💛💞መልካም ልቦች™💞💛


Гео и язык канала: Эфиопия, Амхарский
Категория: Другое


🥀♡ ማፍቀር ስትጀምር ከእምነት ጀምር ♡🥀
⚡️WELLCOM TO MELKAM LBOCH 💜
💚 በዚህ ቻናል ውስጥ ደስ የሚሉ የ ፍቅር ቃላቶች፣ግጥሞች፣የፍቅር ታሪኮች ያገኛሉ !
● ቻናላችንን SHARE ያድርጉ 🙏
➤ For any promotion and Advertising 📩
👉 @Z_afro ያነጋግሩ::

Связанные каналы

Гео и язык канала
Эфиопия, Амхарский
Категория
Другое
Статистика
Фильтр публикаций


🐍አሁኑኑ Start በማለት ጀምሩት 1ወር አለው ለማለቅ🫥 task የሚለውን በመንካት ቶሎ ማደግ ያስችላቹሀል🤩


ZOO አዲሱ የX-Empire ፕሮጀክት...

| ምትሰበስቡት ነጥብ ቀጥታ ወደ ቶክን ይቀየራል
| ፕሮጀክቱ ለጥቂት ግዜ የሚቆይ ስለሆነ አያሰላቻም
| አጨዋወቱ እንስሶችን በተሰጣችሁ Feed መመገብና Upgrade ማድረግ ነው
| ብዙ ሰው ስላልበዛበት በግዜ ብትጀምሩ ይመረጣል
| አጨዋወቱን በቪዲዮ በቅርብ ግዜ ዉስጥ እንለቅላችኋለን

ለመጀመር
http://t.me/zoo_story_bot/game?startapp=ref756016762


ፅጌሬዳ



ክፍል 35


ማሂ እንደተባለው ቀኝ እጇ ላይ እና ጎኗ ላይ የደረሰባት አደጋ እጇ መንቀሳቀስ እንዳይችልና በስርአት መራመድ እንዳትችል አድርጓታል ቁጭ ማለትም ብዙም አትችልም ።

እኛ ግቢውን አሟሙቀን እሳት እያነደድን ጥብስ እየጠበስን አንዳችን አንዳችንን ስናስተናግድ እሷ የተዘጋጀላት ፍራሽ ላይ ጋደም ብላ በፈንጠዝያ ታየናለች።

እየሰራሁ አይኔ ከሷ ላይ አይነቀለም አይኗ ከኔ ላይ አይነቀለም እንደልጃገረድ ስታሽኮረምመኝ ሳሽኮረምማት አመሸን።

ቡሀላ ላይ በላልተን ወደ መጠጥ ሲገባ ትላልቆቹም የራሳቸውን ወሬ እኛም የራሳችንን ወሬ ያዘንና ጨዋታውን አደራነው።

እህቴ እኔ ምልሽ ማሂ ግን እዚህ ቤት ውስጥ አንቺና አባትሽ ብቻ ስትኖሩ የመጠፋፋት አደጋ አጋጥሟችሁ አያቅም እእእ መንግስት ግን ይሄን ሁሉ ይዞታ ይዛችሁ እንዴት ዝም አላችሁ የላይኛው ሳሎናችሁ ብቻኮ 3 ቤተሰብ
የታችኛው 5 ቤተሰብ የሚያኖር ቤት ነው አንቺና አባትሽ ብቻችሁን ተሸክማችሁት ኖርር አላችሁ አደል አለቻት።

ማሂ ፈገግ ብላ ይሄ የምታይው ቤት ቤት እንዳይመስልሽ መሰረቱ የተጣለው በናቴ ባባቴ የደም ላብ ነው።
አባቴ ከዚህም በላይ ይገባዋል።

ከናቴጋ ሲጋቡ የኔን መታጠቢያ ቤቴን የምታክል ቤት ተከራይተው ነበር የሚኖሩት።
ያው ምን ዋጋ አለው እናቴ ይሄንን ሳታይ ተንደላቃ ለመኖር ሳትታደል ቀረች የሷን እጣ ፈንታ እኔ ወሰድኩት አለች እንባ እየተናነቃት።
የዛኔ እህቴ ደንገጥ አለችና አረ ማሂ እኔኮ ለቀልድ ነው ጨዋታውን ያነሳሁት ምኑን ከምኑ አገናኘሽው ገና መች ፈጣሪን አመሰግነሽ ጨረሽና ነው ወደለቅሶ የገባሽው ብላ ተቆጣቻት።

ስንሳሳቅ አመሸን ያ ድንጋጤ ሰሞኑን የነበረው ሀሳብ ጭንቀት ሆስፒታል የማደሩ ድካም ባንዴ ለማጥፋት እየሞከርን ያለን ነው ሚመስለው።

ማሂ ፈገግ ብላ ሁላችንንም በየተራ ካየች ቡሀላ አይገርምም ግን እንደቀልድኮ ሰፊ ቤተሰብ ኖረን ።

ያለምክንያት አደለም ገና እንዳየሁህ እንደዛ ያሳዘንከኝ መጥቼ መተኛት ያልቻልኩት።
ለማንኛውም ግን የናትህና ያባትህ ቤታቸውን ዘግተው መምጣታቸው ምን ያህል እንዳስገረመኝ አልገባችሁ አለች።

አረ ማሂ የኛ ወላጆችኮ እንደዚህ ናቸው ሀዋሳ ላይ በደግነታቸው በፍቅራቸው ነው ሚታወቁት ላንቺ ደሞ ይሄ ሲያንስብሽ ነው ምን አደረጉልሽና አልተሸከሙሽ ዋናው ነገር እንኳን ተረፈሽልን አለቻት።

ሰአቱ ወደሌሊቱ ሲቃረብ ሁላችንም ገባንና ቦታ ቦታችንን ያዝን።

ጠዋት ላይ እህቴ የማሂን ልብስ ቀይራላት ለቁርስ ይዛት መጣች።
ቁርሳችንን እየበላን እናቴና አባቴ ዛሬ እንሂድ መባባል ጀመሩ አቶ ሳሙኤልም እሺ መልካም እኔ ነኝ ማደርሳችሁ አሉ።
እነሱ አይሆን አንተ ታማሚ ልጅ ቤት ትተህ እኛን ለማድረስ እዛ ድረስ አትንከራተትም አሉ።

ምግቡን በልተን እስክንጨርስ እየተከራከሩ ማሂ እረጅም ሰአት ቁጭ ማለት ስለማትችል ወደ አልጋዋ ይዣት ሄጄ አስተኛኋትና ቁጭ ብለን ማውራት ጀመርን በመሀል ስልክ ተደወለላት ።
አንስቼ የተደወለላት ቁጥር አሳየኋት አላቀውም አንሳና ስፒከር ላይ አርገው ጆሮዬ ላይ ይዤ ማውራት አልችልም አለች።

እሺ ብዬ አነሳሁና ስፒከር ላይ አደረኩላት።

ሄሎ አለች።
ሄሎ አንቺ በረሮ አላት ከወዳኛው መስመር የሚመጣው የወንድ ድምፅ።

አቤት አቤት ምን አልክ አለች ኮስተር ብላ

ምን አልክ ነው ያልሽው ያልኩትማ መች ነው የጀመርነውን ምንጨርሰው እያልኩሽ አይገርምሽም እንደዛ ተገጭተሽ መትረፍሽ አላት።

የዛኔ ከሷ በላይ የኔ ፊት ቅይር አለ ።
አንተ የቀድሞ ባለቤቷ ነህ እንዴ አልኩት???!
ኦኦኦ ይገርማል ጎረምሳሽ እንዳለ አላወኩም ነበር የጎዳናው ልጅ ነህ አደል አለኝ እያፌዘ።

ስልኩን ይዤ ከተቀመጥኩበት ብድግ አልኩኝ ትሰማኛለህ ከእንዳንተ አይነት ከድንጋይ የባሰ ድንጋይ ከሆነ ሰውጋ በማውራቴ አፍራለሁ ግን አንድ ነገር ልንገርህ ወንድ ልጅ ከሆንክ ጓዳ ጓዳውን እየተደበክ ሴቷጋ ደውለህ አታስፈራራ እኔጋ ደውል ከሷጋ ለቀረህ ለእያንዳንዱ ጉዳይ እኔ አለሁ።
ሌላው የምነግርህ ነገር ምንም የወንድነት መስፈርት የማታሟላ ተራ ሰው መሆንህን ልነግርህ እፈልጋለሁ አልኩት።

ብሮ አፍህን በከፈትክ አደለም
ለማንኛውም የጀመርኩትን እጨርሰዋለሁ በልልኝ አለኝና ስልኩን ዘጋው።

ፈጠን ብዬ ሄጄ ለአቶ ሳሙኤል ስልኩን ሰጠኋቸውና ለፖሊሶቹ እንዲልኩላቸው አደረኩ።

ወደ ማሂጋ ስመለስ በንዴት ፊቷ ቀልቶ እያለቀሰች ነው።
ምኗ ደደብ ነኝ ከዚህ ጋር የሆንኩት
አሁን ላይ ከሱጋ ቆሜ ለታየሁት ሁላ እያፈርኩ ነው።

ቆይ እኔ ሳላስቀይመው ካፌ ክፉ ሳይወጣ ከሌላ ሴትጋ አልጋዬ ላይ ይዤው ።
ገመናው ሸፍኜ እንደፈለገ ይሁን ብዬ ከህይወቱ ስለወጣሁ ለኔ ይሄ ነው ሚገባኝ እእ።
ቆይ ዝም ስላልኩት የፈራሁት መስሎት ነው ወይስ ዘላለሙን እየተጫወተብኝ እንዲኖር ስላልፈቀድኩለት ነው።

ቆይ አባቴ በትንሽ ቀን ውስጥ ልክ ካላስገባዎ ምን አለች በለኝ አለች።

አቅፌ አፅናናኋት የራሴን ንዴት ወደጎን ጥዬ የሷን ማብረድ ጀመርኩ።

በድንገት ጭንቅላቴ ውስጥ አንድ ሀሳብ ተተኮሰ ከተቀመጥኩበት ተስፈንጥሬ ተነሳሁን ማሂ ላይ ትኩር ብዬ እያፈጠጥኩ ለምን ወደ ሀዋሳ አኔድም ለምን ከዚህ አካባቢ ትንሽ እራቅ አንልም በዛውምኮ እናቴ አሪፍ አድርጋ ታስታምምሻለች እህቴም አሁን ስራ እየሰራች ስላልሆነ ቀን ቀን እኛጋ ትውላለች እኔም የቀሩኝን ጉዳዮቼን እጨራርሳለሁ ማሂ በኔ ይሁንብሽ ህክምናሽንም እዛ ሚገርም ሆስፒታል እንድትከታታይ እናደርጋለን በፈጠረሽ እሺ በይኝ አልኳት።

አይኗን ሳታሽ እሺ እኔ ደስ ይለኛል ግን አባቴስ አለች።

ችግር የለም እሳቸውም ስራ ሲኖራቸው እዚህ ሳይኖራቸውም ደሞ ሀዋሳ እያሉ መቆየት ይችላሉ ትንሽ ጊዜኮ ነው አልኳት።

እሺ ግን አባቴን ጠይቀው መጀመሪያ አለችኝ።


✎ክፍል 36 ነገ ማታ 2:30 ይቀጥላል♥️    ቶሎ እንዲ🀄️ጥል LIKE♥️ እና Share አድርጉ።


  ይ🀄️ላ🀄️ሉን
https://t.me/+4dGFaH_mUnExZjg8
https://t.me/+4dGFaH_mUnExZjg8

💝የዩቲዩ ገፃችን💝
https://www.youtube.com/@Kezerareaction333
https://www.youtube.com/@Kezerareaction333

4.1k 0 21 14 275

🐍አሁኑኑ Start በማለት ጀምሩት 1ወር አለው ለማለቅ🫥


ZOO አዲሱ የX-Empire ፕሮጀክት...

| ምትሰበስቡት ነጥብ ቀጥታ ወደ ቶክን ይቀየራል
| ፕሮጀክቱ ለጥቂት ግዜ የሚቆይ ስለሆነ አያሰላቻም
| አጨዋወቱ እንስሶችን በተሰጣችሁ Feed መመገብና Upgrade ማድረግ ነው
| ብዙ ሰው ስላልበዛበት በግዜ ብትጀምሩ ይመረጣል
| አጨዋወቱን በቪዲዮ በቅርብ ግዜ ዉስጥ እንለቅላችኋለን

ለመጀመር
http://t.me/zoo_story_bot/game?startapp=ref756016762


ፅጌሬዳ



           ክፍል 34

አዎ ማስረጃዎቹ የሚያሳዩት እሱን ነው እርሶ ሀሳብ አይግባዎት የገባበት ገብተን እንይዘዋለን።
ከዛ በፊት ግን እርሶ ሚጠረጥሩት አካል ካለ ለኛ ብታሳውቁን ነገሩ ይበልጥ ቀላል ይሆናል ።
ምናልባት ማህሌት ከዚህ በፊት የተጣላችው ወይ ያስፈራራት ሰው ካለ ድንገት የነገረቾት ነገር ካለ ብትነግሩን
አንተም ምናልባት ቅርበት ካላችሁና ጓደኛህ ከሆነች ማወቅህ አይቀርም ትንሿ ፍንጭ ለኛ ትልቁን ወንጀል ማጋለጫችን ናት አለ ወደኔ ዞሮ እያየ
አይ አለቃ እኔ ምንም አላውቅም ።
ድንገት ግን አዲስ ነገር ካለ እናሳውቅሀለን አልኩት ።
እቶ ሳሙኤል እጃቸውን ከአገጫቸው ላይ ሳያነሱ አለቃ ይሄን ጉዳይ እንደቀላል እንድታዩት አልፈልግም ልጄ ማለት ለኔ ምን እንደሆነች መገመት አይከብዳችሁም ደሞ እርግጠኛ ነኝ ይሄ ከእናንተ አቅም በላይ አይሆንም እምነቴን በናንቴ ላይ ነው የጣልኩት ብለው ሞቅ ያለ ሰላምታ አቅርበውላቸው ስልክ ተቀያይረው  ከፖሊስ ጣቢያ ወጣን ።

መኪና ውስጥ ገብተን ወደ ሆስፒታል  እየሄድን እንደዚህ አይነት ቦታ ላይ ህመምህን ጉዳትህን ዋጥ አድርገህ ጉልበት ያለው ጀግና ሰው ሆነህ ነው መታየት ያለብህ ።

ተራ ሰው ሆነህ ስትቀርብ ጉዳይህንም እንደተራ ያዩታል ከበድ ያለ ስትሆንባቸው ደሞ ጉዳይህንም ያከብዱታል አሉኝ።

እንባ እየተናነቃቸው ነበር ሲያወሩ የነበረው በህይወት ዘመኔ እኔ እስከማቀው አንድም ቀን ከሰውጋ ጠላትነት ኖሮኝ አያውቅም ከሰውጋ ተጣልቼ ለእርቅ ተቀምጬም
አላውቅም።

እኔ ማንንም ስለማጥቃት አስቤ ሰውም ሊያጠቃኝ አስቦ የሚያውቅ አይመስለኝም።

ከኔ ደሞ አስር ሺ እጥፍ ማሂ ትብሳለች እንኳን የመግደል ሙከራ ሊደረግባት ይቅርና ክፉ ስድብ ለመስደብ እንኳን ምታሳሳ ልጅ ናትኮ ማን እሷ ላይ ይህን ሊያስብ ይችላል አሉ።

የኔም ጥያቄ እሱ ነው አንድ ነገር ልነግሮት ፈልጌ እየፈራሁ ነው ማለቴ ድንገት ሊያናድዶት ይችላል ብዬ አሰብኩ አልኳቸው።
ምንድነው ንገረኝ በዚህ ሰአት የንዴት ጥቅ ውስጤ እየተቀጣጠለ ነው ዝም ስላልኩኝ ስላልጮኩኝ የተረጋጋሁ እንዳይመስልህ በውስጤ መያዝ ስለለመድኩ ንዴትንም ብሰሸጭቴንም ሀዘኔንም ውስጤ ስለምጨርስ ነው ንገረኝ አሉኝ።

ያው ማለቴ ባለፈው ማሂ ደውላልኝ እያወራን ነበር ከዛ ግን የሆነ ሰው እየተከተለኝ ነው ብላ አረጋግጪ ስላት ድንገት ካይኗ ተሰወሩ ።
በሚቀጥለው ቀንም እንደዛው የሆነ መኪና እየተከተለኝ ነው ብላኝ ነበር።

ይሄ ነገር ከተደጋገመ ብዬ በሚቀጥለው ቀንም ስጠይቃት ማንም የለም ስትለኝ ዝም አልኩኝ ይኸው ይሄ ነገር ተፈጠረ አልኳቸው።
መኪናውን ሲጥጥጥ አድርገው አቆሙት እና ከምር እንደዛ ብላህ ነበር ከምር አንተ ይሄን ሰምተህ እንደተራ ነገር ችላ አልከው እሷስ ከኔ ካባቷ ይህን ደበቀች ማመን አልችልም አሉኝ በሀዘኔታ አይን እያዩኝ።

አደለምኮ ቀለል አድርጋ ስትነግረኝ እኔም ያን ያህል እንደትልቅ ነገር አላሰብኩትም ይቅርታ አድርጉልኝ አልኳቸው።

አስኳሁን ፖሊሶቹ ልክ ላይሆኑ ይችላሉ አደጋ ሊሆን ይችላል እነሱ የግድያ ሙከራ የደረሰ መስሏቸው ነው ማሂ ስትነሳ አደጋ ነው ትለኛለች ብዬ ተስፋ እያደረኩ ነበር በውስጤ
ግን አሁን አንተ አረጋገጥክልኝ ማሂ ሞታ ቢሆን ለራስህ የዘላለም ፀፀት ነበር ምትይዘው ምን ችላ መባል እንዳለበትና እንደሌለበት ጠንቅቀህ ማወቅ ነበረበህ አሉኝ እያፈጠጡ።
አንገቴን ደፍቼ ዝም አልኳቸው።
    
ሆስፒታል ስንደርስ እህቴና ሰራተኛዋ ምሳ ይዘው ሊመጡ ወደቤት ሄደዋል ሌሎቹ ቁጭ ብለው እየጠበቁ ነበር።

አቶ ሳሙኤል ስቅቅ እያሉ ተጨነቄ አስጨነኳችሁ አደል ቤታችሁን ዘግታችሁ እዚህ ሆስፒታል ተቀምጣችሁ ልትውሉ ነው አሏቸው።
እናቴ በዛ ጣፋጭ አንደበቷ  ተው እንጂ እንደዚህ አይባልም አንተ ለኛ ልጃችንን ወልደህ አደል እንዴ የሰጠኸን እኛ አሁን ምን አደረግንልህና ነው ና ይልቁኑ አረፍ በል አለቻቸውና አረፍ አሉ።

ምሳችንን ይዘውልን መጡና በላን ።
ዶክተሩ ቁርጥ ያለውን ነገር እስኪነግረን እየጠበቅን ነበር ።

ማታ ላይ አቶ ሳሙኤልና አባቴ ዶክተሩጋ ገቡና አወሩት ።
ሲመለሱ ምን እንዳላቸው ለመስማት ጓጉተን እየጠበቅን ነበር።
ምናልባት ሆስፒታል ውስጥ አንድ ሳምንት ወይም 15 ቀን ካልሆነም ከዛ በታች ልትቆይ ትችላለች እንዳላቸው ነገሩን።

አቶ ሳሙኤል ሰብሰብ አደረጉንና በቃ አሁን ቁርጡን ስላወቅነው እናንተም ወደቤታችሁ ወደ ሀዋሳ ተመለሱ ናታኔም ከኔጋ ይቆያል አሉ።

