ነገሩ እንዴት ነው? እጅግ አሳሳቢ❗
ኮሮና ቫይረስ የተገኘባቸው የ61 ዓመቱ የአዳማው ሰው፣ አብረዋቸው ንክኪ አድርገው የነበሩ 24 ሰዎች በክትትል ላይ እንደሚገኙ እና ከእነሱ ጋር የተገናኙ ሰዎችን የማጣራት ሂደት ላይ እንደሆኑ ጤና ሚኒስትር ገልጾልን ነበር። እሳቸው ንክኪ የነበራቸው መጀመሪያ ከተለየው ጃፓናዊ ሰው ጋር ነበር አሉ፤ መግለጫው በደፈናው በስራቸው የተነሳ፣ ከአንድ የውጭ ዜጋ ጋር ንክኪ የነበራቸው ብሎ ነው የሚገልጸው። (ከመጋቢት 10 ወዲህ የታወቀ የውጭ አገር ዜግነት ያለው ቫይረሱ ያለበት የተገለጸ ሰውም የለም።)
ይኽ ማለት፥ ወይ ጃፓናዊው ቀድሞ መረጃ አልሰጠም ወይም በአግባቡ አልተጠየቀም፤ ወይ ደግሞ መረጃ ሰጥቶ በኣፈጻጸም ክፍተት ችላ ተብሎ ቆይቷል፤ ወይም መረጃውን ሰጥቶ ሰውዬው ከተገኙ በኋላ፣ ደም ሰጥተው ተመልሰው ወደ ኑሯቸው ሄደዋል።
ሰውዬው በሙያቸው ፋርማሲስት ሲሆኑ፣ ዕሁድ ዕለት ታመው፣ ሰፈር ውስጥ ያለች ነርስ ጠርተው መርፌ ወግታቸው፣ ከዚያ በኋላ በመደበኛ የፋርማሲ ሥራቸው ላይ ነበሩ። ከመጋቢት 9 ጀምሮ የህመም ስሜት ሲሰማቸው ራሳቸውን አግልለው ቆይተው እንደነበር የተገለጸው ልክ አይደለም። (ምናልባት ቀድሞ በተያዘው ጃፓናዊ ግለሰብ ጥቆማ መሰረት እርሳቸው ምርመራ የጀመሩበት ቀን ተገልጾ፣ ወይም እሳቸው የተናገሩት ነው ሊገለጽ የሚችለው፤ ያም ሆነ ይህ ራሳቸውን አግልለው አልቆዩም ነበር።)
ጭራሽ፥ ፖሰቲቭ መሆናቸውን ሲያውቁ፣ ዳሎል ሆቴል ተደብቀው ሌሎች የቤተሰቡ አባላት የት እንዳለ አናውቅም ብለው፣ የመጀመሪያ ልጃቸው ሀኪም በመሆኑ ግንዛቤው ስላለው ነው እንዲሄዱ ያደርገው። መጀመሪያም ምልክቶቹ ይታዩባቸው ስለነበር የደም ናሙና የተወሰደው በልጃቸው ጥረት ነው። (ምልክቱ እየታየበት ሀኪም ቤት መሄድ ማይፈልግም አለ ማለት ነው)
ከሃያ አራቱ ሰዎች መካከል፥ 5ቱ ቤተሰቦቻቸው እና፣ መርፌ የወጋቻቸው ነርስ፣ በዕለቱ (መጋቢት 16) ደም ለመስጠት ሄደው፣ "ውጤት ከሶስት ቀን በኋላ" ተብለው በራሳቸው መኪና ነው የተመለሱት፤ ነርሷ ጭራሽ በስልክ ተጠርታ ታክሲ ተሳፍራ ነው የሄደችው አሉ። በርግጥ ደም ሰጥተው ከተመለሱ በኋላ፣ ከቤት አልወጡም አሉ፤ እግዚአብሔር ይስጣቸው፥ እነሱም ሀላፊነት የሚሰማቸው ሆኑ፤ የሰፈሩ ሰውም በስጋት እየጠበቃቸው ነበር። (ቢወጡ ኖሮስ ምን ሊያደርግ?)
