ሱን የቻለ ድርሻ እንዳለውና በኢስላማዊ የግብይት ስርዓት ተቀባይነት እንዳለው ነው። (አል ሙግኒ 6/385
4) የዱቤ ግብይት ላይ ክፍያው ዘግይቶ በመከፈሉ ምክንያት የዋጋ ጭማሪ ማድረግ ከጥንት ጀምሮ ሙስሊሞች የሚተገብሩት እና ማንም ያላወገዘው ጉዳይ በመሆኑ እንደ ኡለማዎች ስምምነት “ኢጅማዕ” አስቆጥሮታል።
መጅመኡል ፊቅሂል ኢስላሚይ / አለም አቀፍ የፊቅህ ጥናት አካዳሚ/ በቁጥር 51/2/6 ባስተላለፈው ውሳኔ «ወደፊት በሚከፈል (የዱቤ) የሽያጭ ዋጋ ላይ አሁን ከሚከፈለው (የካሽ) የሽያጭ ዋጋ መጨመር ይፈቀዳል» ብሏል።
የቀድሞ የሳዑዲ ዓረቢያ ሙፍቲ የነበሩት እውቁ ዓሊም የተከበሩ ሸይኽ ዓብደልዓዚዝ ኢብን ባዝ -ረሂመሁላህ- በዱቤ ለሚሸጥ ዕቃ ዋጋውን ጨምሮ መገበያየት ትክክለኝነት ተጠይቀው ይህን መልሰው ነበር፤
ሸይኽ ኢብን ባዝ፦ "ይህ ግብይት ምንም ችግር የለዉም፤ ምክንያቱም የካሽ ግብይት ከዱቤ ጋር ይለያያል።
ሙስሊሞች እስካሁን ድረስ ይህን አይነት ግብይት ሲፈፅሙ መኖራቸውም በመፈቀዱ ላይ ስምምነት (ኢጅማዕ) እንዳላቸው ነው የሚያሳየው። ጥቂት ዓሊሞች ያፈነገጠ እይታ ይዘው ክፍያን በማዘግየት ምክንያት የሚደረጉ የዋጋ ጭማሪዎችን ከልክለዋል። ይህንን እንደ አንድ የወለድ (ሪባ) አይነትም ወስደውታል። ነገር ግን ይህ ፍጹም ሪባ አይሆንም። ምክንያቱም ነጋዴው ምርቱን በዱቤ ሲሸጥ በዱቤው የተስማማው ከዋጋ ጭማሪው ለመጠቀም አስቦ ነው። ገዥውም በዋጋ መጨመሩ ሲስማማ በወቅቱ ክፍያውን በካሽ መፈፀም ስለማይችል ግዜ ማግኘቱን በማሰብ ነው። ስለዚህ ሁለቱም በግብይቱ ተጠቃሚ ናቸው። ከመልእክተኛው /ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም/ ይህ የተፈቀደ መሆኑን የሚያመላክት ሐዲሥ ተላልፏል። የአላህ መልዕክተኛ አብደላህ ኢብን አምር ኢብን አስን /ረዲየላሁ ዓንሁማ/ ጦር እንዲያደራጅ አዘውት አንድን ግመል ወደፊት በሚከፈል ሁለት ግመል ሲገዛ ነበር። በሌላ በኩል ግብይቱ አላህ ማንኛውንም ግብይት መዋዋልን ባዘዘበት የቁርዓን አንቀጽ ውስጥ ይካተታል።
يا أَيُّهَا الَّذينَ آمَنوا إِذا تَدايَنتُم بِدَينٍ إِلى أَجَلٍ مُسَمًّى فَاكتُبوهُ
"እናንተ ያመናችሁ ሆይ እስከተወሰነ ግዜ በዕዳ የተዋዋላችሁ ግዜ ፃፉት" አል በቀራህ 282
ግብይቱ በዚህ አንቀፅ ውስጥ ከሚካተቱት የሚፈቀዱ የዕዳ አይነቶች አንዱ ነው፤ ግብይቱ የ'በይዕ-አሰለም' (ቀድሞ ከፍሎ ዘግይቶ የመረከብ) አይነትም ነው!" [ፈታዋ ኢስላሚያ 2/331[
