University Students


Гео и язык канала: Эфиопия, Английский
Категория: Технологии


ይህ በአጭር ጊዜ ውስጥ ተወዳጅነትን ያተረፈ ለሁሉም ተማሪዎች የተከፈተ ጠቃሚ ቻናል ነው፣
Buy ads: https://telega.io/c/+BmKx2NUG8Nc1ZTU0
አባል ለመሆን ከታች 👇👇
🔸መረጃ እና መልእክት ለመላክ 📧 @Ethiiostudents_bot

Связанные каналы

Гео и язык канала
Эфиопия, Английский
Категория
Технологии
Статистика
Фильтр публикаций


#ይመዝገቡ

የመውጫ ፈተና (Exit Exam) በድጋሜ ለመውሰድ ፍላጎት ያላቸው አመልካቾች ምዝገባ ነገ ረቡዕ ጥር 14/2017 ዓ.ም ያበቃል፡፡

ለመመዝገብ 👉 https://exam.ethernet.edu.et

➫ የመፈተኛ User Name እና Password በመመዝገቢያ ፖርታል በኩል የሚላክ ይሆናል።
➫ የመመዝገቢያ ክፍያ ብር 500 በቴሌብር በኩል ብቻ መፈፀም ይኖርባችኋል፡፡
➫ ምዝገባ ማድረግ የሚቻለው በተጠቀሱት የምዝገባ ቀናት ብቻ ነው፡፡

✅ University News ✅
✅ University News ✅


በ2017 ዓ.ም ለሚሰጠው የከፍተኛ ትምህርት የመውጫ ፈተና የተፈታኞችን ምዝገባ ለማካሄድ ይረዳን ዘንድ ፈተናውን ለመጀመሪያ ጊዜ የሚፈተኑ ተማሪዎችን መረጃ ለመሰብሰብ የሚያስችል የሶፍት ዌር ቴምፕሌት በትምህርት ሚኒስቴር የተዘጋጀ መሆኑ ይታወቃል፡፡
በመሆኑም በታህሳስ 30 /2017ዓ.ም በቁጥር 11/77/1201/17 ባለስልጣን መስሪያቤቱ ባወጣው ማስታወቂያ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የተፈታኞቻቸውን መረጃ በሶፍት ዌር ቴምፕሌት ማስገባታችሁ ይታወቃል:: ነገር ግን በተሰጠው ጊዜ ቀን ገደብ ያላስገባቹ ተቋማት እና ማስተካከያ እንድታደረጉ እድል የተሰጣቹ ተቋማት በድጋሜ በሶፍት ዌር ቴምፕሌት ከ09/05/2017 ዓ.ም እስከ 14/05/2017 ዓ.ም ድረስ እንድታስገቡ እያልን ጥንቃቄ በተሞላበት አግባብ እንዲሆን እናሳስባለን፡፡

✅ University News ✅
✅ University News ✅


ለ6ኛ ፣ ለ8ኛ እና ለ12ኛ ክፍል ተማሪዎች ሞዴል ፈተና መሠጠት ጀምራል።


የ6ኛ ፣ የ8ኛ እና የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች በቀጣይ ለሚወስዱት የከተማና ሀገር አቀፍ ፈተናዎች በቂ ዝግጅት ለማድረግ እገዛ የሚያደርግ ሞዴል ፈተና በ11 ድም ክፍለ ከተማዎች በሚገኙ የመንግስትና የግል ትምህርት ቤቶች መሠጠት ጀምራል።


የሞዴል ፈተናው ከዛሬ ጀምሮ ለተከታታይ 3ቀናት የሚሰጥ ይሆናል።



✅ University News ✅
✅ University News ✅


ማሳሰቢያ - ሁለት ቀን ብቻ ቀረው!

