🌺🌸🌺🌸 ትርታዬ 🌺🌸🌺🌸
🌼🌼🌼 ክፍለ አስራ ሰባት (17) 🌼🌼🌼
🌻ልብ አንጠልጣይ እና አስተማሪ ታሪክ🌻
አስተዛዝናው ተመልሳ ሄደች ልክ እሷ እንደተመለሰች
ጌዲዮ ፊትለፊቱ ሄደና ስማ መቅደስን እንኳን በውንህ በህልምህም የግልክ አታደርጋትም የእውነት ግን በራሴ አፈርኩ አንተን አምኜ እዚህ ድረስ መልፋት አልነበረብኝም ይህንን ትርኪ ሚርኪህን በለመድካቸው ላይ ግን ለዚህ ሁሉ ወጪ ስንት ብር ፈጀብህ እያለ የዮናስን ንዴት በእጥፍ ጨምሮ ሄደ ዮናስ መጠጡን እየገለበጠ በፍቅር እንቢ ካልሽ የበቀል ልቡን አሳበጠው........
...........ከዛም በንጋታው ጌዲዮና መቅደስ ተያይዘው ለጥናት ወደጫካው ሄዱ አጥንተውም እንደጨረሱ ታሪኩ እንዲነግራት አስገደደችው እሱም
.....እኔ ምንም ሌላ ታሪክ የለኝም ታሪኬ አንድ ግን ብዙዋ እናቴ ናት ተወልጄ ያደኩት በደቡብ ወሎ ወረኢሉ ጃማ የሚባለው ገጠራማ ስፍራ ነው አባቴን አላውቀውም በልጅነቴ ነው የሞተው ከኔ በፊት እናቴ ሶስት ልጆች ሞተውባታል እኔንም ስለት ተስላ ነው ያደኩላት ግን ባድግም የአራት አመት ልጅ እያለሁ በየቦታው ይጥለኝ ጀመር እማ በሀዘን ላይ ሀዘን ተጨመረባት አስበሽዋል ሶስት ልጆቿን ባሏን ያጣች ሴት መከራ በዛላይ እኔም በሽተኛ መሆኔ አላፊው አግዳሚው አላስቀምጥ አላት ያባቴ ዘመዶችማ ለነገሩ እሷ ስላለችኝ እንጂ እንኳን ያባቴን የራሷንም ዘመዶች አላቃቸውም ምክንያቱም የሷ ቤተሰቦች እንድታገባ ሲለምኗት አሻፈረኝ ካገባሁ ልጄ ይጎዳብኛል ስላለች እስከዛሬ ድረስ ማንም የሚፈልጋት የሚጠይቃት የለም አየሽ እናቴ ለኔ ስትል ስንት ነገር እንዳጣች አባ ሲሞት ቆንጆ ወጣት ነበረች ብታገባ ኖሮ እንደ ወንድ ሞፈርና ቀንበር አንዴ ከጓሮ አንዴ ከጓዳ ባልተንከራተተች ነበር ግን ለኔ ስትል ሁለት መልክ አወጣች መከራ ትንሽ ነው ብዙ ብዙ ነገር አየች
እኔ እናቴ የማስደስታት ቀንበር ይዤ ስከተላት አልነበረም ጓሮ ሄጄ ስቆፍር እንጨት ስሰብርላት አይደለም እውነተኛው የናቴ ደስታ ደብተር እስኪቢርቶዬን አንግቤ ለትምርት ስወጣ ነው ብዙ ጊዜ ትምርት አልማርም እላታለሁ እሷ ግን ምክንያቴን ስለምታውቅ ሰምቶ እንዳልሰማ አይቶም እንዳላየ ሁን ትለኛለች እዚህ ለመድረሴ የናቴ ትልቁ ምክሯ ይህ ነበር የልጆች ጨዋታን እየተጫወትኩ ሳይሆን እያየሁ እየዘመርኩ ሳይሆን እየሰማሁ ነው ያደኩት ማንም ልጅ ከኔ መጫወት ቢፈልግ እንኳን አይችልም ምክንያቱም የትኛውም እናት አባት አይፈቅድም መቅዲ እኔኮ ከሰው ጋር ስሆን አይደለም የሚያመኝ ግን ማንም አይረዳኝም ብሎ ለብዙ ግዜ ያመቀው ቁስል ስለሆነ ዛሬ ግን ፈነዳና አመመው ሳይጨርስላት እንባው ቀደመው አስተዳደጉ በሙላ አይኑ ላይ ተስሎ ስቅስቅ ብሎ አለቀሰ መቅደስም አንጀቷን በልቶት አብራው አለቀሰች..........
ጌዲዮ እንደምንም እንባውን ጠራርጎ ታሪኩን ቀጠለላት አየሽ እኔን ማንም ከሰው ተራ ቆጥሮኝ ስላላደኩ ዛሬም ሰው እፈራለሁ ብቸኝነቴን እመርጣለሁ ዝምታዬን እወደዋለሁ ለኔ የመኖር ምክንያቴ እናቴ ናት እሷ ናት ታሪኬ እንዳባት ሞፈር ተሸክማ እንደህት መክራ እንደወንድም ጋሻ ሆናኝ ከናት በላይ ብዙ ሆና ያኖረችኝ ታሪኬ እናቴ ብቻናት አየሽ መቅደስ አንቺ እኔን ከመደገፍሽ በፊት ከናቴ በቀር ማንም ጎንበስ ብሎ አንስትትምኝ አያውቅም ለዚም ነው አንቺን እንደናቴ ያየሁሽ አላት ሳያውቀው ለሷ ያለውን ስሜት ነገራት መቅደስ እጆቿን ከጉንጩ ሰዳ እንባዉን ጠረገችለት
ለብዙ ጊዜ ፍቅራቸውን እንዴት መግለፅ እንዳለባቸው ሲጨነቁ የነበሩት ጥንዶች ዛሬ ያለማንም ጣልቃ ገብነት አንድ ሜዳ ላይ ተገናኙ በርግጥም እውነተኛ ፍቅር የቃላት ድርደራ አይፈልግም ለካ እውነተኛ ፍቅር ባይን ጥቅሻ ብቻ ያግባባል በቃ በዝምታ ተያዩ ለመጀመሪያ ጊዜ ጌዲዮ ከንፈሩን ከሴት ከንፈር አገናኘው መቅደስ ለብዙ ጊዜ የናፈቀችውን ጌዲን በቅፎቿ አስገባችው በቃ ያለምንም አፈቅርሀለሁ አፈቅርሻለሁ ያለማንም አጃቢ በከንፈራቸው ቃልኪዳን አሰሩ
የፍቅር ድግሳቸው ትተጠነሰሰ ማንም ባይገምትም የጌዲዮና የመቅደስ ፍቅር እውን ሆነ የዛኑ ቀን ነበር ግቢው ይህን እውነት የሰማው ዮናስ ጌሙን ባደባባይ ተሸነፈ መቅደስ ከሱ ቁንጅና ይልቅ የጌዲዮ መልካምነት አሸነፋት ከዮናስ ማስመሰል የጌዲዮ ፍቅር በለጠባት የውጭ ማንነቱን ሳይሆን በውስጥ መልካም ስብእናው ባደባባይ የጌዲዮ ነኝ አለች ....
አብሮነታችሁን በላይክ ግለፁልን👍
ክፍል 18 ይቀጥላል...