጓጉታ ባንቺ የተነሳ ጭራሽ መውደቄን ወደድኩ ምን ብዬ እንደማመሰግንሽ አላቅም ለውለታሽ የሚመጥን ቃል የለኝም እውነት ግን እግዚአብሔር አንቺን ሲፈጥር ብዙ ጥበቡን አፍስሶብሻል አላት
መቅደስ ይህንን የተስፋ ቃል በመስማቷ ቀኑን ሙሉ በደስታ ጮቤ ስትረግጥ ዋለች.......... መቅደስ ምንም እንኳ ከጌዲዮ ፍቅር ባትጀምርም አሁን ካይኗ ስር በመሆኑ ደስታዋ ተመልሷል ጌዲዮም እንደዛው......
.......አሁን ወሩ የፈተና ነው ጎበዝ ተማሪዎች በጥናት ተጠምደዋል እንደወይንሸት ያሉት ደግሞ እንዴት አስተማሪዎቻቸውን ማማለል እንዳለባቸው ብቻ ሁሉም በየፊናው እየተዘጋጁ ነው።
...............ጌዲዮም እንደለመደው ጫካ በመሄድ ማጥናቱን ተያይዞታል በነገራችን ላይ መቅደስ አሁንም ሳያያት ትከተለዋለች እናም ዛሬም ሳያያት ከኋላ ኋላው ሄዳ ከቅርብ እርቀት ሆና እያየችው ነው ግን ይህን የምታደርገው አንድ ቀን በህልሟ ጫካ ውስጥ ወድቆ አውሬዎች ሊበሉት ሲሉ በላብ ተጠምቃ ከንቅልፏ ባና ከዛ ወዲ እውን እንዳይሆን እየፈራች ከግቢ ሲወጣ አብራው ትወጣለች............
........እናም ብዙ ቆየ በተስፋ ስትጠባበቀው ቆይታ የሆነ ሰአት ላይ በጫካው የጦጣዎች ትርኢት ተመለከተች ከዛም ቀልቧን ሳቡት ከዛፍ ዛፍ ሲዘሉ ሲቦርቁ ስታይ ለግዜው ጌዲን ለጥናቱ ተወችው ከዛም ስልኳን አውጥታ መቅረፅ ጀመረች ጌዲዮ በዛን ሰአት ጥናቱን ጨርሶ መፅሀፎቹን ሰብስቦ ተነሳ ተነስቶ እንደዞረም መቅደስን አያት ብታየው በተደበቀች ነበር ግን አላየችውም በጦጣዎቹ ሁኔታ እየሳቀች ካሜራዋን ደቅና እየቀረፀች ነው
ጌዲዮ የልቡን ጀግና በተመስጦ እያደነቀ ለደቂቃዎች ሲያያት ቆይቶ ፊትለፊቷ ሄደ ከዛም እረጋ ባለ ድምፅ መቅዲ አላት መቅደስ በድንጋጤ ጮሀ አውቃ ፌንት እንደነቀለ ሰው እጁ ላይ ወደቀች እሱም እውነቷን መስሎት ሊያነቃት ብዙ ጣረ ከዛም የያዘውን ሀይላንድ ውሀ እላይዋ ላይ ደፋው ሆን ብላ እያለከለከች ነቃች
................እሱም ምነው ምን ሆንሽ አላት እሷም እንዴ አስደነገጥከኝ እኮ አለችው በርግጥ ከሚባለው በላይ ደንግጣለች ከዛም እንደማያቅ ሆና ቆይ እዚህ ምን ታደርጋለህ አለችው...
ክፍል 15 ይቀጥላል
ለሀሳብ አስተያየት 👉 @Dinomu
ለመቀላቀል 👉 @mazngna