በሲዳማ ክልል እና በወላይታ ዞን የመንግስት ባለስልጣናት ከህገወጥ የነዳጅ አዘዋዋሪዎች ጋር እየሰሩ እንደሆነ ተጠቆመ
ወላይታ ሶዶን ጨምሮ አጠቃላይ በደቡብ ህዝቦች ክልል እንዲሁም በሀዋሳ ከተማ ቤንዚን ከጠፋ በርካታ ቀናት ማለፉ የሚታወቅ ሲሆን ለነዳጅ እጥረቱ እንደ ዋና ምክንያት እየተነሳ ያለዉ የህገወጥ ንግድ መበራከት ነዉ ቢባልም የችግሩ ጥልቀት ከዛም ያለፈ እንደሆነ ምንጮቻችን ጠቁመዋል።
ከወደብ ተጭኖ የሚመጣ ነዳጅ ከማደያ ባለቤቶች፤ ከፀጥታ አካላት፤ ከንግድና ገበያ ልማት ጽ/ቤት እንዲሁም ከደላሎች ጋር ባለ የጥቅም ትስስር በጥቁር ገበያ ከ150-200 ብር በጅምላ እየተሸጠ እንደሆነ ለማወቅ ተችሏል።
ዛሬ ላይ በጥቁር ገበያዉ በድብቅ ቤንዚን በችርቻሮ እስከ 250 ብር እየተሸጠ እንደሆነ የተረጋገጠ ሲሆን ለበርካታ ወጣቶች የስራ ዕድል በመፍጠር፤ ቤተሰብ ማስተዳደሪያነት የሚጠቀሙ ባለ3 እግር ባጃጅና ባለ2 እግር ሞተሮች ሙሉ በሙሉ ማለት በሚያስችል ሁኔታ አገልግሎት መስጠት አቁመዋል።
ስሜ አይጠቀስ ያሉ አንድ የወላይታ ሶዶ ባለ ሶስት እግር ባጃጅ አሽከርካሪ "በዚሁ ስራ ራሴን እና ቤተሰቤን የማስተዳደር ነበርኩ፣ ነገር ግን በቤንዚን ምክንያት እኔም ሆነ ሌሎች ጓደኞቼም ሥራ መሥራት ተቸግረናል" ያለ ሲሆን በሶዶ ከተማ ያሉ ማደያዎች በጠቅላላ ቤንዚን የለም የሚል ማስታወቂያ እየለጠፉ ይገኛሉ ብሏል።
አክሎም "ነገር ግን ቤንዚን በሁለት ሌትር የውሃ ሃይላንድ በከተማዋ መንገዶች ይቸበቸባል። ከየት የመጣ ነው ሲባል እነዚህ ማደያዎች በህገወጥ መንገድ ለቸርቻሪዎች እየሸጡ ሁሉም አይነት አሽከርካሪዎች ከነዚህ ቸርቻሪዎች 1 ሌትር በ 200 ብር እየገዙ ይጠቀማሉ" ብሏል።
በዚህ ምክንያት አሽከርካሪዎች እንዲሁም ተጠቃሚዎች ለከፋ ችግር ተዳርገናል፣ ለማን አቤት እንበል? ማደያዎች አልቋል ባሉት ማግስት በየሜዳው የሚሸጠው ከየት የመጣ ነው? በማለት ለመንግስት ጥያቆያቸውን አቅርበዋል።
በተመሳሳይ በሲዳማ ክልል፣ ሀዋሳ ከተማ እጥፍ ዋጋ በማስከፈል ነዳጅ በየመንገዱ እየተሸጠ እንደሆነ ታውቋል። መንገድ ላይ መሸጡ ብቻ ሳይሆን እንደ ውሀ ያለ ባእድ ነገር ተቀላቅሎ እየተሸጠ እንደሆነ ጠቁመው የመንግስት ሀላፊዎች እንዳሉበት እንደሚሰሙ ጠቁመዋል።
MeseretMedia
@Addis_Reporter