አባቴ እኔ ከዚህ ለመሄድ ምንም የሚያስቸኩል ጉዳይ የለኝም እዚሁ ነው ምቆየው አለ።
እናቴም እኔ ቢያንስ አንዳንድ ቀን ሆስፒታል እያደርኩ እንድታርፉ አደርጋችኋለሁ እዚሁ ነው ምሆነው አለች።

እህቴም ቀጠለች ምንም ቢሆን ሚዜዬ ነበረች በደስታዬ ቀን ከጎኔ ቆማለች ሰርጌን አድምቃልኛለች ስለዚህ አሁን እሷ ሆስፒታል ተኝታ ለመሄድ የሚያስቸኩለኝ ጉዳይ የለም አለች።

አቶ ሳሙኤል ፈገግ አሉና መቼስ ልጄ ሆስፒታል ከገባች ጀምሮ የሚመጣውን ሰው አይታችሁታል  እኔ ከተማው ላይ የማላቀው የማያቀኝ ሰው ያለ እስከማይመስለኝ ድረስ ነው ሚሰማኝ ለማሂ ሰርግ አድማቂ የነበሩ ሚዜዎቿ አጃቢዎቿ መቀመጫ እስኪጠፋ የነበሩት እነዛ ሁላ እንግዶች ዛሬ የሉም  የመጡትም የይውጣልኝ ደረስ ብለው ለመመለስ ነው ።
እናንተ ግን በቃ እኔጃ
ፈጣሪ ሰዎችን ደስተኛ ሊያደርግ ሊያከበር ሲፈልግ ሰው ነው ሚሰጣቸው ሁላችሁንም አመሰግናለሁ።

ግን ችግር የለውም  በቃ ሂዱ እዚህ ምንም አንሰራም አሉ ።
እኔ ባይሆን እህቴ አዲስ ሙሽራ ስለሆንሽ ከባልሽጋ ብትመለሽ ባይ ነኝ እናቴና አባቴ ግን በናንተ ፍላጎት ይሁን አልኳቸው።

አዎ ልጄ በቃ እናንተ ሂዱና ባይሆን ትመለሻለሽ ከሆስፒታል ምትወጣ ቀን ቤቱን አሟሙቀሽ ትጠብቂናለሽ አለቻት እናቴ።
በቃ እናንተ እንዳላችሁ ብላ እህቴና ባሏ  በነጋታው ወደሀዋሳ ተመለሱ።

በሶስተኛው ቀን ማሂ መናገር ጀመረች ፖሊሶቹ በምን ፍጥነት እንደመጡ ሳይታወቅ መጡና መረጃ ልንወስድ ነው ብለው ወደ ውስጥ ገቡ ለሷ አንዳንድ ጥያቄዎችን ማቅረብ ጀመሩ ።
ማሂ ብዙ ሳትለፈልፍ የቀድሞ ባለቤቴ ነው እንደዚህ ያደረገኝ ከስራ ቦታ ወጥቼ እየሄድኩ ሲከተለኝ ነበር ።

የማይሆን ቦታ ላይ ስደርስ መኪናዬን ከአስፋልት አስወጥቶ እንዲገለባበጥ ለማድረግ ከኋላ መጥቶ ገጨኝ አለች።

አንቺ እሱ መሆኑን እንዴት አወቅሽ ከኋላ ከገጨሽ አሏት ፖሊሶቹ።

እኔ ከኋላ እየተከተሉኝ እንደሆነ ስላወኩ ተጠንቅቄ ነበር ስነዳ የነበረው እና መጥቶ ከገጨኝ ቡሀላ መስታዎቱን ከፍቶ ምን አይነት ጉዳት እንዳደረሰብኝ ቼክ እያደረገ ነበር ጋቢና አብሮት ጠቆር ያለ ፂማም ልጅ ነበረ አለች። አንዳንድ ጥያቄዎችን ከጠየቋት ቡሀላ ምስጋናቸውን አቅርበው  ለአቶ ሳሙኤል የልጆትን ባል ቤት ልታሳዩን ትችላላችሁ አሏቸው ...

እሺ ብለው አብረዋቸው ሄዱ ግን እሱ ቤት አልነበረም ።
አቶ ሳሙኤል ፊታቸው ጥቁር እንዳለ ተመልሰው መጡ ።

አየህ አደል ልጄ አንዳንድ ሰዎች ወደህይወትህ በግድ ጥላቻን ይጠራሉ።
ማሂ ምን ብትበድለው ምን ብታስቀይመው በትዳር ተጣምረው ሚስቴ ነሽ ብሎ የተቀበላትን ሴት ለመግደል ይሞክራል።


✎ክፍል 2 ነገ ማታ 2:30 ይቀጥላል♥️    ቶሎ እንዲ🀄️ጥል LIKE♥️ እና Share አድርጉ።


  ይ🀄️ላ🀄️ሉን
https://t.me/+4dGFaH_mUnExZjg8
https://t.me/+4dGFaH_mUnExZjg8

💝የዩቲዩ ገፃችን💝
https://www.youtube.com/@Kezerareaction333
https://www.youtube.com/@Kezerareaction333

5.3k 0 24 15 339

ጨርሰክ እንውጣ አሉኝ አዎ አልኳቸውና ከግቢ ወጣን ።
ወዴት ነው ምንሄደው አልኳቸው።
ፍትህ ወዳለበት አሉኝ።
እሺ ብዬ ዝምም አልኩ
ትንሽ ከሄድን ቡሀላ ቆምንና ምግብ እንብላ አሉኝ። ባልፈልግም እሳቸው እንዲበሉ ብዬ እሺ አልኳቸው እኔ የቀረበውን ምግብ ነካ ነካ ሳደርገው እሳቸው ጥርግ አድርገው በሉና ከጨረስክ እንሂድ አሉኝ።

እሺ ብዬ ተከተልኳቸው ጉዟችንን የፖሊስ ጣቢያው በር ላይ ቋጨነው።

ቆፍጠን በል ፖሊሶቹ ፊት ውስጥህ ካለው ጉዳት ይልቅ ፊትህ ላይ የሚነበበውን ቁጣ አሳያቸው ።
በምንም ሁኔታ ስሜታዊ እንዳትሆን ትኩረታቸውን ሙሉ በሙሉ ማግኘት አለብን አሉኝ እሿ አልኳቸው ወደ ውስጥ ሲገቡ ተከተልኳቸው።

ገና ከበር ጀምሮ ሞቅ ያለ ሰላምታ ቀረበላቸው።
ውስጥ ላይ ጉዳዩን የያዘው ዋናው እየጠበቀን ነበር ።

አቶ ሳሙኤል ቆፈጠን ብለው ሰላምታ ካቀረቡ ቡሀላ እኔን አስተዋውቀው ቁጭ አሉ።

በጣም ይቅርታ ጉዳቱ የደረሰ ቀን ምንም በስርአት ላወራችሁ ልሰማችሁ አልቻልኩም ተገቢውን መረጃም አልሰጠኋችሁም በሱ ደሞ እንደምትረዱኝ ተስፋ አደርጋለሁ ጉዳዩንም ችላ እንዳላላችሁትና የሆነ ፍንጭ እንዳገኛችሁ ተስፋ አደርጋለሁ አሉ።

አዎ በሚገባ የእርሶ ልጅን ጉዳይ ችላ ማለት በራሱ እንዴት ይታሰባል አለ

የዛኔ አቶ ሳሙኤል በፖሊስ ጣቢያም እጃቸው ሰፋ ያለ እንደሆነ ገባኝ ንግግራቸውን በጥሞና ለማዳመጥ ቁጭ አልኩኝ።

አእእ እንግዲህ እኛ እጃችን ላይ ያለው መረጃ ልጆት ላይ የደረሰው አደጋ በድንገት የተፈጠረ ሳይሆን ሆን ተብሎ ታስቦበበት የተደረገ መሆኑን አረጋግጠናል።

መኪናዋ ላይ የደረሰው አደጋ በከፍተኛ ሁኔታ ጥቃት ለማድረስ ታስቦበት ቢሆንም እንግዲህ በፈጣሪ እርዳታ ልጆት ተርፋለች ግን መኪናዋን ማየት እንችላለን እሱ ትልቅ ማስረጃ ነው።
ይበልጥ ደሞ ልጆት እስክትነቃ ነው እየጠበቅን ያለነው።

እሷጋ ሁሉም እውነታ አለ በሰአቱ ምን እንደተፈጠረ ጉዳት ያደረሰባት አካል ማን እንደሆነ ታውቃለች ብለን ተስፋ እያደረግን ነው አለ ።

አቶ ሳሙኤል ፊታቸው ቅይር አለ።

እጃቸውና እግራቸው መንቀጥቀጥ ጀመረ።

so ልጄ ላይ የግድያ ሙከራ ነው የተደረገባት እያላችሁኝ ነው አሉ

5.5k 0 20 13 280

ፅጌሬዳ




ክፍል 33



በውስጤ ስንቱን ስለት እንደተሳልኩት እኔና መድሀኒአለም እናውቃለን።

እግሬ እየተሳሰረ ነበር ሰዎች ጉልበቴ ከዳኝ ሲሉ  ምን ማለት እንደሆነ አይገባኝም ነበር የዛን ቀን ግን በደንብ ተገለጠልኝ።
ሆስፒታል ስደርስ አቶ ሳሙኤል ሰራተኛቸውና የስራ ባልደረቦቻቸው አብረዋቸው ቁጭ ብለዋል ።

አየኋቸው አቶ ሳሙኤልን አየኋቸው ደና ናት ደና ናት አልኳቸው ካፋቸው ሚወጣውን ቃል ነበር ምጠብቀው ደና አደለችም ግን ትሆናለች አሉ
እኔን ሲያዩ እንደ አዲስ እያለቀሱ ነበር
አይናቸው ለማየት እስከሚያስቸግር ቀልቷል አብጧል ፊታቸው ፍም መስሏል ያ ግርማ ሞገሳቸው ባንድ ቀን ግፍፍ
ብሏል የለበሱት የሌሊት ቢጃማ ነው።

እኔን ሲያዩ ባሰባቸው ሁለታችንም ማልቀስ ጀመርን
ተው ተረጋጉ ደግ አደለም እንደዚህ አይኮንም ብለው ተቆጡን ።

እሺ አሁን ምን እስኪሉን እየጠበቅን ነው አልኳቸው።
ከአቶ ሳሙኤል ጓደኞች መሀል አንዱ ሰውዬ መጡና ልጄ ቢያንስ አንተ ወጣት ነህ ልብህን ጨከን አድርግና አባቷን አረጋጋ እንጂ አንተ አትባስ እኛ የዶክተሩን ምላሽ እየጠበቅን ፈጣሪ ከልሏታል በጣም አልተጎዳችም እሺ አሉኝና ወደ ወንበሩ ወስደው አስቀመጡኝ።

ከዛ ቀን በፊት የማላቀው መኪና ውስጥ የተዋወኩት ልጅ እንደጓደኛ አብሮኝ ሆኖ ሆስፒታል ውስጥ ሲጨነቅ ነበር ገረመኝ አንዳንድ ሰው ግን ምን አይነት ልብ እንዳለው ብቻ ይገርማል።

እኛ ቁጭ ብለን እየጠበቅን አባቴ ደወለና የት ናችሁ ምን ሆስፒታል ነው ያለችው አለኝ።

አብሮኝ ለነበረው ልጅ ያባቴን ስልክ ሰጥቼው እንዲቀበለው ነገርኩት እሺ ብሎ ወጣና ተቀብሏቸው መጣ ።

እናቴ አባቴ እህቴና የእህቴ ባል ነበረሰ የመጡት ሳያቸው ልክ ማሂ የዳነች ነው የመሰለኝ ደስ አለኝ።

አቶ ሳሙኤል ብድግ አሉና አረ በፈጣሪ ስም እናንተ አሁን ለምን ተቸገራችሁ በምን ፍጥነት ነው የመጣችሁት ቤታችሁን ዘግታችሁ መጣችሁ አደል አሉ እንባ እየተናነቃቸው።

እቅፍ አደረጋቸውና አይዞህ ጓዴ በህይወት ውስጥ መውደቅ መነሳት መታመም መዳን ያለ ነገር ነው ምንም አትሆንም ሳምንት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ቆማ ስትራመድ ታያታለህ በፈጣሪ እምነት ይኑርህ አላቸው።

አምናለሁ እሱ እንደሰው አደለም ፍርዱ አይጓደለም ማሂ ምንም አትሆንም የየዋህ አምላክ አይተዋትም አሉና ከአባቴጋ ተያይዘው ቁጭ አሉ ።
ሰአቱ ወደ11 ሰአት እየተጠጋ ነበር ማንም ነገር አይለንም የአቶ ሳሙኤል ጓደኞቹም ምን እንደሚሉ ሳንሰማ አኔድም ብለው ቁጭ ብለው እየጠበቁ ነበር
እኛም ቁጭ አልን እናቴ እጄን ጥብቅ አድርጋ ይዛ አይን አይኔን ታየኛለች ልጄ ሁኔታህን እየፈራሁት ነው ተረጋጋ እንጂ የምታምነው አምላክ አይተዋትም አለችኝ።

ወደ 12.30 ላይ ዶክተሩ መጣና አሁን ደና ናት ግን መቼ እንደምትነቃ አናቅም ተረጋጉ ምንም አትሆንም ትንሽ ቀኝ እጇ ነው የተጎዳው ።
አንዳንዴ ከህመሙ በላይ ድንጋጤው እራሳችንን እንዳናውቅ ያደርገናል አሁን ሁላችሁም እዚህ ማደር ስለማትችሉ ከሁለት ሰው ውጪ ወደቤት ሂዱ አለን።

አቶ ሳሙኤል ሂዱ ሁላችሁም እኔ አድራለሁ እረፍት አድርጉ አሉን።

አባቴ አረ እኔ የትም አሌድም እዚሁ ነው አብሬህ የማድረው አለ።
እኔም ከዚህ ንቅንቅ አልልም ሞቼ እገኛለሁ አልኩ።

ከስንት ክርክርና ጭቅጭቅ ቡሀላ እኔና አቶ ሳሙኤል ብቻ ልናድር ሌሎቹ ወደቤት እንዲሄዱ አደረግን።

አቶ ሳሙኤል እንቅልፍ ባይናቸው ሳይዞር አድረው ውለው ድጋሜ እንዴት ቁጭ ብለው እንደሚያድሩ ጨንቆኝ ነበር።

ትንሽ እረፍት እንዲያደርጉ ብጠይቃቸውም አይ ልጄ እረፍት በዚህ ሰአት ለኔ ያስፈልገኛል ብለህ ነው ምኑን አረፍኩት አሉ።

ሌሊቱን ቁጭ ብለን አይናችን እንደፈጠጠ ስለማሂ ከልጅነቷ ጀምሮ ያሳለፉትን ቁጭ ብለው በእንባ አጫወቱኝ።

አንድም ቀን ታማ እንኳን ሆስፒታል ገብታ እንደማታቅ ነገሩኝ።

የዛኔ ወደራሴ አስተዋልኩኝ በቃ ይሄ ነገር ከኔ ነው ችግሩ ፊደልም ከራስ ምታት የዘለለ በሽታ ይዟት አያቅም ነበር ከኔጋ ብትተዋወቅ ግን ባንዴ ከነልጃችን ህይወቷን አጣች ፈጣሪ ሆይ እኔ ቆይ ያን ያህል ክፉ ሰው ነኝ እንዴ ከሰው የተለየ ሀጥያት የሰራሁት ምኑጋ ብዬ እራሴን ጠየኩ።
ድንገት ጭንቅላቴ ውስጥ የሆነ ነገር ብልጭ አለብኝ ።
ማነው ሲከተላት የነበረው ማነው ከኋላዋ እየሄደ ሲያስጨንቃት የነበረው ።

እኔ ምሎት አቶ ሳሙኤል ቆይ ማሂ አደጋ የደረሰባት ከሰውጋ ተጋጭታ ነው ወይስ ድንገት ከሆነ ነገርጋ ተጋጭታ ነው እስኪ የተፈጠረውን ንገሩኝ አልኳቸው።

ልጄ አሁን ይሄ ነው የምልህ ነገር የለኝም

ቆይ ልጄ ብቻ ትንቃልኝ አይኗን ትግለጥልኝ ከዛን ቡሀላ ነው የተፈጠረውን በደንብ የማጣራው አሁን ሌላ ነገር ማሰብ አልችልም ጭንቅላቴ ውሰሰጥ ከማሂ ሳቅ ፈገግታ ከሷ ምስል ውጪ ምንም ነገር የለም ትንቃልኝ ብቻ አንዴ አሉኝ።

እንዲሁ ለስሙ እሺ በቃ ተውት አልኳቸው እኔ ግን መተው አልቻልኩም ቆይ ማሂ ከሰውጋ ተጣልታ ይሆን??

