ድመት ድመት መሆኗን ዘንግተህ እንደ በግ treat ልታደርጋት ብትሞክር ፊትህ ላይ ዳማ ትሰራልሃለች፡፡ በጉንም እንደ ድመት ልታጫውተው ከሞከርክ በቴስታ ብሎ ሰማይ ምድሩን ያዞርብሃል፡፡ ከሰዎች ጋር ያለህ ግንኙነት ጥሩ እንዲሆን የምትፈልግ ከሆነ ሰዎችን ዕወቃቸው ባህሪያቸውንና አመለካከታቸውንም አጥና ፡፡
ህይወት ሰፊ ነች አጋጣሚዎቿም ብዙ ናቸውና የተለያየ ዐይነት ባህሪ ካላቸው ሰዎች ጋር ልታገናኝህ ፣ ልታዛምድህና ልታቆራኝህ ትችላለ ፡፡ አንዳንዱ በባህሪው ግትር ፣ ቁጡ ፣ ነጭናጫ ፣ ጭምት ፣ አዝግ ፣ ተንኮለኛ ፣ አልማጭ ፣ ራስ ወዳድ ፣ ጉረኛ ፣ ትዕቢተኛ ፣ ገለልተኛ ፣ ስግብግብ ፣ ሴሰኛ ፣ ፣ ጨካኝ ፣ ሴረኛ ፣ እኔ ብቻ ልደመጥ ባይ ፣ እኔ ብቻ ቆንጆ ነኝ ባይ ሊሆን ይችላል ፡፡ ሌላው ደግሞ በተቃራኒው አዛኝ ፣ ተጫዋች ፣ ትሁት ፣ ለሰው ሟች ፣ ቁጥብ ፣ ተናናሽ ፣ ፣ ለስላሳ ፣ ተግባቢ ሊሆን ይችላል ፡፡ ለሁሉም በሽተኛ ተመሳሳይ መድሃኒት እንደማይሰጠው ሁሉ የተለያየ ባህሪ ላላቸው ሰዎችም ተመሳሳይ approachን ማንፀባረቅ ተገቢ አይሆንም ፡፡
ምን አልባት ሁሌም ትሁት እና ለስላሳ መሆን ላያዋጣ ይችላል ፡፡ አንዴ ምን ሆነ መሰላችሁ , የሆነ ጓደኛዬ ወደ መስጂድ ለመሄድ ከቤቱ ወጥቶ መንገድ ጀመረ ፡፡ ውስጥ ለውስጥ እየተጓዘ ሳለም የሆነ ዕብድ ቋጥኝ የሚያህል ድንጋይ ይዞ በሚያስፈራ አካኋን ወደሱ አቅጣጫ እየተግተለተለ ሲመጣ ተመለከተ ፡፡ ፈርቶ ወደኋላ ቢሮጥ ዕብዱ የያዘውን ድንጋይ ሊወረውርበት ይችላል ፡፡ ብልጡ ጓጀኛዬ ፈጠን ብሎ እሱም ዕብዱ የያዘውን የሚያስንቅ ኪሊማንጃሮ የሚያህል ዐለት ተሸከመና ወደ ዕብዱ አቅጣጫ በፍጥነት መራመድ ጀመረ ፡፡ ወዲያውም ዕብዱ ፊቱን አዙሮ በመጣበት ነካው ፡፡ 💪😎
አንዳንዴ እንዲህም ይሰራል ( ሞክራችሁት ብትፈነከቱ እኔ የለሁበትም 😁 )
ያ ማለት ግን አፀያፊ ስድቦችን የሰደባችሁን ስደቡ
ያዋረዳችሁንም አዋርዱ ማለት አይደለም ፡፡ ለአንዳንዶች ከመልስ ይልቅ ዝምታ ከመብረቅ የበለጠ የሚጮህ አስደንጋጭ መልስ ይሆናል ፡፡
©