Healing Valves Ethiopia


Kanal geosi va tili: Efiopiya, Amharcha
Toifa: Tibbiyot


የተሰበሩ የህፃናት ልቦችን በህብረት እንጠግን ።

Healing Valves Ethiopia - is a support group established to create awareness and to help children suffering from life threatening heart diseases in Ethiopia. It works to bring persistent cardiac care by the local team.

Связанные каналы

Kanal geosi va tili
Efiopiya, Amharcha
Statistika
Postlar filtri


13ኛው የሂሊንግ ቫልቭስ ኢትዮዽያ/HVE/ የነፃ ልብ ቀዶጥገና

ከጎንደር ዳባት ልዩ ስሙ ጃናሞራ ተወልዳ ያደገችው የ18 አመቷ ልጃገረድ በአ/አ በቤት ሰራተኝነት አራት አመት አሳልፋለች:: ከገበሬ ወላጆቿና ከአራት እህቶቿ ተለይታ በአ/አ የተቀበላት ከሆስፒታልና ከክሊኒክ ያልለያት ከቶንሲል ጋር ተያይዞ የሚከሰተው የልብ በሽታ ነበር::

ባልተለመደ ሁኔታ የታዳጊዋ አሰሪና አሳዳጊ ልዩ ጥረት ታክሎበት የታዳጊዋን ህይወት አድኑልኝ በማለት ወደ ሂሊንግ ቫልቭስ ኢትዮዽያ/HVE/ በር በመምጣት አንኳክታለች:: "ልጅ ስለሌለኝ እንደ ልጄ እሳሳለታለሁ" የምትለው ይህች ልበ ቀና አሳዳሪዋ; ለገበሬ ወላጆቿ የታዳጊዋ ጤንነት ከጊዜ ወደ ጊዜ አሳሳቢ እንደሆነባትና ለልብ ቀዶ ጥገናውም የሚጠየቀው እስከ ግማሽ ሚሊዮን ብር ክፍያ እንደሆነ አልያም ወደ ውጭ ሀገር ወስዶ ማሳከም መሆኑን ብትገልፅላቸውም የወላጆቿ መልስ "እኛ ጋር ትምጣ ፀበል እንወስዳታልን" ነበር ትላለች::

በግራ በኩል በአንደኛው የልብ በር /Mitral valve/ ከፍተኛ ማፍሰስ /Severe Regurgitation/ ምክንያት ከፍተኛ የልብ ድካም /StageIII,IV congestive heart failure/ ውስጥ የነበረች ሲሆን መፍትሄውም የታመመውን የልብ በር መቀየር ከተቻለ ደግሞ መጠገን ነበር:: በመሆኑም በዛሬው እለት (12/02/15) በHVE ቅን ቤተሰቦች የገንዘብ እርዳታና በድርጅታችን የነፃ የልብ ቀዶ ጥገና አድራጊ ቡድን ልዩ ትብብር የዚህች ታዳጊ የነፃ የልብ ቀዶ ጥገና በተሳካ ሁኔታ ተከናውኗል:: የታዳጊዋን የልብ በር/Mitral valve/ መቀየር ሳያስፈልግ የተሳካ የልብ በር ጥገና/Mitral valve repair/ ማካሄድ ተችሏል::

The 13th free Rheumatic heart disease/RHD/ valve surgery by Healing Valves Ethiopia/HVE/

The 18years old girl, who was born and grown up in North Gonder, Dabat, at the rural area called Janamora, was a housemaid in Addis Ababa for the past four years.

Distant from her farmer parents and four sisters, she spent the last four years shopping doctors and visiting clinics to get relief from her heart problem. She was diagnosed to have rheumatic heart disease/RHD/, a heart valve disease caused by neglected and repeated tonsillar infection. She discontinued her education from 4th grade because of her illness.

Her employer could have simply send the young girl to her rural home when she is unable to work, let alone the repeated medical attention she was requiring. But that was not the case. Her employer took her to various hospitals to get her cured. Unfortunately her employee was requiring a heart surgery which costs not less than half a million Ethiopian birr or to take her abroad.

With despair, the employer informed the farmer parents of the young girl by phone about her deteriorating situation. Their answer was genuine, simple and straight “Bring her home, we will take her to the holy water”.