እኔ እስከማቀው እኔ ላይ ወይ አባቷ ላይ ትነጫነጭ እንጂ ከሌላ ሰውጋ ክፉ ቃል  አደለም ቀርቶ ሰዎችን በሙሉ አይኗ አታይም ።
ብቻ ሀሳብ......................
ሌሊቱ ነጋ
በሌሊት ቤተሰቡ እንዳለ ተሰብስቦ ምግብ ቋጥረውልን መጡ እናቴ ገና አይኗን እንዳየሁት ሌሊቱን ሙሉ እንዳልተኛች አወኩኝ።

በቃ እናንተ ቁርስ ብሉ እኛ እዚህ እንሆናለን አሉን።
አቶ ሳሙኤል አልበላም እኔ አራበኝም አሉ እኔም በቃኝ አልኩኝ።
አባቴ ተቆጣ አይ እንግዲህ እሷ እስክትነቃ እናንተ መሞት የለባችሁም ግዴታ ነው ብሎ ይዞን ሄደ ሻይ አዘዘና ምግቡን ከፈተልን እንዲሁ ግዴታ ለነፍሳችን ማቆያ ያህል ቀመስንና በቃን ብለን ከደነው ።

ተመልሰን ቁጭ እንዳልን ዶክተሩ መጣና ነቅታለች ግን አሁን ምንም መናገር ማውራት አትችልም አይኗን ስለገለጠች እናንተም ማየት ትችላላችሁ እንድትረጋጉ ብዬ ነው አለን ።

ሁላችንም እሷን ለማየት ሰፍ ብለን ቆምን አይኗ ከርተት ከርተት ሲል አሳዘነችኝ ያ ሁላ ነገር ተሰካክቶባት ሳይ በጣም ከበደኝ ውስጤ ድብልቅልቅ አለ ።

በእጄ ምልክት ሰጠኋት አይኗን ጨፈን አድርጋ ገለጠችው።

አቶ ሳሙኤል ድርቅ ብለው አይናቸውን ከሷ ላይ ሳይነቅሉ ቆሙ ህመም  ፀጥ እንደሚያስብል አቀዋለሁ በሳቸው ደሞ አረጋገጥኩ።

እናቴና እህቴ በድንጋጤ እያለቀሱ ያይዋታል።
በቃ ይበቃችኋል ዞር በሉ ከመስታወቱጋ ተባልንና ዞር አልን።

ማሂን እንደዛ ሆና ማየት ህመም ብቻ አደለም ሚሰማኝን ስሜት መለየት እስኪያቀተኝ ድረስ ነበር።

ልክ ማሂን ካየን ቡሀላ  አቶ ሳሙኤል አባቴን አደራ ልጄን እስክመለስ ያንተ አደራ ናት አሉት እኔን ተከተለኝ ብለው ወደፊት ሄዱ።

ማሂን ለመጠየቅ የመጡ ሌሎች ሰዎችም እዛው ነበሩ ግን አንዳቸውንም ሰላምታ እንኳን አልሰጧቸውም ነበር።
ወዴት እንደምንሄድ ግራ እየገባኝ ዝም ብዬ ተከተልኳቸው መኪናቸው ውስጥ ገብተን ወደቤት ሄድን ግቢ ውስጥ ከጥበቃው ውጪ ማንም አልነበረም ወደ ውስጥ ገባን።

ልብስህን ቀይር ብለው ቀጭን ትዛዝ ሰጡኝ ።
እሺ ብዬ ገብቼ ልብሴን ቀያየርኩኝ እሳቸውም የሌሊት ልብሳቸውን አውልቀው ሱፋቸውን ለበሱ ።

ምን እየተፈጠረ እንደሆነ አልገባኝም ነበር የሆነ ሰአት ልክ ፊልም ላይ እንደምናየው ሄደን ማሂን እንደዚህ ያደረጋትን ሰው አግተን ልንገለው ይሆን እንዴ እላለሁ መልሼ ደሞ አንተ እብድ ነህ እንዴ ማን እንደሆነ በምን ታውቃለህ እያልኩ ከራሴጋ እሟገታለሁ።


✅️“… ብገልህ ደስ ይለኛል !... እንንንንቅ አድርጌ እንደዚህ … “ አንገቴን አንቃ … አይኖቿ ደፍርሰዋል … አፏ መጠጥ መጠጥ ይሸታል … አልታገልኳትም ! … ስለማውቃት እንኳን እጄን ላነሳባት ያነቀችውን አንገቴን ላስለቅቃት አልሞከርኩም … 

✔️“በ…ል ታገለኛ ! አስለቅቀኝና ምታኝ!..” … የያዘችው የዋይን ጠርሙስ ስባሪ ያሳቅቃል … ራሷን እንዳትጎዳ ነው ፍርሃቴ …

ገና ከመግባቴ ነው በጩኸት የተቀበለችለኝ …ስራ አምሽቼ ነው የገባሁት…  አስቀድሜ ገዝቼ ያመጣሁትን ዋይን መንጭቃ ተቀብላኝ ወደጭንቅላቴ አስተካክላ ወረወረችው … ነጩን ግድግዳ ስስ ቀይ ቀለም አለበሰው … ስብርባሪው መሬት ተበተነ … ፀጉሯ ተበታትኗል … ያደረገችው የሌሊት ፒጃማ ለአስፈሪነቷ ተጨማሪ ሆኗታል … ተንደርድራ ሄዳ የጠርሙሱ ግማሽ አልተሰበረ ኖሮ አነሳችው … ወደኔ መንገድ ጀመረች …

“እገድልሃለው!... “ ወደኋላ ሸሸሁ …

✔️“ብጥስጥስ ነው የማደርግህ …!” ስባሪውን አስቀድማ… ሶፋውን ከነሲሊፐር ጫማዋ ረግጣ ከበላዬ ቆመች … የሶፋው ጠርዝ የሌሊት ፒጃማዋን ይዞ በከፊል ተራቆተች 

“ጭንቅላትህን ከአንገትህ ለያይቼ ደምህን….” መሸሻዬን ጥግ ጨረስኩ … ትልቁ ሶፋ ላይ ተንጋለልኩ … የጠርሙስ ስባሪ የያዘው እጇ ወደኔ ተሰነዘረ …ተረጋግቼ ክንዷን ያዝኩና ብዙም ባላሰበችው ሁኔታ በቅልጥፍና ስባሪውን አስጣልኳት … ጥንካሬዋ  እኔ የጥቁር ቀበቶ ባለቤቱን እንኳ በቀላሉ የምቋቋመው አይደለም !

በምድር የቀረችኝ ልቤ ላይ ቦታ ያላት ብቸኛ ሴት ናት … ማንም በሌላት እንቁ ሴት ነፍስ ላይ ብቸኛው ንጉስ ነኝ ! …  እናት አባት እህት ወንድም ዘመድ አላውቅም … ጭልም ካልኩበት ፀሃይ ሆና የመጣችልኝ እቺው ውዷ ሚስቴ ናት ! …

✔️እሷ ፀሃይ ከሆነችኝ ድፍን አስር አመት …
በተገናኘኝ በሁለተኛ አመታችን ሌላ ዘመድ እንዳለኝ ሌላ ስሜን አስከትላ የምትጠራ ነፍስ ሆዷ ውስጥ እንዳለች ስታበስረኝ አልቅሼ በማላውቀው ሁኔታ አለቀስኩ !.... ለህይወት ጉጉ ሆንኩ … ስልችት ያለኝ ህይወት ከእንደገና ታድሶ ብርሃን ሆኖ ያጓጓኝ ጀመር …

✔️ልጄን እቅፌ ላይ ሳያት እግዜር በፍጥረቱ ምን ያህል ተደንቆ እንደነበረ በስሱ ገባኝ!... እግዜርን ሆንኩት … ልጄን ቁልቁል እናቷ ደረት ላይ እያየኋት ብዙ አሰብኩ …ብዙዙዙዙዙዙዙዙዙዙዙ!

በዳዴ ስትሄድ… “አባዬ!” ስትለኝ … በትናንሽ ከንፈሮቿ ስትስመኝ … የአንገቷ ጠረን … እኔና እናቷ መሃል ስትሆን … ትናንሽ እግሮቿን በስስት ስስማቸው … ከፍ ብላልኝ እሽኮኮ አድርጌ ትምህርት ቤት ስወስዳት … ሳደምጣት … እጄ ላይ እንቅልፍ ሲወስዳት ( አይኖቿ ተከድነው ስታምር ደግሞ ) … ደስታዋን ሀዘኗን (ውይ ሀዘንስ አይይብኝ .. የውዴንም የልጄንም ሀዘን እኔ ልዘን !) በእቅፏ ስትነግረኝ … ስታጋራኝ …. በጣም ብዙ አሰብኩ !

ብዙዙዙዙ ብመኝም አልሆነም !... ምክንያቱ ግልፅ ባልሆነ ሁኔታ ውዴ እቅፍ ውስጥ እያለች በአራስነቷ ጥላን ሄደች ! … ለክርስትናዋ እንኳ አልደረሰችም … አግኝቼ አጣሁ !... ልጄ ትንሹዋ እኔ ሞተች ! … በልጃችን እልፈት ክፉኛ ባዝንም አልተቀየምኳትም …
ከዛን በኋላ ለኔ ስትል የተፅናናች ትምሰል እንጂ ሀዘኑ ከሰውነት አወጣት … የሷ ፀሃይ እየጠለቀች … አይኔ እያየ ጀምበሬ ታዘቀዝቅ በአስፈሪው ደመና ትዋጥ ጀመር… ለልጃችን ሞት ራሷን ሙሉ በሙሉ ተጠያቂ አድርጋ ለራሷ ይቅርታ የማታደርግ ሆነችብኝ !...

እንዲህ እንደዛሬው የልጃችንን ልደት እየጠበቀች በፀፀት ራሷን ትቀጣለች … ሌላ ማንነት ውስጥ ሰምጣ ቀረችብኝ … ያልሞከርኩት ሃኪም ያልሞከርኩት ፀበል ያላየሁት ነገር አልነበረም !... ቢያንስ በወር አነዴዴ እዚህ ማንነት ውስጥ ሆና አገኛታለሁ … መቼ እንደምትቀየር ስለማላውቅ ሁሌም ከኔ አልፋ ራሷን እንዳትጎዳ ነው ፍርሃቴ ! … በዚህ ሌላኝው ማንነቷ ፍርሃት እሷም ሰው አትቀርብም … ሌላ ልጅ ለመውለድ አልደፈረችም !

የልጃችን የሙት መንፈስ እንደሚያሰቃያት ደህና ስትሆን እያነባች ደጋግማ ነግራኛለች … እያነባች ማታ ስላደረገችው ነገር ይቅርታ ትጠይቀኛለች … እያነባች ድጋሚ እንደማታደርገው ትነግረኛለች … እያነባች ቁስሌን ትጠርጋለች …

ከነእንባዋ እስማታለሁ …. ሌላ ቀን ቢደገምም … ሌላ ጊዜ እነደዛው አስፈሪ ብትሆንም ዛሬም ከነእንባዋ እስማታለሁ … ዛሬም ከነአውሬ ማንነቷ ባልቀነሰ ፍቅር አፈቅራታለሁ …

ትላንት ካደረገቸው ትዝ የሚለኝ ያ ነፍስ ነጣቂ  አሳሳሟ ነው …

ትላንት ትዝ የሚለኝ ያ በሳቅ እንባ የሚያመጣ ጨዋታዋ ነው …ከዛ አሟሚ የፍቅር ቃሎቿ … ስሜ አፏ ላይ ፍስስ የሚለው… ስስቷ…. ጥፍጥናዋ ብቻ ነው … !

ትዝ የሚለኝን የመምረጠጥ መብት ለራሴ ሰጥቻለሁ !... የምወደውን ብቻ ነው የማስታውሰው !... ትውስታዬ ላይ ብርሃኗ እቺው ውዷ ሚስቴ ናት!

እና……!

ነገም ያን ዋይን ይዤ እሄድና እንደሌላው ጊዜ የሰራችውን ምግብ እየተሳሳቅን ከበላን በኋላ እንደአዲስ ቀለበት ተንበርክኬ አጠልቅላታለሁ … (እንደሁሌው ህመሟ ሲነሳ አውልቃ ብትጥለው  እንኳ እስካልቀየማት ድረስ )

ነገም ገና እንደገባሁ ከንፈሯን ስሜ በሌሊት ልብሷ ታቅፌያት መኝታ ቤታችን ወስጄ …
ነገም ብትቧጭረኝ … ብትመታኝ … ልትገለኝ ብትጥር…

ነገም… በቡጭሪያዋ የቆሰለ ገላዬን እየነካካች …በእንባዋ ብታጥበኝ … እንደሁሌው “… ስትሄድ ገድለኸኝ ሂድ! “ ብትለኝ …

ነገም… 
ነገም..
ነገም…

ነ…ገም …. አሁን ከማፈቅራት በላይ አ.ፈ.ቅ.ራ.ታ.ለ.ሁ
!...

  ይ🀄️ላ🀄️ሉን
https://t.me/+4dGFaH_mUnExZjg8
https://t.me/+4dGFaH_mUnExZjg8

💝የዩቲዩ ገፃችን💝
https://www.youtube.com/@Kezerareaction333
https://www.youtube.com/@Kezerareaction333

5.5k 0 27 12 121

ሌሊት እናቴ ቀድማኝ ተነስታ ቤቱን ፏ አድርጋ ቡና አፍልታ ሰላም ግባ አለችኝ እሺ ብዬ የናቴን ምርቃት ተቀብዬ አባቴ እስከመኪናው ሸኝቶኝ አሳፍሮኝ ስራዬን አስተካክዬ እንድመለስ ነግሮኝ ተሰነባብተን ጉዞ ጀመርኩ ።

ሲነጋጋ ድንገት ማሂ ከጓደኞቿጋ ትወጣ ይሆን እንዴ ለነገሩ ምን ጓደኛ አላት ቆይ ለአቶ ሳሙኤል ልንገራቸው ድንገት ከቤት ከወጣች ደሞ ስገባ አጣታለሁ አልኩኝና ደወልኩ አይነሳም ደግሜ ደወልኩ አይነሳም ግራ ገባኝ አቶ ሳሙኤል ምንም ቢፈጠርኮ ስልክ ሳያነሱ አይቀርም ቆይ ለማሂ ልደውል እንዴ ብቻዬን እየተብሰለሰልኩ ስልኬ ጠራ አቶ ሳሙኤል ነበሩ።

አነሳሁት ይቅርታ የኔ ልጅ አላየሁትም ነበር አሉኝ።
ድምፃቸውን ስሰማ ልቤ ስንጥቅ አለ ምንም ልክ አልነበሩም።


ድምፆት ምንድነው ምን ተፈጠረ አልኳቸው ።

ሆስፒታልኮ ነው ያለሁት ማሂ ልትሞትብኝ ነው አሉ ስቅስቅ እያሉ እያለቀሱ ነበር የነገሩኝ።

6k 0 21 35 357

ፅጌሬዳ



ክፍል 32


ወደ ውስጥ ስገባ ቤተሰቡ የሞቀ ጨዋታ ላይ ናቸው ስለድሮ አንስተው እተሳሳቁ ያወጋሉ።

እኔ ብተኛ ጥሩ እንደሆነ ነግሪያቸው ወደመኝታዬ ገባሁ።

ውስጤ ድብልቅልቅ ያለ ስሜት ነበር ልስቅ ፈልጌ መሳቅ አቃተኝ ላለቅስ ፈልጌም ማልቀስ አቃተኝ።

ስልኬን አነሳሁና ለማሂ ተኛሽ እንዴ ብዬ ላኩላት ዝም አለችኝ።

ለመተኛት ሞከርኩ በግራ ብል በቀኝ ብል እንቅልፍ አልወስድ አለኝ።
ቀድሞ ሚተኛው ጭንቅላታችን መሆኑን ዘንግቼዋለሁ መሰለኝ።

ተገላብጬ ተገላብጬ የሆነ ሰአት ለካ እንቅልፍ ጥሎኛል
ስልኬ ሲጠራ በእውኔ ይሁን በህልሜ እየተምታታብኝ ነበር።
ድጋሜ ሲጠራ አነሳሁና አየሁት ማሂ ናት ተስፈንጥሬ ከአልጋው ወረድኩ አነሳሁትና ማሃ ደና ነሽ ማሂ ምን ሆንሽ ማሂ አልኳት።

እንዴ ተረጋጋ እንጂ አጣደፍከኝኮ ምንም አልሆንኩም እንቅልፍ እንቢ ብሎኝኮ ነው ደሞ መጠጡ ነው መሰለኝ ቤት ከገባሁ ቡሀላ በጣም አመመኝ አለች።

እና ምን አደረግሽበት እንዲተውሽ እእ አሁን ደና ነሽ ??
ብቻ ውስጤ ስፍስፍ ነገር አለ እዛ ቤት የሆነ ነገር ሆና የምታድር መሰለኝ ኤጭ ምነው አቶ ሳሙኤል በሄዱ ኖሮ ይሄ ሁላ ጭንቀት አይኖርም ነበርኮ ብዬ አሰብኩ።

ከማሂጋ ትንሽ ካወራን ቡሀላ መቼ እንደምመለስ ጠየቀችኝ አልወሰንኩም ባሁኑ እንኳን ትንሽ መቆየቴ አይቀር የትምህርት ማስረጃዎቼን ማስተካከል አለብኝ በዛ መታወቂያ ላውጣና በስሜ የባንክ አካውንት እንኳን ይኑረኝ እንጂ አንቺጋ እያስቀመጥኩኮ ላምንሽ እራሱ አልቻልኩም አልኳት።


ሀሀ ተው ባክህ እንደውምኮ እኔ ነኝ ከባንክ በላይ አስተማማኝ ሰው ለማንኛውም ቶሎ ብትመለስ ነው ሚሻልህ ካልሆነ የሆነ ቀን ከእንቅልፍ ስትነሳ ሳሎን ቁጭ ብዬ ነው ምታገኘኝ አለች።

አድርጎት ነው  በይ ደና ደሪ እንቅልፌን ልተኛ አንቺም በእንቅልፍ አሳልፊ አልኳትና ስልኩ ተዘጋ።

በነጋታው እናቴ ቁርስ ደረሷል ብላ ቀሰቀሰችኝና ተነሳሁ።
ቁርሴን በላልቼ ስጨርስ ማሂጋ ደወልኩ አታነሳም አቶ ሳሙኤልም ደወሉ አታነሳም ጥበቃውጋ ደወሉና ከቤት እንዳልወጣች አረጋገጡ።

እሳቸውን ወደ አዲስ አበባ ሸኝተን ስላደረጉልን በሙሉ አመስግነን
ለኔም ቶሎ ወደ አዲስ አበባ እንድመለስ ከታላቅ አደራጋ አስጠንቅቀውኝ ሄዱ።

ስመለስ ማሂ ደወለችና ተኝታ እንደነበር ነገረችኝ።
በቃ አባቴ እየመጣ ከሆነ ቤቱን አሰማምረን እንጠብቀው ዛሬ ስራ አልገባም ከሱጋ የልብ የልባችንን ስናወራ ብናመሽ ይሻላል አለች።
እሺ በቃ ብያት ወደቤት ተመለስኩ ከሰአት ደሞ እህቴ ቤት ሄድኩኝ።
እዛም ስንጨዋወት አመሸንና ወደቤት ተመልሼ ከቤተሰቦቼጋ አመሸሁ።

የዛን ቀን ከማሂጋ ሳናወራ አደርን በነጋታው ከቤት ስራ ቦታ እስክትደርስ አወራን ።
ማታም ስትመለስ እንደዛው እያወራን ነበር አረ ናታኔም የሆነ ሰውዬ ዛሬም እየተከተለኝ ነው መሰለኝ ወይስ በሀሳቤ እንደዛ ስላሰብኩ ነው የተከተለኝ የመሰለኝ አለች።

እሺ ቆይ አንደ ነገር ልንገርሽ አሁን ኖርማል ከምትሄጅበት መንገድ ያገኘሽው የመጀመሪያ መታጠፊያ ላይ ታጠፊና ዞረሽ ተመለሽ አልኳት ።

እሺ ቆይ ከፊት ለፊቴ መታጠፊያ አይታየኝም አለች።

ትንሽ ቆየችና ይኸው አሁን እየታጠፍኩ ነው አለች።
እሺ በቃ ዝም ብለሽ ወደፊት ንጅው ከዛ መኪናው እየተከተለሽ ይሁን አይሁን ቼክ አድርጊ አልኳት።

አደረኩኮ ስታጠፍ አብሮኝ ታጠፈ አሁንም ከኋላዬ ነው ጭራሽ እየቀረበኝ ነው አለች።

ምን እሺ ማሂ ፖሊስጋ ትደውያለሸ ወይስ ምን እናድርግ ማን ሊሆን ይችላል አልኳት።

አረ ማንምጋ አልደውልም መኪናውን አቁሜ ልውረድና ቼክ ላድርግ እንዴ አለች አንቺ ያምሻል እንዴ ብዬ ጮኩባት።

እንዴ ምን ችግር አለው አስፋልት መሀል ላይኮ ነው ያለሁት ጨለማ ውስጥ አደለሁ አለችኝ።
የማወራው ጠፋኝ የሷም ድምጿ ጠፋ ማሂ ሄሎ ማሂ አንቺ ማሂ ብላት ብጣራ ምላሽ አጣሁ ዘግቼ መልሼ ደወልኩ።

አታነሳም ደገምኩት ሊዘጋ አካባቢ አነሳችው።
እእ ማሂ አታስጨንቂኝ ምን እየተፈጠረ ነው አልኳት መኪናውን አቁሜ ከመኪናው ስወርድ መኪናው ባጠገቤ ከነፋስ በፈጠነ አነዳድ ለትንሽ ስቶኝ አለፈ ታርጋውን እንኳን መያዝ አልቻልኩም አለች።

የዛኔ ጭንቀቴ ይባስ ጨመረ
እሺ አፍጥኚው መኪና ውስጥ ግቢና ወደቤትሽ ሂጂ አልኳት።

እሺብላ ተመልሳ ወደቤቷ መንዳት ጀመረች ሰፈሯ ደርሳ እንኳን ከኋላይ ያሉ ከፊት ለፊቴም የቆሙ እየመሰለኝ እየደነገጥኩ ነው እያለችኝ ነበር።

ቤት መግባቷን ካረጋገጥኩ ቡሀላ ስልኩን ዘግቼ ምን እየተፈጠረ እንዳለ ማሰብ ጀመርኩ.......

