🌹 "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። 🌹
🌹 #ጥቅምት ፳፰ (28) ቀን።
🌹 እንኳን #ለቅዱስ_አማኑኤል_ዓመታዊ_በዓል፣ #አባቱ_ኖኅ_እግዚአብሔር_የያፌትን_አገር_ያስፋለት ብሎ ለመረቀው #ለቅዱስ_ያፌት_ለመታሰቢያ_በዓሉ፣ #ለቅዱሳን_ሰማዕታት_ለመርትያኖስና_ለመርቆሬዎስ ለዕረፍታቸው በዓል፣ እግዚአብሔር አምላክ በሰላም አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰቡ፦ #ከአባ_መቅብዩ፣ #ከአባቶቻችንም_ከቅዱሳን_ከአብርሃም_ከይስሐቅና_ከያዕቆብ ከመታሰቢያቸው ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።
✝ ✝ ✝
🌹 #ቅዱሳን_ሰማዕታት_መርትያኖስና_መርቆሬዎስ፦ እሊህም ለቊስጥንጥንያ ሊቀ ጳጳሳት ለአባ ጳውሎስ ደመ መዛሙርቱ ናቸው ይህም እንዲህ ነው አርዮሳዊ የሆነው ሁለተኛው ንጉሥ ቈስጠንጢኖስ አባ ጳውሎስን በተጣላው ጊዜ ወደ አርማንያ አጋዘውና በዚያም በሥውር አሥር ቤት ውስጥ አንቀው እንዲገድሉት አደረገ እሊህ ቅዱሳን መርትያኖስና መርቆሬዎስ ግን የዕረፍቱን ቀን ገድሉንም ጻፉ አርዮሳዊውያን ንጉሥ ረገሙት።
🌹 አንድ ክፉ ሰውም ወደ ንጉሡ ሒዶ እነርሱ እንደረገሙት ወነጀላቸው ንጉሡም ያን ጊዜ ከአታክልት ቦታዎች በአንዲቱ ቦታ ተቀምጦ ሳለ ወታደሮች ልኮ ወደርሱ አስቀረባቸው በሰይፍም እንዲገድሏቸው አዝዞ ገደሏቸው በዚያም በገደሏቸው ቦታ ቀበሩአቸው እስከ ዮሐንስ አፈ ወርቅ ዘመንም በዚያ ቦታ ኖሩ እርሱም ዜናቸውን በሰማ ጊዜ መልእክተኞችን ልኮ ሥጋቸውን ወደ ቊስጥንጥንያ በክብር አስመጣ ያመረች ቤተ ክርስቲያንንም ሠርቶላቸው ሥጋቸውን በውስጧ አኖረ በዚችም ቀን ጥቅምት 28 በዓልን አደረገላቸው። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም ቅዱሳን ሰማዕታት መርትያኖስና መርቆሬዎስ በጸሎታቸው ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን። ምንጭ፦ የጥቅምት28 ስንክሳር።
✝ ✝ ✝
🌹 #የዕለቱ_ምስባክ፦ "ትውልደ ጻድቃን ይትባረኩ። ክቡር ወብዕል ውስተ ቤቱ። ወጽድቁኒ ይነብር ለዓለም"። መዝ 111፥12-13 ወይም መዝ 71፥15። የሚነበቡት መልዕክታት ዕብ 6፥9-15፣ 1ኛ ጴጥ 4፥12-ፍ.ም እና የሐዋ ሥራ 3፥12-17። የሚነበበው ወንጌል ሉቃ 20፥36-41። የሚቀደሰው ቅዳሴ የሠለስቱ ምዕት ቅዳሴ ነው። መልካም የቅዱስ አማኑኤል በዓል፣ የአቡነ ይምአታ የዕረፍት በዓልና የጽጌ ጾም ለሁላችንም ይሁንልን።
@sigewe
https://t.me/joinchat/AAAAAFGQ22bI0Ij80hYpFA
https://www.facebook.com/profile.php?id=61552828743736&mibextid=ZbWKwL
https://www.facebook.com/profile.php?id=61552828743736&mibextid=ZbWKw