የወንጌል አማኞች አብያተክርስቲያናት ካውንስል ረቂቅ አደረጃጀት
(ክፍል 1/3)
የወንጌላዊያን አብያተ ክርተክርስቲያናት ሕብረት ከተራ ማህበርነት ምዝገባ ወደ ሃይማኖት ተቋምነት የሚያሸጋግረው ረቂቅ አዋጅ መዘጋጀት ተጀምሯል፡፡
✿በረቂቅ አዋጁ የሚደነገጉ ድንጋጌዎች፦
1. የወንጌል አማኞች አብያተክርስቲያናት ካውንስል ኃይማኖት ተቋም እንደሆነ እውቅና የሚሰጡ ድንጋጌዎች፤
2. ካውንስሉ ለአባል ቤተ እምነቶችና ተቋማት በሕጋ ፊት ውክልና እንዳለው፤
3. ለአባል ቤተእምነቶች ሕጋዊ ሰውነት(የስራ ፈቃድ) ሳይሆን የአባልነት ሴርቲፍኬት እንደሚሰጥና እንደምሰርዝ፤
4. ካውንስሉ የራሱ ሕገ ደንብ፣ የስነ ምግባር ደንብ፣ መመሪያዎችና ሌሎች አደረጃጀቶች ማዘጋጀት እና ማሻሻል እንደሚችል፤
4. ሰባት አንቀጾች ያለው መሰረታዊ የእምነት መግለጫ እንደሚኖሩ ከአርቃቂ ሕግ ባለሙያዎች ክርስቲያን ፖስት ያገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡
✿በሕገ ደንብ
-የካውንስሉ የሥልጣን አካላት ይገለጻሉ፤
-መደበኛ አባላት፣ ተባባሪ አባላትና አጋር አባላት መስፈርት ያስቀምጣል፤
-የካውንስሉ የሀገር አቀፍ እርከኖችና መዋቅሮች ሥልጣንና ተግባራት ይደነግጋል፤
-የተቋሙን እሴቶች ይደነግጋል፤
-ሕገ ደንቡ በቅርቡ በሁለት ሳምንታት በመስራች ጉባኤ ይጸድቃል፡፡
✿መስራች አባላት፦
1. የኢትዮጵያ ቃለ ሕይወት ቤተክርስቲያን፣
2. የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተክርስቲያን መካነ ኢየሱስ፣
3.የኢትዮጵያ ወንጌላዊያን አብያተ ክርስቲያናት ሕብረት እና
4. የኢትዮጵያ ጴንጤቆስጣል አብያተክርስቲያናት ሕብረት ናቸው፡፡
-ካውንስሉ ከተመሰረተ በኃላ ተራ ቁጥር 1 እና 2 በመደበኛ አባልነት ይጠቃለላሉ፤
-ካውንስሉ ከተመሰረተ በኃላ ተራ ቁጥር 3 እና 4 በጠቅላላ ጉባኤያቸው ሕጋዊ ሰውነታቸውን ያከስማሉ፤
-ሌሎች አብያተክርስቲያናት ሕብረቶችም በጠቅላላ ጉባኤ ከስመው ሊደራጁ ይችላሉ፡፡ በመስፈርቱ መሰረቱ አባልነታቸው ይወሰናል፡፡
@Christianpost1
@Meleket_Tube