ግን ምንም ነገር ጭንቅላቴ ውስጥ ሊመጣልኝ አልቻለም ።
ማን ሊከታተላት ይችላል የሆነ ሰአት አውቃ ወደአዲስ አበባ እንድመለስ ምክንያት እየፈጠረች ይሆን እንዴ ብዬ አሰብኩ።

እንዲሁ እንደጨነቀኝ ነጋልኝ።

በጠዋት ተነስቼ ደውዬ አወራኋትና ከአባቴጋ ወደ ቀበሌ ሄድን የተወሰነ ነገር ጨራርሰን ወደ ቀድሞ ትምህርት ቤቴም ሄደን ያለውን መረጃ ወሳሰድን እስከመቼ እንደሚያልቅልን ጠያየቅንና ለምሳ ወደቤት ተመልሰን ።
ማሂጋ ደውዬ  ደህንነቷን አረጋገጥኩና ከአባቴጋ ዞር ዞር ማለት ጀመርን።

ብዙ ሚያቃቸው ሰዎች ስላሉ ያን ያህል ከባድ አልሆነብንም ነበር።

እኔ ማታ ደርሶ ማሂ ዛሬም ሚከተላት ሰው መኖርና አለመኖሩን ለማረጋገጥ ቸኩዬ ነበር።

ያ የፈራሁት ማታ ደረሰና ማሂ ከስራ ወጥታ ወደቤት እየሄደች ደወለችልኝ እስከቤት አውራኝ ብላኝ እያወራን ነበር ዛሬም ሚከተልሽ ሰው አለ እንዴ አልኳት እኔጃ እስካሁን ምንም አላየሁም አለች።

ተመስገን አልኩኝ እስከቤት ድረስ ምንም የተከተላት ሰው አልነበረም ቤት ከደረሰች ቡሀላ ተሰነባብተን ስልኳ ተዘጋ።

እውነት ለመናገር ማሂ በጣም ናፍቃኝ ነበር አንዳንዴ መኪና ሳይ ዝም ብለህ ገብተህ ሂድ ሂድ ይለኛል ድንገት ደርሼ ሰርፕራይዝ ባደርጋትስ ብዬ እመኛለሁ።

ካባቴጋ እያወራን ዞሮ ዞሮ ቤቱን ካልሸጥነውኮ እዚሁ ነው ምንኖረው ትምህርትህንም እዚሁ ነው ምትቀጥለው አለኝ::
ችግር የለም ቀስ ብለን እንወስናለን የናንተን እርግጠኛ ልሁን ብዬ ነው እንጂ የኔን መውደቂያ ማመቻቸት አያቅተኝም እዚሁም መማር እችላለሁ አልኩት።

እዛ ያለውን ጉዳይ ከጨራረስኩ ቡሀላ ማሂ ሳታስበው ድንገት ሄጄ ሰርፕራይዝ ላደርጋት አስቤ ነበር መች እንደምመጣ ስትጠይቀኝ አላወኩም እቆያለሁ አልኳት ናፍቀኸኛል ቶሎ ና አለችኝ እሺ አልኳት በኔ ቤት እሁድ ካባቷጋ ቁጭ እንዳለች ድንገት ቤት ደርሼ አስደነግጣታለሁ ብዬ ነበር።

ቅዳሜ ማታ ከስራ እየተመለሰች እያወራን ነበር በመሀል ምን ሆና እንደሆነ አላቅም በቃ ቻው አንዴ ጓደኞቼ waiting እየገቡብኝ ነው ላውራቸው አለችኝ
ላስጨንቃት ስላልፈለኩ እሺ በቃ ስትገቢ እናወራለን አልኳትና ስልኩ ተዘጋ።

ቤት ገብታ ካሁን ካሁን ትደውልልኛለች ብዬ እየጠበኳት ዝም አለችኝ ።
እኔ ደወልኩላት ስልክ አታነሳም ምን ይዘጋሻል ቤት እስክትገቢ እንዳወራሽ ብቻ ነበር እንዴ ምትፈልጊው  አልኳት አሁንም ዝም አለች ።

በቃ ደክሟት ይሆናል ለነገሩ አሁን አውርተን ድጋሜ ካላወራን ብዬ ምን ያሟዝዘኛል ቆይ እንደውም ነገ ስልኬን እዘጋና ቤት እስክደርስ አላወራትም አልኩኝ ለራሴ።
ተነስቼ ይዤ የመጣሁትን ልብስ አስተካከልኩኝና ከተትኩኝ በጠዋት ልክ ለበአል ልብስ ተገዝቶለት አንዴ ነግቶ በለበስኩት ብሎ እንደሚጠብቅ ህፃን ነበር የሆንኩት አንዴ ነግቶ ሄጄ ሰርፕራይዝ ባደረኳት መቼስ ስታየኝ እንዴት እንደምትጮህ እያልኩ በሀሳቤ እየሳልኩት ብቻዬን ፈገግ እላለሁ።


ፅጌሬዳ




          ክፍል 31


አንተምኮ አናደኸኝ ነው አውቀህ ምትሸውደኝ ነገር በጣም ያበሳጨኛል።

እውነቱን ንገሪኝ ካልከኝ ባለፈው ሰክሬ የነበረ ቀን በህልሜ ሳይሆን የእውነት እንደሳምኩህ አቃለሁ በእርግጥ አስቤው አደለም ያደረኩት ግን አንተ በህልምሽ ነው ብለህ እንደህፃን ልታጃጅለኝ ሞከርክ ጭራሽ አጠገብሽ ከሌላ ሴትጋ ስልክ ባወራ ምን ችግር አለው አልከኝ አደል።

ብቻ እኔም ጥፋተኛ እንደሆንኩ አቃለሁ አንዳንዴ ካቅም በላይ መቅበጥ ያምረኛል።

አንተን ደሞ ቶሎ ቶሎ የማኩረፍ አባዜ አለብኝ ሁሌ አኩርፌህ ትንሽ እቆይና ይፀፅተኛል ግን ላለመሸነፍ ዝም እላለሁ

ግን ከምር ጨካኝ ነህ እንደዚህ ቁርጥ አድርገህ ጥለኸኝ ትሄዳለህ እኔ ብሆንኮ አያስችለኝም በስማም አንተ ግን ብቻ ተወው አለች።

እሺ ትቼዋለሁ አሁን የት ደረሽ ቤት አልደረሽም እንዴ አልኳት።

አረ ገና መቼ አንተን እያወራሁ ቀስ እያልኩ ነው እየነዳሁ ያለሁት በዛ ላይ መንዳት ሁላ እያቃተኝ ነው አብረን ብንሆን አንተ ታግዘኝ ነበር አለች።
ያው ምን ታረጊዋለሽ ወይ ሌላ ሹፌር ብታዘጋጂ ጥሩ ነበር አልኳት።

ላንድ መኪና አንድ ሹፌር መች አነሰው እጅ ሲበዛበት ብልሽት ነው ትርፉ
አለችኝ።

ከት ብዬ ሳኩኝና አንቺ ልጅ ግን ይሄ ፀሀፊነትሽ ቅኔ ተናጋሪ እያረገሽ ነው አልተቻልሽም አልኳት።

አረ ቆይ የሆነ ዘፈን ልጋብዝህማ አለችና ዘፈኑን ሞቅ አድርጋ ከፍታ አብራ መዝፈን ጀመረች ።

የፍቅር አዲስን ዘፈን ነበር እያጫወተች የነበረው።

አለም ማነው ወደሱ ቤት ስቦ የሚወስደኝ
አለም ለምንድነው ከቶ እሱን ያስወደደኝ


ዝም ብላ እየተፍለቀለቀች አብራ ትዘፍናለች እኔም ብቻዬን እየሳኩ አዳምጣታለሁ ቁጭ ብዬ እየሰማኋት ድንገት ቀና ስል እናቴ ቆማ ፈገግ እያለች ታየኛለች ሳያት ደነገጥ ብዬ ተነሳሁና ምነው እማ ፈለግሽኝ እንዴ አልኳት ።

አረ ልጄ እንደዚህ ብቻህን ፈገግ እያልክ ሳይህ ያንተ ፈገግታ ተጋብቶብኝኮ ነው ስትጠፋብኝ ልይህ ብዬ ይቅርታ አውራ አረብሽህ አለች።

አረ እማ ማሂኮ ናት እንደውም ሰላም በያት ነይ እንኪ አልኳት ስልኩን
ውይ ገምቼ ነበር አቶ ሳሙኤል እየደወለላት መስመር ተይዟል አለኝ ስልኳ ሲለኝ ካንተጋ እያወራችሁ መሆኑን ለማረጋገጥኮ የወጣሁት አለች ።

ማሂ እናቴን አውሪያት ዘፈኑን ዝጊው አልኳት ውይ አማቴን ላወራት ነው ናፍቃኝ ነበር ስጣት አለችኝ።

እናቴ ስልኩን ተቀበለችኝና አወራቻት ሰላምታ ተለዋወጡ ስለስራ ተጠያየቁና ተሰነባበቱ።
በሉ በቃ አውሩ ብላ እናቴ ወደ ውስጥ ገባችና ጋቢ ይዛልኝ መጥታ አለበሰችኝ።

ጋቢዬን ለብሼ ተስተካክዬ ቁጭ አልኩኝ  እስከቤት እንደማወራት ቃል ገብቼላት ስለነበር ስልኩን መዝጋት አልችልም።


እሺ ምን እናውራ ወሬ ሁላ እየጠፋብኝ ነውኮ አልኳት።
እና እኔ የወሬ ማመንጫ ማሽን ያለኝ ይመስልሀል እንዴ እኔም እየጠፋብኝ ነው አለች።

እንደዛ ከሆነ በቃ አናውራ ዝም ብለን አብረን እንደተቀመጥን አስቢና ዘፈን እንስማ አልኳት እሺ ምረጥ አለችኝ።

አንቺ ደስ ያለሽን ክፈቺ በቃ አብረን እንዝፈን አልኳት።

እሺ ብላ የሀይልዬ ታደሰን በስስት ነበር የማይሽ ቢከፋኝ ዛሬ ስለይሽ ያራቀኝ መንገድ ካጠገቤ ጥሎብኝ መከራ ለልቤ

እንደናት ቆጥሬሽ እንዳጋር
ስንት አልም ነበረ ካንቺጋር
ፍቅርሽን እንደራሴ አምኜ
አልቻልኩም ልረሳሽ ጨክኜ።

ማሂ ይሄ ላንተ ነው ቢከፋኝ ዛሬ ስለይህ ብለህ በወንድ ቀይረህ ስማው አለች።

እኔ ዘፈኑን እየሰማሁ እንባ እየቀደመኝ ነበር ።
ዘፈኑ ወደኋላ መለሰኝ አስታውሳለሁ ፊደል የሞተች ሰሞን ነበር።
ጎዳና ላይ አድሬ ምግብ ከቀመስኩ ስንት ቀን እንደሆነኝ እንኳን ማስታወስ እስኪከብደኝ ድረስ እርቦኝ ምግብ ቤት ለምግብ ቤት ትራፊ አለ እያልኩ እየዞርኩ ሁሉም ጠዋት ነው አሁን የለንም እያሉ እየመለሱኝ ባጋጣሚ አንዱ ምግብ ቤት በርጋ ቆሜ የሀይልይ ይሄ ዘፈን ተከፍቶ ነበር ።

ሙዚቃው ስለኔ ህይወት እያቀነቀነ ያለ ይመስል በቆምኩበት ድርቅ ብዬ ቆሜ መስማት ጀመርኩ።
የድምፁ ቅላፄ ዘፈኑ ብቻ ረሀቤን ሁላ አጠፋው እንባዬ ደረቴን እስኪያበሰብሰው ድረስ አለቀስኩ።
ከሸቃቀልኳት ላይ 5 ብር እየከፈልኩ ይሄን ዘፈን ቢያንስ አምስት ስድስቴ እንዲያሰሙኝ አደርግ ነበር የኔና የፊደል ብሄራዊ መዝሙር የሆነ ሁላ እስኪመስለኝ ነበር ምወደው።

አሁንም ልክ ስሰማው በሀሳብ ወደኋላ ጎተተኝ።
ማሂ ዝም ብላ እየዘፈነች ሰማኸው አደል ትለኛለች እኔ አዎ አዎ ከማለት ውጪ መልስ አልሰጣትም ነበር።

ለማንኛውም ልደርስ ነው ደሞ እስካሁን የሆነ ሰው እየተከተለኝ ነበር እንዳትጨነቅ ብዬ ነው ያልነገርኩህ አንተን እያወራሁ በመስታወት ውስጥ እያየሁት ነበር ወደጎን ስታጠፍ ይታጠፋል ስቆም ይቆማል በፍጥነት ስነዳ በፍጥነት ይነዳል ስንቴ ልጋጭ ነበር አሁን ግን ሰፈር ደረስኩ አለችኝ።

ምን አንቺ ምንድነው ምታወሪው ማነው ሚከተልሽ አልኳት ከተቀመጥኩበት እንዴት እንደተነሳሁ ሁላ ትዝ አይለኝም።
ምን አቃለሁ ብቻ የሆነ መኪና ዝም ብሎ እየተከታተለኝ ድንገት ካይኔ ተሰወረ ወደሰፈር ለመግባት እራሱ እየፈራሁ ነው ቆይ ዝጋው ስልኩን በር ላይ እንዳልቆም ቀድሜ ልደውልላቸው አለችኝ።

አይ አልዘጋውም ማሂ ገና ሳትደርሺ ጀምረሽ ክላክስ አድርጊ ይከፍቱልሻል አልኳት እሺ አለችኝ።
በስልክ ውስጥ ጆሮዬን አስኪያመኝ ድረስ ክላክስ አደረገች።

በቃ ከፈቱልኝ ወደግቢ እየገባሁ ነው አታስብ ግን ማን ሊሆን ይችላል አሁን እራሱ ድንገት ከኋላዬ ዘለው ሚያንቁኝ ሚያንቁኝ እየመሰለኝ ነው አለች።

ውይ ማሂ እያስጨነቅሽኝ ነው ከሰውጋ ተጣልተሻል ወይ ያስፈራራሽ ሰው አለ እንዴ አልኳት::

አረ ጭራሽ ምን እንደማያቀኝ ትሆናለህ እኔ ከማንጋ ልጣላ እችላለሁ ተወው በቃ አባቴ ቤት ስለሌ ገና ሳልገባ ጀምሮ የፍርሀት ስሜት ተሰምቶኝ ይሆናል በቃ ቤት ገባሁ ።
ሌሊት እንቅልፍ እንቢ ካለኝ እደውልልሀለሁ እሺ እንድታነሳው አለችኝ

እሺ በቃ ማሂ አደራ የሆነ ነገር ካለ አሳውቂኝ እስከኔም አስፈራራሽኝኮ አንቺ ቦቅቧቃ ደሞ እንዳትፈሪ እሺ ብያት ስልኩ ተዘጋ።


✎ክፍል 32 ነገ ማታ 2:30 ይቀጥላል♥️    ቶሎ እንዲ🀄️ጥል LIKE♥️ እና Share አድርጉ።


  ይ🀄️ላ🀄️ሉን
https://t.me/+4dGFaH_mUnExZjg8
https://t.me/+4dGFaH_mUnExZjg8

💝የዩቲዩ ገፃችን💝
https://www.youtube.com/@Kezerareaction333
https://www.youtube.com/@Kezerareaction333

8.1k 0 29 12 358

ፅጌሬዳ




          ክፍል 30

ሁሉም ወደየቤቱ መሄድ ጀመረ እህቴ እኔ እናቴና የህቴ ባል ብቻ ቀረን።

ከዛን ቡሀላ ማውራት ጀመርን ምን ወሰናችሁ አልኳቸው።
እኔና አባትህ እዚሁ ለመኖር ወስነናል ድንገት ተነስቶ መሄድ ሚለው ነገር ቢቀር ባይ ነኝ ።
አሁን ልጄም ደርሳ ለትዳር በቅታልኛለች በማንኛውም ሰአት እናቷጋ መምጣት ብትፈልግ ጎረቤቷ ብሆን ይሻለኛል አባትህም እንደበፊቱ ስራውን መስራት ይችላል።
አንተም ብትሆን ወደዚሁ ተመልሰህ መኖር አለብህ።
መታወቂያህን እናወጣልሀለን ትምህርትህን የማታም ቢሆን ተምረህ መፈተን አለብህ።

ከዛን በመረጥከው ዘርፍ መማር ትችላለህ አለችኝ እናቴ።

እሺ እማ የናንተን ውሳኔ ልወቀው ብዬ እንጂ የኔ ነገር እንኳን አያስጨንቅም አልኳትና እጇን እያሻሸሁ ትኩር ብዬ አየኋት ፊትሽ አሁን እንደድሮው ሆኗል ተመስገን ብዬ ሳም አደረኳት።

አሁን በምን እጨነቃለሁ ውስጤም እርፍ ሲል መልኬም ተስተካከለ አደለ አለችና ያንን ነፍስ የሚዘራውን ፈገግታዋን ለገሰችኝ።

አቶ ሳሙኤልና አባቴ በሄዱበት ሲቆዩ እዚሁ ለማደር አስበው እንደሆነ ገባኝ።

ማታ አካባቢ ላይ ተመለሱ
ልክ እንደገቡ አይ የኔ ልጅ አባትህኮ በጨዋታ አታሎ እዚሁ አሳደረኝ ማሂ ትናደድብኛለች እንደው ምን ይሻለኛል ደውዬም እንዳልነግራት ፈራሁ አሉ።

አረ ችግር የለውም ምንም አትልም ደውሉላት ብያቸው ወደ ውጪ ይዣቸው ወጣሁ ደወሉላት ሄሎ የኔ ልጅ እንዴት አመሸሽልኝ።
ደና !
ምነው ድምፄሽ ቀዝቅዟል ??

አልቀዘቀዘም ቆየህኮ አለች!!
አይ የኔ ልጅ ቆየሁ አደል እዚህኮ ጨዋታ ይዤ መሸብኝ በናትሽ የኔ ልጅ እንዳትቀየሚኝ ነገ በሌሊት እመጣለሁ አሏት።

እሺ ገምቼ ነበር ችግር የለም አባቴ በቃ አንተ ዘና በል ከነሱጋ ስለኔ እንዳትጨነቅ እሺ ብላ ስልኩን ዘጋችው።

ተመልሰን ወደ ውስጥ ገባንና ሁላችንም የሞቀ ጨዋታ ያዝን እናቴና አባቴ ለአቶ ሳሙኤል ያላቸውን ክብር በቃላት መግለፅ ከባድ ነው።

ሲመሻሽ እህቴና ባሏ ወደቤታቸው
ሄዱ።
እኔ ሸኝቻቸው ተመለስኩና ጨዋታውን ተቀላቀልኩ በጨዋታችን መሀል ሁሉ ማሂ ትዝ እያለችኝ ነበር።

ወደ ምሽቱ ሶስት ሰአት አካባቢ ላይ ስልኬ ላይ ተከታታይ text ገባልኝ
ከማሂ ነበር
አንተ ማትረባ??
በጣም ትገርማለህ ጨክነህ ጥለኸኝ መሄድህን ማመን አልችልም ለነገሩ ባዳ ያው ባዳነቱን አይለቅም እንኳን ሄድክ እንደውም ተገላገልኩህ ይላል።

እሺ ብቻ አልኳት።

ግን በጣምም ለምኝኝ ያልክ አልመሰለህም እእእ ???

