የጤና ባለሙያዎችን ያድኑን ዘንድ እንዴት እንገዛቸው??
መንግስት ብዙ ነገሮች ከአቅሙ በላይ ሊሆን ስለሚችን ወደ መንግስት ብቻ ማፍጠጥ አያዋ ጣም።
①ባለሃብቶች ምን ያድርጉ?
ባለሃብቶች ህዝብ ባይኖር ሃብት አያገኙም,ሀገር ባይኖር ኪሳቸው አይሞላም። ስለዚህ ይህ ሰአት የህዝብ ልጅነታቸውን ማሳያ ነው ። ስለዚህ ጤና ባለሙያዎችን ከአደጋ ለመጠበቅ ምን ያድርጉ?
1) በተቀናጀ መልኩ ካለምንም የጤና ተቋም ጣልቃገብነት የባለሙያ ደህንነት መጠበቂያ መሳሪያዎችን ገዝቶ መስጠት። መንግስትም የዚህን ቢሮክራሲ ግንብ መደርመስ አለበት
2)በተለያዩ የእድርና የሲቪክ ማህበራት ስም በመታቀፍ እነዚህን የባለሙያ ደህንነት መሳሪያዎች ለማህበራቱ በማስረከብ እንዲደርስ ማድረግ
3)ለህክምና የተመረጡ ተቋማት ዘንድ በመሄድ የሚያስፈልጋቸውን ነገር በዝርዝር በመፃፍ ገዝቶ በቀጥታ ወደተቋሙ ማድረስ።
4) ታካሚ ለማጓጓዝ የሚሆኑ ተሽከርካሪዎችን አልጋዎችንና ወንበሮች ገዝቶ በቀጥታ ሄዶ መስጠት
የባለሙያ ደህንነት መጠበቂያ የሚባሉት
1)የፊት መሸፈኛ ማስክ(N95)
2) ሙሉ ሰውነት የሚሸፍን የፕላስቲክ ልብስ
3)ቦቲ የሚመስል ጫማ
4)ፈሳሽ ሳሙናዎች ና ዲተረጀንት
5)የውሃ ታንከሮች
6)አልክሆልና በረኪና
7)የታካሚ አልጋዎች በቀላሉ የሚመረቱትን
8)የማጓጓዣ አይነቶች ከሚኒባስ እስከ አይሱዙ
እነዚህ በማውጣት ይሄን ቀን ተባብሮ ማለፍ
②ተራው ህዝብ ምን የጠበቅበታል?
አብዛኛው የአገራችን ህዝብ ገራገርና ከሳይንስ እውቀት ይልቅ ወደእምነት ብቻ እንዲደገፍ የተደረገ ህዝብ ስለሆነ ለዚህ አስቸጋሪ ወቅት ግን ሳይማሩም ለሳይንስ እጅ መስጠት ወሳኝ ነው። ምን ይጠበቃል ከማህበረሰቡ?
1) የጤና ባለሙያዎችን ከመቼውም ጊዜ በተሻለ መጠን የሚመክሩንን ምክር መቀበል መተግበርና ከበሽታው መጠበቅ።
2)በሽታው የመከሰት አዝማሚያ የተመለከተ ማንኛውም ሰው የትኛውንም የጤና ባለሙያ "ራሴን እጠረጥራለሁ" ብሎ በመንገር የሚያክሙን ባለሙያዎች እንዲጠነቀቁ ማንቃት።
3)ሳልና ትኩሳት ያለበት ማንኛውም ሰው ከዱባይም መጣ ከታች ጋይንት በዚህ ሰአት ራሱን ኮሮና እንደያዘው ቢጠረጥርና ደውሎ ለቴሌ ወይም ባለሙያ ቢያማክር ጤና ባለሙያው ይጠቀማል ህዝብ ይጠበቃል።
4) ማንኛውም ራሱን የጠረጠረ ታካሚ የትኛውንም የጤና ባለሙያ ሳያገኝ በፊት ወደጤና ተቋም ሳይሄድ በፊት
★ወይ ለኢትዮቴሌኮም ስልኮች መደወል አለበት
★አለዚያም በአካባቢው ላሉ ጤና ተቋማት በስልክ ማሳወቅ አለበት
5)በዚህ አደገኛ ሰአት ከፍተኛ ልፋት ላይ ያሉ ባለሙያዎችን በቃልም ሆነ በአካል አለመተናኮስ ።በተለይ አስታማሚ ሆናችሁ ወደጤና ተቋም የምትሄዱ ለወገናችሁ ጭንቀት ከባለሙያው አትበልጡምና ከዚህ ድርጊታችሁ መታቀብ አለባችሁ።
6)ከተማ ላይ የሚሰጡ የጤና ትምህርቶችን ማድመጥ መረዳትና መተግበር
7)በበጎ ፈቃደኝነት ላይ መሰማራት የምትፈልጉ ወጣቶች ቀድማችሁ ከባለሙያዎች ስልጠና መውሰድ ና ትምህርት ማግኘት
8)ከተሰጡ ምክሮች ባለማፈንገጥ ራስንም ቤተሰብንም ሆነ ጤና ባለሙያን አደጋ ላይ አለመጣል።
③የመንግስት ባለስልጣናት(ካድሬዎች) ምን ያድርጉ
የመንግስት ባለስልጣናት የትኛውም ሃገር ስራ እንጂ ሰራተኛ ተኮር ሆነው አያውቁም። በዚህ ሰአት ይሄን ባህሪያቸውን ያውልቁት
1) ማንኛውንም የጤና ባለሙያ ምክረሃሳብ ከመቀበል ውጭ "የትሰራታለህ" ፍጥጫ ውስጥ ባለመግባት ባለሙያውን አለማደናገርና አለማስፈራራት
2) ለባለሙያው ደህንነት ተገቢ የሆኑ ከፀጥታ ማስከበር እስከ ግለሰባዊ የመጠቀሚያ እቃዎች ማፈላለግና ማሟላት ላይ አተኩሮ መስራት።
3)ጊዜው የመደብ ህክምና የሌለበት እንደመሆኑ መጠን ማንኛውንም ሰብአዊ ፍጡር እኩል እንዲስተናገድ የድርሻህን መወጣት
4)ህብረተሰቡንና አጋር አካላትን በማስተባበር ለባለሙያው መጠቀሚያና መጠበቂያ የሚሆኑ እቃዎችን ከቢሮክራሲ በራቀ መንገድ መግዛትና አቅርቦትን ማስተካከል
5) በዚህ ሰአት የሚገኙ ሃብቶችን መስረቅ አንተም ቤተሰብህም ላይጠቀሙበት ይችላሉና እንዲሁም መተንፈስ ያቃተውን ሰው ህይወት መስረቅ ነውና እጅ መሰብሰብ።
6)ተጠርጣሪን በተመለከተ በቀጥታ ከባለሙያ ጋር በመሰባጠር በተረጋጋ መንፈስ ወደህክምና ተቋም ማምጣት። ራሴ እይዛለሁ ብትል ኮሮናን ራሱን ልትይዘው ስለምትችል።
አላህ አገራችንን ሰላም ጤናና የተረጋጋች ያድርግልን።
ዶክተር አህመድ ሰይድ