🌺🌸🌺🌸 ትርታዬ 🌺🌸🌺🌸
🌼🌼🌼 ክፍለ አስራ ስድስት (16) 🌼🌼🌼
🌻ልብ አንጠልጣይ እና አስተማሪ ታሪክ🌻
.
.
.
የተዋወቁት አባዬ መምህር እማዬ ተማሪ ሆነው ነበር አሁን ላይ ጥሩና ስኬታማ ቤተሰብ አለን ሁሉም ወንድምና እህቴ የማዕረግ ተመራቂ ናቸው እኔም ጠንካራ እንድሆን ዘውትር ያበረታቱኛል እንደውም የውጪ እድል መቶልኝ አልፈልግም ብዬ ነው ዛሬ ላይ በጅማ ዩኒቨርሲቲ የዶክትሬት ትምህርቴን የምማረው ምክንያቱም ሳይማር ያስተማረኝን ህብረተሰብ እኔም ወግ ደርሶኝ ማገልገል እፈልጋለሁ ይህንን ሳደርግ ከቤት አንድም ተቃዋሚ አልገጠመኝም በቃ ይኸው አሁንም እየተማርኩ ነው እልሀለሁ አለችው ጌዲዮም ዋዉ የሚያስቀና ቤተሰብ ውስጥ ነው የበቀልሽው አላት መቅደስም አመሰግናለሁ ስትለው አረ ምንም አይደል ደግሞ ተምረሽ አንቺም ጥሩ ቦታ እንደምትደርሺ አልጠራጠርም አላት ................
.
.........ከዛም የሱን እንዲነግራት ስጠይቀው ነገ ዲያሪውን አገላብጦ መጥቶ እንደሚነግራት ቃል ገብቶላት ተነስተው ወደግቢ ተመለሱ .........
ልክ እንደተለያዩም ዮናስ አስቆማት እሷም ሰላም ካለችው ቡሀላ በጣም ለጥብቅ ጉዳይ እፈልግሻለሁ አላት እሷም ምን እንደሆነ ስጠይቀው ማታ እራት እየበላን እነግርሻለሁ ብሎ ትልቅ ሆቴል ከምሽቱ ሁለት ሰአት እንድትመጣ ጋበዛት በፍፁም እንዳትቀርም አስጠነቀቃት እሷም የማትረሳው ውለታው አስገድዷት ውስጧ
ቢደነግጥም ፍቃደኛ ሆነች
......መቅደስም የመሄጃዋ ሰአት ደረሰ ወይንሸትም እንዴ መቅዲ አትቀባቢም እንዴ ዮናስ ጋር እኮ ነው የምትሄጂው ያውም እራት አለቻት ባክሽ ብዙም ደስተኛ አይደለሁ እንደውም እሱ ሆኖብኝ ነው እንጂ አልሄድም ነበረ አለቻት ወይንሸትም ቢሆንም አንዴ ተስማምተሻል ዝንጥ ብለሽ ነው መሄድ ያለብሽ ስለዚ አሁን ይሄንን ልበሺ ይሄንን ተቀቢ እያለች ያለውድ በግዷ ውበቷ ጎልቶ እንዲታይ አረገቻት ከዛም ተሰናብታቸው ስትሄድ ወይንሸት ወዲያው ተከትላት ወጥታ ጌዲዮን በሌላ ተማሪ አስጠራችውና ደብዳቤ ሰጠችው።
........እሱም ከፍቶ ሲያነበው ስማ አንተ በሽተኛ ነግሬህ ነበረ መቅደስ የኔ ናት ለማንኛውም እንድታምነኝ ስል ዛሬ ምሽት የፍቅር ጥያቄ አቀርብላታለሁ ከቻልክ መጥተክ መታደም ትችላለህ ዮናስ ይላል እሱም ወሬኛ ብሎ ደብዳቤውን ቀደደና ወደዶርም ሊመለስ ሲል መቅደስን በዛ በጨለማ ንግስት መስላ ከግቢ ስትወጣ ከሩቅ አያት ጌዲዮ ማመን አቃተው ባይፈልግም ፍቅር ነውና ተከትሎ መጨረሻቸውን ሊያይ ከኋላዋ ተከተላት.........