በድጋሜ እሺ አልኳት።

ጥሩ ግን አንድ የመጨረሻ ነገር ልጠይቅህ ሰዎች አንተ ፊደልን ባፈቀርክበት ልክ ማፍቀር ይችላሉ ወይስ ፊደል መስተፋቅር አሰርታብህ ነው እንዲህ ምትሆንላት እስቲ ንገረኝ አለች።


በቃ ትርፍ ንግግር አትናገሪ ማሂ ደህና ደሪ አልኳት።

ባድር ባላድር አንተ ምናገባህ ??
ቆይ እኔ ምኔ ነው ሚደብርህ እእ ተናገር እስቲ ላንተ ብቁ እንዳልሆን የሆንኩት ምኑጋ ነው ብላ ላከችልኝ ዝም አልኳት።

5 ደቂቃ ምናምን ቆየችና ደወለች ወጣ ብዬ  አነሳሁት ዘፈኑ ድብልቅ ያለ ቦታ ላይ ናት ጫጫታው ጩኸቱ ለጉድ ነው
ገና ከማንሳቴ ምን ይዘጋሀል እያወራሁህ አለች።
አፏ ተሳስሮ አታቀውም ነበር ምታወራውን ሁላ ።

ማሂ ደናነሽ አልኳት ደንግጬ ምን ደህንነት አለ አንተ እያለህ።

ድሮምኮ ብቸኝነቴን አቀዋለሁ  አለች እንባ እየተናነቃት ነበር

ማሂ የት ነው ያለሽው ግን ከራስሽጋ ነሽ አልኳት አዎ ከራሴጋ ነኝ ።
ግን አንተ ማትረባ ሰው መሆንህን ልነግርህ እፈልጋለሁ አለች።

እሺ ማሂ እኔ ምንም ልሁን ግን አሁን ቤት ካልሆንሽ ቤት ግቢ በፈጣሪ አልኳት ።
አያገባህም ቤት ብገባ ባልገባ
ይመለከትሀል ሲጀመር አንተ ለኔ ምኔ ነህ አለችኝ።

እሺ እኔ ላንቺ ምንም አልሁን አንቺ ግን ለኔ በጣም የምወድሽ የማከብርሽ ለማየት እንኳን የምሳሳልሽ ሰው ነሽ አልኳት ።

እእእ ምን አልክ ምን አልክ ቆይ አንዴ ልውጣ ብላ ከጫጫታው ውስጥ ወጣች
እስኪ አሁን ድገመው ያልከውን አለችኝ።
ምኑን አልኳት።

አሁን አንቺ ለኔ ምንድነሽ ነው ያልከኝ ተሳስተህ ነው ወይስ ከልብህ ነው
ከልብህ ከሆነ አንዴ ድገምልኝ አለች እሺ አልኳት።

አንቺ ለኔ በጣም የምወድሽ የማከብርሽ እዚህ ምድር ላይ ትልቅ ቦታ ከምሰጣቸው ሰዎች ዋናዋ ነሽ አልኳት።

ከት ብላ ሳቀች አንተ ገገማ እና እስከዛሬ ይሄን አትነግረኝም ነበር እእእ ቆይ ነገ ጠዋት ግን ተሳስቼ ነው አላልኩሽም አትለኝም አደል ለነገሩ ተወው ሪከርድ አድርጌሀለሁ አለች እየተፍለቀለቀች ብታምንም ባታምንም ስካሬ ሁላ ጠፋልኝ ቆይ አንዴ ሂሳብ ከፍዬ ልውጣ ጠብቀኝ እሺ እስከቤት እናወራለን ብላ ስልኩን ዘጋችው።

እኔ ትክዝ ብዬ ቁጭ አልኩኝ ማሂ ለኔ የሚሰማት ስሜት ምን እንደሆነ አቀዋለሁ ግን ማመን አልፈልግም እኔ ለሷ የሚሰማኝን ቁርጥ ያለውን ነገር አላቀውም ልቤ ውስጥ ያለው ፍቅር አሁንም ድረስ የፊደል እንደሆነ ማሰብ እፈልጋለሁ።

ከፊደልጋ ያሳለፍኩትን ጊዜ ፍቅር እሷ ከመሬት በታች ሆና እኔ ከመሬት በላይ ሆኜ ከሌላ ሴትጋ ባሳልፈው የምረግጠው አፈር ሁላ የሚታዘበኝ ይመስለኛል።

አንዳንዴ ደሞ ምናልባት ፈጣሪ እንደካሳ የሰጠኝ ሴት ማሂ ትሆናለች ብዬ አስብና መልሼ ደሞ አይሆንም ብዬ እራሴን እሸውደዋለሁ።

ያኔ ስትስመኝ ደስ ብሎኝ ነበርኮ ግን ደሞ ደስታዬን ማመን አልፈለኩም።

አንዳንዴ ዝም ብዬ ከማሂ መራቅ እፈልጋለሁ ዘላለሜን ልቤ ለፊደል ብቻ እንደሆነ መኖር እመኛለሁ።

ለማሂ የሚሰማኝን የፍቅር ስሜት በአግባቡ አላቀውም ሀዘኔታ በሚል ተልካሻ ምክንያት እራሴን እሸውደዋለሁ።

ግን ልክ ስንጣላ ይመስለኛል በደንብ ስሜቴን የተረዳሁት ።

ብቻዬን እየተብሰለሰልኩ ማሂ መልሳ ደወለች።

ሳቋ አልተቋረጠም ነበር።
እና ምን ላይ ነበርን ??

እኔጃ ምን ላይ ነው ያቆምነው አልኳት።

እኔጃ ብታይ ዛሬ ውጪ ሌሊቱን ሙሉ እየጠጣሁ ላድር ነበር ግን በቃ ስናወራ ደስ ስላለኝ ወደቤት እየተመለስኩ ነው አንተ ለካ ስካርን ድንጋጤ ያጠፋዋል ግን ምን ብለኸኝ እንደዚህ የሆንኩት ልቤ እስካሁን እየመታ ነው አለች።

እኔጃ እኔኮ እረሳለሁ ግን ምን ብዬሽ ነው እንደዚህ የፈነደቅሽው አልኳት መልሼ።

ያው እወድሻለሁ ነዋ ግን ምትወደኝ በምን መንገድ ነው መውደድ መውደድ የትኛውን መውደድ ነው ግን ምትወደኝ እእእ አለች።

አይ ማሂ እኔ ማቀው አንድ መውደድ ነው እኔ እወድሻለሁ ብዬሻለሁ አንቺ በምትፈልጊው አረዳድ ተረጅው ለኔ ችግር የለውም ግን ባለፈው በጣም አናደሽኝ ነበር ለዛ ነው ወደሀዋሳ የመጣሁት አልኳት።


✎ክፍል 31 ነገ ማታ 2:30 ይቀጥላል♥️    ቶሎ እንዲ🀄️ጥል LIKE♥️ እና Share አድርጉ።


  ይ🀄️ላ🀄️ሉን
https://t.me/+4dGFaH_mUnExZjg8
https://t.me/+4dGFaH_mUnExZjg8

💝የዩቲዩ ገፃችን💝
https://www.youtube.com/@Kezerareaction333
https://www.youtube.com/@Kezerareaction333

9.1k 0 33 12 318

ፅጌሬዳ




       ክፍል 29


ለሌሊት 11 ሰአት የሞላሁት አላርም ቀሰቀሰኝና ተነሳሁ ልብሴን ለባብሼ ማንም ሳያየኝ ከግቢ ለመውጣት ሹክክ እያልኩ ስራመድ አቶ ሳሙኤል እታችኛው ሳሎን ሱፋቸውን ዝንጥ ብለው እንደለበሱ ቁጭ ብለዋል።

ሳያቸው ልክ መልአከ ሞት ከፊት ለፊቴ የተቀመጠ እንጂ እነዚያ ደጉ ሰውዬ አቶ ሳሙኤል የተቀመጡ አይመስልም ነበር።

እእእእእ አቶ እእ ሳሙኤል ምነው በሰላም ነው ምነው አልኳቸው።


ተው እንጂ ልጄ ቢያንስ ሳልሸኝህ ሰላም ግባ ሳልልህ ዝም ብለህ ብትሄድ ላንተስ ህሊናህ ያርፍልሀል አሉኝ ።

አይ እኔኮ እንዳልረብሾት ብዬ ነው እንጂ ሌላ አደለም ደሞ እመለስ የለ እንዴ አልኳቸው ጥሩ ለማንኛውም እኔ ነኝ ቤተሰቦችህጋ ማደርስህ አሉኝ።
አኔ አይሆንም ሞቼ እገኛለሁ ብቻዬን እሄዳለሁ አልኩኝ እሳቸው እየተቆጡ አይ እንግዲህ አንዴ ተናገርኩ ተከተለኝ ብለው ወደመኪናቸው ገባንና ጉዞ ጀመርን።

ግን ድንገት እንድትወስን ያደረገህ ምንድነው አሉኝ።

አረ ድንገትኮ አደለም ያው ቤተሰቦቼም ትንሽ ሰሞኑን ተጨንቀዋል ከስልክ በላይ ደግሞ በአካል ሄጄ ብንወያይ መልካም ነው ብዬ አስቤ ነው አልኳቸው

ጥሩ ከቤተሰቦችህጋ ለማውራት ብለህ እንጂ ከማሂጋ ተጣልታችሁ ምናምን አደለም ማለት ነው አሉኝ።

አፌ ተሳስሮ ዝም አልኩኝ።
ልጄ እኔ አባት ነኝ ከአባትነቴም በላይ ህይወት ብዙ ነገሮችን አስተምራኛለች ከዛ ውስጥ ሰዎችን በዝምታ መረዳት ነው።

ሳላወራ ሳለፈልፍ ቀደም ቀደም ሳልል ዝም ብዬ  ሰዎችን መረዳት በዝምታዬ ውስጥም ለሰዎች መዳኒት መሆንን እፈልጋለሁ።

አንተና ማሂ እንደተጣላችሁ ማወቅ ለኔ ያን ያህል ከባድ አደለም ያንተም ሀዋሳ መሄድ ጥሩ ነው ምናልባት ትንሽ ስትራራቁ የልጅነት ፀባያችሁ ይለቃችሁና እንደትለቅ ማሰብ ትጀምሩ ይሆናል።

እኔ ማሂን አቃታለሁ በጣም ጎበዝ ጠንካራ ትግስተኛ ሁሉንም ሰው መረዳት ምትችል ልበ ሩህሩህ ሁሌም ቢሆን ከራሷ ጥቅም ሰዎችን ምታስቀድም ሴት ናት ።

ግን ትልቁ የማሂ ድክመት በጣም የቀረበችው የራሴ ነው  ብላ ያሰበችው ሰው ከሆነ እዛ ሰው ላይ ነፃነቷን ማወጅ ትፈልጋለች እንደህፃን መቅበት መሞላቀቅ ያምራታል ያንን ደሞ ሰው አይረዳትም
አንተንም ጨምሮ እንዳልተረዳሀት ነው የገባኝ አሉኝ።

አረ እንደዛ አደለም እኔኮ በጣም ተረድቻታለሀ ብታኮርፈኝም እችላታለሁ ድንገት ተነስታ ቅይር ትልብኛለች ትናደድብኛለች እኔ ግን እንደምንም ዋጥ እያደረኩት ለመቻል እሞክራለሀ አሁን ግን ጭራሽ የምር አኮረፈችኝ ሃናግራት ብሞክርም አልሰማ አለችኝ ቆይ የኔ ጥፋት ምኑ ላይ ነው።
እኔኮ ምንም ብታደርገኝ ብትገለኝ ሁላ አልቀየማትም ውስጧን አቀዋለሁ ክፋት የለባትም በሰዎች ላይ ተንኮል ምቀኝነት ሚለውን ነገር አታስብምኮ ግን በቃ ብቻ እኔ አሁንም እንደተጣላን አይሰማኝም ለጊዜው ከአይኗ ሰወር ልበል ብዬ የው እንጂ አልኳቸው።

ጥሩ አደርግ ነገሮችን ለማብረድ መሞከርህን ሳላደንቅልህ አላልፍም ግን አደራ እንዳትቀየማት እሺ እኔም ዛሬ እንደምትሄድ አልነገርኳትም እራሳችሁ ጨርሱ እኔ ጣልቃ ከምገባባችሁ አሉኝ።

በጣም አመሰግናለሁ ድሮ ልጅ እያለሁ የሌሎችን አባት አይቼ የኔን አባት ሳይ እዚህ ምድር ላይ ተከብሮ ሚያስከብር ለልጆቹ ሟች ቁም ነገረኛ አባት ያለው የኔ አባት ብቻ ይመስለኝ ነበር እርሶን ካየሁ ቡሀላ ግን ትክክል እንዳልነበርኩ ተረዳሁ ማሂ እናቷን ባታቃትም እርሶን የመሰለ ከናትም ከአባትም ከጓደኛ ከእህትና ከወንድም የበለጠ ሁሉን ያሟላ አባት ስላላት እድለኛ ናት እርሶ እስካሉላት  ድረስ የትኛውም ጉድለቷ ክፍተቷ ይታያታል ብዬ አላስብም።


ብቻ የአባትና የልጅ ወግ ይዘን የልብ የልባችንን እያወራን ስለቤቱም እያወጋን አዲስ አበባ ያሉትን የቤቶች ዋጋ እየነገሩኝ መንገዳችንን ቀጠልን።

ወደ ሁለት ሰአት አካባቢ ላይ ማሂ ደወለችና አባቴ የት ሄደህ ነው ሳትነግረኝ አለቻቸው።

ይቅርታ ልጄ ሰላም እንዳልነሳሽ ብዬ ነው ወደ ሀዋሳ ሄጃለሁ አሏት።

ምን ጮኸች ሳትነግረኝ ወደሀዋሳ ሄድክ አባዬ እኔ አላምንም ቆይ ምን ልትሰራ ነው የሄድከው አለች?

ትንሽ ጉዳይ አለችኝ እመለሳለሁኮ የኔ ልጅ አሏት ።
እሺ በቃ መልካም ቀን ዛሬ አብረን እንውላለን ብዬ አስቤ ነበር በቃ ችግር የለውም አለቻቸውና ስልኩ ተቋረጠ።

ሀዋሳ ከደረስን ቡሀላ ማሂ ደግማ ደወለች አባዬ ከማንጋ ነው የሄድከው አለች።

ምነው ልጄ ለምን ጠየቅሽኝ አሏት??

ንገረኝ ከማንጋ ነው አብራችሁ ነው እንዴ የሄዳችሁት አለች ስፒከር ላይ ስለነበር ድምጿን በደንብ እየሰማሁት ነበር።

አዎ የኔ ልጅ አድርሼው ልመለስ ብዬኮ ነው አሏት።

እውነት ይሄን ካንተ አልጠብቅም በፈጣሪ ስም እኔን በመሀል ቤት አገለላችሁኝ ማለት ነው እሱ ወደ ሀዋሳ ሲሄድ እኔ አላውቅም እእእ ቆይ እኔ ለሱ ይሄን ያህል ጨካኝ ነኝ ለነገሩ አንተ አባቴ ያለነገርከኝን እሱ እንዲነግረኝ መጠበቄ ነው የኔ ጥፋት ቻው አንዳችሁም እንዳትደውሉልኝ በጣም ነው ያዘንኩብህ ብላ ስልኩን ዘጋችው።

አየህ አደል ማሂ እንደዚህ ናት ይሄኔ መጣላታችሁንም እረስታው ይሆናልኮ አሉኝ።

እያወራን ወደቤት ገባን ቤት ሁሉም ተሰብስበው እየጠበቁን ነበር የእህቴ ባል ቤተሰቦች ሳይቀሩ መጥተው ነበር።

ሁሉንም በየተራ ሰላም ብዬ ተቀመጥኩኝ ከናቴ አጠገብ እቅፍ አድርጋ እያሻሸሸችኝ አይን አይኔን እያየችኝ ቁጭ አለች ወደራሷ ጥብቅ አድርጋ አስጠጋችኝና እኔኮ በህልሜ በህልሜ እየመሰለኝ ነው።

የሆነ ሰአት ተነሽ ነግቷል የሚሉኝ እየመሰለኝም እሳቀቃለሁ ብላ ግንባሬን ሳም አደረገችኝ ቡናው ተፈላ ቤቱ በእጣን ጭስ ደመቀ ሁሉም ሳቅ ጨዋታውን አደራው።

አባቴ ከነግርማ ሞገሱ ሶፋ ላይ ቁጭ ብሎ ከአቶ ሳሙኤልጋ የልብ የልባቸውን ያወጋሉ

እኔም ከናቴ አጠገብ ተነሳሁና ወደ እህቴ ባልጋ ሄድኩኝ። አጠገቡ ቁጭ ብዬ እንደወጣት እንደጓደኛ አወራሁት ስለትዳራቸው ጠየኩት በአግባቡ አጫወተኝ ቀለል ያለ ምርጥ ልጅ ነው ብዙ ማውራት እንደማይወድ ከሁኔታው ያስታውቃል ።

ምሳችንን በላልተን ቡናችንን ከጠጣጣን ቡሀላ አቶ ሳሙኤልና አባቴ  እስቲ አንዳንድ ነገሮችን አየት አየት አድርገን እንምጣ አሉና ከቤት ወጡ።


✎ክፍል 30 ነገ ማታ 2:30 ይቀጥላል♥️    ቶሎ እንዲ🀄️ጥል LIKE♥️ እና Share አድርጉ።


  ይ🀄️ላ🀄️ሉን
https://t.me/+4dGFaH_mUnExZjg8
https://t.me/+4dGFaH_mUnExZjg8

💝የዩቲዩ ገፃችን💝
https://www.youtube.com/@Kezerareaction333
https://www.youtube.com/@Kezerareaction333

8.3k 0 32 21 361

ፅጌሬዳ




            ክፍል 28

በነጋታውም ደገመችው ሳታናግረኝ ቀድማ ወደስራ ሄደች ።
ነገሩን እንዳመረረችው ገባኝ ።

እውነት ለመናገር ከሷጋ ስጣላ ስራ ቦታ ሄጄ ንጭንጭ ነው ምለው አንዳንዴ ማወራውን ምሰራውን ሁላ አላቀውም ልክ ጎዳና ላይ እንደነበርኩባቸው ጊዚያት ባዶነት ይሰማኛል ልክ ማረባ ሰው የሆንኩ ያህል ነው ሚሰማኝ።

ግን ደሞ በቃ ከመሬት ተነስታ እንደዚህ ምትሆን ከሆነ ምን ማድረግ እችላለሁ ብቻዬን እየተብሰለሰልኩ ስልኬ ጠራ ሳላስበው ፈገግ አልኩ።

ሄሎ ማሂ አልኳት ደስታ ውስጤን ውርር እያደረገው

ሰላም እንዴት ነህ ዛሬም order የተደረጉ እቃዎች አሉ ሲመችህ ናና አድርሳቸው ብላ ምላሼን ሳጠብቅ ስልኩን ዘጋችው ይሄ እሳት ላይ ውሀ የመከለስ ያህል ነበር ባንዴ ደስታዬ ጥፍት ያለው ።

ስራዬን ጨራረስኩ መሄድ አልፈለኩም ግን ግዴታ ብሩ እንደሚያስፈልገኝ ስለማቅ ብቻ ማሂጋ ሄድኩ።

ገና ሱቋጋ ሳልደርስ ፊቴን ክስክስ አደረኩትና ወደሱቋ ገባሁ ሰላምታ እንኳን ሳልሰጣት እቃዎቹን ስጭኝ አልኳት ሰጠችኝ ከሱቁ እየተቻኮልኩ ወጣሁ ብዙ እቃ ስለነበር ማደርሰው መሸብኝ።

አንዱን ካሳንቺስ ካደረስኩ ቀጣዩ ወሎ ሰፈር ሊሆን ይችላል ከዛ ስመለስ ወደ ጣፎ ልሄድ እችላለሁ በዛው ሰሚት ያዘዘም ይኖራል ብቻ ጡዘት ቢበዛውም ግን ብሩም አሪፍ ነው።

