Postlar filtri


ሚያዝያ 11ቀን 2016 ዓ.ም

ለውድ የጆርጎ አካዳሚ ት/ቤት ወላጆች

በቀን 9/8/2016 ዓ.ም በላክነው መልዕክት መሠረት የወላጆች ስልጠና መኖሩን አሳውቀናል።

በመሆኑም ስልጠናው ጠቃሚ መሆኑን አውቃችሁ ነገ ቅዳሜ 12/08/2016 በ2:30 ተገኝታችሁ የስልጠናው ተሳታፊ እንድትሆኑ በድጋሚ ለማስታወስ እንወዳለን።

ማሳሰቢያ:-
ስልጠናው የሚከናወነው ከጠዋቱ 2፡30  እስከ 7:00 ነው።
                                       ጆርጎ አካዳሚ


ሚያዝያ 9ቀን 2016 ዓ.ም

ለውድ የጆርጎ አካዳሚ ት/ቤት ወላጆች

በ21/7/2016ዓ.ም በነበረን ስብሰባ ባሳወቅነው መሠረት ለሶስት ዙር ለተማሪዎች ስልጠና ሰጥተን አጠናቀናል።ለወላጆችም ስልጠናውን መስጠት አስፈላጊ ሆኖ አግኝተነዋል።

በመሆኑም:-
ወላጆች ከልጆቻቸው ጋር ያላቸው ግንኙነት ምን መምሰል አለበት በሚል ርዕስ በሀገር አቀፍ ደረጃ ዕውቅና ባላቸው በእንዴ ኮሙኒኬሽን ኮንሰልታነሲ ካውንስሊንግ አገልግሎት በቀን 12/8/2016ዓ.ም ስልጠናውን ለመስጠት ዝግጅቱን ስለጨረሰ በተጠቀሰው ቀን እና ሰአት ተገኝታችሁ ስልጠናውን እንድትካፈሉ ስንል እንጠይቃለን።

ማሳሰቢያ:-
ስልጠናው የሚከናወነው ከጠዋቱ 2፡30  እስከ 7:00 ነው።
                                       ጆርጎ አካዳሚ


ውድ ወላጆቻችን

ለሁሉም የእስልምና እምነት ተከታዮች

እንኳን ለዒድ አል-ፊጥር በዓል በሰላም አደረሰዎ!

በዓሉ የሠላም፣ የደስታ፣ የፍቅርና የመተሳሰብ እንዲሆንልዎ ከልብ እንመኛለን!

ዒድ ሙባረ

ጆርጎ አካዳሚ ት/ቤት


መጋቢት 17 ቀን 2016 ዓ.ም

ለውድ የጆርጎ አካዳሚ ወላጆች/አሳዳጊዎች
ቢሾፍቱ

ጉዳዩ ፡- የወላጆች/አሳዳጊዎች አጠቃላይ የስብሰባ ጥሪ

የጆርጎ አካዳሚ ት/ቤት አጠቃላይ የወላጆች/አሳዳጊዎች ስብሰባ የፊታችን ቅዳሜ መጋቢት 21ቀን 2016 ዓ.ም ከጠዋቱ 2፡30 ሰዓት ጀምሮ ይካሄዳል፡፡

ስለሆነም በዕለቱ በት/ቤት ቅጥር ግቢ ውስጥ እንዲገኙና በስብሰባው ላይ እንዲሳተፉ  በአክብሮት እናሳውቃለን፡፡

በሰዓቱ ጀምረን እንድናጠናቅቅ በሰዓቱ እንዲገኙልን ከአደራ ጭምር እናሳስባለን፡፡

ጆርጎ አካዳሚ ት/ቤት


የካቲት 22 ቀን 2016 ዓ.ም

ለውድ የጆርጎ አካዳሚ ት/ቤት ወላጆች

ረቡዕ የካቲት 20 ቀን 2016 ዓ.ም በላክንላችሁ ደብዳቤ መሠረት የአመቱን ሁለተኛው የወላጅ ከመምህር የ15 ደቂቃ የገፅለገፅ ውይይት ነገ ቀዳሚ 23/06 /2016 ዓ/ም እንደሚደረግ ገልፀናል።

በመሆኑም ከቀኑ   2:00 -6:00 ባለው ጊዜ ውስጥ መጥጣችሁ ስለ ልጆቻችን እንድንነጋገር በድጋሚ እናስታውሳለን።

ለልጆ ቅድማያ ስለሚሰጡ እናመሠግናሐን።

ጆርጎ አካዳሚ


01/06/2016 ዓ.ም

ለውድ የጆርጎ አካዳሚ ት/ቤት ወላጆች

የሁለተኛ መንፈቅ አመት ትምህርት ሰኞ 04/06/2016 ዓ.ም እንደሚጀምር አሳውቀን ነበር ።

ነገር ግን ከሰኞ 04/06/2016 ጀምሮ በቢሾፍቱ ከተማ ትምህርት ፅህፈት ቤት የተዘጋጀ ለመምህራን እና ለትምህርት አመራሮች ስልጠና እንደሚሰጥ አሳውቀውና።