Not blessed with her own child, the kind-hearted employer used to feel and took care of the young girl as her own child. Finally while she was trying to reach out for sponsors to finance the surgery for this young girl she came across to Healing Valves Ethiopia/HVE/.

The 18years old young girl was in severe form of heart failure (stage III,IV CCF) due to severe mitral valve regurgitation (one of the left side heart valve). The solution at best would be to repair the damaged valve or else to replace the valve by an artificial one.

Because of the charity from HVE families and the volunteer free service by the local heart team the surgery for this serving servant young girl was done successfully today(October 22, 2022). The local team performed successfully mitral valve repair with out the need to replace it to her best future demand.


ስድስት ሰአት በፈጀው የልብ ቀዶ ጥገና Healing Valves Ethiopia (HVE) በዛሬው እለት 11ኛውን የነፃ የህይወት አድን የልብ ቀዶ ጥገና አከናወነ::

የ14 አምቷ ልጃገረድ ከወራቤ አካባቢ የመጣች ሲሆን በተፈጥሮ ካለባት የልብ ችግር (PDA) በተጨማሪ ከተንሲል ጋር ተያይዞ በሚከሰት የልብ በር በሽታ (Severe Mitral Valve regurgitation secondary to RHD) በከፍተኛ የልብ ድካም ውስጥ ነበረች:: በአንደኛ አመት የ Healing Valves Ethiopia ምስረታ ክብረ በአል ላይ በኦድዮ ቪዥዋል አርቲስት ሳምኤል ሀይሉ ተበርክቶ በጫረታ በ250,000 ብር የአዳማ ነዋሪ በሆኑት በአቶ ተስፋዬ ባሌማ አሸናፊነት መወሰዱ ይታወሳል::

Healing Valves Ethiopiaም ይህንን ገቢ ለዚህ የልብ ቀዶ ጥገና በመጠቀም እንዲሁም ሌሎች በረከቶቻችንን አክለን የዚህን ፈታኝ የልብ ቀዶ ጥገና ማከናውን ችለናል:: ልዬ ምስጋና ለአቶ ተስፋዬ ባሌማ እና ለሳምኤል ሀይሉ::


Numbers are ticking
Life is going
Healing Valves Is doing

In a six-hours taking open-heart surgery Healing Valves Ethiopia today(27/08/22) performed the 11th free voluntary surgery. Mitral valve repair and PDA closure was done for a 14 years old girl from a place called Worabe after she presented with severe mitral regurgitation due to RHD and a congenital heart disease called PDA. Thanks to the fund raised during first year anniversary of HVE by the auction from the picture donated by Audio Visual Artist Samuel Hailu and the subsequent winner by Ato Tesfaye Ballema, we managed to perform this demanding and life-saving surgery.


ሂሊንግ ቫልቭስ ኢትዮዽያ(HVE) በዛሬው እለት 9ኛውን የህይወት አድን የልብ ቀዶ ጥገና በስኬት አከናወነ:: የሸዋ ሮቢቱ የ17 አመት ታዳጊ አንደኛው የግራ ልብ በር (mitral valve)የተቀየረለት ሲሆን ከቶንሲል ጋር ተያይዞ በሚመጣ የልብ በር በሽታ (RHD)ለብዙ አመታት ሲሰቃይ ነበር::
እኛም የHVE የበጎ አድራጊ ቡድን ከአድካሚው የልብ ቀዶ ጥገና በኾላ በሾርባ ችርስ ድሉን አክብረናል::

Today HVE performed successfully the 9th life-saving open heart surgery for a 17 years old boy from Shewa Robit. We performed Mitral Valve Replacement for severe mitral valve stenosis and regurgitation due to RHD.




ውድ የሂሊንግ ቫልቭስ ኢትዮጵያ (HVE) ቤተሰቦች
እና ደጋፊዋች በሙሉ

ሂሊንግ ቫልቭስ ኢትዮጵያ (HVE) ከጥቅምት 12 ቀን 2013 ዓ.ም. ጀምሮ በኢፌድሪ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ኤጀንሲ በመዝገብ ቁጥር 5181 ተመዝግቦ የተመሰረተ ሃገር በቀል የበጎ አድራጎት ድርጅት ሲሆን: የተቋቋመበት ዋነኛ አላማ በሃገራችን የሚታየውን ከቶንሲል ጋር ተያይዞ በሚፈጠር የልብ ህመም (Rheumatic Heart Disease) ለሚሰቃዩ ከ18 ዓመት በታች ላሉ ታዳጊዋች የህይወት አድን የልብ ቀዶ ጥገና ህክምና አገልግሎት ድጋፍ ማድረግ ነው፡፡