ማታ 2.30 አካባቢ ነበር ቤት የደረስኩት ስደርስ አቶ ሳሙኤል ቁጭ ብለው በር በሩን እያዩ ነበር ማሂ ግን ተኝታለች።

ሰላምታ ሰጠኋቸውና አጠገባቸው ሄጄ ቁጭ አልኩኝ ና እስቲ ልጄ ሰሞኑን ፊትህ ልክ አደለም ህይወት እንደሰለቸችው ሰው እየሆንክ ነው የቤተሰቦችህ ነገር እያስጨነቀህ ይሆን እንዴ ምንድነው የደበረህ ያስከፋህ ስራህ ላይ አልሳካ ያለህ ነገር አለ እንዴ አሉኝ።

አይ የለም ብቻ አልኳቸው።

አይዞህ የኔ ልጅ ትንሽ ጊዜ ነገሮች እስኪስተካከሉ ብቻ ነው እሺ እኔ ምን አይነት ስራ እንደምሰጥህ ታያለሀ ግን እስከዛው ወጣት ስለሆንክ በአዲስ ጉልበት በደንብ ተንቀሳቀስ የኔና ያንተ አባትና ልጅነታችን መቼም አይፋቅም እሺ አሉኝ።
የዛኔ እንባዬ መጣ አቀፍኳቸው በእውነት እንደዚህ አይነት አስተሳሰብ ያለው ደግ ልበ ቀና ሰው ያለ አይመስለኝሥ ነበር።
አመሰግናለሁ አባት በሌለኝ ሰአት አባት
ቤተሰብ በሌለኝ ሰአት በረተሰብ ስለሆናችሁኝ አባቴን በኔ ምክንያት ያጣውን ክብሩን ስለመለሳችሁልኝ ብቻ አመሰግናለሁ ፈጣሪ ይሄንን ውለታ ምመልስበትን እድሜ ብቻ ይስጠኝ አልኳቸው።

ጀርባዬን መታ መታ እያደረጉ አየህ ውስጥህ ልክ አደለም ብዬሀለሁኮ እቀፈኝና በደንብ አልቅሰህ ይውጣልህ ነገሮችን በውስጥህ እንዳታስቀምጥ በሽታ ነው ወይ አልቅሰህ ይውጣልህ ወይ ተናገረው አሉኝ።

ዝም ብዬ ማልቀስ ጀመርኩ ምን ማልቀስ ብቻ ተንሰቀሰኩ ማለት እችላለሁ እንጂ።

አልቅሼ ስጨርስ ቀና ብዬ አይናቸውን ለማየት እያፈርኩ ገብቼ ተኛሁ።

ስላለቀስኩ ትንሽም ቢሆን ቀለል ብሎኝ ነበር ግን ረሀቡ በተራው አላስተኛም አለኝ።

ጠዋት ቁርስ እንደበላሁ ነው ለካ የዋልኩት በጣም ብዙ ቦታ ስለዞርኩም የበላሁት ተራግፏል ።

ተመልሼ ተነስቼ አልበላ ነገር ደበረኝ እየራበኝ እንዳልተኛ ደሞ ራበኝ
ለትንሽ ደቂቃ በእንቅልፍ ለማሳለፍ ትግል ጀመርኩ ግን አቃተኝ።

ኤጭጭ አሁንስ ቆይ በረሀብ ከመሞት መብላት አይሻለኝም እንዴ
አንዴ እነሳለሁ አንዴ እቀመጣለሁ በዛ መሀል ሰራተኛዋ በሰሀን ምግብ ይዛ መጣችና ጋሼ ናቸው እራት ሳይበላ እንዳይተኛ ያሉት አለችኝ።

ከሰማይ መና እንደወረደለት ሰው በውስጤ ፍንድቅ እያልኩኝ ተቀበልኳትና ጥርግ አድርጌ እራቴን በልቼ ተኛሁ።

በነጋታው ከእንቅልፌ እንደተነሳሁ አባቴጋ ደወልኩና እሁድ ወደ ሀዋሳ እንደምመጣ ነገርኩት ።

ለምን ልጄ በሰላም ነው ተጣላህ እንዴ ከነሳሙኤልጋ አለኝ።

አጋጣሚ እናቴም አብራው ነበረች ልጄ ከመጣህ ቡሀላ ናፍቆትህ ብሶብኛል እባክህ ና ባይሆን ትመለሳለህ አለችኝ።

እሺ እናቴ እመጣለሁ እኔም ናፍቃችሁኛል አልኳትና ወዳባቴ ተመለስኩ

አባቴ  ከነሱጋ ተጣልቼ ሳይሆን እዛው ሆኜ ያለውን ነገር በደንብ ብናወራ ብዬ አስቤ ነው አልኩት ።

እሺ ልጄ ናልኝ እኔም ወደዛ መምጣቴ ስለማይቀር ባይሆን አብረን እነመለሳለን አለኝ።

እኔ እንኳን ስለመመለሴም እርግጠኛ አደለሁም ግን በቃ ስመጣ ሁሉንም እናወራዋለን ወደስራ ልሄድ ነው አይርፈድብኝ ብያቸው ስልኩን ዘጋሁትና ተነስቼ ለባበስኩና ከአቶ ሳሙኤልጋ ቁርሳችንን መብላት ጀመርን ።

ማሂ ሰሞኑን ሌሊት ሹልክ እያለች ነው ምትወጣው ሰላም ነው አደል ካንተጋም ታወራላችሁ አደል?? አሉኝ

አረ አዎ ሰላም ነን ስራ በዝቶባት ይሆናል አልኳቸው ምንም እንዳልተፈጠረ ነገር አድርጌ።

የኛ ስራ ዛሬ በጣም ቢዚ ከሆንን ነገ ሊጠፋ ይችላል ዛሬ ስራ ጠፍቶ ቁጭ ብለን ከዋልን ደሞ በሚቀጥለው ቀን የትኛውን መኪና እንደምንሰራ እስኪቸግረን ድረስ ስራ ሊበዛ ይችላል ዋናዎቹ መካኒኮች ወይም chif  መካኒክ የሚባሉት አንዳንዴ አስከሌሊቱ 6 ሰአት እየሰሩ ሊቆዩ ሁላ ይችላሉ።

እኔ ወደስራ ስገባ በጣም በስራ ተወጥረው ነበር እኔም ልብሴን ቀያይሬ  ተቀላቀልኳቸውና ከሁሉምጋ እየተሳሳቅሁ መስራት ጀመርኩ ምሳም ከነሱጋ አብሬ በላሁ።

ማታ ላይ ወደቤት ከመሄዴ በፊት ለማሂ text አደረኩላት ።

አባትሽ መጠርጠር ሳይጀምሩ አይቀሩም ከቻልሽ ዛሬ በጊዜ ነይ አይዞሽ ምንም አላወራሽም ግን ሁሌ ድብብቆሽ ስንጫወት መጠርጠራቸው የማይቀር ነው አልኳት።

እሺ አለችኝ።

ቤት ስሄድ ቀድማ ገብታ ጠበቀችኝ እንደኖርማል ሰላም አልኳትና እራት አብረን በላን ።
ትንሽ ሰብሰብ ብለን አወራንና ሁላችንም ወደመኝታችን ሄድን።

ያች ሶስት ቀን እንደምንም አለፈችና ቅዳሜ ማታ ማሂ ከመምጣቷ በፊት ለአቶ ሳሙኤል ወደ ሀዋሳ ልሄድ እንደሆነ ቤተሰቦቼ እንደናፈቁኝ ስራም ለተወሰነ ጊዜ ብቻ እረፍት እንደሰጡኝ የትምህርት ማስረጃዬንም ማስተካከል እንዳለብኝ መታወቂያም እንደሚያስፈልገኝ ብቻ ብዙ ሰአት ብቻዬን ለፈለፍኩኝ።

ፈገግ አሉና እሺ ልጄ አንተ ሚበጅህን መች አጣኸው ሰላም ግባ ሰላም ተመለስ አሉኝ።

እሺ ብዬ ጉልበታቸውን ስሜ ወደመኝታ ቤት ገባሁ ሰሞኑን የሰራሁትን ብርና እራሴ በእጄ የገዛሁትን ልብስ ብቻ ያዝኩኝ ማሂ የገዛችልኝን እየመረጥኩ አስቀመጥኳቸው በኔ ቤት እኔን ቅጥል እንዳደረገችኝ እሷም ቅጥል እንድትል ብዬ ነበር።

አቶ ሳሙኤል አሁን ባልነገሯት ከሄድኩ ቡሀላ ባወቀች እያልኩ ፀሎት ማድረግ ጀመርኩ።

ልብሶቼን እያስተካከልኩ 3 ሱሪና ሁለት ቲሸርት አንድ ሸሚዝ ብቻ ያዝኩኝ በትንሽዬ ቦርሳ ውስጥ ከተትኳት ሻወር ወሰድኩኝ ምለብሰውን ልብስ አዘጋጀሁኝና ተኛሁ ።


✎ክፍል 29 ነገ ማታ 2:30 ይቀጥላል♥️    ቶሎ እንዲ🀄️ጥል LIKE♥️ እና Share አድርጉ።


  ይ🀄️ላ🀄️ሉን
https://t.me/+4dGFaH_mUnExZjg8
https://t.me/+4dGFaH_mUnExZjg8

💝የዩቲዩ ገፃችን💝
https://www.youtube.com/@Kezerareaction333
https://www.youtube.com/@Kezerareaction333

9.5k 0 34 19 396

ፅጌሬዳ




        ክፍል 27


ለምን ይሄን የማደርግበት  እኔን ሊያሳምነኝ የሚችል  አንድ ምክንያት ብቻ ንገሪኝና አደርገዋለሁ አልኳት ።

በቃ አሳማኝ ይሁን አይሁን አላቅም ግን እኔ ደስ አይለኝም አለቀ።

የራስሽ ጉዳይ ነው አወራለሁ ብለህ ካሰብክ አውራ ግን ለኔ ትኝሽ resepect ካለህ በቃ አታውራ ደስ አይለኝም አለች።

ሳቄን መቆጣጠር አቃተኝ ማሂ ግን ደና ነሽ ማለቴ አሁን የኔ ስልክ ማውራት አለማውራት ላንቺ ክብር ከመስጠትጋ ምን አገናኘው አልኳት ።

በቃ ትርፍ ንግግር አልፈልግም ወደ ቤት ሄጄ እረፍት ማድረግ እፈልጋለሁ አለችና ወደኋላ ተመለሰች አልተከተልኳትም
ለራሴ ጊዜ መስጠትን ፈልጌ ነበር ወደፊት ወክ እያደረኩ መራመድ ጀመርኩ ።

አባቴ ያለኝን ነገር እንደ አዲስ ማሰላሰል ጀመርኩ ።

አሁን ቤቱ ባይሸጥና ወደዚህ ባይመጡኮ የአቶ ሳሙኤልን እዳ ከየት አምጥተን እንከፍላለን።
እኔስ ተመልሼ እዛ ሄጄ ልኖር ነው ወይስ እዚህ እነማሂጋ እስከመቼ ልቆይ ነው ግራ ገባኝ ።

የቤተሰቦቼ ህይወት መስመር ከያዘና ከተስተካከለ እነሱ ሚመቻቸው ቦታ ቢኖሩ ደስታዬ ወደር የለውም ግን ተመልሶ አባቴ በእዳ መያዝና መጨነቁ አይቀርም እኔ ደሞ ምን ሰርቼ ነው እዳቸውን ልከፍልላቸው ምችለው እቃ ለማድረስ ከተማ ለከተማ ዞሬ ነው ወይስ ደሞ ጋራዥ ውስጥ መሬት ለመሬ ተንከባልዬ ነው አላቅም ብቻ ምን ማሰብ እንዳለብኝ እስኪያቅተኝ ድረስ ሆድ ባሰኝ ውስጤን ባዶነት ተሰማኝ።

በመሀል አባቴ ደወለና አሁን እናውራ እንዴ ቤት ነህ?? አለኝ
አይ አባቴ ልገባ ነው ትንሽ ነው የቀረኝ ቆይ መልሼ እደውልልሀለሁ ብዬው ስልኩ ዘጋሁት።

ወደቤት ተመለስኩ
ቤት ስገባ ማሂ ጋቢ ለብሳ ያባቷ ጉልበት ላይ ተደግፋ ተኝታለች ።

አባቷ ፀጉሯን እያሻሹ ይደባብሷታል ሲያዩኝ ኖር ልጄ ተቀመጥ ተቀመጥ አሉኝ።

በእግዜር አይገባም ብያቸው ቁጭ አልኩኝና አባቴጋ ደወልኩ

አነሳው ከሁሉምጋ ሰላምታ ከተቀያየርኩ ቡሀላ ወደጉዳያችን ገባሁ ስፒከር ላይ አድርጌው ነበር ማወራቸው

መጀመሪያ የናቴ ሀሳብ ምን እንደሆነ ጠየኳት እኔ ልጄ ሁለት ልብ ነኝ እዚህ ብንኖርም ብዬ አስባለሁ በሌላ በኩል ደሞ ምናልባት ቢሸጥም ትርፋማ ልንሆን እችላለሁ ብዬ አሰብኩ ግን ከኔ በላይ የውጭውን ነገር እናንተ ታቁታላችሁ
አለች።

እህቴን በተራዋ ጠየኳት እሷ አሁን ከባለቤቷጋ እየኖረች ስለሆነ ዞሮ ዞሮ ከሀዋሳ እንደማትወጣ ነገረችኝ።

አባቴ ደሞ በተራው እኔን ጠየቀኝ ቁርጥ ያለ ነገር መናገር አልቻልኩም በቃ አንተና እማዬ ቁርጥ ያለ ውሳኔ ላይ ድረሱና አሳውቁኝ እኔ በሁለቱም ሀሳባችሁ እስማማለሁ አልኩት አቶ ሳሙኤልም ጎሽ ልጄ እንደሱ ነው ሚሻለው እነሱ እንዲወስኑ እድሉን ስጣቸው አሉኝ።

አንዳንድ ነገር ካወራን ቡሀላ ውሳኔ ላይ ሲደርሱ ደውለው እንዲያሳውቁኝ ነግሪያቸው ስልኩ ተዘጋ።

አቶ ሳሙኤል ውሎዬ እንዴት እንደነበር ስራ እንዴት እየሄደልኝ እንደሆነ ያለውን ነገር እንደ አባት ከጠየቁኝ ቡሀላ
ገብቼ ተኛሁ ።

አንዳንዴ ጭንቅላታችን ሀሳብ በዝቶበት ይሁን ብቻ እኔጃ ግን የትኛውን ነገር ማሰብ እንዳለባችሁ እራሱ ግራ ገብቷችሁ አያውቅም በቃ ለማሰብ ሞክሬ ግን ማሰብ በራሱ ከበደኝ

በነጋታው ማሂ ሳትቀሰቅሰኝ ቀድማ ወደስራዋ ሄደች አቶ ሳሙኤል ቁርስ እየጠበቁኝ ነበር በሰላም ነው ማሂ በጠዋት የወጣችው አልኳቸው።

አዎ ልጄ ስራ ቦታ ሚጠብቁኝ ሰዎች አሉ ለነሱ ቶሎ እቃ መስጠት አለብኝ ብላ በጠዋት ነው የወጣችው አሉኝ።

ቁርስ በላልተን ስንጨርስ ልብሴን ቀያይሬ ወጣሁ።
ልክ ከቤት እንደወጣሁ ደወልኩላት አታነሳም ደሞ በምን አኩርፋ ይሆን ይቺ ልጅኮ ጤነኛ አደለችም እያልኩ ወደ ስራዬ ሄድኩ ቀኑን ሙሉ በስራ ተወጥሬ ነበር ስራውን እየለመድኩት ስመጣ መኪና እየፈታሁ የውስጡን ነገር ደሞ እነሱ እንዲጨርሱት ለባለሙያ መስጠት ጀመሪያለሁ  3000  የተቀበልኩትን እቃ ለነሱ ከ7እስከ 8 ሺ እሸጥላቸዋለሁ ።

የዛን ቀን እስከ 11 ሰአት ድረስ አንድ መኪና አስቸግሮን እሱን ለመጨረስ ስንለፋ ነበር ።

11 ሰአት ላይ ማሂጋ ልሂድና በዛው ምሳ እንበላለን አብረን ወደቤት እንመለሳለን ብዬ ሱቋ ሄድኩ።

ብታይ እንዴት እንደራበኝ ጠዋት ደሞ ምንድነው ስልክ ማታነሺው ለማንኛውም ነይ በቃ አብረን ምሳ እንብላ አልኳት።

አይ በልቻለሁ አንተ ብላ አለችኝ ፊቷን እንደቋጠረችው።

ማለት ሳትደውይልኝ በላሽ ምን ሆነሽ ነው አልኳት ሁኔታዋ ግራ አጋብቶኝ።
ምንም አልሆንኩም አንተ ወደህይወቴ ሳትመጣ በፊትምኮ ብቻዬን ነበር ምበላው አለችኝ ተኮሳትራ።

ነገሮችን ለማብረድና ለመሳቅ እየሞከርኩ በናትሽ ቀኑን ሙሉ ከመኪናጋ ስታገል ውዬ በጣምም ደክሞኛል አሁን ደሞ ያንቺን ኩርፍታ መቋቋም አልችልም አትጃጃይ በናትሽ አላሳዝንሽም እንዴ አልኳት።

ምንም አልመሰላትም ነበር ንግግሬ

እኔ ምን አልኩህ በልቻለሁ አልበላም ነውኮ ያልኩት አለችኝ ጭራሽ እንደመቆጣትም እያደረጋት ነበር።

እሺ ብያት ሱቁን ትቼ ወጣሁና ወደቤት ሄድኩ እውነት ለመናገር taxi ውስጥ እንባ እየተናነቀኝ ከራሴጋ ላለማልቀስ እየታገልኩ ነበር ሰፈር የደረስኩት።

ከtaxi ከወረድኩ ቡሀላ በእግሬ እየተራመድኩ ብዙ ነገር ማሰብ ጀመርኩ ማሂ ከመጠን በላይ አናዳኛለች ለምን እንደዚህ እንደምትሆን ፈጣሪ ይወቀው ግን ይሄ ኩርፍታ ሚባል ነገር በጣም ነው አብሮን ያለን ሰው የሚጎዳው።

ቤት ስገባ አቶ ሳሙኤልም ቤት አልነበሩም  ደወልኩላቸው

ወደድርጅታቸው ሄደው እዛው ከስራ ባልደረቦቻቸውጋ እራት ለመብላት እንደወጡና እዛው እንደሚያመሹ ነገሩኝ

ምግቤን በላላሁና ቁጭ አልኩኝ ሲደብረኝ እህቴጋ ደወልኩና እረጅም ሰአት አወራን ከሷጋ ስጨርስ ከናትና አባቴጋ አወራሁ አባቴ በዛውም ግቢውን በባለሙያ እያስገመተው እንደሆነና አሪፍ ገንዘብ እንደሚያወጣ ነገረኝ
በዛውም እኔ እዚህ ያለውን የቦታ ሁኔታ በደንብ አጥንቼ እንድነግረውም ጨምሮ ነገረኝና ስልኩ ተዘጋ።

ብዙም ሳይቆይ ማሂ መጣች ነገ የታዘዙ እቃዎች አሉ እና በሚመችህ ሰአት መጥተህ አድርሳቸው አለችኝ።

ሰራተኛዋ መጥታ እራት ላቅርብልሽ እንዴ ብላ ጠየቀቻት አይ በልቼ ነው የመጣሁት ደክሞኛል ልተኛ ነው ብላ ወደክፍሏ ገባች።

ሁኔታዋ በጣም አናደደኝ በፍጥነት መኝታ ቤት ገብቼ አልጋው ላይ ተዘረርኩ ትራሱን አፌ ላይ አፍኜ ለመጮህ ሞከርኩ ወደውስጥ እንጂ ወደ ውጪ መጮህ አልቻልኩም ነበር።

ምን አስቀይሚያት እንደሆነ ለማሰብ በሞከርኩ ቁጥር እንባዬ ይፈሳል ለቅሶዬን ዋጥጥ ለማድረግ ብሞክርም አቃተኝ
የበታችነት የባዶነት ስሜት ተሰማኝ።

በነጋታውም እኔ ከመነሳቴ በፊት  ቀድማኝ ወጥታ ነበር።

በቃ ጥሩ እኔ ማንንም መለመን የለብኝም  ስራዬን ልሰራራና ወደ ቤተሰቦቼ እመለሳለሁ

ተቀብያት ከሱቁ ወጣሁ እቃዎቼን አደራርሼ ስመለስ የእቃውን ብር ለሷ ሰጠኋት የራሴን ትርፍ ደሞ እራሴጋ አስቀረሁት ።
ማታ ቤት ስገባ ለአቶ ሳሙኤል በደንብ ሰላምታ ካቀረብኩ ቡሀላ ዛሬ በጣም እንደደከመኝ እራትም በልቼ እንደመጣሁ መተኛት እንደምፈልግ ነግሪያቸው ወደ መኝታ ቤቴ ገባሁ

ይቀጥላል....