በመሆኑም የሁለተኛ መንፈፈቅ አመት መደበኛ ትምህር የሚጀምረው ሰኞ 11/06/2016 ዓ.ም መሆኑን ማሳወቅ እንወዳለን።


ጆርጎ አካዳሚ


09/05/2016 ዓ.ም

ለውድ የጆርጎ አካዳሚ ት/ቤት ወላጆች

ነገ  ጥር 10 ቀን 2016 ዓ.ም በዐሉን ምክንያት በማድረግ መንገድ ስለሚዘጋጋ የመማር ማስተማር ሂደቱ እስከ አምስት ሰዓት (5:00) ነው።

ስለዚህ ወላጆች መንገድ ከመዘጋጋቱ በፊት ተማሪዎችን እንድትወስድ እናሳስባለን።

ጆርጎ አካዳሚ


ጥር 7 ቀን 2016 ዓ.ም

ለውድ የጆርጎ አካዳሚ ት/ቤት ወላጆች፤

የተማሪዎች ወርሀዊ ክፍያ ወር በገባ ከ25-30 መከናወን እንዳለበት ይታወቃል ።

በመሆኑም ክፍያ ያልፈጸማችሁ ወላጆች ቅጣት ወስጥ ከመግባቱ አስቀድሞ ክፍያችሁን እንድትፈጽሙ በተደጋጋሚ እያሳወቅን እንገኛለን ።

ነገር ግን ችላ ብላችሁ ክፍያችሁን በአግባቡ እየፈጸማችሁ ያልሆናችሁ ወላጆች አላችሁ።

በዚህ ምክንያት ክፍያቸውን በአግባቡ ያልፈጸሙ ተማሪዎችን እስከ ሀሙስ 9/05/2016 ዓ.ም ከፍያችሁን ካልፈጸማችሁ አርብ 10/05/2016 ዓ.ም ለተማሪዎች በአካል ደብዳቤ ለመስጠት ስለምንገደድ ይህ  ከመሆኑ በፊት ክፍያተችሁን እድታጠናቅቁ አጥብቀን እናሳስባለን።

ወቅቱን ጠብቃችሁ እየከፈላችሁ ላላችሁ ወላጆች ምስጋናችን የላቀ ነው።


ጆርጎ አካዳሚ


ታህሳስ 25 ቀን 2016 ዓ.ም

ለውድ የጆርጎ አካዳሚ ት/ቤት ወላጆች

ነገ ታህሳስ 26/ቀን 2016 ዓ.ም የአመቱን የልጆች የደስታ ቀን የምናከብ መሆኑን እያስታወስን ሁሉም ተማሪዎች የተለያዩ ባህላዊም ሆነ የግል ልብሳቸውን ለብሰው መምጣት ይችላሉ።

መርሃግብሩ የሚጠናቀቀው ከቀኑ በ6:00 ስለሆነ  ወላጆች በሰዓት  ተገኝታችሁ ተማሪዎችን እድትወስዱ።

ማሳሰብያ:- ሰኞ 29/04/2016 እና ማክሰኞ 30/04/2016 የተማሪዎች የእረፍት ጊዜ ነው።

ረቡዕ 1/05/2016 ዓ.ም መደበኛ ትምህርት ይጀምራል።

ጆርጎ አካዳሚ


ታህሳስ 5 ቀን 2016 ዓ.ም

ለውድ የጆርጎ አካዳሚ ት/ቤት ወላጆች፤

የተማሪዎች ወርሀዊ ክፍያ ወር በገባ ከ25-30 መከናወን እንዳለበት ይታወቃል ።

በመሆኑም ክፍያ ያልፈጸማችሁ ወላጆች ቅጣት ወስጥ ከመግባቱ አስቀድሞ ክፍያችሁን እንድትፈጽሙ በተደጋጋሚ አሳውቀናን ።

ነገር ግን ችላ ብላችሁ ክፍያችሁን በአግባቡ እየፈጸማችሁ ያልሆናችሁ ወላጆች አላችሁ።

በዚህ ምክንያት ክፍያቸውን በአግባቡ ያልፈጸሙ ተማሪዎችን በአካል ደብዳቤ ለመስጠት ስላሰብን ይህ ከመሆኑ በፊት ክፍያተችሁን እድታጠናቅቁ አጥብቀን እናሳስባለን።