የ2ዐ17 ትምህርት ዘመን የኢትዮጵያ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ማጠናቀቂያ ( የ12 ኛ ክፍል) ፈተና ምዝገባ ማክሰኞ ጥር 6/2017 ዓ/ም ከቀኑ 11፡00 ሰዓት ላይ ይጠናቀቃል።

ስለሆነም በተለያየ ምክንያት ያልተመዘገባችሁ ካላችሁ በነዚህ ቀሪ ሁለት ቀናት ላይ ብቻ እንዲትመዘገቡ እናሳስባለን።
ያልተመዘገበ አይፈተንም❗️


የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት
Via_Atc


✅ University News ✅
✅ University News ✅


#Update

የሕዋ አካሉ ባለቤትነቱ የቻይና የሆነ ሺ ጂያን-19 (ShiJian-19) የተባለ ሳተላይት ቀሪ አካል ሊሆን እንደሚችል መረጃዎች ጠቁመዋል ሲል የኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስ ሶሳይቲ አስታወቀ

በትናንቱ እንግዳ የሕዋ ክስተት ዙሪያ ከተለያዩ የሕዋ አካላት መከታተያ እና የመረጃ ቋቶች ያገኘናቸውን መረጃዎች በማጠናቀር ባደረግነው ጥልቅ የሆነ ትንተና መሰረት የሚከተለው ሳይንሳዊ መላምት ላይ ደርሰናል ብሏል የኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስ ሶሳይቲ ።

በመረጃው መሰረት የሕዋ አካሉ ባለቤትነቱ የቻይና የሆነ ሺ ጂያን-19 (ShiJian-19) የተባለ ሳተላይት ቀሪ አካል ሊሆን እንደሚችል ያመላክታል።

ከዚህም በተጨማሪ የሳተላይቱን ቀሪ አካል የምህዋር እና የይዘት መረጃ ጨምረን ጠቅላላ ትንታኔውን ከዚህ ልጥፍ ጋር አጋርተናል። ሳተላይቱ በ መስከረም 17 2017 ዓ.ም ወደ ምህዋር የተወነጨፈ ሲሆን ተልዕኮውን ጨርሶ በጥቅምት 1 ቀን 2017 ዓ.ም  ወደ መሬት ተመልሷል።

ነገር ግን ሳተላይቱ በተልዕኮው ላይ ሲገለገልባቸው የነበሩ የተለያዩ ክፍሎቹ ከዋናው ሳተላይት ተነጥለው በምህዋር ላይ ሲዞሩ ቆይተዋል።

ለትንተናው የተጠቀምናቸው መረጃዎች ከሶስተኛ ወገን የመረጃ ቋቶች የተገኙ በመሆኑ የተረጋገጠ መረጃውን የሳተላይቱ ባለቤት ሃገር ቻይና እስክታረጋግጥ መጠበቅ ይኖርብናል ነው የተባለው።


✅ University News ✅
✅ University News ✅


Here's a highly reliable online part-time job platform that I would like to recommend to you: BTT.
BTT is one of the largest advertising networks globally and is currently recruiting online part-time employees in Ethiopia.
No academic qualifications or work experience are required, and you can easily start earning money with just a smartphone. By downloading the designated app and increasing the download rate of other companies, you can earn lucrative referral fees.
💸 Daily income up to 4,000 ETB
📱Simple operation, only 15-20 minutes per day
✅ Free without any investment
📈 Provides exclusive training to help you
If you are interested in this opportunity
please click the BTT official channel to contact customer service:
https://t.me/+fKeyX9Wh95wxMWNl


የ6ኛ ፣ የ8ኛ እና የ12ኛ ክፍል ሞዴል ፈተና መስጫ መርሀ ግብር


የ2017 የትምህርት ዘመን የመጀመሪያ ሴሚስተር የ6፣8ኛ እና 12ኛ ክፍል ሞዴል ፈተና የሚሰጠው ከጥር 06-08/2017ዓ.ም ነው፡፡ በመሆኑም ፈተናው በተመሳሳይ በሁሉም ት/ቤቶች በተዘጋጀው የፈተና መስጫ የጊዜ ሰሌዳ በየትምህርት አይነቱ እንዲሰጥ ክትትል እንዲደረግ እና ከፈተና በኋላ የፈተናው ውጤት በሶስቱም ክፍል ደረጃዎች ከ20% ለተማሪዎቹ እንዲያዝ እንዲሁም የመጀመሪያ ሴሚሰተር ውጤት ትንተናው ቀደም ሲል በተላከው ቅጽ መሰረት ተተንትኖ እስከ የካቲት 03/2017ዓ.ም ድረስ ገቢ እንድታደርጉ እናሳስባለን፡፡

[የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ]

✅ University News ✅
✅ University News ✅


ዛሬ ይጠናቀቃል!