ምንም እንኳ በአመት የ50 ህፃናትን የህይወት አድን የልብ ቀዶ ጥገና ለማድረግ አቅዶ  የተነሳ ቢሆንም ማሳካት የተቻለው የስምንት ሕፃናትን የልብ ቀዶ ጥገና በማድረግ የልጆቹን ህይወት ለመታደግ ችሏል፡፡ ይህ የአገር በቀል ድርጅት ሙሉ በሙሉ በሀገር በቀል እውቀት ከማሳካቱም ባሻገር ለኦፕሬሽኑ አስፈላጊ የሆነውን ወጪ ማሰባሰብ ችሏል::

በዚህም መሰረት በመጪው ሐምሌ 10 ቀን 2014 ዓ.ም. በአዲስ አበባ ቦሌ አትላስ አካባቢ በሚገኘው ማግኖሊያ ሆቴል ከጠዋቱ 3፡00 ጀምሮ አንደኛ ዓመት ክብረ በአላችንን በደማቅ ስነ ስርአት ታዋቂ እንግዶች በተገኙበት ይከበራል:: በዚሁ ባዘጋጀነው የአንደኛ አመት ምስረታ በአል ላይ እንድትገኙልን በአክብሮት እንጠይቃለን፡፡ በእለቱም HVE ቤተሰቦች ጋር በቅርበት እንተዋወቃለን ስላከናወናቸው ስኬቶች እንወያያለን::በቀጣይ ስለምንጓዝባቸው እርምጃዎች አስተያየቶቻችሁን እንሰበስባለን፤ በእለቱም የተለያዩ ታዋቂ አርቲስቶች ማዝናኛቸውን ያቀርባሉ::


ለሂሊንግ ቫልቭስ ኢትዮጵያ (HVE) ደጋፊዎችና አባላት

ሂሊንግ ቫልቭስ ኢትዮጵያ (HVE) ከጥቅምት 12 ቀን 2013 ዓ.ም. ጀምሮ ከኢፌድሪ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ኤጀንሲ በመዝገብ ቁጥር 5181 ተመዝግቦ የተመሰረተ ሃገር በቀል የበጎ አድራጎት ድርጅት ሲሆን የተቋቋመበት ዋነኛ አላማ በሃገራችን የሚታየውንና ከቶንሲል
ጋር በተያያዘ በሚፈጠር የልብ ህመም (Rheumatic Heart Disease) ለሚሰቃዩ እድሜያቸው ከ18 ዓመት በታች ለሆኑና ለህክምናው የገንዘብ አቅም ለሌላቸው ህጻናት ዘላቂ የሆነ የህክምና አገልግሎት ድጋፍ ማድረግ ነው፡፡

ባለፈው አንድ አመት የ50 ህፃናትን ህይወት
ለመታደግ አቅዶ የተነሳ ቢሆንምለስምንት ሕፃናት ሙሉ ወጪያቸውን በመሸፈን ከፍተኛ የልብ ቀዶ ጥገና በማድረግ የልጆቹን ህይወት ለመታደግ ችሏል፡፡

በቅርቡ አንደኛ ዓመት ክብረ በአላችንን ለማክበር በዝግጅት ላይ መሆናችንን ገልጸንላቸሁ የነበረ መሆኑን ይታወሳል፣ በዚህም መሰረት በመጪው ሐምሌ 10 ቀን 2014 ዓ.ም. በአዲስ አበባ ቦሌ አትላስ አካባቢ በሚገኘው ማግኖሊያ ሆቴል ከጠዋቱ 3፡00 ጀምሮ ባዘጋጀነው መርሃ ግብር ላይ እንድትገኙልን በአክብሮት እንጠይቃለን፡፡

