በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሃዱ አምላክ አሜን !!!
የእምነት መመሪያዎች / Guidelines of Faith/
ምዕመናን ሃይማኖትን ከምግባር፣ ምግባርን ከሃይማኖት አስተባብረው ይዘው እንዲጓዙና በሥርዓተ አምልኮ ጸንተው እንዲኖሩ ቤተክርስቲያን ምእመናንን የምትመራባቸው ሶስት የእምነት መመሪያዎች አሉ እነሱም፡-
ዶግማ
ቀኖና
ትውፊት ናቸው
ዶግማ
ዶግማ ፡- ቃሉ የግሪክ ሲሆን ትርጉሙም መሰረተ እምነት፣ የማይለወጥ፣ የማይቀየር፣ የማይሻሻል፣ የማያረጅ ማለት ነው፡፡ ነገረ መለኮትን የምንማርበት ነው፡፡ ለምሳሌ፡- ሶስትነቱ አንድነቱ የማይነጠል አንድነቱ ሶስትነቱን የማይጠቀልል መሆኑን የምንማርበት፣ ተዋህዶን/ ክርስቶስ ከሁለት አካል አንድ አካል ከሁለት ባህርይ አንድ ባህርይ መሆኑን የምንማርበት፣ እመቤታችን ወላዲተ አምላክ መሆኗን . . . የመሳሰሉትን የቤተክርስቲያን አስተምህሮዎችን የምረዳበት ነው፡፡
ቀኖና
ቀኖና፡- በጽርዕ ካኖን፡- ሕግ፣ ሥርዓት፣ ደንብ፣ ፍርድ ማለት ነው፡፡
በግእዝ ቀነነ ከሚለው ግስ የተገኘ ሲሆን አገገ፣ ሰራ፣ ደነባ፣ ሕግ፣ ሥራት ደንብ አቆመ፣ ቀኖና ሰጠ ማለት ነው፡፡
ሥርዓት ማለት፡- ሕግ አታድርግ የሚለው ሲሆን ትዕዛዝ አድርግ የሚለው ሲሆን ሥርዓት ግን ከሕግ ተወልዶ በትዕዛዝ የሚደረግ ንጹህ ውሳኔ ርቱዕ ብያኔ ነው፡፡ ሥርዓት ህግንና ትዕዛዝትን ያጠቃለለ ነውው፡ ት.ሕዝ 43፡11፣ መዝ 118፡71-72፣ 83 / ዘሌ 20፡8
በመላእክት ጌታ ዘንድ ይድኑ ዘንድ በሃይማኖት የሚሰጥና የጻድቅ ቃል የሚያጸና ነው መ.ሄኖ 17፡1-7
ሥርዓት አስተማሪ እግዚአብሔር ነውው፡ መዝ 118፡24 ፣ 71
ሥርዓት መድኃኒት ነው መዝ 118-155
ሥርዓት ለእግዚአብሔር ተገዢ መሆናችንን የምንገልጽበት ነው ፡፡ ት.ሚል 3፡7-10
እግዚአብሔር አምላክ አስቀድሞ በሙሴ ላይ አድሮ ሥርዓትን ሰራልን ኃላም በሐዋርያት ላይ አድሮ ጽኑ ሥርዓትን ሰራልን፡፡
ኃላም 318 ሊቃውንት ከመጽሐፍ ቅዱስ አግኝተው የሠሩልንን ሕግ ደንብ ስርዓት ሰርተውልናል፡፡ በአጠቃላይ በሐዋርያት፣ የሐዋርያት ተከታዮች በሆኑ ጉባኤ ሰርተው የሰሩልንን ሥርዓት ማንም ሰው ሌላውም ሊያሻሽል አይችልም እግዚአብሔር ከፃፋቸው መጻሐፍት የተገኙ ስለሆነ፡፡
‹‹ እኛስ ብዙ ነገርን አልተናገርንም ብዙ ምስክርንም ልንጽፍ አልወደድንም በዚች በጻፍናት መጻፍ ላይ የሚጨምርም ወይም ከርሱ የሚያጎድል ከእርሱ ከሚጻፈው መጽሐፍ ከቅጁ የሚጨምር የሚያጎድል በፍትሐ እግዚአብሔር ይጠየቅበታል፡፡ ›› ዘዳ 4፡2፣ 12፡32፣ ማቴ 12፡36-37፣ ራዕይ ዩሐ22፡18-21፣ ሃ.አበው ዘሠለስቱ ምዕት ም22፡16