ወቅቱን ጠብቃችሁ እየከፈላችሁ ላላችሁ ወላጆች ምስጋናችን የላቀ ነው።


ጆርጎ አካዳሚ


24/03/2016

ለውድ ወላጆች በሙሉ

ከወረዳው ትምህርት ቢሮ በደረሰን አስቸኳይ መልዕክት መሠረት በነገው ዕለት መምህራን ስልጠና ስላላቸው ትምህር አይኖርም።

ፈተናው ወደ ረቡዕ 26/03/2016 ዓ.ም ተዘዋውሯል ።

ጆርጎ አካዳሚ




ህዳር 20  ቀን 2016 ዓ.ም

ለውድ የጆርጎ አካዳሚ ት/ቤት ወላጆች፤

የተማሪዎች ወርሀዊ ክፍያ ወር በገባ ከ25-30 መከናወን እንዳለበት ይታወቃል ።

በመሆኑም ክፍያ ያልፈጸማችሁ ወላጆች ቅጣት ወስጥ ከመግባቱ አስቀድሞ ክፍያችሁን እንድትፈጽሙ በተደጋጋሚ አሳውቀናን ።

ነገር ግን ችላ ብላችሁ ክፍያችሁን በአግባቡ እየፈጸማችሁ ያልሆናችሁ ወላጆች አላችሁ። በዚህ ምክንያት ክፍያቸውን በአግባቡ ያልፈጸሙ ተማሪዎችን ሰኞ ህዳር 24/2016 ዓ.ም  በሚጀምረው አጋማሽ ፈተና ላይ ላለማስቀመጥ እንገደዳለን።ስለዚህ ቀድማችሁ ክፍያችሁን እድታጠናቅቁ ከወዲሁ እናሳስባለን።

ወቅቱን ጠብቃችሁ እየከፈላችሁ ላላችሁ ወላጆች ምስጋናችን የላቀ ነው።


ጆርጎ አካዳሚ


Workalem B dan repost


በሀገር አቀፍ የሂሳብ ውድድር ላይ አሸናፊ ሆነው ለተመለሱ ተማሪዎቻችን የእውቅና መስጠት መርሃ ግብር ተከናውኗል።


ጥቅምት 5 ቀን 2016 ዓ.ም

ለውድ የጆርጎ አካዳሚ ት/ቤት ወላጆች፤

የተማሪዎች የጥቅምት ወር ወርሀዊ ክፍያ ከመስከረም 25-30 መሆኑ ይታወቃል ።

በመሆኑም ክፍያ ያልፈጸማችሁ ወላጆች ቅጣት ወስጥ ከመግባቱ አስቀድሞ ክፍያችሁን እንድትፈጽሙ አበክረን እናሳስባለን ።

ወቅቱን ጠብቃችሁ እየከፈላችሁ ላላችሁ ወላጆች እናመሰግናለን።


ጆርጎ አካዳሚ


መስከረም 28 ቀን 2016 ዓ.ም

ለውድ የጆርጎ አካዳሚ ት/ቤት ወላጆች፤

የተማሪዎች የጥቅምት ወር ወርሀዊ ክፍያ ከመስከረም 25-30 መሆኑ ይታወቃል ።

በመሆኑም ክፍያ ያልፈጸማችሁ ወላጆች ቅጣት ወስጥ ከመግባቱ አስቀድሞ ክፍያችሁን እንድትፈጽሙ አበክረን እናሳስባለን ።

ወቅቱን ጠብቃችሁ እየከፈላችሁ ላላችሁ ወላጆች እናመሰግናለን።


ጆርጎ አካዳሚ




ለ2016 ዓ.ም  የትምህርት ዘመን እንኳን  አደረሰን።

የ2016ዓ.ም መደበኛ ትምህርት መስከረም 21/2016 ዓ.ም እንደሚጀምር ይታወቃል።

ስለሆነም ሁሉም ተማሪዎች አስፈላጊውን ዝግጅት በማድረግ በተጠቀሰው ቀን ትምህርት ቤት እንዲመጡ ስንል በደስታ እናሳስባለን ፤የነርሰሪ ተማሪዎች ከሰኞ መስከረም 21 እስከ አርብ መስከረም 25 በትምህርት ቤት ውስጥ የሚቆዩት እስከ 6:00(ግማሽ ቀን)ነው።
     ማሳሰቢያ
1. የተማሪዎች ምሳ ዕቃ ላይ ስማቸው በማይለቅ    ነገር ይፃፍ።
2. የመማሪያ ቁሳቁስ ያላስረከባቹ ወላጆች ሰኞ 7:00 ነው የምንረከበው።

ጆርጓ አካዳሚ


የ2ኛ ፣4ኛ እና 6ኛ ክፍል መጽሐፍ አዲስ ስርዓተ ትምህርት ስለሆነ ለጊዜው አልደረሰልንም እና ሲደርስ የምናሳውቅ ይሆናል።

20 ta oxirgi post ko‘rsatilgan.