ከላይ ከቀረበው ማብራሪያ በረጅም ግዜ ክፍያ የሚደረግ የሽያጭ ውል ላይ በካሽ ከሚከፈለው ሽያጭ የዋጋ ጭማሪ ማድረግ እንደሚቻል ለማየት ችለናል። ግብይቱም በሸሪዓው የማይከለከልና ሙስሊሞች እስካሁን ሲገለገሉበት የቆየ የዑለማዎች ስምምነት ያለበት ሀላል ግብይት መሆኑን እንረዳለን። ስለሆነም፤ በአሁኑ ሰዓት እየተለመዱ የመጡት የመኖሪያ ቤት፣ የመኪና፣ የማሽነሪ እና መሰል ነገሮችን ለመግዛት በጭማሪ ክፍያ የሚፈፀሙ የዱቤ ሽያጭ ግብይቶች የተፈቀዱ ናቸው። ሆኖም ግብይቶቹ የሚፈቀዱት መስፈርቶችን እስካሟሉ ድረስ ብቻ ነው።
3/ ለዱቤ የጭማሪ ግብይት ወሳኝ መስፈርቶች
1) ሻጭ ሊሸጥ የሚገባው የራሱ ያደረገዉን እቃ ብቻ ነው፦ በእጁ ያልገባን ሸቀጥ ወይም በእሱ ይዞታ ያልገባን ነገር የመሸጥ እና የመለወጥ መብት የለውም። ይህንን በማስመልከት ሐኪም ኢብኑ ሂዛም የተባሉት ሰሀቢይ እንዲህ ብለዋል፤ “አንድ ሰው የሌለኝን እቃ እንድሸጥለት ሲጠይቀኝ እሸጥለትና ከሱቅ ገዝቼ አስረክበዋለው” በማለት መልዕክተኛውን ጠየኳቸውና “የሌለህን እቃ አትሽጥ አሉኝ” (ሀዲሱን ነሳኢ፣አቡዳዉድ እና ቲርሚዚይ ዘግበውታል፤ አልባኒም ሰሂህ ብለውታል) በሌላ ዘገባም፤ አንድን ሸቀጥ ከገዛህ በእጅህ ሳታስገባው እንዳትሸጠው” ማለታቸውን ኢማሙ አህመድ እና ነሳኢይ ዘግበዋል።
2) ከካሽ እና ከዱቤ አንዱን መርጦ መወሰን፦ አንድ ሰው ይህንን እቃ በካሽ 10 ብር በዱቤ 15 ብር እሸጣለው ካለ፤ ገዥ ከሁለቱ አንዱን (ካሽ ወይም ዱቤ) መርጦ ስምምነቱን ከሁለቱ በአንዱ ተመን ላይ ሊወስኑ ይገባል። ግብይቱ የተፈጸመው ከሁለት አንዱን ሳይወስኑ በማመንታት ከሆነ አይፈቀድም። ምክንያቱም በአንድ ግዜ ለሚሸጥ እቃ በሁኔታዎች የታጠሩ ሁለት ተመኖች ላይ መስማማት አይፈቀድም። ነገር ግን ሁለቱ ምርጫዎች ቀርበው ውሳኔው በአንዱ ከጸና ችግር የለም።
አል ኢማም አትቲርሚዚይ በዘገቡት ሐዲሥ አቡ ሑረይራ “የአላህ መልዕክተኛ በአንድ ግብይት ውስጥ ሁለት (አሻሚ) ስምምነቶችን መስማማትን ከልክለዋል” ብለዋል። የሀዲሱ ዘጋቢ አል ኢማም አቲርሚዚይ እና ሌሎች ታላላቅ የሐዲሥ ተንታኞች እንዳሉት፤ ይህ ሐዲሥ የሚመለከተው አንድ እቃ በካሽ እና በዱቤ ዋጋው ሲለያይ ከሁለት አንዱ ላይ ስምምነቱ ያልጸናበትን ግብይት መሆኑን ተናግረዋል።
