TGStat
TGStat
Введите текст для поиска
Расширенный поиск каналов
Russian
Язык сайта
Russian
English
Uzbek
Вход на сайт
Каталог
Каталог каналов и чатов
Поиск каналов
Добавить канал/чат
Рейтинги
Рейтинг каналов
Рейтинг чатов
Рейтинг публикаций
Рейтинги брендов и персон
Аналитика
Поиск по публикациям
Мониторинг Telegram
SAMUEL GIRMA - LAWYER 🇪🇹
10 Feb, 19:19
Открыть в Telegram
Поделиться
Пожаловаться
Репост из:
ሕግ አገልግሎት Legal Service
Prev
Next
ይህ ጉዳይ የሚመለከተው የውርስ ሀብትን መሰረት ባደረገ ክርክር በፍትሐ-ብሔር ሥነ-ሥርዓት ሕግ ቁጥር 358 ስለሚቀርብ የፍርድ መቃወሚያ ነው፡፡
በፍትሐ-ብሔር ሥነ-ሥርዓት ሕግ ቁጥር 358 ላይ እንደተመለከተው ማንኛውም በፍርዱ ተካፋይ ሊሆን የሚገባው ሰው ተካፋይ ባልሆነበት ሁኔታ የተሰጠው ፍርድ መብቱን የሚነካ ከሆነ ፍርዱ ከመፈፀሙ በፊት መቃወሚያውን ሊያቀርብ እንደሚገባ ተደንግጎ ይገኛል፡፡ ነገር ግን የሱን መብት የሚነካ ክርክር መኖሩን ያወቀ ማንኛውም ሰው ፍርድ መሰጠቱን ሳይጠብቅ ፍርድ ከመሰጠቱ በፊት ወደ ክርክሩ ገብቶ ተከራክሮ መብቱን ሊያስጠብቅ እንደሚገባ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር 41 ላይ ደንግጎ ይገኛል።
ስለሆነም ፍርድ ሲሰጥ ጠብቀው በመምጣት የተሰጠው ፍርድ ይነሳልኝ በማለት አቤቱታ ማቅረብ የፍትሐ-ብሔር ሥነ-ሥርዓት ሕግ ቁጥር 358 ላይ የተመለከተውን የህግ ድንጋጌ አላማ የሚያሳካ አይደለም፡፡ ይሁን እንጂ ይህ ድንጋጌ የውርስ ሀብት ክርክርን በተመለከተ ተፈፃሚነት ያለው አይደለም::
እንኳን የውርስ ሀብቱ ሳይክፋፈል ቀርቶ ከተከፋፈለ በኋላም በሌለበት የውርስ ሀብቱ የተከፋፈለበት አካል በሚያቀርበው አቤቱታ ክፍፍሉ ሊፈርስ እና እንደገና ክፍፍል ሊደረግ እንደሚገባ በፍትሀብሄር ሕግ ቁጥር 1080 ላይ ተደንግጎ ይገኛል።
በመሆኑም: ምንም እንኳን አመልካቾች ያቀረቡት የፍርድ መቃወሚያ አስቀድሞ የነበረውን ክርክር በሚያውቁበት ሁኔታ ቢሆንም መቃወሚያ የቀረበበት ክርክር የውርስ ሀብትን መሰረት ያደረገ ከሆነ የውርስ ሀብቱ ክፍፍል ከተደረገ በኋላም ቢሆን፤ በፍትሐ-ብሔር ሥነ-ሥርዓት ሕግ ቁጥር 358 የፍርድ መቃወሚያ መቅረብ ይችላል፡፡
ሰ/መ/ቁ144359
×