✎ክፍል 28 ነገ ማታ 2:30 ይቀጥላል♥️    ቶሎ እንዲ🀄️ጥል LIKE♥️ እና Share አድርጉ።


  ይ🀄️ላ🀄️ሉን
https://t.me/+4dGFaH_mUnExZjg8
https://t.me/+4dGFaH_mUnExZjg8

💝የዩቲዩ ገፃችን💝
https://www.youtube.com/@Kezerareaction333
https://www.youtube.com/@Kezerareaction333

10.6k 0 31 36 305

ፅጌሬዳ



      ክፍል  26

አረ አቶ ሳሙኤል ከሴት ልጅ በላይ  ወንድ ልጅ ነው ጠቃሚው እሱ ነው መከታ ሚሆነው እኔ እሻሎታለሁ አልኳቸው።
ማሂ እየሳቀች ከኋላ የመጣ አይን አወጣ አሉ ጭራሽ ሴት ልጅ ያን ያህል አስፈላጊ አደለም እያልክ ነው ለነገሩ አባቴ ከኔና ካንተ ማንኛችን እንደምንጠቅመው ያቃል አደል እንዴ አባቴ አለች እየተፍለቀለቀች።

አረ እኔ ስቀልድ ነው ልጆቼ
ሁሉም ሰው የየራሱ የሆነ ቦታ አለው የሚፈለግበት ልክ አለው አንዱን በአንዱ ቦታ መለካት ጥሩ አደለም አሉንና እኔ እንቅልፍ ሰአቴ እየደረሰ ስለሆነ ልተኛ በቃ እናንተ ተጫወቱ ብለው ተነሱ

እንዴ በዚህ ሰአት መተኛት የጀመርከው ከመቼ ጀምሮ ነው ትንሽ ቆይ እንጂ አለች ማሂ !!

አይ ልጄ ዛሬ ደከምከም ብሎኛል ልተኛ ብለው ወደመኝታ ቤታቸው ገቡ።

ማሂ አይን አይኔን እያየች አባቴኮ በውስጡ ስለሚይዝ ነው እንጂ በጣም አስከፍቼዋለሁ አውቆኮ ነው ሚስቀው
ወይኔ በናትህ እሱ እንደዚህ ከሚከፋብኝ ከሚያዝንብኝ ባልነግረው ይሻለኝ ነበር አለች።

አረ ማሂ ተረጋጊ እኔና አንቺ እንድናወራ ብለውኮ ነው ምናልባት ከፍቶሽ ደብሮሽ አዝነሽ ከሆነ ከኔጋ እንደጓደኛ እንድታወሪም አስበው ይሆናልኮ በቃ ተረጋጊ እራስሽን አታስጨንቂ አልኳት።

ምሽቱን ዝም ብለን ስናወራ ስንሳሳቅ አመሸንና እሷም ካባቷጋ እኔም ከትራሴጋ ተቃቅፈን ተኛን።

በነጋታው በጠዋቱ ያባቴ ስልክ ነበር ከመኝታዬ ያነቃኝ
ሄሎ አባቴ !
እንዴት አደርክ ልጄ ከእንቅልፍህ ቀሰቀስኩህ መሰለኝ እንዲሁ ስብሰለሰል አድሬኮ ካንተጋ ባወራ ቀለል ይለኛል ብዬ ነው ልጄ ሀሳብህንም ብትነግረኝ መልካም ነው አይመስልህም አለኝ።

አረ ልክ ነህ አባቴ ግን ስለምንድነው ምናወራው ማለቴ ያስጨነቀህ ነገር አለ እንዴ አልኩት።

ምን መሰለህ ልጄ መቼስ አሁን እዚህ ያለንን መሬት ሸጠን ወደ አዲስ አበባ ለመምጣት ተስማምተናል ግን ምን መሰለህ እዚህ ያለው ግቢያችን በጣም ሰፊና ንፁህ እንደሆነ ታቃለህ
ይሄንን  ግቢያችንን ብንሸጠው እና እዛ ለመግዛት ብንሞክር እዛ የተሻለ ቦታ እንኳን አይገዛልንም እዚህና እዛ መሬት ሰማይና ምድር ነው ።
በዛ ላይ አሁን ልጄን ከዳርኳት የሰፈሩ ሰው እንደቀድሞው ሲያከብረኝ ጎንበስ ቀና ሲልልኝ ሳይ ደሞ ድጋሜ ሰፈሩን ትቼ መሄዴ ልቤን እርብሽ እርብሽ አደረገኝ።

ተወልደን ተድረን ወልደን ከብደን ከኖርንበት ቤት መውጣት ለናትህም ቢሆን ሊከብዳት ይችላል ልጄ አንተ እንደሀሳብ ምን ትለኛለህ አለኝ ።

ዝም አልኩኝ እኔጃ አባቴ ከናቴና ከእህቴጋ አውሩበትና አብራችሁ ሆናችሁ ደውልልኝ እኔም እስከዛ ትንሽ ላስብበት አልኩትና ስልኩን ዘጋሁት።
   
ከመኝታዬ ተነሳሁና ተጣጠብኩኝ ማሂም አባቷም ተነሱ ቁርስ ቀረበና እየበላን ለሁለቱም ያለውን ነገር ነገርኳቸው በነሱ በኩል ምን እንደሚያስቡ ጠየኳቸው።

ማሂ ድንግጥ ብላ እንዴ ማለት እነሱ ቤታቸውን ሸጠው ካልመጡ አንተ ልትሄድ ነው አለችኝ??

አይ ማሂ እሱን ፈጣሪ ያውቃል አልኳት

ፈጠን ብላ አይ በቃ ይሽጡት አለች።

አቶ ሳሙኤል ገልመጥ አደረጓትና ተይ ልጄ እንደዚህ አይባልም ።
እሱ የነሱ ውሳኔ ነው

እኔ ያለውን ነገር ካባትህጋ አወራለሁ አንተም አስቲ በደንብ አስብበትና ማታ ቁጭ ብለን ደውለን እናወራቸዋለን አሉኝ።
እሺ ብዬ ከቁርስ ቡሀላ  እንደተለመደው ማሂ ወደ ጋራዥ አድርሳኝ ብዙ ዴሊቬሪ እቃዎች ስላሉ ከሰአት ሱቅ እንድመጣ ነገራኝ ተለያየን።

ባጋጣሚ ጋራዥም ብዙ ሚያስፈልጉ እቃዎች ስለነበሩ ካንዱጋ ሌላውጋ ስሽከረከር ሳላቀው 8 ሰአት ሆነ
የቀረኝን አንድ እቃ ለሞተረኛ ላኩና እኔ ወደማሂጋ ሄድኩ:: እስከዛ ሰአት ድረስ ምሳ ሳትበላ እየጠበቀችኝ ነበር።

አብረን ምሳ በላንና እቃዎቼን ይዤ እንደተለመደው አሪፍ ብር ሰርቼ ተመለስኩ ብሩን ለማሂ ሰጠኋትና አስቀምጭው አንችጋ አልኳት ።

ወደቤት አብረን እየተመለስን ስልኬ ጠራ
delivery ያደርስኩላት አንድ ልጅ 200 ብር ቲፕ ሰታኝ ነበር ።
እሷ ናት የደወለችው መጀመሪያ አላወኳትም ነበር ከዛ ግን ስሟን ስትነግረኝ ትዝ አለኝ ፈታ ያለች ልጅ ናት እያወራን በመሀል እኔ መሳቅ ጀመርኩ ደንበኛ እንደምትሆን ምናምን እየነገረችኝ በዛውም ጓደኛሞች መሆን እንደምንችልም ነገረችኝ።
ማሂ ፊቷ እየተቀየረ መኪናውን በፍጥነት መንዳት ጀመረች ቆይ መልሼ እደውልልሻለሁ ብዬ ስልኩን ዘጋሁትና ቀስ በይ እንጂ ማሂ ምን ሆነሻል አልኳት።

ለማውራት አልተመቸህ ሆኖ ነው መቼ ነው መልሰህ ምትደውልላት ደሞስ ስራህን አደል እንዴ የሰራኸው ከደንበኛጋ እንደዚህ መገልፈጥ ምን ይሉታል አለችኝ እየተኮሳተረች።

አይ እንግዲ ማሂ ደሞ ችግር አለብሽ ማንን ማውራት እንዳለብኝና እንደሌለብኝ አንቺ ነሽ እንዴ ምትነግሪኝ እንዴ ደሞስ ደንበኛ ሰው አደለም ያለው ማነው ጓደኛሞች እንሁን አለችኝ እሺ አልኳት አለቀ አንቺ ምን ያናድድሻል ስላት መኪናውን አቆመችና ውረድ አለችኝ።

የምርሽን ነው ልውረድ??
አዎ ውረድ አሁን ደውልላትና እዚሁ ጨርሰህ ና ወደቤት አለችኝ እንደለመደችው እንባ እየተናነቃት ነበር ስታወራ ።

ሁኔታዋ ግራ ስላጋባኝ ዝም ብዬ ቁጭ አልኩኝ።
አትወርድም እኔ ልውረድ አለችኝ በድጋሜሜ


የዛኔ በአንዴ ቅይርር አልኩኝ
ለምንድነው ከገዛ መኪናሽ ምትወርጅው እኔ ወርድልሻለሁ እንጂ ኤጭ አሁንስ በጣም ነው የሰለችኝ ማሂ አሁን ይሄ ምኑ አናዶሽ ነው እንደዚህ ምትቀየሪው ካንቺጋ እንደልጅ መጣላት መታረቅ እየሰለቸኝ ነው በቃ እንደውም እራሴን ማዳመጥ እፈልጋለሁ በእግሬ እመጣለሁ ሂጅ ብያት ልወርድ ስል  መኪናውን አስነስታ ነዳችው።

አንቺ ግን ጤነኛ ነሽ ማሂ ቆይ ልክ ነው ማደርገው ብለሽ ታስቢያለሽ ማሂ ለኔኮ ብዙ ነገር አድርገሽልኛል አሁን ሰው ሆኜ ብዬድ ብለብስ ቢያምርብኝ ከሰዎችጋ ብግባባ ለሁሉም ነገር ምክንያቷኮ አንቺ ነሽ ንፁህ ልብ እንዳለሽ አቃለሁ ግን ማሂ እኔ ይሄ ምታኮርፊው ነገር የሆነ ቀን እንዳይሰለቸኝ እፈራለሁ በናትሽ በቃ እንደልጅ ቶሎ ቅይር ቅይር አትበይ እሺ እኔ ብዙ ሚያስጨንቀኝ ና ውስጤን ባዶነት እንዲሰማኝ የሚያደርገኝ ብዙ ነገር  እንዳለ ታቂያለሽ በዛ ላይ አንቺ በየደቂቃው ስትቀያየሪቢኝ ደሞ በጣም ይከፋኛል ያበሳጨኛል
ማሂ አብረሽው ምትውይው ሰው ሁሌ ደስተኛ ሲያደርግሽ አብረሽ ስትስቂ ስትደሰቺ ስትከፊም አብረሽ ሲሆን ነው ደስ የሚለው እንጂ አሁን እየሳቅሽ ነው ሳልጨርስ ምታኮርፊ ከሆነ ከባድ ነው።

ብታምኝም ባታምኚም ያን ያህል ጊዜ ከፊደልጋ ስንቆይ አንድም ቀን አኩርፋኝ አታውቅም ምንም ነገር ሲፈጠር በግልፅ ነው ምንነጋገረው እንጂ አንኮራረፍም አልኳት።

ዝም አለችኝ
ዝምታዋ ደሞ መልሶ አስፈራኝ ሰው ዝም ሲል በውስጡ ትልቅ ነገር እያብሰለሰለ ነው ዝምታ ሲበዛ ያስፈራኛል ።

ግቢ ውስጥ ከደረስን ቡሀላ መኪናዋን አቆመችና ወረድን ወደቤት ልትገባ ስትል ነይ የሆነ ቦታ ደርሰን እንምጣ ብዬ ወደውጪ ይዣት ወጣሁ።

እንደዛ ከሆነ ሁለተኛ አጠገቤ ሴት እንዳታወራ ያሁኗንም ልጅ ብሎክ አድርጋትና አሳየኝ አለችኝ።


✎ክፍል 27 ነገ ማታ 2:30 ይቀጥላል♥️    ቶሎ እንዲ🀄️ጥል LIKE♥️ እና Share አድርጉ።


  ይ🀄️ላ🀄️ሉን
https://t.me/+4dGFaH_mUnExZjg8
https://t.me/+4dGFaH_mUnExZjg8

💝የዩቲዩ ገፃችን💝
https://www.youtube.com/@Kezerareaction333
https://www.youtube.com/@Kezerareaction333

9.8k 0 32 11 338

ፅጌሬዳ




     ክፍል 25


አልተከተልኳትም ብቻዬን እየሳኩኝ ካባቴጋ ተሰብስበው ወደ ሚጫወቱት ሰዎችጋ ተቀላቀልኳቸው።

አጠቃላይ የሰርጉ ድግስ እስኪያልፍ ድረስ ሁላችንም እዛው ቆየን።

እህቴን በክብር ከዳርን ቡሀላ አባቴ የመሬቱን ሽያጭ እንዲጨራርስ እዛው ቀረ እኔ ማሂና አቶ ሳሙኤል ወደ አዲስ አበባ ተመለስን ።

ወደ አዲስ አበባ ከተመለስን ቡሀላ ማሂም ወደ ስራዋ ገባች ።
እኔም ወደ ጋራዤ ሄጄ ስራዬን ጀመርኩ ቀኑን ሙሉ ከዛ እዚህ ስሯሯጥ አንዱን መኪና ስንፈታ ሌላኛውን ስንገጥም እቃ ለማምጣት አንዴ እዚህ አንዴ እዛ ስል ድክም ብሎኝ መሸልኝ።

ማታ  ላይ ማሂ ደወለችልኛና ሱቅ ጠራችኝ ሄድኩኝ።
ፊቷን ጥላዋለች ምነው የኔ ጥንቸል ፊትሽን ጣልሽው አልኳት።
አንሳልኛ ከጣልኩት አለች እንዳኮረፈች።

የዛኔ ደንገጥ ብዬ ማሂ የተፈጠረ ነገር አለ እንዴ ምን ሆነሻል አልኳት።

አዎ ባክህ አሁን ቤት ምን ብዬ እንደምሄድ ጨንቆኛል ሰርጉጋ ከመሄዳችን በፊት ባለቤቴ ወደ ውጪ ሄዷል ብዬ አባቴን ዋሸሁት።
ዛሬም ተመልሼ ስሄድ መጠርጠሩ አይቀርም ቢጠይቀኝ ምንድነው ምለው አለች እንደጨነቃት ፊቷ ይናገራል።

መልስ አጥቼ ዝም አልኳት!!

እሺ ምን እናድርግ ዞሮ ዞሮኮ ማወቃቸው አይቀርም እስከመቼ ለመደበቅ ነው ያሰብሽው  እውነቱን ብትጋፈጪ አይሻልሽም ደሞኮ ገና በፍርድ ቤት መፋታት አለባችሁ እሱን ሁላ ነገር ብቻሽን ማድረግ አትችይም ስለዚህ ካሁኑ እውነቱን ተናገሪና ተገላገይ አልኳት።

ትኩር ብላላ አየችኝና ቆይ ግን አሁን እንዳወራኸው ቀላል ይመስልሀል እእ ቆይ በምን ተፋታችሁ ቢለኝስ ምን መልስ ልሰጠው ነው ከሌላ ሴትጋ አልጋዬ ላይ ያዝኩት ነው ምለው ወይስ ከመጀመሪያውም ከሱ ፍቅር አልያዘኝም ነበር ልለው ነው እእ ቆይ እስቲ ንገረኝ ልጄ ተሞሸረች አገባች ወግ ማእረግ ያዘችልኝ ብሎ ተደስቶ ሳይጨርስ ደስታውን ላጨልምበት አለችኝ በጥያቄ አይን እያየችኝ ውይ ማሂ እኔ እንደዚህ ስታይኝ ይጨንቀኛል እሺ እኔ ምን ላድርግልሽ በምንድነው ላግዝሽ ምችለው አልኳት።

ጥያቄዬን በጥያቄ ትመልስልኛለህ እንዴ እኔምኮ ምን እንደማደርግ ስለጨነቀኝ ነው አንተን የጠራኹህ በናትህ የሆነ ነገር ማድረግ አለብን አሁን ቤት ስሄድ ለሚጠይቀኝ ጥያቄ መልስ የለኝም በቃ ወደ ቤት አልሄድም room ይዤ አድራለሁ አለች እንባ እየተናነቃት።

አይ ማሂ እንደሱማ አይሆንም በቃ ዞሮ ዞሮ መሰማታቸው አይቀርም አደል መጀመሪያ እንደደረስን ትንሽ ከባልሽጋ ሰላም እንዳልሆናችሁ ትነግሪያቸዋለሽ ከዛን ቡሀላ ቁጭ አድርገው ከጠየቁሽ ሁሉንም በግልፅ መናገር ነው እንዴ ስለምን ውጭ ስለማደር ነው ምታወሪው እንደትልቅ ሰው አስቢ እንጂ ብዬ ተቆጣኋት ።

ሁለታችንም ቁርጥ ያለውን ነገር መወሰን አቅቶን ሱቅ ቀምጠን አንዱን ሀሳብ ስናነሳ ሌላኛውን ስንጥል 3 ሰአት ሆነ።

አቶ ሳሙኤል ደወሉና ምነው ቆየህ ማሂም ስልክ አታነሳም አላገኘሀትም እንዴ አሉኝ።

አረ አብረን ነን ዛሬ በጣም ብዙ ምናስረክበው እቃ ነበረን እና እሱን ስናደርስ መሸብን መንገዱ ደሞ ዝግ ነው አሁን እራሱ ማሂን ቤትሽ እስክቴጂ ይመሽብሻል እኛጋ እደሪ እያልኳት ነው የደወሉት እኛጋ ትደር አይሻልም አልኳቸው።

አረ ልጄ እውነትህን ከዚህ ሰአት ቡሀላ ብቻዋን እንዳትልካት ባይሆን ባለቤቷን እኔ አወራዋለሁ በዚሁ ኑ በቃ መሽቷል አሉን
እኔና ማሂ ተያየንና እፎይ አልን።
ስልኩን ዘጋነውና ወደ ቤታችን ለመሄድ ሱቃችንን ቆልፈን ወጣን

ወደ ቤት እየሄድን እኔ መንገድ ላይ ከምገለብጥህ መኪናውን አንተ ንዳ አለችኝና ቁልፍ ሰጠችኝ።

መንገድ ላይ እየተጓዝን ግን ነገስ ምን እለዋለሁ አለችኝ በጥያቄ አይን እያየችኝ።

በቃ ነገን ነገ ያውቃል እንዳትጨናነቂ ደሞ ሰላም ያለው እንቅልፍ ተኚ እሺ ይሄንን እያሰብሽ አፍጠሽ እንዳይነጋ አልኳት።

ቤት ስንደርስ አቶ ሳሙኤል እራት እንኳን ሳይበሉ ቁጭ ብለው እየጠበቁን አገኘናቸው ።

ምነው አባቴ አትበላም ነበር እንዴ ለምን እስካሁን ቆየህ አለች ማሂ እየሳመቻቸው።

ምን ባክሽ ልጄ በፊትም አንቺ ስትወጪ ናታኔምን  ተካሽልኝ ከዛ ደሞ አባቱን

ዛሬ ከቤቱ ሰው ሲጠፋ ጨነቀኝኮ አስኪመጣ እየጠበኩ አንቺም መጣሽልኝ ሰብሰብ ብለን እንብላ በቃ አሉን።

ተሰብስበን እራታችንን እየበላን ባልሽጋ ደውለሽ አሳወቅሽው አደል አሏት ፈጠን ብላ አዎ አባዬ አለች ።

በነጋታው ቁርሳችንን በላልተን እኔን ጋራዥ አድርሳኝ እሷ ወደ ሱቋ ሄደች።
እስከምሳ ሰአት ሰራራሁና ምሳ አብረን እንበላለን ስለተባባልን ማሂጋ ሄድኩ እዛ ስደርስ ሱቋ ዝግ ነበር።

ደወልኩላት ውስጥ ነኝ ብላ ሱቁን ከፈተችልኝ
አንቺ ያምሻል እንዴ እዚህ ቁጭ ብለሽ እንዴት ሱቅ ትዘጊያለሽ አልኳት ??

