ሐምዱ ቋንጤ
✍
ምን ዐይነት ጌታ ነው ንገሩኝ በጌታ??
ከደም ጋ ተዋህዶ የሚኖር በማህፀን
በስጋ በአጥንት ሙሉው የሚሸፈን፣
በሆድ ውስጥ ጨለማ በማህፀን የሚኖር
ግራ ቀኝ እያለ በሆድ ውስጥ የሚዞር፣
እስኪወለድ ድረስ ዘጠኝ ወር የሚፈጅ
እድሜው ሲሸመግል እንደ ሰው ሚያረጅ፣
ከሽንት መውጫ በኩል ከእናቱ ሚወለድ
ከዝያም አምላክ ሊሆን ለእሱ እንዲሰገድ፣
ምን ዐይነት ጌታ ነው ንገሩኝ በጌታ
በማህፀን ተረግዞ የሚወለድ ጌታ???
የእናቱ ጡት ይዞ የሚ ያለቃቅስ
የሚ ያባብሉት ጠብቶ እስኪጨርስ፣
በደረት ሚታቀፍ ሚታዘል በጀርባ
መራመድ እስኪችል ወጥቶ እስኪገባ፣
ልብስ ሚቀየርለት የሚታጠብ ገላው
ሰውነቱን ቆሾ ቅማል እንዳይበላው፣
ሲርበው ሚበላ ሽንት ቤት የሚጠቀም
ጉዳት ሚደርስበት ጭራሽ የሚታመም፣
ምን ዐይነት ጌታ ነው ንገሩኝ በጌታ
ሚርበው ሚጠማው የሚቸገር ጌታ??
ጠላት የሚያባረው
ከያዘው ሊገለው፣
እሱም የሚደበቅ
በጠላት እጅ ላይወድቅ፣
ከጠላት የሚሸሽ ራሱን ለማትረፍ
አይደለም የሌሎች ችግራቸው ሊቀርፍ፣
ከጠላት አደጋ
ለራሱ ሚሰጋ፣
ለኔስ ምን ሊጠቅመኝ
ከምን ሊያድነኝ?
ምን ዐይነት ጌታ ነው
ከጠላት ሚሰጋው?
የጌትነት አቅሙ
ለመቼ ነው ጥቅሙ?
ምን ዐይነት ጌታ ነው ንገሩኝ በጌታ
ከጠላት የሚሸሽ የሚደበቅ ጌታ??
ካለ ማፈራቸው
ይባስ ድፍረታቸው፣
"ተሰቀለ" አሉ
እላይ ከመስቀሉ፣
"ደሙን አፈሰሱት
በእሾህ እየወጉት"፣
"ጌታ ሞተ" አሉ እንዲህ ተሰቃይቶ
ጌታ ጌትነቱን በጠላት ተቀምቶ¡¡
ይመለስ ጥያቄው ሁሌም ይጠየቃል
በእየሱስ ጌትነት ለሚሉት "አምነናል"፤
እየሱስ ተሰቅሎ ከሆነ የሞተው
ጌታን የገደለው ሞትን ማን ፈጠረው?
ምን ዐይነት ጠላት ነው ጌታን የበለጠው?
ጌታውን እንዲበልጥ ችሎታ ማን ሰጠው?
መስቀል ምን አስቦ ዝምታን መረጠ
ጌታው እላዩ ላይ እየተረገጠ??
ምድር እንዴት ቻለች ምንስ አስጨከናት
የጌታዋን አፅም ተከፍኖ ሲሰጣት??
ቀንና ሌሊቱ እንዴት መሽቶ ነጋ
ጌታውን ተሰቅሎ በስለት ሲወጋ??
አለም እንዳይጠፋ ማን ተቆጣጠረው
ጌታውን ሞቶበት ማን ችሎ አስቆየው??
ጥያቄው መልሱ ወይም ተመለሱ
ውሸቱን ትታችሁ እውነቱን አድርሱ።
ከምትሉት ሁሉ ዒሳ የጠራ ነው
ቢኾን እንጂ ነብይ አላህ የመረጠው፤
ክህደት ተደምስሶ አላህ እንዲመለክ
ስለ እስልምና ለሰው ልጆች ሊሰብክ፤
በተውሒድ ልኮታል
ነብይ አድርጎታል፤
የእኛም የእሱ አምላክ
ብቻው የሚመለክ፤
የአለም ፈጣሪ
የሌለው ተጋሪ፤
ብቸኛው አላህ ነው በደንብ ተገንዘበው
ዒሳም ይህን ነበር አስተምሮ የሄደው።
በአላህ እመኑ በብቸኝነቱ
ዒሳም ከፍ አታርጉት ከነብይነቱ።
ባሪያና ነብይ ይህን ነው ደረጃው
ከዚህ ሌላ ያለ ከፋ መመለሻው።
🖊 አቡ ሙSሊM ሐምዱ ቋንጤ
🗓ጥር2/05/2013
👇👇👇ለመከታተል👇👇👇
https://t.me/islmina_min_ale
ምን ዐይነት ጌታ ነው ንገሩኝ በጌታ??
