የጉዞ ማስታወሻ
~
በቅርቡ ለሳምንት ያክል በአንድ የአፍሪካ ሃገር ውስጥ ቆይታ አድርጌ ነበር። ጉብኝቱ ላይ የተገኘሁት በአንድ በሙስሊሞች ዙሪያ ሰፋፊ ኸይር ስራዎችን በመስራት ላይ በተሰማራ ወዳጅ ያላሰብኩት ግብዣ ተደርጎልኝ ነው። በቆይታዬ ላይ እንዲሁ ትኩረቴን የሳቡኝን ነገሮች ማንሳት ወደድኩኝ።
1- ኢስላምን ለማስፋፋት፣ ሙስሊሞችን ለማገዝ ሃብታቸውን በማፍሰስ፣ ከሃገርና ከቤተሰብ ርቀው ደፋ ቀና የሚሉ 0ረቦችን ተመልክቻለሁ። ከኛ ጋር የማይቀራረብ ምቾት የለመዱ ከመሆናቸው ጋር ሁለ ነገራቸውን ጥለው ለዲን መስዋእትነት ሲከፍሉ ሳይ የኛ ስንፍና ፍንትው ብሎ ነው የታየኝ። እኛኮ በገዛ ሃገራችን ውስጥ በየገጠሩ እየወጣን የረባ እንቅስቃሴ አናደርግም። ባለንበት ከተማ ውስጥ እንኳ የረባ ትጋት የለንም። እኛኮ አላህ ከሰጠን ሃብት ለደዕዋ የምንዘረጋው እዚህ ግባ የሚባል አይደለም። እኛኮ ከስራችን እንቅፋታችን ይበዛል።
2- ሌላው የገረመኝ ነገር በሃገሪቱ ውስጥ በረጅም ዘመናት ኢስላምን ረስተው ከነጭራሹ ሃይማኖት አልባ የሆኑ ህዝቦች መኖራቸውን መስማቴ ነው። ይሄ አስደንጋጭ ነገር ነው። ወደኛ ተመልሼ ሳስብ ተቀራራቢ እውነታዎች እንዳሉ ነው የገባኝ። ሰሜን ሸዋ ላይ በርካታ ዐረብኛ ፅሁፍ የተተከለባቸው መቃብሮች አሉ። የጥንት አርጎባዎች መቃብር ናቸው። ዛሬ አካባቢው ኦርቶዶክስ ነው። ሃዲያዎች በአብዛኛው ወደ ጴን .ጤነት ተቀይረዋል። ደቡብ ጎንደር ላይ እምነት አልባ የሆኑት አውራ አምባዎች የእስልምና ታሪካቸው የሩቅ አይደለም። እነዚህ የለየላቸው ክስተቶች ናቸው። በደርግ የሶሻሊዝም ፋሽን ከኢስላም የራቁት ቀላል አይደሉም። ዛሬም በየ ገጠሩ እጅግ ብዙ ወገናችን ሙስሊም ነው ለማለት በሚከብድ ሁኔታ ላይ ነው ያለው። አጥብቀን ካልሰራን ብዙ የባሱ ነገሮች ይከሰታሉ።
3- የኛ ሃገር ሙስሊም ተጨባጭ ከብዙ ሃገራት አንፃር ሲታይ ከነ እንከኑ የተሻለ እንደሆነ ያለኝን ግምት አሁንም ከፍ አድርጌያለሁ። በጀማዐ ሶላት ታዳሚ ብዛት፣ በሴቶች አለባበስ፣ በወጣቱ ዲናዊ ንቅናቄ፣ ... ሌላው ቀርቶ ከብዙ የዐረብ ሃገራት ሳይቀር የተሻለ ነው። ይሄ አላህን ልናመሰግንበት የሚገባ ነው። ቀጥሎም ለዚህ ለውጥ አሻራቸውን ያሳረፉ መሻይኾች፣ ዱዓቶች ለኢትዮጵያ ሙስሊም ባለ ውለታ ናቸው።
4- በሄድኩበት ሃገር ሌላው ያስተዋልኩት የደዕዋውን እንቅስቃሴ የሚመሩት እንዳለ የመዲና ኢስላማዊ ዩኒቨርሲቲ ምሩቆች ናቸው። ይሄ የዚህን ትልቅ ተቋም ትልቅ አበርክቶ የሚያሳይ ነው። በኛ ሃገር ደዕዋ ላይም የመዲና ኢስላማዊ ዩኒቨርሲቲ ጥሩ አስተዋጽኦ አለው። ይሁን እንጂ ደዕዋው ላይ ካሉት ይልቅ ለአመታት ሲማሩ ቆይተው ባክነው የሚቀሩት ይበዛሉ።
5- ሌላው የጃሚ0 ትምህርት በቂ የዒልም ትጥቅ እንደማያስታጥቅ ነው ከብዙዎች አቅም የተረዳሁት። ከሃገር ውጭ ትምህርት ላይ ያላችሁ ወገኖች በግል እየጣራችሁ ራሳችሁን በሚገባ እንድታበቁ አደራ እላለሁ። ካልሆነ ግን የማይጠቅም ስምና ጉራ ነው የሚተርፋችሁ።