ሂሊንግ ቫልቭስ ኢትዮጵያ


ደስታዬን ተምኑልኝ

በ 48 ሰአት ውስጥ ሁለት አስቸጋሪ የሚባል የልብ ቀዶ ጥገና ሰርቼ ስለነበር በድካም የዛለውን አካሌን ላሳርፍ ስል በቴሌግራም አማካኝነት ከቱርክ ኢስታንቡል በተንቀሳቃሽ ምስል የታገዘ መልእክት አይኔን በእንባ; ልቤን በሀሴት ልፋቴን በድል ሞላው::
ከሁለት አመት ተኩል በፊት በቅዱስ ዻውሎስ ሆስፒቲል የኩላሊት ንቅለ ተከላ ለማካሄድ ወረፋ ደርሶት በሆስፒትል ቢገኝም በቅድመ ዝግጅት ምርመራ በሁለት የልብ በሮች ላይ ከፍተኛ የሚባል ችግር እንዳለ ተነግሮት በቅድሚያ ይህ ከፍተኛ የህይወት አድን የልብ ቀዶ ጥገና አካሂደህ ከተረፍክ ብቻ ተመለስ ስለተባለ ወጣት አጫውቼአቹህ ነበር:: ከስምንት ወር በፊትም በወጣው የልብ ጠጋኙ ማስታወሻ መፅሀፌም ላይ " ላያስችል አይሰጥ" በሚል ንኡስ አርእስት የቀረበው የዚህ ወጣት ታሪክ ሲሆን በሀኪም ፔጅም ላይ የዚህ የልብ ቀዶ ጥገና ስኬት አቅርበን ነበር:: ህይወቱን በዳያሊስስ (dialysis) ላይ ያደረገውና አይሳካለትም የተባለው ወጣት ሁለት የልብ በር ቅየራ የልብ ቀዶ ጥገና (Double Valve replacement surgery for patient on dialysis in our country by the local team)በድል አጠናቀቀ:: ይሁን እንጂ በሀገራችን ይሰጥ የነበረው የኩላሊት ንቅለ ተከላ ተቋረጠ:: በCOVID-19 ወረርሽኝ መከሰት እና መያዝ ሲቀጥልም በሌሎች ቤተሰባዊ ችግር ይህ ታካሚ ተስፋ ቆርጦ በዳያሊስስ (dialysis) ላይ እንዳለ ከሁለት አመት በላይ የተቀመጠ ሲሆን የኛም የልብ ቀዶ ጥገና ህይወቱን ቢያተርፈውም ለታሰበለት አላማ ባለመዋሉ እዝነን ነበር::
እነሆ ይህንን ታሪካዊ የልብ ቀዶ ጥገና በሰራን ከሁለት አመት ተኩል በህዋላ ዛሬ ማታ የተንቀሳቃሽ ምስል ድጋፍ ያለው መልእክት እንዲህ ይላል" በቱርክ ኢታንቡል የኩላሊት ንቅለ ተከላው በሰላም ትካሂዶልኝ በመልካም ሁኔት እያገገምኩ እገኞለሁ ምስጋናዬም ለአንተና ለመላው የልብ ህክምና ቡድን ይድረሳቹህ " ሲል እንባ የተናነቀው ያ የማውቀው እና የማይሰበረውን ወጣት በደስታ ሰክሮ አየሁት:: እኔም የነዘነዝኳቹ በምክንያት ነበረና ደስታዬን መዝኑልኝ ደስታዬንም ተካፈሉኝ አልኳቹህ::


OUR CBE account of Healing Valves Ethiopia (HVE)
1000382769523. Thank you for your help and Support.




መጋቢት 23፣ 2014

የልብ ህመማቸው ከፍተኛ ደረጃ ላይ ለደረሰ ከፍለው መታከም ለማይችሉ ከ18 ዓመት በታች ለሆኑ ህፃናት ይህ መልካም ወሬ ነው፡፡

ነፃ ህክምና ያገኛሉ ተብሏል፡፡

ወንድሙ ኃይሉ

#Ethiopia #ShegerWerewoch #የልብ_ሕሙማን #ሕፃናት #ነፃ_ህክምና

ሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
https://bit.ly/33KMCqz


Healing Valves Ethiopia (HVE) is a locally registered Ethiopian resident charity, registered at the Federal Democratic Republic of Ethiopia Agency for Civil Society Organizations with a registration number 5181. Healing Valves Ethiopia works to provide support for pediatric Rheumatic Heart Disease patients throughout the country.

