ምዕራፍ 3 የደዕዋ ግልፅ መውጣት
ክፍል 17 ሙርሊሞቹን ማሰቃየት
ሙስሊሞችን መቅጣትና ማሰቃየት በሚዘገንን ሁኔታ ቀጠለበት።
፨ቢላል ቢን ረባህ(ረ አ)የኡመያ ቢን ኸለፍ አልጁመሒ ባሪያ ነበረ። ኡመያ ቢላልን አንገቱ ላይ ገመድ በማድረግ ለልጆች ይሰጧቸዋል ልጆች እየጎተቱ ይጫወቱበቴል። እሱግን "አሐድ አሐድ " ይል ነበር። በእኩለቀን በጠራራ ፀሀይ ይዞት ይወጣና በጣም የሚያቃጥል ድንጋይ ወይም አሸዋ ላይ በጀርባው ያስተኛዋል። ከዚዬም በጣም ትልቅ ድንጋይ አስመጥቶ በደረቱላይ ያስቀምጣል። ከዚያም እንድህ ይለዋል። እስከምትሞት ድረስ ወይም በሙሐመድ ክደህ (ከፍረህ)አል-ላትና አል-ዑዛን እስከምትገዛ ድረስ በዚህ ሁኔታ ትቆያለህ ይለዋል። እሱ ግን "አሐድ አሐድ" (አንዱ አምላክ አንዱ አምላክ )ይል ነበር።
፨ከእለታት አንድ ቀን እንደዚሁ ሲያሰቃዩት አቡበክር (ረ.ዐ) በአጠገቡ አለፉና ገዝተውት ከባርነት አወጡት።
፨ዐሚር ቢን ፉሃይራ ራሱን እስኪስትና የሚናገረውንም ማወቅ እስኪሳነው ድረስ ይሰቃይና ይቀጣ ነበር።
፨አቡፉከይሃም ተሰቃየ።ስሙ አፍለህ ይባላል። ከአዝድ ጎሳ ነው ተብሏል። የበኒ ዐብድዳር ባሪያ ነበር። በሀይለኛ ሙቀት በእኩለቀን ላይ እግሩን በብረት አስረውት ራቁቱን አስወጥተውት በሆዱ በቃጠሎ አሸዋ ላይ ዬስተኙታል። ከዚያም መንቀሳቀስ እንዳይችል ትልቅ ድንጋይ ከጀርባውላይ ያደርጋሉ። ራሱን እስኪስት ድረስ በዚህ ሁኔታ ይቆያል። በሁለተኛው ሂጅራ (ስደት)ወደ ሃበሻ እስከተሰደደበት ጊዜ ድረስ በዚህ መልኩ ሲሰቃይ ቆየ። አንድ ጊዜ ሁለት እግሮቹን በገመድ በማሰር ጎትተውት በአሸዋ ላይ ጣሉት። ከዚያም ሙቷል ብለው እስኪጠረጥሩ ድረስ አነቁት። አቡበክር በዚህ ሁኔታ ሲያዩት ገዙትና ነፃ አወጡት።
፨ኸባብ ቢን አል አረት በጃሂልያ ዘመን ከተማረኩት ሰዎች አንዱ ነበር። ኡሙ አንማር ቢንት ሲባዕ አል ኹዘዒያ ገዛችው። ቀጥቃጭ ነበር። እሱ ሙስሊም ሲሆን አሳዳሪው እሙ ዐንማር በእሳት አሰቃየችው። በሙሀመድ(ﷺ) እንዲከፍር በእሳት በቀላ ብረት ጀርባውን ትጣብሰው ነበር ።ይህም ቢሆን ኢማንንና ለአላህ እጅ መስጠትን እንጂ ሌላ አልጨመረለትም ።ሌሎች ሙሽሪኮችም አንገቱን እየጠመዘዙ ጸጉርን እየነጩ በተደጋጋሚ በተቀጣጠለ ከሰል ላይ እየወረወሩት ያሰቃዩት ነበር። ከዛ በጣም ከባድ ድንጋይ በደረቱ ላይ ሲያስቀምጡበት መነሳት ያቅተዋል።
፨ ዘኒራ ሮማዊ ባሪያ ነበረች። ሰለመች። ለአላህ ስትል ተሰቃየች ።አይዋንም ታማ ታወረች ።አል ላትና አል ዑዛ ናቸው አይንሽን ያሳወሩሽ ተባለች ።በፍጹም አላህ እንጂ እነሱ አይደሉም ከፈለገ ይከፍትልኛል አለች። በ በማግስቱ ጧት አላህ አይኗን መለሰላት።ይህ ከመሐመድ ድግምቶች አንዱ ነው አሉ።
፨ ኡሙ ዑበይስ ሰለመች። የበኒ ዙህራ ባሪያ ነበረች ።ጌታዋ አል አስድ ቢን አብድ የጉስ ያሰቃያት ነበረ።ከአላሆ መልክተኛ (ﷺ)ቀንደኛ ጠላቶችና በሳቸው ከሚሳለቁት ሰዎች አንዱ ነበር።
፨ ከበኒ አዲይ የአምር ቢን ሙአምሚል ባሪያ (ጃሪየቱ አምር ቢን ሙአምሚል ሰለመች። ኡመር ቢን አልኸጣብ በዚያን ጊዜ ስላልሰለሙ የመሰቃዯት ነበር።እስከሚደክማቸው ድረስ ይደበድቧትና ይተዋታል።ከዛያም ስለ ሰለቸኝ እንጂ አልተውሽም ነበር ይሏታል።እኔን እንደቀጣሃኝ አላህ ይቀጣሃል ትላቸው ነበር።
፨ሰልመው ከተሰቃዩት ሴት ባሪያዎች ናህዲያና ሴት ልጅዋ ይጠቀሳሉ።የአንዲት የበኒ አብድዳር ሴት ወይዘሮ ነበሩ። አቡበክር(ረ.ዐ)ኣሚር ቢን ፉሃይራንና አቡ ፋከይሃን ገዝተው ከባርነት እንዳወጧቸው ሁሉ እነዚህንም ሴት ባሮች ገዝተው ከባርነት ነፃ አወጧቸው።አባታቸው አቡ ቁሃፋ አቢበክርን ደካሞች ባሮችን ነፃ ታወጣቸዋለህ። ጠንካራ ጠንካራ ወንዶች ባሮቾን ነፃ ብታወጣ ይከላከሉልሃል፣ይረዱሃል፣እያሉ ይወቅሷቸውነበር። መልሳቸውግን እኔ የአላህነረ ውደታ ነው የምፈልገው ነበር።አላህ(ሱ.ወ)አቡበክርን...........ይቀጥላል
https://t.me/Menhaj_Asselefiya