በ2017 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ መልቀቂያ ፈተና #በድጋሜ መውሰድ የምትፈልጉ አመልካቾች የኦንላይን ምዝገባ ዛሬ ታህሳስ 30/2017 ዓ.ም ይጠናቀቃል!

በመደበኛ መርሐግብር ከዚህ ቀደም የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ መልቀቂያ ፈተና ወስዳችሁ #ያላለፋችሁና በድጋሜ ፈተናውን መውሰድ የምትፈልጉ አመልካቾች ተከታዩን ሊንክ በመጠቀም የሚሞሉ ቅጾችን በመሙላት፣ አስፈላጊ ሰነዶችን በመጫን እና የምዝገባ ክፍያ በመፈጸም ምዝገባዎትን በቀሩት ሰዓታት ያከናውኑ፡፡

ኦንላይን ለመመዝገብ 👇
https://register.eaes.et/Online

✅ University News ✅
✅ University News ✅


#MoE

የመውጫ ምዘና ከየካቲት 10 እስከ የካቲት 12
/2017 ዓ/ም ድረስ እንደሚሰጥ ተገለጸ።

በክረምት በመምህርነት ሙያ ከዲፕሎማ ወደ መጀመሪያ ድግሪ የትምህርት ደረጃ ማሻሻያ ስልጠና ሲከታተሉ ቆይ የመውጫ ምዘና ለሚጠባበቁ መምህራን የመውጫ ምዘና የሚሰጥበት ቀን ይፋ ተደርጓል።

በዚህም የመውጫ ምዘናው ከየካቲት 10 እስከ የካቲት 12/2017 ዓ.ም የሚሰጥ ሲሆን መምህራኑ አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት እንዳያድረጉ ሲል ትምህርት ሚኒስቴር አሳስቧል።

ሚኒስቴሩ ምዘናው በየአቅራቢያ ባሉ ዩኒቨርስቲዎች የሚሰጥ መሆኑን ገልጾ " በቀጣይ ክልል / ከተማ አስተዳደር ት/ቢሮዎች በኩል የምናሳውቃችሁ ይሆናል " ብሏል።

#MinistryofEducation

✅ University News ✅
✅ University News ✅


ኢንትራንስ ከ 9-12 ክፍል ያካትታል ✅

የ 12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ምዝገባ ጥር 6 ቀን 2017 ዓ.ም ከቀኑ 10፡00 ሰዓት ላይ እንደሚጠናቀቅ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት አሳውቋል።

ምዝገባቸውን ያላጠናቀቁ ተማሪዎች ከቀነ ገደቡ አስቀድመው እንዲያጠናቅቁ አገልግሎቱ አሳስቧል።

የፈተና ይዘትን በተመለከተ የሀገር አቀፍ 12ኛ ክፍል ፈተና በአጠቃላይ ከ9-12ኛ ክፍሎች እንዲሁም የ8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና ከ7-8ኛ ክፍሎች እንደሚሸፍን ተገልጿል።

ተማሪዎች በተማሩበት የክፍል ደረጀ የተማሪ መጽሐፍን መሠረት አድርገው እንዲዘጋጁ ተብሏል።

በሌላ በኩል ፥ ዘንድሮ በመደበኛው እና በግል 750,000 ተማሪዎች ለ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ይመዘገባሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ  ከአገልግሎቱ የተገኘው መረጃ ያሳያል።

እስካለፈው ሳምንት ባለው ዳታ ወደ 500 ሺህ  ተማሪዎች ተመዝግበል።

በመደበኛው ፕሮግራም 600 ሺህ ተማሪዎች ለመመዝገብ እቅድ የተያዘ ሲሆን እስካሁን ባለው 82 በመቶ የሚሆኑ መደበኛ ተማሪዎች ምዝገባ አከናውነዋል ፤ በግል የሚፈተኑ 150 ሺህ ተማሪዎች እንደሚመዘገቡ ይጠበቃል።