[ይኽን ከጻፍኩት በኋላ፥ ነርሷ ዛሬ ተጠርታ ተገልሎ መቆያ ውስጥ መሆኗን ሰማሁኝ። እንዳለኝ መረጃ፥ ነይ ተብላ በታክሲ ነው የሄደችው፤ ውጤቷ አልተነገራትም። ቤቱንም ገና ዛሬ ዲስኢንፌክታንት ረጭተዋል።]
መጀመሪያ ሰውዬው ቤት ልጆቹ በር አንከፍትም ብለው፣ ፖሊስ አስገድዶ ነው በር የከፈቱት አሉ። ይኽም ያለውን የግንዛቤ ችግር ያሳያል። መታመም ወንጀል አይደለም። መንግስት አግልሎ የማቆየቱን ስራ የሚሰራው ለእነሱም ለአገርም ጥቅም እንደሆነ ትምህርት መስጠት አለበት። ካለዚያ በየቤቱ ህክምናውን ሽሽት የሚደበቀውን አስቡት።
እንግዲህ ዛሬ ሁለት ተጨማሪ የተገኙት የአዳማ ነዋሪዎች የ61 ዓመቱ ሰው ቤተሰብ ናቸው።
ይኽንን ነገር የምጽፈው ቫይረሱን ለማስቆም ያለው የለይቶ ማቆያ አያያዝ ጉዳይ ላይ ከፍተኛ ትኩረት እንዲደረግ ለማሳሰብ ነው። ነገ በሚያስደነግጥ ነገር ከምንነቃ፣ ዛሬ እውነታን ተጋፍጠን ቀዳዳዎችን መድፈን አለብን።
1) መንግስት ትክክለኛ መረጃ ይስጥ! ወረርሽኙ የመንግስት ስህተት አይደለም። ስህተት የሚሆነው መረጃ ሆነ ብሎ ግልጽ አለማድረግ፣ ማለባበስ፣ የመከላከል ጥረቶች ላይ ክፍተት መፍጠር እና ቸልተኝነት ናቸው።
2) ሌሎች አገራት ውስጥ፣ ቻይናን ጨምሮ፣ በቶሎ መመርመሪያዎች ቁሶች እየተገኙ እየተሻሻሉ እንደሆን ሰምተናል። ታዲያ ለምን ከቻይና ጋር ተጠያይቆም ቢሆን፣ በአስቸኳይ የተሻሻሉ መመርመሪያዎች አይላኩልንም?
3) ግንዛቤ ማስጨበቻዎችን በደንብ መስራት፣ ለህክምና ተገሎ መቆየት ያለውን አዎንታዊ ሚና ማስረዳት ማሳሰብ ያስፈልጋል። እኛም ብንሆን እንደማህበረሰብ ቫይረሱ ላለበት ሰው የማግለል ፀባይ ማሳየት የለብንም።
4) እርግጠኛ ባልሆንም፥ ከአዳማ አዲስ አበባ ተልኮ ነው የሚመረመረው አሉ። ጊዜ እና ወጪ ለመቆጠብ፣ ለምን መመርመሪያ ስልጠናዎቹን እና አስፈላጊ ቁሶች (kits) አይላኩላቸውምና ራሳቸው እንዲመረምሩ አይደረግም?
5) ቫይረሱ ካለበት ሰው ጋር ንክኪ ያደረጉ ሰዎች፣ ደም ተወስዶ ውጤቱ እስኪታወቅ ድረስ ለምን ተገልለው እንዲቆዩ አይደረግም? በርግጥ ቀላል ወጪ እና ቦታ የሚጠይቅ ላይሆን ይችላል፤ ነገር ግን ከአቅማችን በላይ ቢሆንና ሊደርስ ከሚችለው ጋር ሲነጻጸር ይኽንን ማድረግ የሚረክስ ይመስለኛል።
ለምሳሌ ፋርማሲስቱ ከጃፓናዊው ጋር ንክኪ እንዳላቸው ታውቆ ከነበረ ምርመራ የጀመሩት፣ ቤት በመሄድ ፈንታ ተለይተው ቢቆዩ ኖሮ፣ ቢያንስ ሁለቱ የቤተሰቡ አባላት ያለመያዝ እድል ይኖራቸው ነበር። ያልተለየውን ቤቱ ይቁጠረው።
6) ቫይረሱ ካለበት ሰው ጋር ንክኪ ያደረጉ ሰዎች ለምርመራ ሲሄዱ፣ ለምን በአምቡላንስ አይሆንም? ነርሷ በታክሲ ተሳፍራ መሄዷ ሲታሰብ ምን ማለት እንደሆነ አስቡት። ተመልሳስ ስንቱን አክማለች? የሆነው ሆኗል፤ በቀጣይ ግን እንዲህ ዓይነት ክፍተቶች መደፈን አለባቸው።
#Covid19Ethiopia
~ yohanes molla