Bahiru Teka dan repost
✅ የእህታችን መዲና ሞት አሳዛኝ የሚያደርገው ምንድነው ?
ክፍል ሁለት
እህታችን መዲና ህመሟ ወደ ሞት የተሳፈረችበት መጓጓዣ መሆኑን ስታውቅ ከልጆቿ ጋር የነበራትን ሁኔታ ቀየረች ። የመጀመሪያው ጠዋት ወጥቶ ወደ ተቀጠረበት ሱቅ ስለሚሄድ እቤት ብዙ አይገኝም ። ሁለቱ ልጆቿ አንዱ ወንድሞችን አስቸግሬ የአመት እንዲከፈልለት አድርጌ ሁለተኛውን ደግሞ ት/ቤቱን ስላለው ሁኔታ አስረድቼ እንዲቀበሉት አድርጌ እየተማሩ ነው ።
እነዚህ ልጆች ከእናታቸው ውጪ የሚያውቁት የለም ከት/ ቤት ሲመጡና በእረፍት ቀን ካጠገቧ ዞር አይሉዩም ።
እሷ አልጋ ላይ እነርሱ መሬት ላይ ሆነው ይተያያሉ ። እናት ለልጆቹ ተንሰፈሰፈ ሲባል የሷ አቻ የለውም ። የሆነ ሳአት ወጥተው ከተጫወቱ ይታጠቡ ልብስ ይቀየርላቸው ትላለች ። ቢያንስ በቀን ሁለቴ ታጥበው ልብስ ይቀየርላቸዋል ። በሳምንት ሁለቴ ገላቸው ይታጠባል ። ምግባቸው እሷ ሳታየው አይቀርብላቸውም ። የመጨረሻውዎቹ ሁለት ወሮች አካባቢ በልጆቿ ላይ ሁኔታዋን ቀየረች ።
ይህ የሆነው በሞት እንደምትለያቸው ስታውቅ ነበር ። አጠገቧ እንዳይቀመጡ ማድረግ ጀመረች ። ፊት ነሳቻቸው ታመናጭቃቸዋለች ። ይህን የምታደርገው ውስጧ እየተሰቃየ ስለያቸው እንዳይጎዱ ይጥሉኝ በሚል አሳዛኝ ውሳኔ ነው ። ምክንያቱ በማይገባቸውና በማያውቁት ሁኔታ የእናታቸው ሁኔታ የተቀየረባቸው ህፃናቱ ግን መሄጃ የላቸውምና ወደርሷው ነው የሚመለሱት ። ትስቅልን ይሆናል ታቅፈን ይሆናል በሚል ያዩዋታል ይቀርቡዋታል ይጠጉዋታል ። ሁኔታዋ ከእለት እለት እየተባባሰ ሁለመናዋ እየከዳት መጣ ። አይኗን መክፈት ያቅታት ጀመር ምላሷ በምትፈልገው መልኩ ማዘዝ አቃታት ። አጠገቧ ላሉ እህቶች እያቃሰተችና በተራ ተራ ፊደሎችን በትግል እያወጣች ለልጆቼ እናታችሁ አላህ ወስዷታል በሉዋቸው አለቻቸው ። መጨረሻ ላይ አላህ ሆይ ልጆቼን አደራ ብላ ከአላህ በኋላ የልጆቼን አደራ እኔን ለማዳን ለተሯሯጡ እህቶቼና ወንድሞቼ ሰጥቻለሁ ብላ በዱንያ ላይ ላታያቸው ትታቸው ወደ ማይቀረው አገር አኼራ ሄደች ።
ክፍል አንድን ለማግኘት
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
https://t.me/bahruteka/5731
https://t.me/bahruteka