#ቅንጭብጭብ_ኢትዮጵያ
“ደርቡሾች በጎንደር ዳግም እንዳይደርሱ
መተማ ተቀምጧል ዮሃንስ ራሱ”
“አፄ ዮሃንስ መጋቢት 1 ቀን ቅዳሜ በመተማ ተዋግተው ከቆሰሉ በኋላ በሽሽት ጉዞ ላይ እሁድ መጋቢት 2 ቀን በተወለዱ በ54 በነገሱ በ18ዓመት በ1881 ዓ.ም ዐረፉ፡፡ በማግስቱ መጋቢት 3 አትባራ ወንዝ ዳር ደርቡሾቹ ደርሰው ጭንቅላታቸውን በመቁረጥ ውጊያው በሱዳኖች አሸናፊነት መፈፀሙን አወጁ” ሲሉ የንጉሱን የመጨረሻ ቀናት ያስረዳሉ ተክለፃዲቅ መኩሪያ “አጼ ዮሃንስና የኢትዮጵያ አንድነት” በሚለው መፅሃፋቸው፡፡
ለምን መተማ ላይ ተሸነፍን?
“ደርቡሾች በመተማው ጦርነት ድሉን ያገኙት በቅድሚያ የሀበሻን ጦር ለመመከት እንደሚችሉ ተመካክረው በሁለት ረድፍ በጥናት ባሰሩት የመከላከያ ምሽግ መሆኑ፤ የኛዎቹም የተሸነፉት በያዙት የጦር መሳሪያና በሰራዊታቸው ብዛት በመተማመን በእልህ ተጋፍጠው በነዚያ ምሽጎች ላይ በመውደቃቸው ሲሆን፤ ይልቁንም ወደፊት ቀድመው እንደተራ ወታደር በመዋጋት የነበሩት የንጉሰ ነገስቱ በድንገተኛ ጥይት ተመተው በመውደቃቸው ነበር፡፡”
ስለ አፄ ዮሃንስ አሟሟት በኋለኛው ጊዜ እንደዚህ ተብሎ ተገጥሞላቸዋል፡፡
አፄ ዮሃንስ ሞኝ ናቸው
እኛም ሁላችን ናቅናቸው
ንጉስ ቢሏቸው በማኸሉ
ወሰን ጠባቂ ልሁን አሉ፡፡
በጎንደር መተኮስ በደንቢያ መታረድ አዝኖ ዮሃንስ
ደሙን አፈሰሰ እንደ ክርስቶስ፡፡
እንዳያምረው ብሎ ድሀ ወዳጁን
መተማ አፈሰሰው ዮሃንስ ጠጁን፡፡
የጎንደር ሀይማኖት ቆማ ስታለቅስ
አንገቱን ሰጠላት ዳግም ዮሃንስ፡፡
@kinchebchabi @kinchebchabi