ሂሊንግ ቫልቭስ ኢትዮጵያ ሃገር በቀል የእርዳታ ድርጅት ሲሆን፣ በኢትዮጵያ ፌደራላዊ ሪፐብሊክ የሲቪክ ማህበረሰብ ድርጅቶች ኤጀንሲ በምዝገባ ቁጥር 5181 ህጋዊ ሰውነት አለው፡፡ ሂሊንግ ቫልቭስ ኢትዮጵያ በሃገር አቀፍ ደረጃ በሬማቲክ ሃርት ዲዝዝ (Rheumatic Heart Disease) የተጠቁ ህፃናትን (እድሜያቸው ከ18 ዓመት በታች የሆኑ) የሚረዳ ድርጅት ነው፡፡ በዚህም መሰረት በRheumatic heart disease የተጠቁ በከፍተኛ ድህነት ውስጥ ያሉ እና አፋጣኝ የልብ ቀዶ ጥገና የሚያስፈልጋቸውን ታዳጊዋችን ለመርዳት ያለም ድርጅት ነው:: ድርጅታችንም በአመት የ50 ህይወት አድን የልብ ቀዶ ጥገና በበጎ አድራጊ የአገር ቤት እውቀት ለመስራት የተነሳ ሲሆን እስካሁንም ለ8 ትዳጊዋች የህይወት አድን ቀዶ ጥገና መስራት ችሏል::


Dear friends, as the truth in the cliche “ a trouble shared is a trouble halved” and I want to reach out to you in order to make you the member of HVE support group. HVE is doing a life saving open-heart surgery for destitute pediatric age groups (


Dear friends and family of Healing Valves Ethiopia (HVE), Yesterday HVE volunteer team successfully performed a life saving open-heart surgery for a 12 years old boy from South Wolo, a village called Wegid. Because of his heart failure, He was unable to play with his friends and couldn’t go to school. He was just waiting for his death until he suddenly came to HVE. Salhadin is now in good condition, recovering well,separated from ventilator machine and breathing by his own. We all wish a fast and smooth recovery to this young boy.
Thank you all!




የ17 አመቱ የግንደበረት ነዋሪ 7ኛው የHVE ነፃ የልብ ቀዶ ተጠቃሚ ሆነ:: በከፍተኞ የልብ ድካም ውስጥ የነበረው ታዳጊ ከሞት አፋፍ ላይ የነበረ ሲሆን በሀገር በቀል በጎ አድራጎት ድርጅት በሆነው HVE እና የነፃ በጎ አገልጋይ የሀገራችን ልጆች በሁለት የልብ በሮች ላይ የተሳካ ቀዶ ጥገና ተከናወነለት:: በዛሬው እለት (እሁድ) የቤተሰባቸውን ጊዜና ደስታ የሰውት እነዚህ የበጎ ፈቃደኞ አገልጋዮች በተሳተፋበት 5 ሰአት በፈጀ የልብ ቀዶ ጥገና ላይ እጅግ አስጨናቂና አስፈሪ በሆነ ሁኔታ ውስጥ ለሰባተኛ ጊዜ የቁርጥ ቀን ልጆች መሆናቸውን አሳይተዋል:: ክብርና ምስጋና ለአገር በቀል የልብ ቀዶ ጥገና ቡድን:: በአሜሪካ የHVE እህት ድርጅት ለምታደርጉት ያልተቋረጠ እርዳታ በታካሚ ቤተሰቦች ስም ከልብ የመነጨ ምስጋናችን ይድረሳቹህ::

Today healing valves Ethiopia (HVE) performed the 7th life saving open-heart surgery for a 17 years old boy from Gindeberet. In post RHD severe mitral valve stenosis and severe tricuspid regurgitation with recurrent heart failure, the young boy successfully underwent mitral valve replacement plus tricuspid valve repair. A volunteer local team member of HVE put aside family and personal joy and spent the precious Sunday on saving a life for free. We salute the local volunteer team and respect to your commendable performances. We are always grateful to our sister company in US to make this true by supporting financially.




🕌እንኳን ለ1442ኛው የኢድ አል አድሃ አረፋ በአል በሰላም አደረሳችሁ✨
መልካም በዓል!




#WeLostALegend

20 ta oxirgi post ko‘rsatilgan.

1 064

obunachilar
Kanal statistikasi