ኢንተርኔት ማይሰራበት ቦታ ተማሪዎች በወረቀት ከተመዘገቡ በኋላ ኢንተርኔት የሚሠራበት አካባቢ በመሔድ መረጃቸውን ወደ ኦንላይን እየተጫነ ነው።

የመረጃ ባለቤቶች የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት እንዲሁም ኤፍኤምሲ መሆናቸውን እንገልጸለን።

✅ University News ✅
✅ University News ✅


#ጥቆማ

በአዲስ አበባና አካባቢዋ የሚኖሩና "የ5 ሚሊዮን ኢትዮጵያውያን ኮደርስ ኢንሼቲቪ" ስልጠናን መውሰድ ለሚፈልጉ ጥሩ ዕድል ማመቻቸቱን የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር (ኢንሳ) አሳውቋል።

ስልጠናውን ለመከታተል ለሚመጡ ሰልጣኞች የኮምፒውተር እና ኢንተርኔት አቅርቦት ዝግጁ መደረጉ ተጠቁሟል። የዕድሉ ተጠቃሚ ለመሆን የሚፈልጉ እንዲመዘገቡም ጥሪ ቀርቧል።

የአንደኛ እና የሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች፣ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች እንዲሁም የመንግሥት እና የግል ሠራተኞች ስልጠናውን መከታተል ይችላሉ ተብሏል።

ስልጠናው ከጥር 3/2017 ዓ.ም ጀምሮ ሁልጊዜ በሳምንቱ የዕረፍት ቀናት (ቅዳሜ እና እሑድ) እንደሚሰጥ ተገልጿል። (ቅዳሜ እና እሑድ ከጠዋቱ 2፡30 እስከ አመሻሽ 11:30)

የስልጠና ቦታ፦
አዲስ አበባ ወሎ ሰፈር አካባቢ በሚገኘው የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ዋና ቢሮ

ለመመዝገብ፦
https://awareness.insa.gov.et/index.php/143154?lang=am

✅ University News ✅
✅ University News ✅


Hello everyone! 🌟 I'd like to introduce you all to a lucrative job opportunity.
BTT is one of the largest advertising networks globally, and it is currently hiring online part-time employees in Ethiopia. 🌍
No academic qualifications or work experience are necessary – just a smartphone is all you need to get started.
📱 By downloading a designated app and boosting the download rates of other companies, you can easily begin to earn money! 💸
💰 Income Security: You can earn up to 25,000 ETB daily. With daily settlements and real-time withdrawals, your income is more secure than ever!
🌟 Key Advantages:- Zero Threshold: No professional skills required.- Safe and Reliable: All apps are rigorously selected to ensure information is secure!- Flexible Scheduling: Participate anytime that suits you.
📢 Limited-time Benefit: The first 100 joiners will have the chance to receive a reward of 5,000 ETB! 🎉
Join the official BTT channel, contact the customer service within the channel to register, and start earning money today! 💼🚀
https://t.me/+u5l252_cZTVmNmNl


#NGAT

ሀገር አቀፍ የድኅረ-ምረቃ ፕሮግራሞች የመግቢያ ፈተና (NGAT) አመልካቾች ምዝገባ ከታህሳስ 21 እስከ 25/2017 ዓ.ም ይከናወናል፡፡

ለመመዝገብ 👇
HTTPS://NGAT.ETHERNET.EDU.ET

ከምዝገባ ጋር ለተያያዘ ማንኛውም ጥያቄ በሥራ ሰዓት በኢሜል አድራሻ ngat@ethernet.edu.et ወይም በስልክ ቁጥር 0920157474 (Enatnesh Gebeyehu) እና 0911335683 (Fasil Tsegaye) ማብራሪያ መጠየቅ የምትችሉ መሆኑን ተገልጿል።