3) የክፍያ ማዘግየት ቅጣት፦ ገዥ በስምምነቱ መሰረት የሚጠበቅበትን ክፍያ መፈጸሙ ግዴታው ነው። ሆኖም፤ በተለያዩ ምክንያቶች ከተወሰነለት የመክፈያ ግዜ ቢያዘገይ በገንዘብ መቅጣት አይቻልም። ይህንን ስምምነቱ ላይ መስፈርት አድርጎ ማስቀመጥም አይፈቀድም። ብድርን ተከትሎ የሚመጣ የገንዘብ ጥቅም ወለድ ነውና የዱቤ ሽያጭ ላይ በገንዘብ መቅጣት አይፈቀድም።
4) ለዱቤ አገልግሎት ልዩ ክፍያ መጠየቅ አይፈቀድም፦ ተመኑ ለእቃው እንጂ ለዱቤ አገልግሎት መሆን የለበትም። ለምሳሌ የዕቃው ዋጋ በካሽ 10 ብር ሲሆን በዱቤ 15 ብር ነው። የዱቤ አገልግሎት ደግሞ በየወሩ 2% ክፍያ ይጨመራል ማለት አይፈቀድም። ምክንያቱም ከወለድ ግብይት ጋር ያመሳስለዋል። መጅመኡል ፊቅሂል ኢስላሚይ / አለም አቀፍ የፊቅህ ጥናት ባስተላለፋቸው ውሳኔዎች ላይ የሚከተለውን አስፍሯል፤
«በዱቤ ሽያጭ ስምምነት ላይ የዱቤ ወይም የረጅም አከፋፈል አገልግሎትን ክፍያ አሁን እቃው ካለው ተመን ለይቶ ከዱቤው ጋር የተያያዘ ልዩ ክፍያ መጥቀስ አይፈቀድም። ይህ ተስማሚዎቹ የአገልግሎቱን ክፍያ ቢስማሙበት ወይም በተለመደውን የኮሚሽን ተመን ቢከተሉ ክልክልነቱን አያስቀረውም።»
መጀለቱል መጅመዑል ፊቅህ 6ተኛ አመት ቅጽ 1/ ገጽ 193
4/ የቴሌ የብድር አገልግሎት
በቅርቡ የተጀመረው የኢትዮ ቴሌኮም የባላንስ የዱቤ ሽያጭ ተመሳሳይ ጥያቄ ያስነሳል። ተገልጋዮች ለሞባይል ቅድመ ክፍያ ተጠቃሚዎች ከአቅራቢያቸው ካርድ መግዛት በማይችሉበት አጋጣሚ ከቴሌ አገልግሎቱን በዱቤ አግኝተው በሌላ ግዜ ካርድ ሲሞሉ ከጭማሪ ክፍያ ጋር ሂሳቡን ይቆረጥባቸዋል። አንዳንዶችም ይህ አሰራር ወለድ ስለሆነ ተጠንቀቁት የሚሉ መልእክቶችን በሰፊው ያሰራጫሉ።
በየሀገራቱ የቴሌኮም ድርጅቶች "ብድር" እያሉ በሚሰጡት ባላንስ ላይ የሚጠይቁት ጭማሪ እንደሚፈቀድ ኡለማዎች ገልፀዋል። ከቴሌ የምናገኘውን የክሬዲት ባላንስ ካስተዋልን፤ ድርጅቱ በገንዘብ ዋጋ የተመነለትን የስልክ ማነጋገሪያ አገልግሎት፤ ካሽ ከፍለው ለሚገዙ ሰዎች ከሚሸጥበት የዋጋ ተመን ላይ የተወሰነ ጭማሪ አድርጎ በዱቤ ይሸጥልናል።
ተጠቃሚው ባላንስ ሲያልቅበት አሁን ካርድ መግዛት ባይችልም የፈለገውን ባላንስ ይሰጠውና ካርድ ገዝቶ ሲሞላ ቴሌ ለሰጠው የዱቤ ሽያጭ የሚያስከፍለውን ጭማሪ ደምሮ ይቆርጥበታል። ምንም እንኳ ቴሌ ይህንን አገልግሎት 'ብድር' ብሎ ቢጠራውም እውነታው ግን "አገልግሎቱን" በዱቤ ሸጦ ክፍያውን በጭማሪ መቀበል ስለሆነ የተፈቀደ ግብይት ነው።
ይህ የኢትዮ ቴሌኮም አገልግሎትን በዱቤ የመሸጥ ግብይት፤ በፊቅህ ድርሳናት “ኢጃራህ” የሚባለው የአገልግሎት (የሰርቪስ ሽያጭ) ነው። የሰርቪስ ሽያጭ የተ