ከደም ጋ ተዋህዶ የሚኖር በማህፀን
በስጋ በአጥንት ሙሉው የሚሸፈን፣
በሆድ ውስጥ ጨለማ በማህፀን የሚኖር
ግራ ቀኝ እያለ በሆድ ውስጥ የሚዞር፣
እስኪወለድ ድረስ ዘጠኝ ወር የሚፈጅ
እድሜው ሲሸመግል እንደ ሰው ሚያረጅ፣
ከሽንት መውጫ በኩል ከእናቱ ሚወለድ
ከዝያም አምላክ ሊሆን ለእሱ እንዲሰገድ፣
ምን ዐይነት ጌታ ነው ንገሩኝ በጌታ
በማህፀን ተረግዞ የሚወለድ ጌታ???
የእናቱ ጡት ይዞ የሚ ያለቃቅስ
የሚ ያባብሉት ጠብቶ እስኪጨርስ፣
በደረት ሚታቀፍ ሚታዘል በጀርባ
መራመድ እስኪችል ወጥቶ እስኪገባ፣
ልብስ ሚቀየርለት የሚታጠብ ገላው
ሰውነቱን ቆሾ ቅማል እንዳይበላው፣
ሲርበው ሚበላ ሽንት ቤት የሚጠቀም
ጉዳት ሚደርስበት ጭራሽ የሚታመም፣
ምን ዐይነት ጌታ ነው ንገሩኝ በጌታ
ሚርበው ሚጠማው የሚቸገር ጌታ??
ጠላት የሚያባረው
ከያዘው ሊገለው፣
እሱም የሚደበቅ
በጠላት እጅ ላይወድቅ፣
ከጠላት የሚሸሽ ራሱን ለማትረፍ
አይደለም የሌሎች ችግራቸው ሊቀርፍ፣
ከጠላት አደጋ
ለራሱ ሚሰጋ፣
ለኔስ ምን ሊጠቅመኝ
ከምን ሊያድነኝ?
ምን ዐይነት ጌታ ነው
ከጠላት ሚሰጋው?
የጌትነት አቅሙ
ለመቼ ነው ጥቅሙ?
ምን ዐይነት ጌታ ነው ንገሩኝ በጌታ
ከጠላት የሚሸሽ የሚደበቅ ጌታ??
ካለ ማፈራቸው
ይባስ ድፍረታቸው፣
"ተሰቀለ" አሉ
እላይ ከመስቀሉ፣
"ደሙን አፈሰሱት
በእሾህ እየወጉት"፣
"ጌታ ሞተ" አሉ እንዲህ ተሰቃይቶ
ጌታ ጌትነቱን በጠላት ተቀምቶ¡¡
ይመለስ ጥያቄው ሁሌም ይጠየቃል
በእየሱስ ጌትነት ለሚሉት "አምነናል"፤
እየሱስ ተሰቅሎ ከሆነ የሞተው
ጌታን የገደለው ሞትን ማን ፈጠረው?
ምን ዐይነት ጠላት ነው ጌታን የበለጠው?
ጌታውን እንዲበልጥ ችሎታ ማን ሰጠው?
መስቀል ምን አስቦ ዝምታን መረጠ
ጌታው እላዩ ላይ እየተረገጠ??
ምድር እንዴት ቻለች ምንስ አስጨከናት
የጌታዋን አፅም ተከፍኖ ሲሰጣት??
ቀንና ሌሊቱ እንዴት መሽቶ ነጋ
ጌታውን ተሰቅሎ በስለት ሲወጋ??
አለም እንዳይጠፋ ማን ተቆጣጠረው
ጌታውን ሞቶበት ማን ችሎ አስቆየው??
ጥያቄው መልሱ ወይም ተመለሱ
ውሸቱን ትታችሁ እውነቱን አድርሱ።
ከምትሉት ሁሉ ዒሳ የጠራ ነው
ቢኾን እንጂ ነብይ አላህ የመረጠው፤
ክህደት ተደምስሶ አላህ እንዲመለክ
ስለ እስልምና ለሰው ልጆች ሊሰብክ፤
በተውሒድ ልኮታል
ነብይ አድርጎታል፤
የእኛም የእሱ አምላክ
ብቻው የሚመለክ፤
የአለም ፈጣሪ
የሌለው ተጋሪ፤
ብቸኛው አላህ ነው በደንብ ተገንዘበው
ዒሳም ይህን ነበር አስተምሮ የሄደው።
በአላህ እመኑ በብቸኝነቱ
ዒሳም ከፍ አታርጉት ከነብይነቱ።
ባሪያና ነብይ ይህን ነው ደረጃው
ከዚህ ሌላ ያለ ከፋ መመለሻው።
🖊 አቡ ሙSሊM ሐምዱ ቋንጤ
🗓ጥር2/05/2013
👇👇👇ለመከታተል👇👇👇
https://t.me/islmina_min_ale