በኢትዮጵያ የማስታወቂያ ስነ-ምግባር ረቂቅ ደንብ ላይ ውይይት ተደረገ
አዲስ አበባ፣ ህዳር 05/2017 ዓ.ም
የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን በኢትዮጵያ የማስታወቂያ ስነ-ምግባር ደንብና መመሪያ ረቂቅ ሰነድ ላይ ከማስታወቂያ ም/ቤት አባላት ጋር ውይይት አደረገ፡፡
መድረኩ በረቂቅ ደንቡ ላይ ውይይት በማድረግ ግብዓቶችን ለማሰባሰብ እና ረቂቁን በማዳበር ፀድቆ ወደስራ እንዲገባ ለማስቻል ያለመ ሲሆን ሰነዱ በባለሥልጣኑ የማስታወቂያ ክትትል ዴስክ ኃላፊ ወ/ሮ በድርያ ውልጫፎ ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል፡፡
በውይይቱ ላይ ማብራሪያ የሰጡት የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ ዮናስ ፋንታዬ፤ በባለሥልጣኑ የተዘጋጀው ረቂቅ ሰነድ ፀድቆ ወደ ስራ ሲገባ ከዚህ በፊት የነበሩ ህገ ወጥ የማስታወቂያ አሰራሮችን ማስቀረት እንደሚቻልና ህጋዊ አሰራሮችን ለማጠናክር ምቹ ሁኔታዎችን እንደሚፈጥር ገልጸዋል፡፡ ደንቡ በኢትዮጲያ የሚሰሩ የማስታወቂያ ስራዎች የህብረተሰቡን እሴትና ማንነት የጠበቁ እንዲሆኑ ለማድረግ እንደሚያስችልም አቶ ዮናስ አያይዘው ተናግረዋል፡፡
የውይይቱ ተሳታፊዎች በበኩላቸው ለዘርፉ ወጥ የሆነ አሰራር መመሪያ አለመኖር ለስራቸው እንቅፋት እንደፈጠረባቸው ገልፀው፤ ይህ የማስታወቂያ ስነ-ምግባር ደንብና መመሪያ ረቂቅ መዘጋጀቱ ለስራቸው ጥራት እና መሻሻል አስፈላጊ መሆኑን ተናግረዋል።
*በመገናኛ ብዙኃን እና በማስታወቂያ ይዘቶች ላይ የህግ ጥሰት፣ የሙያ ስነ-ምግባር ግድፈት፣ የጥላቻ ንግግር እና የሐሰተኛ መረጃ ሲመለከቱ በ9192 ነፃ የስልክ መስመር ደውለው ማሳወቅዎን አይርሱ፡፡
#ብቁ_መገናኛ_ብዙኃን_ለማህበረሰባዊ_ንቃት
#የጥላቻ_ንግግርና_ሐሰተኛ_መረጃን_በጋራ_እንከላከል