6- ሌላኛው በሄድኩበት ሃገር ያየሁት ሙስሊሞች ሰፊ ነፃነት ያላቸው መሆኑ ነው። ከመንግስት በኩል ጫና የለባቸውም። ዐረቦች በነፃነት ሙስሊሞችን ያገለግላሉ። በሙስሊሞች ለሙስሊሞች የተገነቡ የወንዶች ትምህርት ቤቶች፣ የሴቶች ትምህርት ቤቶች፣ የአይታም ማዕከላት፣ ሌሎችም ተቋማት ውስጥ መስጂዶች አሉ። የመንግስት ኃላፊዎች ባሉበት ምረቃ ላይ ቁርኣን ሲቀራ፣ አዛን ሲደረግ የጎሪጥ የተመለከተው አካል የለም። እኛ ጋር ያለውን ክፋት ርቀቱን አሰብኩኝ።
7- የሃገሪቱ ሙስሊሞች በቁጥራቸውም፣ በዲንም ይሁን በአካደሚ በተማረ የሰው ሃይላቸውም፣ በኢኮኖሚያቸውም፣ በመንግስት መዋቅር ውስጥ ባላቸው ተሳትፎም በጣም ከኛ ያነሱ ናቸው። ከእኛ ባነሰ አቅም ላይ ሆነው ተፍ ተፍ ሲሉ ሳያቸው ግን እኛ አቅማችንን እንደሚገባ እንዳልተጠቀምን ነው የተሰማኝ።
8- ሌላው የደነቀኝ ነገር ሌሎች ህዝቦችን ወደ ኢስላም መጣራት በጣም ቀላል መሆኑ ነው። አንድ ሰው ጎዳና ላይ ደዕዋ ቢያደርግ ብዙ ሰው ሊሰልም ይችላል። ቋሚ ክትትል ካልተደረገ ግን በሌላ ጊዜ ቢመለስ እነዚያን ሰዎች ኢስላም ውስጥ አናገኛቸውም። በቀላል እንደገቡ በቀላል ይወጣሉ፡፡ ሰፊ ስራ ለመስራት ደግሞ የአቅምም፣ የሰው ሃይልም ውስንነት አለ። በኛም ሃገር ተጨባጭ ተግቶ የሚሰራ ጠፍቶ እንጂ በአንዳንድ አካባቢዎች ሰዎችን ማስለም ከባድ ነገር አይመስለኝም።
9- በሄድኩበት ሃገር ፈርጣማ የኢኮኖሚ አቅም ያላቸው ነገር ግን በጣም አነስተኛ ቁጥር ያላቸው ሺ0ዎች አሉ። ደግነቱ ሌሎች ሃገራት ላይ እንደሚታየው ወደ ቡድናቸው የመጣራት ተነሳሽነት የላቸውም። መስጂዳቸው ጭር ያለ ነው። ከህዝቡ እጅግ ዝቅተኛ የኑሮ ሁኔታና ሰፊ መሀይምነት አንፃር ሲታይ ጠንከር ያለ ስብከት ቢኖራቸው አደጋቸው ከባድ ነበር። በነገራችን ላይ ቁጥራቸው እዚህ ግባ የሚባል ባይሆንም ሃገራችን ውስጥ በኢራን ኤምባሲ ድጋፍ በህቡእ የሚንቀሳቀሱ ሺዐዎች አሉ።
10- ሌላው የድርጅቶችን አስፈላጊነት በሚገባ አይቻለሁ። ለሙስሊሙ ህዝብ ድጋፍ እያደረጉ ያሉት ዐረቦች በድርጅት የሚንቀሳቀሱ ናቸው። ያለ ህጋዊ ተቋም (ጀምዒያህ) ምንም አይነት የበጎ አድራጎት ስራዎችን መስራት እንደማይችሉ ሲናገሩ ሰምቻለሁ። በህቡእ ለሚንቀሳቀሱ አካላት የሚሄዱ ገንዘቦችን ለመቆጣጠር ሲሉ መንግስታት የፋይናንስ ፍሰቶችን በጥብቅ ይቆጣጠራሉ። እነዚህ የበጎ አድራጎት ድርጅቶች በርከት ያሉ ትምህርት ቤቶችን፣ መስጂዶችን፣ የጤና ተቋማትን፣ የህክምናና የሙያ ማሰልጠኛዎችን፣ የአይታም ማዕከሎችን በአፍሪካ፣ በአውሮፓ፣ በአውስትራሊያ፣ በኤሺያ፣ በአሜሪካ አቋቁመዋል። የመጠጥ ውሃ ጉድጓዶችን ይቆፍራሉ። ሰፋፊ እርዳታዎችን ያከፋፍላሉ። እነዚህን ስራዎች የሚሰሩት በሚሄዱበት ሃገር ከተከፈቱ ህጋዊ ድርጅቶች ጋር በመተባበር ነው።
=
© IbnuMunewor