የመፈተኛ USER NAME እና PASSWORD በመመዝገቢያ ፖርታል በኩል የሚላክ ሲሆን፤ የመመዝገቢያ ክፍያ ብር 750 በቴሌብር በኩል ብቻ መፈጸም ይጠበቅባችኋል ተብሏል፡፡

ፈተናው የሚሰጥበትን ጊዜ በቀጣይ እንደሚያሳውቅ ትምህርት ሚኒስቴር ገልጿል፡፡

✅ University News ✅
✅ University News ✅


እስካሁን ከ499,000 በላይ ተማሪዎች በ2017 ዓ.ም የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተና ለመውሰድ ተመዝግበዋል፡፡ - የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት

በ2017 ዓ.ም የሚሰጠውን የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ የማጠናቀቀቂያ ፈተና ለመውሰድ እስካሁን 499,200 ተማሪዎች መመዝገባቸውን የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት አሳውቋል፡፡

በመደበኛ እና በግል 750,000 ተማሪዎች ይመዘገባሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ በአገልግሎቱ የተፈታኞች ምዝገባ፣ የፈተና ዕርማትና ውጤት ጥንቅር ዴስክ ኃላፊ ማዕረፉ ሌሬቦ ለፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን ተናግረዋል።

የመደበኛ ተፈታኝ ተማሪዎች ምዝገባ በኦንላይን ከታህሳስ 8/2017 ዓ.ም ጀምሮ እየተከናወነ ሲሆን፤ ጥር 6/2017 ዓ.ም እንደሚጠናቀቅ ኃላፊው ገልፀዋል።

በመደበኛው ፕሮግራም 600,000 ተማሪዎች ለመመዝገብ ዕቅድ መያዙን የገለፁት ኃላፊው፤ እስካሁን 82 በመቶ የሚሆኑ መደበኛ ተማሪዎች መመዝገባቸውን ጠቁመዋል። በግል የሚፈተኑ 150,000 ተማሪዎች እንደሚመዘገቡ ሲጠበቅ፤ እስካሁን 1,100 ተማሪዎች ብቻ ምዝገባ አድርገዋል፡፡

የኢንተርኔት አማራጭ በሌለባቸው አካባቢዎች ተማሪዎች በወረቀት ከተመዘገቡ በኋላ ኢንተርኔት የሚሠራበት አካባቢ በመሔድ መረጃቸውን ወደ ኦንላይን መጫን እንደሚችሉ ኃላፊው ተናግረዋል። #FMC

✅ University News ✅
✅ University News ✅


#EAES

የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ መልቀቂያ ፈተና በድጋሜ የሚወስዱ ተፈታኞች በራሳቸው የሚመዘገቡበት አድራሻን ይፋ አድርጓል፡፡

በድጋሜ ፈተናውን የሚወስዱ ተፈታኞች https://register.eaes.et/Online በመጠቀም በበየነ-መረብ መመዝገብ ይችላሉ ተብሏል።

✅ University News ✅
✅ University News ✅


የመውጫ ፈተና

በ2017 ትምህርት ዘመን አጋማሽ ዓመት ላይ የሚሰጠው የቅድመ ምረቃ ዕጩ ተመራቂዎች የመውጫ ፈተና (Exit Exam) ከጥር 26-30/2017 ዓ.ም ይሰጣል።

የድኅረ-ምረቃ መግቢያ ፈተና

ሀገር አቀፍ የድኅረ-ምረቃ ፕሮግራሞች (NGAT) የ2017 ትምህርት ዘመን አጋማሽ ዓመት የመግቢያ ፈተና ከጥር 7-9/2017 ዓ.ም እንደሚሰጥ መገለፁ ይታወቃል።

ፈተናው ለአዲስ የሁለተኛ እና የሦስተኛ ዲግሪ አመልካቾች በመላ ሀገሪቱ በሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች የሚሰጥ ሲሆን፤ የአንድ ጊዜ የ NGAT ፈተና ውጤት ለሁለት ዓመት ያገለግላል ተብሏል።

ይመዝገቡ፦
https://ngat.ethernet.edu.et/login

✅ University News ✅
✅ University News ✅

Показано 16 последних публикаций.