ትውፊት
ትውፊት አወፈየ ከሚለው የግዕዝ ግሥ የተገኘ ሲሆን ስጦታ፣ ልማድ፣ ትምህርት፣ ወግ፣ ታሪክ ፣ ሃይማኖት ሥርዓት ከጥንት ከአበው ሲያያዝ ሲወርድ ቃል በቃል ሲነገር የመጣ ርትዕት የሆነች የሐዋርያት ሃይማኖት ትውፊት፣ የቅዱሳን መምህራን ትውፊታች፣ ከቅዱሳን ሐዋርያት የተቀበልናቸው መጽሐፍቶቻቸው በአጠቃላይ ያመለክታል፡፡
ትልቁ ነገር ከእውነተኛይቱ ሀይማኖት እንዳይወጣ ዘመን የወለደው ንጉስ እንዳለው ብለው እንዳይበድሉ የሚያደርግና የሃይማኖቱን መሰረት በቅብብሎሽ የሚረዳበት ነው፡፡ ‹‹ የቀደመችውንም መንገድ ጠይቁ ›› እንዳለ አውቆ በመመላለስ ለነፍስ እረፍት የምታሰጠውን በለመለመ መስክ የሚሰማራበትን ከመንገዱ ሳይወጣ በቀናችቱ መንገድ የሚያደርግ ነው፡፡
ከጥሩ ምጭ መንጭቶ ሳይበረዝ ዘመናት ሳይጽሩት የሚጠጡት መጠጥ ነው፡፡
ትውፊት በነቢያት በሐዋርያት መሰረት ላይ የተመሰረተ የማዕዘኑን ራስ ድንጋይ ክርስቶስ ኢየሱስ እንደሆነ በቅብብሎሽ ያገኘው እንደሆነ የሚረዳበት ኤፌ 2፡20 ከተመሰረተው ውጪ ያይደለ በክርስቶስ የተመሰረተ መሰረት እንደሆነ አውቆ እንዲጓዝ የሚያደርግ ነው፡፡ ጠላት ከዘራው እንክርዳድ ከቢጸ ሐሳውያን እንዲሁም ከአርዮስ ከሰባልዮስ ከልዮን ከሉተር. . . . ወዘተ እንክርዳድ የሚጠበቅበት ነው፡፡
‹‹ ከመጀመሪያው በዓይን ያዩትን የቃሉ አገልጋዮች የሆኑት እንዳስተላለፉልን . . ›› ሉቃ 1፡1
‹‹ ወንድቻችን ሆይ እናንተስ የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሐዋርያት መጀመሪያ ያስተማራችሁን ቃል አስቡ ›› ይሁ.1፡17
አባቶች ካስተማሩት ትምህርት ውጪ ወጥቶ እንዳይጎዳ የአባቶችን ትምህርት ተቀብሎ እንዲመላለስ ገላ1፡1
የቀድሞውን የድንበር ምልክት እንዳያፈርሱ የሚያደርግ ጠብቆ እንዲሄድ ምሳ 23፡10 ቅድስት ቤተክርስቲያናችንም ሁል ጊዜ በቅዳሴ ገባሬው ካህን ‹‹ ነዋ ወንጌለ መንግሥት ›› መንግስተ ሰማያትን የሚሰብክ ወደ መንግስተ ሰማያት የምታገባ ወንጌል ይህች ናት ብሎ ለንፍቁ ቄስ ሲሰጥ ንፍቁ(ረዳት ቄሱ ‹‹ ዘአወፈየኒ አወፈይኩክ›› ብሎ የሰጠኝ ወንጌልን ሰጠሁህ ብሎ ለዲያቆኑ ይሰጠዋል፡፡ ይህ ወንጌል ከመሰረቱ ተነስቶ መሰረቱን ሳይለቅ ሳይበረዝ ትውልድ ሳይገድበው በቅብብሎሽ ለትውልድ የሚቆይ እንደሆነና ልጆቿም ተጠብቆ የቆየውን ሀይማኖት ተረክበው ለቀጣዩ ትውልድ ሳያዛንፉ የነቢያት የሐዋርያት መሰረት እንዲያስረክቡ ታስተምራቸዋለች ከእንግዳ ትምህርት ትጠብቃቸዋለች፡፡
.
.
.
ይቆየን !!!
@orthodoxtewahedon
ሼር በማድረግ ለሌሎች ያድርሱ