በቃ ባክህ አስጠላኝ ሰው ማናገር ማየት ሁላ ነው የደበረኝ እራሴን ላዳምጥ ብዬ ነው ለነገ ትዛዝ ተቀብዬልሀለሁ ሸቀል ሸቀል አድርገህ ትመጣለህ አለችኝ።

ነይ በቃ ብያት ለምሳ ይዣት ወጣሁና ምሳችንን በላን ስንጨርስ ትንሽ ምክር ቢጤ ከለገስኳት ቡሀላ ወደ ሱቅ ተመለስን ከመጀመሪያው ትንሽ ቀለል ብሏት ነበር ።

እኔ ከሰአት ጋራዥ ብዙም ስራ ስላልነበር ወደ ቤት ሄድኩ።
የጋራዥ ስራ ደስ ሚለው ጥሩ አለቃ ካለ በፈለጋችሁበት ሰአት መስራት መቻላችሁ ነው።

እንደምንም ደፈር ብዬ ስለማሂ ነገርኳቸው ቀለል አድርጌ ትንሽ ከባሏጋ እንደተጣላችና ለትንሽ ጊዜ እኛጋ እንደምትሆን ይሄንን ለሳቸው ለመናገር እንደፈራች እንዳይሳቀቁ ብላ እንደተጨነቀች ነገርኳቸው።

አይ የኔ ልጅ እውነት ለመናገር የባሏ ሁኔታ ብዙም ደስ አይለኝም ነበር ።
እሷ ከወደደችው ካፈቀረችው የሆነ ጥሩ ነገር ብታይበት ነው ይሁን ብዬ ተቀበልኩት እንጂኮ ፊቱ ላይ ምንም ደና ነገር አይነበብም ለሷም ሆነ ለኔ አክብሮት የለውም ።

ሲሆን ሲሆን የልጄ ባል ማለትኮ ለኔም ልጄ ነበር ግን እንደምታየው ነው አንድም ቀን እንደትልቅ ሰው ቁጭ ብለን እንኳን አውርተን አናቅም ተደዋውለን ስለጤንነታችን ተጠያይቀን አናቅም ልጄን አስከፍቷት ይሆን እንዴ በምን እንደተጣሉ ነግራሀለች አንዴ ልጄ እባክህ ንገረኝ አስከፍቷት ልቧን ሰብሮት ይሆን ??!

አረ ጋሽ ሳሙኤል ለኔ ምንም አልነገረችኝም አሁን ሄጄ አመጣትና  ከሷጋ ሁሉንም ታወራላችሁ እሷ ለመንገር ስለተጨነቀችኮ እኔ ነገሩን ቀለል ላድርገው ብዬ ነው አልኳቸው።


ወደ ማታ አካባቢ እራሳቸው ደወሉና እቤት እንድትመጣ እየጠበቋት እንደሆነ ነገሯት እኔ የሚያወሩበትን ሰአት ልስጣቸው ብዬ ማሂ ቤት ስትመጣ እኔ ወደቤተክርስቲያን ሄድኩ ።

ማታ ላይ ማሂ ደወለችና አውርተው እንደጨረሱና ቤት እንድመጣ ስትነግረኝ ወደቤት ተመለስኩ ።

ወደ ቤት ስገባ ውጪ ተቀምጣ አገኘኋት ያወሩትን ጠየኳት በቃ ከመጀመሪያውም ለሱ ፍቅር እንዳልነበረኝና አባቴን ለማስደሰት ብዬ እንዳገባሁት ከዛ ቡሀላ ግን ፀባዩ በጣም አስቸጋሪ እንደሆነ ከሱጋ መቀጠል እንደማልፈልግ ነገርኩት

አዎ በጣም አመሰግናለሁ ኑርልኝ ብላ አቀፈችኝ ።
በይ አታካብጂ ነገሮችን ከስር ከስር መፍታት መልመድ አለብሽ ከኔ ህይወት ተማሪ አልኳትና ወደ ውስጥ ገባን እየተሳሳቅን እራታችንን በላን ።

ይቀጥላል ...


✎ክፍል 26 ነገ ማታ 2:30 ይቀጥላል♥️    ቶሎ እንዲ🀄️ጥል LIKE♥️ እና Share አድርጉ።


  ይ🀄️ላ🀄️ሉን
https://t.me/+4dGFaH_mUnExZjg8
https://t.me/+4dGFaH_mUnExZjg8

💝የዩቲዩ ገፃችን💝
https://www.youtube.com/@Kezerareaction333
https://www.youtube.com/@Kezerareaction333

11.9k 0 35 14 338

ፅጌሬዳ



         ክፍል 24

ሲመሻሽ በጋራ ተሰብስበን እራታችንን በላንና ሰንጨርስ አቶ ሳሙኤል ዛሬ ግን እንዴት እዚህ አመሸሽ መቼም እነሱ መተዋል የሚል ምክንያት ፈጥረሽ ነግረሽው ነው አደል አሏት ማሂን።

ማሂ የውሸት ፈገግ አለችና አባቴ ጠረንህ ሁላ ናፍቆኛልኮ ዛሬማ ካንተጋ ነው ማድረው አለች።
እኔ መች አጣኋት ይቺን ይቺንማ በይ ነይ ተነሽ አረፍ እንበል አሉና አቅፈዋት ወደመኝታ ቤታቸው ገቡ።

እኔና አባቴ ቁጭ ብለን ማውራት ጀመርን አባቴ ከድሮ ጀምሮ ምን ትጠላለህ ቢባል ከሰው ገንዘብ መበደር ነበር ሚለው አሁን ለእህቴ ሰርግ እንዴት ገንዘብ ለመበደር እንደተስማማ ጠየኩት ???

አባቴ ትኩር ብሎ አየኝና ልጄ ችግር ባለጌ ነው የማትፈልገውን ሰው እንድትሆን ያደርግሀል ጠብቀህ ያቆየኸውን ህግም እንድትሽር ሰው ፊት አንገትህን እንድትደፋ  በቃ ሌላ ማንነት ይሰጥሀል ማጣት መጥፎ ነው ልጄ።

እኔ አሁን ላይ ልጄን አንቀባሮ ከመዳር በላይ ክብር የለም በዛ ላይ ቤቴን ሼጬ ሳይውል ሳያድር እመልሰዋለሁ አደል እንዴ ደሞኮ ሳሙኤል እንዴት አይነት ደግ ልብ ያለው ሰው መሰለህ በዚህ አጭር ጊዜ ውስጥ ተዋውቀንኮ አብሮ አደግ ጓደኛዬ የሆነ ያህል ነው የተቀራረብነው አለኝ።

በጣም ደስ ይላል አባቴ አሁን የድግሱን ሀላፊነት እናቴ ናታ ምትወስደው እኛ መች ነው ምንሄደው አልኩት።
አዎ እናትህ እንኳን ይሄን ብዙም ታቀላጥፋለች የሴት ወንድኮ ናት በዛ ላይ እሷ ሰው ይወዳታል በስራ ብዙ አትቸገረም እኛ 15 ቀን ሲቀረው ነው ምንሄደው አለኝ።

እሺ በቃ አሁን ደክሞሀል ተኛ ብዬ ወደመኝታው አስገባሁትና በረንዳው ላይ ወጥቼ ቆምኩኝና ትንሽ እራሴን ለመሰብሰብ ሞክሬ ተመልሼ ገብቼ ተኛሁ።

የዛን ሰሞን ስራ በሁለቱም በኩል ተጧጡፎልን ነበር ማሂም ባሏ ለስራ ከሀገር እንደወጣና ቤት ውስጥ ብቻዋን ስለሚደብራት እኛጋ እንደምትሆን ለአባቷ ነግራቸው እኛውጋ መኖር ጀምራለች ።
ሰርቼ ከስር ከስር ለእህቴ እንዲያስገቡላት ለሰዎች እሰጣለሁ ብሩን ምክንያቱም እኔ መታወቂያም ሆነ ቡክ የለኝም።

እህቴ በየቀኑ እየደወለች አልፈልግም አትላክልኝ ትለኛለች እኔ ምንም ያህል ገንዘብ ሳገኝ ወደሷ አካውንት አስገባለሁ እንደዛ እንደዛ እያልን ሰርጉ 15 ቀን ሲቀረው አባቴ ወደክፍለ ሀገር እንድንሄድ ጠየቀኝ እኔ ቢያንስ 10 ቀን ብሰራ ብዙ ብር እንደሆነና 5 ቀን ሲቀረው እመጣለሁ ብዬ እሱን ወደሀዋሳ ሸኝቼ እኔ ወደስራዬ ተመለስኩ።

ማታ ቤት ስገባ አቶ ሳሙኤልና አባቴ ተገናኝቶ እንደማያቅ ሰው በስልክ እረጅም ሰአት ያወራሉ።

እኔና ማሂ እዛው አንድ ሳሎን ቁጭ ብለን text እየተፃፃፍን እየተደበቅን እንሳሳቃለን።
በነገራችን ላይ ማሂ የእህት ሶስተኛ ሚዜ ነች።

ለሙሽሪት የሚያስፈልጋትን ሙሉ ወጪ የሸፈነችውም እራሷ ማሂ ነበረች ።

10 ቀኗን ከሚገባው በላይ ተሯሩጬ ሰራሁና 5 ቀን ሲቀረው እኔ አቶ ሳሙኤልና ማሂ ሆነን ወደ ሀዋሳ ሄድን።

ሰፈሩ እንዳለ የድግስ ድባብ ላይ ነው የኛ ግቢ ውስጥ ገቢ ወጪው የሰው ብዛት ድግሱ የዛን ቀን ነበር የሚመስለው እህቴ ታድለው ግን ቤተሰቦችህ ይሄ ሁላ ሰው ልክ እንደራሱ ድግስ ሲሯሯጥ ማየት ደስ ይላል አለች።

አዎ ደስ ይላል እዚህኮ አንዱ ሲደግስ ሁሉም እንደራሱ ድግስ ቀን ከሌሊት ነው ሚሰራው አልኳት።


የሰርጉ ቀን ደረሰ አባቴና እናቴ ምድር ላይ በነሱ ልክ ሰው ያለ አልመስል አላቸው ደስታቸው  ወደር አልነበረውም ማሂም መቼም የሰው ደስታ ከራሷ በላይ ነው ሚያስደስታት ሽር ጉድ ስትል ነበር።

ድግሱ አደለም የተጠራውን ሰው ሌላም ህዝቦ ቢጨመር ያበላ ነበር ከመጠን በላይ ነው የተደገሰው ማለት እችላለሁ በዛው ልክ ደሞ ያልተጠራ ህዝብ አልነበረም።

የኔን መመለስ ያላወቁ አንዳንድ ሰዎች ደሞ ከድግሱ በላይ በኔ ሲገረሙም እያየሁ ነበር ።

አባቴ ወደቀድሞ ክብሩ ሲመለስ የመጣው ሰው ሁሉ እንኳን ደስ አለህ እያለ ከፍ ዝቅ ሲልለት እናቴ የቀድሞ ሳቋ ፈገግታውን ፊቷ ላይ ሳገኘው በጣም ደስ አለኝ። የሰው ሁላ አይን ከኔ ላይ አልነቀል ብሎ ነበር።

የሙሽራው መምጫ ሰአት ደረሰና ሙሽራው ሙሽሪትን በክብር ሊወስድ መጣ እኔ ማታ ከማሂጋ ሚጨፍረው ሶስተኛው ሚዜ ምን አይነት ይሆን የሚለውን ነበር በጉጉት ስጠብቅ የነበረው ።

የፈራሁት አልቀረም ሶስተኛው  ሚዜ በጣም ቆንጆ ፂማም ልጅ ነበር ።
ሳየው ደሜ ፈላ አሁንኮ ከማሂጋ ማታ እንደሚዜ ተቃቅፈው ይጨፍሩ ይሆናል አብረውም ፎቶ ይነሳሉ ቆይ ቢወዳትስ እሷስ እንዳየችው ቢመቻት እያልኩ በውስጤ ሳብሰለስል ቆየሁና
ለራሴ ምን አይነት ቀሽም እንደሆንኩ ነገሬ ወደፕሮግራሙ ተመለስኩ

መመለስ አይበሉት ልቤ ብትንትን ብሎ ነበር ለምን እንደዛ እንደሆንኩ ግን ፈጣሪ ይወቀው ።

ሰአቱ ሲደርስ ሙሽራው ሙሽሪትን ይዞ ወደሱ  ቤት ሄደ ማሂም አብራ ሄደች።
አንቺ እዚሁ ጠብቂያቸው አይባል ነገር ሆኖብኝ እንጂ ምንም ደስ አላለኝም ነበር።
ብቻ ግን ድግሱ በጣም አስደሳች ነበር ሰው ሁሉ ሲጨፍር ሲደሰት አባቴ በደስታ ብዛት መሳቅ እስኪከብደው ድረስ በደስታ ሲፈነድቅ አየሁት ።
አቶ ሳሙኤል ሁሉንም ሰው ልክ እንደሚያቃቸው ነበር ሲያስተናግዱ የነበረው በጣም ደስ ብሎኝ የማደርገው እስኪጠፋ ከሁሉም ሰውጋ እየተሳሳኩ እያሳለፍኩ በመሀል ማሂ ትዝ ትዝ ትለኛለች።
መቼስ በባህላችን መሰረት የሴት ቤተሰብ በሰርግ ቀን ወንዱጋ መሄድ ነውር ስለሆነ እንጂ ሄጄ የማሂን አይን አይን ባየው ደስ ይለኝ ነበር።

ሰርጉ አዳሩንም ጭምር ነበር ማለት እችላለሁ የሰፈሩ ሰው ሲቀውጠው አደረ ሳንተኛ በዛው ነጋ ማሂ ወደ 5 አካባቢ መጥታ ተኛች።

እኔ እንደዛው እንደፈጠጥኩ ነጋልኝ በነጋታው ከድግሱ ያልተናነሰ ሰው መጥቶ ነበር ።

እህቴ ደወለችና እንዴት እየሆንን እንደሆነ ጠየቀችኝ ነገርኳት የሷን አዳርም ጠየኳት አረ ወንድሜ እንዴት ደስ እንደሚል በጣም ደክሞኝ ነበር ግን ጠዋት ከእንቅልፍህ ስትነቃ የምትወደው ሰው እቅፍ ውስጥ መሆን በራሱ ሌላ አለም ነው ።

ብታይ በቃ አለምን በመዳፌ ያደረኳት ያህል ነበር ደስ ያለኝ ።

በዛ ላይ ትናት ያባቴና የናቴን ደስታ ሳይ ምነው ቀደም ብዬ ባገባሁ ነው ያሰኘኝ ብላ ሳቀች።

እኔም በጣም ደስ እንዳለኝ ነግሪያት ለመልሱ እንደምንገናኝ ተስማምተን ስልኩ ተዘጋ።

ማሂ በሚቀጥለው ቀን ያ ሁሉ ሰው ሲመጣ ሲጨፍሩ እንኳን እሷ አልተነሳችም ነበር።

አቶ ሳሙኤል አይ ማሂ ድካምኮ አትችልም የኔ ልጅ አሳዝናኝኮ ነው እንቀስቅሳት እንዴ ሲሉ እናቴ አይ እረፍት ታድርግ ችግር የለም ይደክማታል አለች።
ማሂ አረፋፍዳም ቢሆን ተነሳችና ወደመስተንግዶው ገባች ።

በመሀል በመሀል ስለሰርጉ እየጠየኳት ትመልስልኛለች ።
እና ሚዜውስ እንዴት ነበር ካንቺጋ የደረሰው አልኳት ።

አረ በስማም  አንተ ምን አይነት ሰው እንደሆነ አሳቀቀኝ አይኑን ከኔ ላይ አልነቅል ብሎኝ ነበር ።

መጨረሻ ላይ ፊቴን ሳጠቁርበት ነው ካጠገቤ ዞር ያለው አለችኝ።

አልገባኝም ምን ማለት ነው ከሱጋ ዝም ብዬ መገልፈጥና መጃጃል ነበረብኝ እንዴ ምን አይነት ጥያቄ ነው ብላ እንደለመደችው አኮረፈችና ተነስታ
ሄደች።


✎ክፍል 25 ነገ ማታ 2:30 ይቀጥላል♥️    ቶሎ እንዲ🀄️ጥል LIKE♥️ እና Share አድርጉ።


  ይ🀄️ላ🀄️ሉን
https://t.me/+4dGFaH_mUnExZjg8
https://t.me/+4dGFaH_mUnExZjg8

💝የዩቲዩ ገፃችን💝
https://www.youtube.com/@Kezerareaction333
https://www.youtube.com/@Kezerareaction333


ZOO አዲሱ የX-Empire ፕሮጀክት...

| ምትሰበስቡት ነጥብ ቀጥታ ወደ ቶክን ይቀየራል
| ፕሮጀክቱ ለጥቂት ግዜ የሚቆይ ስለሆነ አያሰላቻም
| አጨዋወቱ እንስሶችን በተሰጣችሁ Feed መመገብና Upgrade ማድረግ ነው
| ብዙ ሰው ስላልበዛበት በግዜ ብትጀምሩ ይመረጣል
| አጨዋወቱን በቪዲዮ በቅርብ ግዜ ዉስጥ እንለቅላችኋለን

ለመጀመር
http://t.me/zoo_story_bot/game?startapp=ref756016762

Показано 20 последних публикаций.