.........መቅደስ ባላት ሰአት ሆቴሉ ገባች ባይኗም ብዙ ወንበሮች ላይ ፈለገችው የለም ከዛም አንድ ወንበር ይዛ ተቀመጠች አስተናጋጅ ፊትለፊቷ መጥቶ ምን ልታዘዝ አላት እሷም ሰው እጠብቃለሁ የሚል መልስ ሰጠችው ከቆይታዎች ቡሀላ ሌላ አስተናጋጅ መጣችና መቅደስ አለቻት እሷም አዎ ነኝ ኦኬ ተከተይኝ አለቻት መቅደስም ግራ በመጋባት ወዴት ስትላት ዮናስ የተባለ ደንበኛችን ነው ይዘሻት ነይ ያለኝ አለቻት እሺ ብላ ተከተለቻት ሁለተኛ ፎቅም እንደደረሱ ስለደረስን አይንሽን ላስርሽ ነው አለቻት መቅደስ ይበልጥ ግራ በመጋባት እኮ ለምን ስትል አርጊ የተባልኩትን ነው ብላ አይኖቿን አስራ ግን ግለጭ ሳትባይ ምንም እንዳታዪ አደራ ብላት የፎቁ በረንዳ ላይ አድርሳት ተመለሰች ዮናስም ከጥቂት ደቂቃ ቡሀላ ግለጪ አላት መቅደስ የታሰረችበትን ጨርቅ ካይኖቿ ስታነሳ የምታየው ነገር ህልም መሰላት አበባ ተጎዝጉዞ ምሽቱ በሻማዎች ደምቆ አለ የተባለ መጠጥ ቀርቦ ዮናስ አንዲት ቀይ ፅጌሬዳ ይዞ ፊቷ ተንበርክኳል
.......በዛ ሰአት ጌዲዮ ዝብርቅርቅ ባለ ስሜት ውስጥ ህኖም እያያቸው ነበር....መቅደስ ግራ ገባት ላንድም ቀን ዮናስን በዚህ መልኩ አስባው አታውቅም ዮናስ ምን እየሆንክ ነው አለችው እሱም ክሽን አድርጎ በሚያወራት አስመሳይ ግን ጣፋጭ በሆነ አንደበቱ መቅዲ ካየሁሽ ቀን ጀምሮ አፍቅሬሻለሁ የልቤ እመቤት አድርጌ ሾሜሻለሁ መቅዲ አንቺ ከማንም በላይ ለኔ ልዩ ነሽ እስከ ሂወቴ ፍፃሜ ያንቺ ብቻ ልሁን ፍቀጂልኝና የፍቅርሽ ባሪያ ልሁን አያለለ ዜማ ቢጨመርበት አንድ ክሊፕ የሚሰራውን ዜማውን አፈሰሰባት ከዛም መቅደስ ምን እንደምትል እንኳን ግራ ገብቷት እየውልክ ዮናስ ይሄን ላረግ አልችልም ብላ ከተንበረከከበት እጆቹን ይዛ አስነሳችው ዮናስ ደሙ ፈላ ግን ለምን አላት እየውልክ እኔ የኔ የምለው የማፈቅረው ሰው አለኝ አንተን ወንድሜ እንጂ ፍቅረኛዬ ላደርግህ አልችልም ዮኒ የእውነት በጣም አዝናለሁ እኔ ያንተ ልሆን አልችልም በቃ ውለታውን በዚ መልኩ ልትከፍለው እንደማትችል ነግራ በጣም አስተዛዝናው ተመልሳ ሄደች.....
#ክፍል 17 ይቀጥላል
ለሀሳብ አስተያየት 👉 @Dinomu
ለመቀላቀል 👉 @mazngna