🌺🌸🌺🌸 ትርታዬ 🌺🌸🌺🌸
🌼🌼🌼 ክፍለ ስምንት (8) 🌼🌼🌼
🌻ልብ አንጠልጣይ እና አስተማሪ ታሪክ🌻
......
መቅደስ ግን ለመሄድ አልፈለገችም ቢሆንም በውለታ ስለታሰረች ፈገግ ብላ ጥያቄውን ተቀበለች።
.......ከዛም ይዟቸው ከግቢ ሲወጣ አሁንም ጌዲዮ አየ ዮናስ ተንኮሉ መቅደስ መቅደስን እየታከከ ነው የሚሄደው።ከጌዲዮ አጠገብ የነበሩ ሁለት ልጆችም አይተው ስለመቅደስና ስለዮናስ ማውራት ጀመሩ አንተ ግን መቅዲ ዮናስን አፈቀረችው አይደል? ... አረ አይመስለኝም ..ተው እንጂ ዮናስን እዚህ ግቢ የማታፈቅረው ሴት አለች ልትለኝ ባልሆነ...በርግጥ ቆንጆ የተባሉት ሁላ ያፈቅሩታል ግን እሱ የሚፈልጋቸው ግዜ ማሳለፊያ አይደል እንዴ?.....ባክህ መቅደስም ተከይፋበታለች ታስታውቃለች ጌዲዮ ለመስማት ተሳነው ከተቀመጠበትም ተነስቶ ወደለመደው ጫካ ሄደ ......
ዮናስ ምሳ ጋብዟቸው ሲያበቃ ለምን አንድ ሁለት እያልን ስንቀውጠው አናመሽም አላቸው ይህን ጊዜ ሰአዳ በሉ እኔን ሸኙኝ አለቻቸው መቅደስም አረ እኔም ጥናት አለብኝ አላመሽም አለች መቅደስ እንድትቀር ወይንሸትና ብርሀን ለመኗት እሷም አይሆንም አለች ከዛ ብርሀን መቅዲ ካላመሸች እኔም አልፈልግም አለች ከዛም በቃ ልሸኛችሁ ብሎ ወደ ግቢ ወሰዳቸውና ከወይንሸት ጋር ተመለሱ።
......ልክ እነመቅደስ ወደውስጥ ሲገቡ እነሱም መታጠፊያውን መንገድ ሲይዙ ወይንሸትና ዮናስ ተቃቅፈው እየተላፉ ሲላቸው እየተሳሳሙ መንገድ ጀመሩ ዮናስና ወይንሸት መቅደስ የማታውቀው ድብቅ ግንኙነት አላቸው ሁለቱም የጥቅም ሰው ስለሆኑ ይስማማሉ ባለፈውም መቅደስ የወደቀችው የጌዲዮ በሽታ ተላልፎባት ነው የሚለውን ወሬ ዮናስ ነው በወይንሸት አፍ ያስለኮሰው ምክንያቱም ሁለቱ እንዲለያዩ ይፈልጋል ዮናስ ጌዲዮንን በነገር ግቢውን ሊያስለቅቁት ለወይንሸት ብር ሰጥቶ አሳምኗታል።
......ይኸው በወይንሸት ስብከት በተደጋጋሚ ዮናስና መቅደስ እንዲገናኙ ሲገናኙም ጌዲዮ እንዲያይ እያደረገች ነው።
....ጌዲዮም የሚሰማው የመቅደስ እና የዮናስ የተቀናበረ የውሸት ፍቅር እውነት ነው ብሎ ሊቀበል እየተገደደ ነው።
....በተለይ ባለፈው አቅፎ ሆቴል ሲያስገባት ካየ ቡሀላ ትምርት በቃኝ እሷን እያየሁ ከምቃጠል ባቋርጥ ይሻለኛል ብሎ ከትምርቱ ሊሰናበት ወስኗል።
.........ጌዲዮ መቅደስን እንዳትጠጊኝ ስለኔ አይመለከትሽም ካላት ቀን ቡሀላ ዘወር ብላም እንዳላየችው ነው የሚያውቀው...አሁንም እራሱን ጠየቀ እውነት አፍቅራኝ ቢሆን አትንኪኝ ስላልኳት እኔን ትታ ሌላ ወንድ ጋር ባትሄድ ነበር አለ።
ከዛም ፍቅሯን መቋቋም ሲያቅተው ካይኗ ብርቅ ይሻለኛል ብሎ ትምህርቱን ሊሰናበት ወደደ መፅሀፎቹን ብቻ ሰብስቦ ለማንም ሳይናገር ወደ መጣበት ሊመለስ ግቢውን ለቆ ወጣ ልክ የግቢውን በር ሲያልፍ አደራ መብላቱን ፍቅሩን ማጣቱን አስታውሶ በቆመበት ወደቀ መቅደስም ከሩቅ አይታው እየሮጠች መጥታ በፊት እንደምታደርገው ክርቢት ምናምን አጭሳ ሰውነቱ ሲረጋጋ ሳይነቃ ልታመልጠው ልትነሳ ስትል አድርጎት የማያውቀውን ወዲያው ነቃ መቅደስ ውሀ ሆነች እንዳይመታት ሁለት ጉንጮቿን በእጆቿ ያዘች ተንቀጠቀጠች ጌዲዮ ግን በልቡ አይኖችሽ ስንቅ ይሁኑኝ ብሎ ፍዝዝ ብሎ አያት አይኖቹ እንባን አፈሰሱ መቅደስ ሳታውቅ ፍቅሯ ተሰናብቷት መንገዱን ቀጠለ መቅደስም ሁኔታው ግራ አጋብቷት ሳታውቀው በቆመችበት ባይኖቿ ሸኘችው.....
...........በቃ ጌዲዮ ሄደ አንድ ሁለት ተብሎ ሶስተኛ ቀን ተቆጠረ መቅደስ ግራ ገባት ከክፍል ተማሪ አንስታ እስከ ዳሬክተር እየተመላለሰች በምን ምክንያት እንደጠፋ ጠየቀች ግን መልስ ማግኘት አልቻለችም የጌዲዮ መጥፋት የዩንቨርስቲውም አሳሳቢ ዜና ሆኑዋል ምክንያቱም ጌዲዮ በጣም ተስፋ የተጣለበት ጎበዝ ተማሪ ነው።.......መቅደስ ምግብ አልበላ ውሀ አልጠጣ አለች ትኩረቷም ከትምርቷ ተነሳ ታመመች ምንም የግሏ ባይሆንም አቅፋ ስታስታምመው የራሷ ያደረገችው ያክል ስለሚሰማት ደስተኛ ነበረች ፍቅሯ የጋራ ባይመስላትም እሷ ግን አይኑ ነበር የፍቅር ምግቧ አሁን ግን ጠፋ ምክንያቱን እንኳን ሳታውቅ ተሰወረባት ብቸኝነት ተሰማት።
.......አሁን የዮናስ እና የወይንሸት ሀሳብ ተሳካላቸው የጀመረውን ጌም ለማሸነፍ አንድ እንቅፋቱን አስወገደ መቼም ከዚህ ቡሀላ ይመጣል ብሎ መገመት ከባድ ነው።
.........
ይቀጥላል ..........
ለሀሳብ አስተያየት 👉 @Dinomu
ለመቀላቀል 👉 @mazngna