🇪🇹 አገለለች
ኢትዮጵያ በበጀት ዕጥረት እራሷን ከውድድሩ አገለለች !
የኢትዮጵያ ከ17 አመት በታች ብሔራዊ ቡድን በዩጋንዳ አዘጋጅነት ከሚካሄደው የሴካፋ ዞን የማጣሪያ ውድድር በበጀት እጥረት ምክንያት ራሷን ማግለሏን እግር ኳስ ፌዴሬሽኑ አስታውቋል፡፡
ባሳለፍነው ወር ላይ የኢትዮጵያ ከ17 አመት በታች ብሔራዊ ቡድን የአፍሪካ ዋንጫ ሴካፋ ዞን ማጣሪያ የምድብ ተጋጣሚዎቿን ማወቋ ይታወሳል፡፡
በዚህም ብሔራዊ ቡድኑ በምድብ አንድ ከዩጋንዳ ፣ ታንዛኒያ እና ቡሩንዲ ጋር ተድልድሎ የማጣሪያ ውድድሩን በዩጋንዳ አዘጋጅነት
* ከታህሳስ 5 እስከ
* ታህሳስ 19/2017 ዓ.ም ለማድረግ ውስኖ ነበር፡፡
አሁን ላይ ኢትዮጵያ ራሷን ከ 17ዓመት በታች የአፍሪካ ዋንጫ ሴካፋ ዞን ማጣሪያ ውድድር ማግለሏ ይፋ አድርጋለች፡፡
ኢትዮጵያ ከውድድሩ ራሷን ያገለለችው በበጀት እጥረት ምክንያት መሆኑን የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ለሴካፋ በላከው ደብዳቤ ገልጿል።
ይህንንም ተከትሎ የማጣሪያ ውድድሩ ምድብ አንድ በሶስት ሀገራት መካከል የሚካሄድ ይሆናል ተብሏል፡፡
⚽️⚽️⚽️
🌴🌴🌴